Telegram Web Link
በተለያዩ ሰበቦች የሶላት ወቅት ያለፈበት ሰው ቀዷእ ያወጣልን?
~

1- ረስቶ ወቅቱ ያለፈበት ሰው ባስታወሰ ጊዜ ይሰግዳል። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
مَن نسِيَ صلاةً، فلْيُصلِّ إذا ذكَرَها، لا كفَّارةَ لها إلَّا ذلِك؛ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
"ሶላትን የረሳ ሰው ሲያስታውሳት ይስገድ። ከዚህ በስተቀር ለሷ ሌላ ማካካሻ የላትም። ..." [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም]

2- ተኝቶ ወቅቱ ያለፈበት ሰው ባስታወሰ ጊዜ ይሰግዳል። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
ليس في النومِ تفريطٌ، ... فمَن فَعَل ذلك فلْيُصلِّها حين يَنتبهُ لها
"በእንቅልፍ ውስጥ ቸልተኝነት የለም። ( ከምርጫው ውጭ ስለሆነ ወንጀለኛ አይሆንም።) ... ይህንን ያደረገ (ተኝቶ ሶላት ያለፈው) ሲነቃ ይስገዳት።" [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም]

3- እብ ~ደት ደረጃ በደረሰ የአእምሮ መታወክ ምክንያት ወቅቱ ያለፈበት ሰው የህመሙ ጊዜ አጠረም ረዘመም ቀዷእ አይጠበቅበትም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦
رُفِعَ القلمُ عن ثلاثةٍ: عن النائمِ حتى يستيقظَ، وعن الصبيِّ حتى يَبلُغَ، وعن المجنونِ حتى يَعقِلَ
"ከሶስት ሰዎች ብእር ተነስቷል። (ስራቸው አይመዘገብም።) የተኛ እስከሚነቃ ድረስ፣ ህፃን ለአቅመ ሃላፊነት እስከሚደርስ ድረስ እና ያበ ደ ሰው እስከሚያውቅ (እስከሚሻለው) ድረስ።" [አቡ ዳውድ እና አነሳኢይ]

4- እራሱን ስቶ የሶላት ወቅት ያለፈበት ሰው ጊዜው አጠረም ረዘመም ቀዷእ አይጠበቅበትም። ሁኔታው እብ ~ደት ላይ ካለ ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው። ይሄ የማሊኪያ፣ የሻፊዒያ እና የከፊል ቀደምቶች አቋም ሲሆን የኢብኑ ሙንዚር፣ የኢብኑ ሐዝም፣ የኢብኑ ዐብዲልበር እና የኢብኑ ዑሠይሚን ምርጫ ነው። ሶሐቢዩ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እራሳቸውን ስተው ቆይተው ኋላ ሲነቁ ያለፋቸውን ሶላት ቀዷእ አላወጡም። [አልሙወጦእ: 2/18] [ሙሶነፍ 0ብዲረዛቅ: 4153]

5- የሰከረ ሰው፦

ሳይሰግድ ወቅቱ ከወጣበት ሶላቱን ቀዷእ ማውጣት እንዳለበት ኢጅማዕ አለ። አላህ እንዲህ ይላል፦
لا تَقْرَبُوا الصَّلاةَ وَأَنْتُمْ سُكَارَى حَتَّى تَعْلَمُوا مَا تَقُولُونَ
"የሰከራችሁ ሆናችሁ ስግደትን አትቅረቡ፤ የምትሉትን ነገር እስከምታውቁ ድረስ።" [አኒሳእ፡ 43]

6- አደንዛዥ እፅ በመውሰዱ እራሱን ስቶ ሶላት ያለፈበት ሰው በራሱ ጥፋት፣ በራሱ ምርጫ የተፈፀመ ስለሆነ ቀዷእ ማውጣት አለበት። ይሄ የሐነፊያና የሐንበሊያ አቋም ሲሆን ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን እና በሰዑዲያ የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት የተጓዙበት ነው።

7- ያለ ምንም ምክንያት ሆነ ብሎ ሶላትን ያሳለፈ ሰው ብዙሃን ዓሊሞች ቀዷእ ማውጣት አለበት ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ በቀዷእ የማይካካስ ወንጀል ስለሆነ የፈፀመው ቢሰግድም ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ ተውበት ነው ማድረግ ያለበት ይላሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ጦዋፈል ወዳዕ
~
የሑጃጅ የመጨረሻ ተግባር ጦዋፈል ወዳዕ ነው። 7 ዙር በከዕባ ዙሪያ ይዞራሉ። ከጦዋፈል ወዳዕ በኋላ መካ መቆየት አይገባም። ስለዚህ የመጨረሻ ስንብቱ ነው መሆን ያለበት። እዚህ ላይ አንዳንዶች የሚፈፅሟቸው ስህተቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ :-

1ኛ፦ ጦዋፈል ወዳዕ ሳያደርጉ ወደ ሃገር መመለስ። የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ግን ጦዋፈል ወዳዕ የለባትም። ነገር ግን ጦዋፈል ኢፋዷህ ያልፈፀመች ከሆነች ስትጠራ ጠብቃ መፈፀም ግድ ይላታል።
2ኛ፦ ጦዋፈል ወዳዕ ካደረጉ በኋላ መካ መቆየትም ስህተት ነው። ጦዋፈል ወዳዕ ማለት የስንብት ጦዋፍ ነው። የሚቆዩ ከሆነ ስንብቱ አልተገኘም። ስለዚህ የቆየ ሰው ሊወጣ ሲል እንደገና ጦዋፍ ሊያደርግ ይገባል።
3ኛ:- ጦዋፈል ወዳዕ ካደረጉ በኋላ ሰዕይ የሚፈፅሙ ማለትም በሶፋና መርዋ መካከል 7 ጊዜ የሚመላለሱም አሉ። ከጦዋፈል ወዳዕ በኋላ ግን ሰዕይ የለም።
4ኛ፦ ጠዋፉን አጠናቀው ሲወጡ ጀርባችንን ለከዕባ አንሰጥም በሚል ፊታቸውን ወደ ከዕባ አዙረው ወደ ኋላ የሚጓዙ አሉ። በዚህ መልኩ እየተጓዙ የሚወድቁ ሁሉ አሉ። ይሄ ከነብያችን ﷺ ያልተገኘ የቢድዐ ተግባር ነው።
5ኛ:- አንዳንዱ ደግሞ ጦዋፈል ወዳዕ አጠናቆ እየወጣ የመስጂደል ሐራም በር ላይ ሲደርስ ይቆምና ወደ ከዕባ ዙሮ በተለያየ መልኩ የሚሰናበት አለ። ይህም አላስፈላጊ ተግባር ነው።

በተረፈ ሐጅ ላይ ያላችሁ ሰዎች መካ እስካላችሁ ድረስ በመስጂደል ሐራም ሶላተል ጀማዐ እንዳያልፋችሁ ጣሩ።
حجا مبرورا وسعيا مشكورا وذنبا مغفورا إن شاء الله

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለመርከዝ አት_ተውሒድ ነባር ተማሪዎች በሙሉ
ከእረፍት መግቢያ ሰዓታችሁ እለተ ሓሙስ ሰኔ 04፣ 2017 ሲሆን ፣ በተባለው ግዜ እንድትገቡ እናሳስባለን።
አዲስ ተማሪዎችን ሰለመዘገብን ዘግይቶ የሚመጣ ነባር ተማሪ ቦታ ሊሞላበት ስለሚችል በተባለው ግዜ እንድትገኙ።
ከዒድ አል አድሓ በዓል በኋላ እንድትመጡ የተነገራችሁ አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ዓርብ ሰኔ 05፣ 2017 ከተጠረኢ ቤተሰብ ጋር መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እስንል እናሳዉቃለን።
አድዲስ መመዝገብ የምትፈልጉ ተማሪቾ ባለን ዉስን ቦታ ነባር ተማሪዎችን (የክረምት የለንም) ሰለመንመዘግብ በሚከተለው የቴለግራም አድራሻ ማናገር ፣ መረጃ ማአገኘት እና መመዝገብ ትችላላችሁ።
መስፈርት፡
ጾታ፡ ወንድ
እድሜ፡ 13 እና ከዛ በላይ
ወርሓዊ ክፍያ መክፈል የሚችል
ተላላፊ እና ቋሚ በሽታ ነጻ የሆነ
ከተለያዩ ሱሶች ነጻ የሆነ
@durise
@durise
@durise
🔶 #سلسلة_الفوائد_المكية (٨٦)

   قال العلامة عبدالرحمن بن ناصر السعدي - رحمه الله تعالى:

"وهكذا ينبغي للعبد، كلما فرغ من عبادة، أن يستغفر الله عن التقصير، ويشكره على التوفيق، لا كمن يرى أنه قد أكمل العبادة، ومن بها على ربه، وجعلت له محلا ومنزلة رفيعة، فهذا حقيق بالمقت، ورد الفعل، كما أن الأول، حقيق بالقبول والتوفيق لأعمال أخر."

📚 تيسير الكريم الرحمن، صفحة [٩١]
https://www.tg-me.com/AbumuslimArabicDuroos/8919
==========
📌 قناة الفوائد المكية

📍 للمتابعة انضم إلى هذه القناة

🌐
https://www.tg-me.com/AbumuslimArabicDuroos
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
~
ላሰባችሁ ለተጨነቃችሁልኝ ሁሉ! አታስቡ አላህ አትርፎኛል ፣ አልሐምዱ ሊላህ። የህመሙ ስሜት ከቀን ቀን እየቀነሰልኝ ነው። በደንብ ለማገገም ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል መሰለኝ። እንዳጠቃላይ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ኢንሻአላህ። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ጀዚለን።
Live stream finished (4 hours)
Forwarded from Abul Abas || معلم القرآن
🔴አስደሳች   ዜና ለሴቶች
🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

🗂 ለሴቶች አዳሪ መርከዝ ተከፈተ

🆕መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽ-ዐሪ ለሴቶች በአዳሪ መርኀግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ ላይ ይገኛል። የምንቀበለው የተማሪ ብዛት ውስን ስለሆነ ቦታ ሳይሞላበዎት ፈጥነው ይመዝገቡ

🔴መሟላት ያለባቸው መስፈርቶ
🔸እድሜ ከ10 - 25 ዓመት ባለው
🔸ክፍያ በአግባቡ መክፈል የምትችል
🔸ከተላላፊ በሽታ ነፃ የሆነች
🔸 ያለ ቤተሰብ ግፊት አምናበት የምትመጣ ተማሪ ።
🔸ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ መሆን የምትችል
🔸ከመርከዙ የሚቀርቡ ምግቦችን የለ መረጣ መመገብ የምትችል 

🗂አድራሻ: አንፎ ድልድይ ፀሀይ ግሮሰሪ አከባቢ

🗂ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡
+251928844757 +251930547776
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/27 09:48:54
Back to Top
HTML Embed Code: