ተውሒድ፣ ትኩረት የተነፈገው ሐቅ
~
ህዝባችን ከተውሒድ ያለውን ርቀት ያስተዋለ ሰው አብዛኛው ዱዓት የሚያተኩረው ሌሎች ርእሶች ላይ ሆኖ ሲመለከት እጅጉን ያዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ ከሱና መስመር ያፈነገጡ አንጃዎች ብቻ የሚወቀሱበት አይደለም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ በሱና ስም በሰለፊያ ስም የሚንቀሳቀሰው እራሱ በሚያሳዝን ሁኔታ በተጨባጭ ለተውሒድ ትምህርት የሰጠው ትኩረት ለተውሒድ የሚመጥን፣ ህዝባችን ያለበትን ችግር ያገናዘበ አይደለም፡፡ ይሄ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁላችንም ጋር የሚታይ ችግር ነው፡፡ ቤተሰቦቻችን ነገ ወይም ከነገ ወዲያ የሚያጋጥማቸው ለህልፈት የሚዳርግ ከባድ አደጋ እንዳለ ብንረዳ በእግር በፈረስ ጠብጥበን ህይወታቸውን ለማትረፍ እንጥራለን፡፡ ዘላለማዊ ህይወታቸውን በሚያበላሸው ሺርክ እንደተወረሩ እያወቅን ግን የምናደርገው ጥረት እምብዛም ነው፡፡ ምናልባት ትንሽ እንጥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውለታቸውን ሐቃቸውን የሚመጥን አይደለም፡፡ በትንሿ ጥረታችን በቂ ነገር እንደሰራን በማሰብ ለራሳችን ዑዝር እየሰጠን እንሸወዳለን፡፡ ከሐቅም በላይ ትልቁ ሐቅ የነገ ህይወታቸውን ከሚያበላሽ ብልሹ መንገድ መመለስ ነው፡፡ ልብሳቸውን ጉርሳቸውን ማሟላት ከዚህ ጋር የሚነፃፀር አይደለም፡፡ የልጆችን ሐቅ በተመለከተም ልክ እንዲሁ ነው፡፡
አሁን ይህቺን ማስታወሻ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ አንድን የጥንቆላ አፕሊኬሽን ሙስሊሞች ሲጠቀሙት ማየቴ ነው፡፡ በዚህ በ “ሰለጠነው” ዘመን የተለያዩ መልኮች ያሏቸው ጥንቆላዎችን በስልክ ሜሴጅ፣ በዋትሳፕ፣ በፌስቡክ፣... በየጊዜው እናያለን፡፡ ታዲያ ይሄ ነገር ከእምነታችን ጋር የሚጋጭ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አልፎ አልፎ ቢታይም በየጊዜው ግን እነዚህን ቆሻሻ ጥንቆላዎች በራሱ የሚጠቀም፣ አልፎም ለሌሎች የሚያሰራጭ ሰው አለመጥፋቱ የሚደንቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ሰዎች መቼ እንደሚሞቱ የሚጠነቁል አፕሌኬሽን ሙስሊም የሆነ ሰው ያውም በረመዳን፣ ያውም በነዚህ በከበሩ አስሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ እየተጠቀመ ማየት ምንኛ የሚያሳዝን ነው?! ሰው እንዴት በማይረባ እንቶ ፈንቶ ፆሙን፣ ሶላቱን፣ ቁርኣን መቅራቱን፣ ዚክሩን፣ ከምንም በላይ ዐቂዳውን አደጋ ላይ ይጥላል?! እስኪ ከአላህ በስተቀር ማንስ ቢሆን የት እንደሚሞት፣ መቼ እንደሚሞት ከየት ሊያውቅ ይችላል?! አላሁል ሙስተዓን!
አንዳንዱ ከሆነ ጥንቆላ ስትመልሰው ይቀበልሃል፡፡ ሌላ መልክ ያለው ጥንቆላ ሲመጣ ግን እንደገና ሰለባ ሲሆን ይታያል፡፡ ከገጠር ድንጋይ ወርዋሪ ጠንቋዮች፣ ከባህላዊ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ ከሲኒ ዘቅዛቂዎች፣ ከመዳፍ አንባቢዎች፣… ስትመልሰው ይቀበልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ የሰውን ልጅ መፃኢ እድል “የሚተነብዩ” አታላይ ኹራፊዮች ግን ባለ ዲግሪው ሳይቀር ይሸወድባቸዋል፡፡ ይሄ ትልቅ መክሸፍ ነው፡፡ ይሄ ከመሰረታዊ የኢስላም ግንዛቤ መራቃችንን የሚያጋልጥ ሙሲባ ነው፡፡ ስለዚህ የኢስላማችንን መሰረታዊ ርእሶች ለመገንዘብ በርትተን ልንጥር፣ የቻለም ሊያስተምር ይገባል ማለት ነው፡፡ አላህ ከሺርክ ይጠብቀን፡፡
በድጋሚ የተለጠፈ
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ዑዝር ቢል ጀህል አለ የሚሉ አካላትን "ለተውሒድ ትኩረት አይሰጡም"፣ "ከሺርክ አያስጠነቅቁም" እያሉ የሚዋሹ አካላት አሉ። ይሄ ውንጀላ ከውሸት ውጭ ሌላ ስም የለውም። ከጥንት እስከ ዛሬ፣ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ ድረስ ተውሒድን በማስተማር፣ ሺርክን በመታገል ላይ ከፊት ረድፍ ላይ የሚገኙ አካላትን ለተውሒድ ትኩረት አይሰጡም ማለት ቡድንተኝነት የሚያመጣው ዳፍንት ነው። ቡድንተኝነት ግልፁን ነገር እንዳይታይ ያደርጋል። እነ ሻፊዒይ፣ ኢብኑ ተይሚያ፣ ሰዕዲይ፣ ዐብዱረሕማን አልሙዐሊሚ፣ አልባኒይ፣ ዐብዱረዛቅ አልዐፊፊ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ወዘተ . ናቸው ለተውሒድ ትኩረት የማይሰጡት? ሐያእ ቢኖራችሁ መልካም ነው። ጅህልና የወለደው የማይረባ ድፍረት ገደል እንዳይከታችሁ። ዑዝር የለም የሚለው የከፊሎች አቋም ልክ ከመሰላችሁ በልክ ሁኑ።
እንዲያውም ዑዝር ቢል ጀህል የለም ከሚሉት ውስጥ ከፊሎቹ ሁሉን አkfረው በራቸውን ስለዘጉ በማስተማር ላይ የረባ ሚና የላቸውም። ይልቁንም ነጋ ጠባ ከነሱ ውጭ ያለን ሁሉ በጅምላ ዓሊሞችን ጭምር ዑዝር ይሰጣሉ በሚል መነሻ ከኢስላም በማስወጣት እና በኢርጃእ በመወንጀል የተጠመዱ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
እንዲያውም ዑዝር ቢል ጀህል የለም ከሚሉት ውስጥ ከፊሎቹ ሁሉን አkfረው በራቸውን ስለዘጉ በማስተማር ላይ የረባ ሚና የላቸውም። ይልቁንም ነጋ ጠባ ከነሱ ውጭ ያለን ሁሉ በጅምላ ዓሊሞችን ጭምር ዑዝር ይሰጣሉ በሚል መነሻ ከኢስላም በማስወጣት እና በኢርጃእ በመወንጀል የተጠመዱ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የኡዱሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች
~
ኡዱሒያ ማለት በዒደል አድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡዱሒያን ያርዱ ነበር፡፡ [ሚሽካት፡ 1475] እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “አቅሙ እያለው ኡዱሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡
ኡዱሒያ ብዙሃን ዑለማኦች ዘንድ የጠነከረች ሱና ነች። ከፊል ምሁራን ዘንድ ደግሞ ግዴታ ነች። ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከሁለቱ ሃሳቦች የሚጎላው ግዴታ ነው የሚለው ነው ይላሉ። ግዴታም ቢሆን ታዲያ ያልቻለ ሰው ኡዱሒያ ለማረድ ብሎ እዳ እንዲገባ / እንዲበደር አይገደድም።
ለኡሑዲያ የሚታረደው እንስሳ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት
1. የሚታረደው እንስሳ ከበግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ውስጥ ብቻ መሆን አለበት።
2. ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ቢበዛ ለ7 ሰው ነው መሆን ያለበት፡፡ ከዚያ መብለጥ የለበትም። አንዱ ለ 7 ሰው ከተቻለ ቁጥራቸው ከ 7 ያነሰ ሆነው ቢያርዱ የበለጠ ያብቃቃል። ፍየልና በግ ለጋራ ማረድ አይቻልም፡፡
3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡
4. የሚታረደው እንስሳ መታወሩ ግልፅ የሆነ፤ ህመሙ ግልፅ የሆነ በሽተኛ፤ ግልፅ የሆነ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛሃኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡ ትንንሽ እንከኖች ችግር አይሆኑም። የተኮላሸ መጠቀም ይቻላል። ነብዩ ﷺ ሁለት የተኮላሹ በጎችን አርደዋል። [ሱነኑል በይሃቂይ]
5. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ባለው ነው፡፡ ነብዩ ﷺ (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪ]
6. ያለ ምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም #ከሴትም ለኡዱሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ [ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሩን ዐለ ደርብ፡ ካሴት ቁ. 72]
7. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡዱሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ﷺ “የኡዱሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡዱሒያ የለውም!” ብለዋል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2/1055] ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡዱሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሶደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ [ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 25/162] ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡
8. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል። ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል። ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡
9. ኡዱሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡
ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡
=
Ibnu Munewor ፣ ጳጉሜ 2/2008

የነገ የሐጅ ተግባር
~
ነገ ዙልሒጃህ 8 /1446 ነው። የውመ ተርዊያህ ተብሎ ይጠራል። ሁጃጅ ወደ ሚና የሚወጡበት ቀን ነው። ተመቱዕ የተሰኘው የሐጅ አፈፃፀምን የነየቱ ሰዎች (አብዛኞቹ ሑጃጅ ይህንን ነው የሚነይቱት)
• ተጣጥበው፣ ከፈለጉ አካላቸውን ሽቶ ተቀባብተው ይዘጋጃሉ።
• ካረፉበት ቦታ ቀጥታ በልባቸው ሐጅን ነይተው ይቋጥሩና “ለበይክ ሐጀን” ብለው በመነሳት ወደ ሚና ይተማሉ።
• ከቻሉ ከቀትር በፊት ረፋድ ላይ በመውጣት ሚና ይደርሱና ልክ ነብዩ ﷺ እንዳደረጉት ዙህርን፣ ዐስርን፣ መግሪብን፣ ዒሻእን እና ሱብሕን እዚያ ይሰግዳሉ። ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው የሚሰግዱት፣ ጀምዕ ሳያደርጉ። ባለ አራት ረከዐዎቹን በማሳጠር ሁለት፣ ሁለት እያደረጉ ይሰግዳሉ።
• በቀጣዩ ቀን ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ወደ ዐረፋ ከመውጣታቸው በፊት ፀሐይ እስከምትወጣ ድረስ ቢቆዩ በላጭ ነው።
• ተልቢያን (ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣...)፣ ዚክርን፣ ቁርኣን መቅራትን ሊያበዙ ይገባል።

የቤትሽን ገመና ውጭ አትዝሪ
~
ተሰባስበው ባሎቻቸውን በማማት የሚጠመዱ ሴቶች አሉ። አንዳንዶቹ ከነዚህ የሃሜት ድግሶች መልስ በባሎቻቸው ላይ ያቄማሉ። ውስጣቸው ይደፈርሳል። ቀጥታ ግጭት ውስጥ የሚገቡም አሉ።
እነዚህ ሃሜቶች አንዳንዴ ሄደው ሄደው ቤት የሚያፈርሱ ሊሆኑ ይችላሉ። ሴቶች በባሎቻችሁ ላይ እንድትሸፍቱ ከሚያደርጉ አጉል መካሪዎች ተጠንቀቁ።

ኡዱሒያ ጋር የሚያያዙ ተጨማሪ ነጥቦች
~
1ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ወንድ ብቻ አይደለም የሚሆነው፣ ሴትም ማረድ ይቻላል። ይሄ የዑለማእ ወጥ ስምምነት (ኢጅማዕ) ያለበት ጉዳይ ነው።
የታረደችው እንስሳ ሆዷ ውስጥ ፅንስ ካለ፣ ካልከበዳቸው መመገብ ይችላሉ። ነብዩ ﷺ ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦
كُلوه إنْ شِئتُم؛ فإنَّ ذَكاتَه ذَكاةُ أمِّه
"ከፈለጋችሁ ብሉት። የእሱ (የሽሉ) እርድ የእናቱ እርድ ነው።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 2827]
ማለትም የሷ ክፍል እንደመሆኑ እሷን ሐላል ያደረጋት እርድ እሱንም ሐላል አድርጎታል ማለታቸው ነው። "ከፈለጋችሁ" ነው ያሉት። ያልፈለገ ለሚፈልግ ሊሰጠው ካልሆነም ሊተወው ይችላል።
2ኛ፦ የሚታረደው እንስሳ ቀንድ ያለው መሆኑ ግዴታ አይደለም። በተፈጥሮው ቀንድ የሌለው ከሆነ ምንም ችግር የለውም።
3ኛ፦ ግልፅ ያልሆኑ ትንንሽ ነውሮች ያሉበትን ማረድ ይቻላል። በጣም አጥብቀን ራሳችንን ልናስቸግር ወይም የተሻለ እንስሳ ልናስመልጥ አይገባም።
4ኛ:- ውጭ ሃገር ለሚኖር ሰው በውክልና የምናርድ ከሆነ ባለ ኡዱሒያው አካል ዒድ ሳይሰግድ ቀድመን ማረድ የለብንም። ይቺን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ። https://www.tg-me.com/ibnhezam/14606
ስለዚህ ባለ ኡዱሒያዎቹ አውሮፓና አሜሪካ የሚኖሩ ከሆኑ ከኛ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ስለማይሰግዱ እናቆየው። እስከ 13ኛ ቀን ድረስ ማረድ ስለሚቻል ስጋት እንዳይገባን።
5ኛ፦ ስጋውን ከፊሉን ቤት ውስጥ ለእለት ምግብ ማዋል፣ ከፊሉን ማስቀመጥ፣ ከፊሉን ደግሞ ሶደቃ አድርጎ ለሰው መስጠት ይቻላል። 1/3ኛ ለእለት ምግብ፣ 1/3ኛ ለሚቆይ፣ 1/3ኛ ደግሞ ለሶደቃ የሚለው መረጃ የለውም። በዚህ መልኩም ይሁን በሌላ በፈለገው መልኩ ማከፋፈል ይችላል።
ከፊል ዓሊሞች ትንሽም ቢሆን ሶደቃ መስጠቱ ግዴታ ነው ይላሉ። ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሙሉውን መጠቀምም ይቻላል።
https://www.tg-me.com/ibnhezam/14661
ስለዚህ ለምሳሌ ቤተሰብ የሚበዛበት ሰው እዚያው ሊጠቀመው ይቻላል ማለት ነው። ወላሁ አዕለም።

فتاوى شرعية لفضيلة الشيخ محمد بن حزام البعداني
بِسْمِ اللّــــهِ الرَّحْمَـــــــــنِ الرَّحِيمِ
📩 السُــــــــــــؤالُ :-
لو أن شخصا وكلك في ذبح أضحيته، وهو من أوروبا أو من أمريكا وأنت مقيم باليمن، هل تذبحها له بعد أن تصلي العيد أنت، أو تنتظر بعد أن يصلي هو العيد في بلاده ؟
📝 الإجـــــــــــابة :…

0ረፋን መፆም ለማይችሉ
~
ነገ ዐረፋ ነው፣ ዙልሒጃ ዘጠኝ። ይህንን ቀን መፆም ትልቅ ዋጋ እንዳለው የሚታወቅ ነው። በተቻለ መጠን ሊያልፈን አይገባም።
በወር አበባ፣ በወሊድ፣ በህመም ሰበብ መፆም የማትችሉ ደግሞ ለመፆም ቁርጠኛ ውሳኔ ከነበራችሁ አትቆጩ። የምታመልኩት የልባችሁን የሚያውቅ ጌታ ነው። በኒያችሁ የሚፈፅሙ ሰዎችን አምሳያ ይመነዳችኋል። ይህንን የሚጠቁሙ መረጃዎች ብዙ ናቸው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"وهذه قاعدة الشريعة: أن من كان عازماً على الفعل عزما جازما، وفعل ما يقدر عليه منه، كان بمنزلة الفاعل".
"ይሄ የሸሪዐ ህግ ነው። አንድን ተግባር ለመፈፀም ቁርጠኛ ውሳኔን የወሰነና የሚችለውን ያደረገ ሰው በፈፃሚ ደረጃ ነው የሚሆነው።" [አልፈታዋ፡ 23/236]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
ነገ ዐረፋ ነው፣ ዙልሒጃ ዘጠኝ። ይህንን ቀን መፆም ትልቅ ዋጋ እንዳለው የሚታወቅ ነው። በተቻለ መጠን ሊያልፈን አይገባም።
በወር አበባ፣ በወሊድ፣ በህመም ሰበብ መፆም የማትችሉ ደግሞ ለመፆም ቁርጠኛ ውሳኔ ከነበራችሁ አትቆጩ። የምታመልኩት የልባችሁን የሚያውቅ ጌታ ነው። በኒያችሁ የሚፈፅሙ ሰዎችን አምሳያ ይመነዳችኋል። ይህንን የሚጠቁሙ መረጃዎች ብዙ ናቸው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"وهذه قاعدة الشريعة: أن من كان عازماً على الفعل عزما جازما، وفعل ما يقدر عليه منه، كان بمنزلة الفاعل".
"ይሄ የሸሪዐ ህግ ነው። አንድን ተግባር ለመፈፀም ቁርጠኛ ውሳኔን የወሰነና የሚችለውን ያደረገ ሰው በፈፃሚ ደረጃ ነው የሚሆነው።" [አልፈታዋ፡ 23/236]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ከሚስትህ ጋር ስለምትፈጽሙት ግንኙነት ውጭ ላይ ለሌላ ሰው አይወራም። ይሄ ሲበዛ አስቀያሚ ነውር ነው። የሐያእ መቅለል ነው። ከሰው አይን ተገልለህ የፈፀምከውን እንዴት ለሰው ታወራለህ?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዙልሒጃህ 9 የሐጅ ተግባር
~
እለቱ የዐረፋ ቀን ነው። ሑጃጅ ዐረፋ ላይ የሚቆሙበት እለት። ዐረፋ ላይ መቆም ከሐጅ ምሰሶዎች ውስጥ አንድ ምሰሶ ነው። ነብዩ ﷺ “ሐጅ ማለት ዐረፋ ነው” ማለታቸው ይህንን እውነታ ያሳያል።
• በዚህ ቀን ሑጃጅ ሱብሕን ሚና ላይ ከሰገዱ በኋላ ፀሐይ ስትወጣ ተልቢያ፣ ዚክር እያደረጉ ወደ ዐረፋ ይጓዛሉ።
• የቻለ ሰው ከእኩለ ቀን በፊት ዐረፋ ይደርሳል። በዙህር ወቅት ዙህርና ዐስርን አንድ ላይ ይሰግዳል።
• ከዚያ በኋላ እስከ መግሪብ ድረስ አጥብቆ ዱዓእ፣ ዚክር ማድረግ ይገባል። ይሄ ቀን በጣም ልዩ ቀን ነው። ሽራፊ ጊዜ ያላግባብ እንዳያልፍ መጠንቀቅ ይገባል።
• ፀሐይ ስትጠልቅ ጉዞ ወደ ሙዝደሊፋ ይሆናል።
• ከዚያም ሙዝደሊፋ ሲደርሱ መግሪብና ዒሻእን አንድ ላይ መስገድ ይገባል። ዒሻእ በማሳጠር ሁለት ረከዐ ነው የሚሰገደው።
• ሙዝደሊፋ ካደሩ በኋላ የሱብሕን ሶላት እዚያው ይሰግዳሉ።
• ከሱብሕ ሶላት በኋላ ወደ ቂብላ በመዞር ዱዓእ፣ ዚክር ያደርጋሉ።
• ከዚያም ተልቢያ እያደረጉ ጀምረተል ዐቀባ ላይ ጠጠር ለመወርወር ይጓዛሉ።
በዚህ ቀን የሚከተሉት ስህተቶች የሚፈፅሙ ሰዎች ያጋጥማሉና መጠንቀቅ ያሻል :-
1ኛ፦ ከዐረፋ ክልል ውጭ መቆም፣ (በእለቱ ሙሉ ጊዜውን ከዐረፋ ክልል ውጭ አሳልፎ ወደ ሙዝደሊፋ የተጓዘ ሰው ሐጅ የለውም። ያለ ዐረፋ ሐጅ የለምና።
2ኛ፦ ወደ ዐረፋ ተራራ ጫፍ ላይ ለመውጣት መጓጓት ስህተት ነው። ዐረፋ ሁሉም መቆሚያ ነው። የተራራው ጫፍ በመውጣት የሚገኝ የተለየ ነገር የለም።
3ኛ፦ ስራዬ ብሎ ወደ ተራራው ዞሮ ዱዓእ ማድረግ ሌላ ስህተት ነው። ሱናው ለዱዓእ ወደ ቂብላ መዞር ነው።

ዒድ የህፃናት ቀን ነው፣ በደስታ ባህር ውስጥ የሚቀዝፉበት። ዒዱን ያደምቁት ዘንድ ፣ በሃሴት ይቦርቁበት ዘንድ አቅማችን በፈቀደ እናግዛቸው። የራሳችንን ብቻ ሳይሆን የጎረቤት፣ የዘመድ ልጆችን ጭምር እናስታውስ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ዒድ የድሃ ቀን ነው። አላህ ያገራለት ሰው ድሃን የሚያስብበት እለት። የዒዱ የደስታ ድባብ እነሱም ጋር ይደርስ ዘንድ ወገን ለወገኑ የሚደርስበት ቀን ነው። ከኡዱሒያ ስጋው መስጠት፣ ከሌሎችም ነገሮች አላህ ባገራልን ማጋራት ይገባል። የጎረቤት፣ የዘመድ ልጆችንም እናስታውስ። አቅመ ደካማ የሆኑ መሻይኾችን፣ ኢማሞችን፣ ኡስታዞችን፣ የመስጂድ ኻዳሚ የሆኑ ሙአዚን፣ ጥበቃ፣ ፅዳት፣ ... እናስታውስ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ስንታዘብ/ስንተዛዘብ ----
መንግስት የ"C" በዓልን ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ መጠን ያለው ዘይት ከውጭ እንዲገባ አድርጓል
የ"C" በዓልን በማስመልከት የሽንኩርት ዋጋን ለማረጋጋትና የዋጋ መናሩን ለመቀነስ ይህን ያህል ቶን ሽንኩርት ከታንዛኒያ አስገብተናል
የ"C" በዓልን በማስመልከት ለ____ ታራሚዎች ምህረት ተደርጓል
የ"C" በዓልን ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን መሰረት ያደረገ አዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ሸማች ማህበራት መደብሮች ላይ ስጋ በከፍተኛ ቅናሽ እየተሸጠ ይገኛል
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የ"C" በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ ሳምንት የሰንደይ ማርኬት(ቅዳሜና እሁድ ገበያ) ክፍት ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ አቅጣጫ አስቀምጧል
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል
የ"C" በዓልን ምክንያት በማድረግ አስተዳደሩ ለ___ የሚጠጉ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት አድርጓል
የ"C" በዓልን ምክንያት በማድረግ አብዛኛው ጣቢያዎች በዐሉ ከመድረሱ ሳምንት በፊት የበዓል መዳረሻ ፕሮግራም ይጀምራሉ፣ የበዓሉ ዋዜማና ማግስት ከፍተኛ በጀት የተመደበበት ፕሮግራም ያቀርባሉ . . .
የበዓሉ ቀን የሚቀርቡ ፕሮግራሚች ይዘት፣ ጥራትና በጀት እንኳ አይነገርም . . . .
የነ ዲንሰፋ በዓል ላይ ግን . . . .
Ezedin Sultan

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዒዱኩም ሙባረክ
~
تقبل الله منا ومنكم
~
تقبل الله منا ومنكم
የዙልሒጃ 10 የሐጅ ተግባራት
~
ዙልሒጃ 10 “የውመ ነሕር” ተብሎ ይጠራል። የእርድ ቀን ነው።
1ኛ፦ በዚህ ሰዓት ሑጃጅ ከዐረፋ ተመልሰው ሙዝደሊፋ ናቸው። አቅመ ደካሞች ወይም ሌሎች ችግር ያለባቸው ሰዎችና የነሱ ረዳቶች ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ከሙዝደሊፋ ወደ ጀምረተል ዐቀባ መውጣት ይችላሉ። ችግር የሌለባቸው ደግሞ አድረው ጠዋት ላይ ይጓዛሉ። በዚህ ጉዞ ላይ ከመገፋፋት መጠንቀቅ ይገባል። ካልሆነ ጉዳት ሊደርስ ይችላል። ጀምረተል ዐቀባ ሲደርሱ 7 ጠጠሮችን ይወረውራሉ። የጠጠሮቹ መጠን የባቄላ መጠን አካባቢ የሚያካክሉ ናቸው።
2ኛ፦ ከዚያም እርድ የያዘ ሰው ያርዳል። ከተቻለ ከሱ ይበላል። ለምስኪኖችም ይሰጣል።
3ኛ፦ ከዚያም ፀጉሩን ይላጫል ወይም ይቆረጣል። መላጨቱ በላጭ ነው። ለሴቶች የጣት ጫፍ የምታክል መቆረጥ በቂ ነው። መቆረጥም ይሁን መላጨት በቀኝ በኩል ቢጀመር በላጭ ነው።
ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ ተግባሮች ቅደም ተከተላቸው ቢጠበቅ መልካም ነው። ቢለያይ ችግር የለውም።
• ከዚያም ወደ መካ ይወርዱና በከዕባ ዙሪያ 7 ጊዜ ጦዋፍ ያደርጋሉ። ይሄ ጦዋፍ “ጦዋፈል ኢፋዷህ” ይሰኛል። ይህንን ጦዋፍ ለመፈፀም የተቸገረ ሰው የአያመ ተሽሪቅ የሚና ቆይታውን አጠናቆ ወደ መካ እስከሚወርድ ድረስ ማዘግየት ይችላል። በዚህ ጦዋፍ ላይ የኢሕራምን ልብስ በቀኝ እጅ ብብት ስር አሳልፎ የግራ ትከሻ ላይ በመጣል ቀኝ እጅን ማውጣት አያስፈልግም። ከጦዋፉ በኋላ ሁለት ረከዕ መስገድ ተወዳጅ ነው።
• ቀጥሎም በሶፋና በመርዋ መካከል 7 ዙር ይመላለሳሉ። ይሄ “ሰዕይ” ተብሎ ይጠራል። የሚጀመረው ከሶፋ ሲሆን መርዋ ሲደረስ አንድ ተብሎ ይቆጠራል። ይህንን ሰዕይም እንደ ጦዋፈል ኢፋዷው ማዘግየት ይቻላል።
ጦዋፈል ኢፋዷ የፈፀመ ሰው በሐጅ ሰበብ የተከለከሉ ሁሉም ክልከላዎች ይነሱለታል።
ማሳሰቢያ፦
-
የሚወረወሩት ጠጠሮች በጣም ትልልቅ መሆን የለባቸውም። አይታጠቡም። በየተራ እንጂ አንዴ አይወረወሩም። ቋቱ ላይ ያልደረሰ ጠጠር ካለ በምትኩ ይወረወራል። ቁጥሩን የተጠራጠረ እርግጠኛውን ይዞ የጎደለውን ይሙላ። (ለምሳሌ 4 ነው ወይስ 5 የወረወርኩት ብሎ ቢጠራጠር 4 ብሎ ይያዝና የቀረውን ይቀጥል።) በውርወራ ጊዜ ተልቢያ አይኖርም። እያንዳንዱ ጠጠር “አላሁ አክበር” እየተባለ ይወረወራል። ጠዋት ያልቻለ ሰው በ10ኛው ቀን ውስጥ እስከሆነ ድረስ በሚመቸው ሰዓት መወርወር ይችላል።
=
Ibnu Munewor

የዙልሒጃ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ የሐጅ ተግባራት
~
እነዚህ 3 ቀናት አያመ ተሽሪቅ በመባል ይታወቃሉ። የስያሜው መነሻ ሑጃጅ ያረዱት ስጋ እንዳይበላሽ ፀሐይ ላይ ያሰጡ ስለነበር ነው።
• ሐጅ ላይ ያለ ሰው 10ኛው ቀን ላይ ጦዋፈል ኢፋዷን ከፈፀመ በኋላ ወደ ሚና ይመለሳል። በነዚህ ጊዜያትም ከቻለ ሶስቱንም የአያመ ተሽሪቅ ሌሊቶች፣ ከቸኮለ ደግሞ ሁለቱን በሚና ያሳልፋል።
• በነዚህ የሚና ቆይታው ሶስቱንም ጀመራት 7፣ 7 ጠጠሮች በድምሩ 21 ጠጠሮችን በየእለቱ ይወረውራል። ሶስቱ ጀመራት ማለትም ጀምረተ ሱግራ፣ ጀምረተል ውስጧ እና ጀምረተል ኩብራ (ዐቀባ) ናቸው። ውርወራ የሚፈፀመው ከቀትር በኋላ ነው። ከቀትር በፊት እንዳይሆን እንጂ በተመቼው ጊዜ መፈፀም ይችላል።
• ጀምረተ ሱግራ ከሚና ወይም ከመስጂደል ኸይፍ በኩል ለሚሄድ መጀመሪያ የሚያገኛት ናት። መሃል ላይ ውስጧ አለች። ኩብራ (ዐቀባ) ደግሞ ከሶስቱ ጀመራት ውስጥ በመካ በኩል የምትገኘዋ ናት ። ከጀምረተ ሱግራ እስከ ጀምረተል ውስጧ የ150 ሜትር ልዩነት አለ። ከውስጧ እስከ እስከ ኩብራ ደግሞ የ 190 ሜትር ርቀት።
• እያንዳንዷን ጠጠር ተክቢራ እያደረገ ይወረውራል።
o ጀምረተ ሱግራን ከወረወረ በኋላ በስተቀኝ በኩል አለፍ ብሎ ወደ ቂብላ በመዞር እጆቹን አንስቶ ረዘም ያለ ዱዓእ ያደርጋል።
o ጀምረተል ውስጧን ከወረወረ በኋላ ደግሞ በስተግራ በኩል አለፍ ብሎ እንዲሁ ረጅም ዱዓእ ያደርጋል።
o ጀምረተል ኩብራን ከወረወረ በኋላ ግን ቆሞ ዱዓእ ሳያደርግ ዝም ብሎ ነው የሚያልፈው።
• በ12ኛው እና በ13ኛው ቀንም ተመሳሳይ ተግባር ይፈፅማል።
• በነዚህ ቀናት ውስጥ ሑጃጅ ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት እያደረጉ አሳጥረው፣ ያለ ጀምዕ በየ ወቅቱ ነው የሚሰግዱት። የሚችሉ ሰዎች እነዚህን ሶላቶች በመስጂደል ኸይፍ ቢሰግዱ መልካም ነው። ካልቻሉ ደግሞ በያቅራቢያቸው በጀመዐ ሊሰግዱ ይገባል።
• በ12ኛው ቀን ለመመለስ የቸኮለ ሰው ግን 13ኛው ሌሊት ሳይገባ ከሚና ሊወጣ ይገባል። 13ኛው ላይ የደረሰ ሶስቱንም ጀመራት ከወረወረ በኋላ ሚና መቆየት የለበትም። ሁሉም ሑጃጅ ወደ መካ ያመራሉ።
• በነዚህ ቀናት ዚክርና ዱዓእ ማብዛት ይገባል። ቆይታውን በእርጋታ፣ በሰኪና ያሳልፋል። መገፋፋትን፣ ከሰዎች ጋር መነታረክ፣ መጋጨትን ይርቃል።

በእርድ ጊዜ እንስሳውን ወደ ቂብላ ማዞር የእርድ ሸርጥ (ቅድመ ሁኔታ) አይደለም። ነገር ግን ኢብኑ ዑመር ወደ ቂብላ ያዞሩ እንደነበር መረጃ መጥቷል። ይህንን መነሻ በማድረግም ወደ ቂብላ ማዞር እንደሚወደድ ዓሊሞች ይገልፃሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
በእርድ ላይ የአላህን ስም ማውሳት ለእርድ ሸርጥ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ሆነ ብሎ ከተወው እርዱ አይበላም። ከተረሳስ? ኢብኑ ዐባስ፣ አልቡኻሪይ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ ኢብኑ ቁዳማህ፣ ... ምንም ችግር እንደሌለው ገልፀዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ጥያቄ፡- ሴት እርድ ማረድ ትችላለች? ያረደችውን መብላትስ ይፈቀዳል?
መልስ፡-
ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በትክክለኛ ሱና እንደተገኘው ሴቷም ልክ እንደ ወንዱ ማረድ ትችላለች፡፡ ሙስሊማ ወይም ኪታቢያ ከሆነች እና #ሸሪዐዊ በሆነ መልኩ ካረደች፣ በሷ ቦታ ሊያርድ የሚችል #ወንድ_ቢኖር_እንኳን ያረደችውንም መብላትም ይፈቀዳል፡፡ ያረደችውን ለመብላት ስታርድ ወንድ በመጥፋቱ ማረዷ መስፈርት አይደለም፡፡
ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ
(መጅሙዕ፡ 23/82)