ውሎህ ከማን ጋር ነው? ምን ይመስላል?
~
ሰው በአብዛኛው ውሎውን ይመስላል። ቁርኝቱ ከመጥፎ ሰዎች ጋር የሆነ ሰው ውስጡ ይደፈርሳል። ብዙ መጥፎ ልማዶችን ይወርሳል። በሱስ የተለከፉ ወገኖች በዚህ ወጥመድ ውስጥ የወደቁት በጓደኛ ነው።
- በጓደኛ ብልግና ውስጥ የተነከሩ አሉ።
- በጓደኛ ራሳቸውንም ሌሎችንም የሚጎዳ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ አሉ።
- በጓደኛ ቁማር ያናወዛቸው አሉ።
- በጓደኛ ከሶላት የራቁ አሉ።
- በጓደኛ በጠዋት በማታ በኳስ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ የተጠመዱ አሉ።
- በጓደኛ ሰንካላ ፍልስፍና ውስጥ ገብተው እምነታቸውን ያጡ ወይም አፋፍ ላይ ያሉ አሉ።
- በጓደኛ ስራቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ትዳራቸውን፣ ቤተሰባቸውን ያጡ አሉ።
በተቃራኒው ፡
- በጓደኛ ከሺርክ፣ ከቢድዐ፣ ከተለያዩ ወንጀሎች የወጡ፣ ወደ ዲን የመጡ አሉ።
- በጓደኛ ከወንጀል የራቁ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ትዳር የመሰረቱ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ስራ ያገኙ፣ የተሻለ አቅም የገነቡ አሉ።
- በጓደኛ ዲንም ዱንያም የተማሩ፣ እውቀታቸውን ያሰፉ አሉ።
- በጓደኛ ከነበሩበት ፈተና ወጥተው ተስፋቸውን ያለመለሙ፣ ነፍሳቸውን ያረጋጉ አሉ።
ስለዚህ፡
ጓደኛችን ማነው? ዝንባሌውና ተፅእኖውስ ወዴት ነው? ወደ ኸይር? ወይስ ወደ ሸር? ጓደኝነታችን አትራፊ ነው ወይስ አክሳሪ? የቁም ነገር ነው? ወይስ እንዲሁ መደበሪያ? ሂሳብ መስራትና መወሰን ይገባል።
ከዚያ በፊት እኛ ለጓደኞቻችን ምን አይነት ሰዎች ነን? ሰዎችን ወደ ሱስ፣ ወደ ወንጀል፣ ወደ ክፋት የምንጎትት ከሆንን ወዮ ለኛ! በራሳችን ብቻ ሳይሆን ባጠፋናቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ነን። ጓደኝነታችን የኸይር ሰበብ ከሆነ ግን መታደል ነው።
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ሰውበጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው" ይላሉ።
* አቡበክር ሲዲቅ ህይወታቸውን ሙሉ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ጓደኛ ነበሩ። እንደሳቸው ያተረፈ ማን አለ?
* አቡ ጧሊብ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አጎት ነው። ደጀናቸው፣ መከታቸው ነበር። የሳቸውን እውነተኝነት በሚገባ ያውቃል። መጥፎ ጓደኞቹ ግን ሐቅ እንደሆነ ለሚመሰክርበት ኢስላም እጅ እንዳይሰጥ ይልቁንም በሺርኩ ላይ እንዲሞት አድርገውታል። ከዚህ በላይ የመጥፎ ጓደኛን አደጋ የሚያሳይ ምን አለ?
ስለዚህ፡ ጓደኞችህ/ሽ እነማን ናቸው? ወዴት እየወሰዱህ/ሽ ነው? ወዴትስ እየወስድካቸው /ሻቸው ነው? ከልብ መገምገምና ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የ "ብያለሁ ንጉስ" - ጋንጃሞ
~
ሰሞኑን ''አንድ እቃ በራሱ የማይገዛ ባንክ / ድርጅት "መኪና ልግዛላችሁ" ብሎ በተጠቃሚው ስም ሂሳብ ከፍሎ ትርፍ የሚጠይቅበት አሰራር የብድር ወለድ እንጂ የሽያጭ ውል አይደለም" የሚል ፅሁፍ ፅፌ ነበር። ስሙን አስሬ በመቀያየር የሚታወቀው ዐብዱልቃዲር ኑረዲን (ምናልባት ይህም እውነተኛ ስሙ ከሆነ) ከ10 ዓመት በፊት ብዬ ነበር እያለ ፅፏል። ልክ ዓለም ፀጥ ብሎ እሱ የጀመረው ሃሳብ ይመስለው ይሆን? ለማንኛውም
1. አንድ ሰው "ንብረት /ሚልክ" ያላደረገውን ነገር መሸጥ የለበትም የሚለው ሃሳብ መሰረቱ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ሲሆን በየ ደርሱ ላይ በስፋት የሚነሳ ነው። እሱ በቅርብ ጊዜ ያቀነቀነው ርእስ የመሰለው ደርስ አካባቢ በቅርብም በሩቅም ባለመኖሩ ነው። እንጂ በየ መሳጂዱ የኪታብ ደርስ ላይ የሚነሳ ነጥብ ነው። እኔ ራሴ የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም ስለዚህ ስናገር። በመንሀጁ ሳሊኪን እና በዑምደቱል አሕካም ደርሶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት አንስቼዋለሁ። የደምፅ ፋይሎች ይኖራሉ። ሰፋፊ ደርሶች ባሉባቸው መስጂዶች ደግሞ በተደጋጋሚ ይነሳል።
2ኛ. "ብዬ ነበር" ማለቱ የተለመደ የሰውየው ውሸት ነው። የሱ ጩኸት ይሄ አይደለም። የሱ ጩኸት "የፊያት መገበያያ ገንዘቦች በሸሪዐ ሚዛን ገንዘብ አይደሉም" የሚል ነው። ስለሆነም {አበላልጦ መዋዋል ወለድ/ አራጣ አይሆንም። በባንክ ቤት ሂሳብ ስትከፍቱ ቀጥታም በወለድ አድርጉትና በየወሩ ወለድ ይታሰብላችሁ} እያሉ መስበክ ነው የሱ "አብዮት"። ዐቅል ቢኖረው ኖሮ ይሄ ሊደብቀው የሚገባ፣ የሚያሳፍር ነውር እንጂ ክሬዲት ይሰጠኝ የሚያስብል ነገር አልነበረም። ግን በምን ዐቅሉ?
ሰውየው ከጫቱ ባልተናነሰ በውሸት ሱስ ተለክፏል።
- ወለድ ነፃ ስለሚባሉት ባንኮች እና ተያያዥ ነጥቦች ሂስ ከተነሳ ዘሎ ይመጣል፣ "ብዬ ነበር" ለማለት።
- "ስለ ዋጋ ግሽበት ሲወራ "ብያለሁኮ!" ይላል።
- ስለ ምንዛሬ ቀውስ ሲነሳ "የሚሰማኝ አጥቼ እንጂ ..." ይላል።
- "ብር ዋጋ እያጣ ስለሆነ ገንዘባችሁን በጥሬ ከምታስቀምጡ ንብረት ግዙበት" የሚል ሲያይ "ይሄው ቀድመው ስንት እንዳላሉኝ እኔ ወዳልኩት እየመጡ ነው፤ ገና መቼ!" እያለ ጮቤ ይረግጣል።
ሰው ዛሬ ከባንክ በወለድ ለመበደር ሰበብ ነው የሚፈልገው። ይሄ ጫት ላይ ተወዝቶ በምርቃና ወደ አራጣ የሚጣራ ሰባኪ ጥሩ ጋሻ ሆኗቸዋል። ሰውየው "የብር ግሽበት"፣ "የዋጋ ንረት"፣ በንዲህ አይነት ቀውስ ጊዜ ሰዎችን ንብረት እንዲይዙ መምከር የሱ የፈጠራ ግኝት ይመስለዋል። ከዚያ ስለነዚህ ጉዳዮች የሚያወራ ባየ ቁጥር "ወደኔ ሃሳብ እየመጡ ነው" ይላል። እነዚህ ቀውሶችና ተያያዥ ጉዳዮች አንተ ሳትፈጠርም በፊት የነበሩ ናቸው። እንዲያውም ወርቅ ከመገበያያነት ሳይጠፋ በፊትም ነበሩ። በ1933 አሜሪካ ላይ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ደግሞ ጀርመን ላይ የገጠመው በታሪክ ጎልተው የሚጠቀሱ ናቸው። በሌሎችም ሃገራት የገጠመ ነው።
ከወለድ ነፃ የሚባሉት ባንኮች ላይ የሚሰነዘሩ ሂሶችም ዛሬ የጀመሩ አይደሉም። እሱ 10 ዓመት ነዋ የሚለው? ከ 26 ዓመታት በፊት የሞቱት ሸይኹል አልባኒይ ስለነዚህ ባንኮች ጠንካራ ሂስ አላቸው። አለማወቅህ ነው ደረትህን ገልብጠህ እንድታወራ የሚያደርግህ።
ለማንኛውም የሸሪዐ ሑክም (ብይን) መሰረቱ ቁርአንና ሐዲሥ ነው። ጉዳዩ ቀድሞ ያልነበረ ወቅታዊ ሆኖ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ቁርአንና ሐዲሥ ውስጥ ምላሹ የማይገኝ ከሆነ ዑለማዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ ካጠኑ በኋላ ከሸሪዐ ማስረጃዎች ጋር አገናዝበው ብይን ይሰጣሉ። ጉዳዮቹ ውስብሰብ በሚሆኑ ጊዜ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎች ጠርተው ዝርዝር ማብራሪያ እና በቂ ግንዛቤ ከያዙ በኋላ ከብዙ አቅጣጫ ገምግመው ፈትዋ የሚሰጡባቸው ተቋማትም አሉ። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ እንደ ጋንጃሞ ያሉ ጥራዝ ነጠቆች ግን ስንዝር የአካዳሚ እውቀታቸው ላይ ተመርኩዘው ምንም በማያውቁት የሸሪዐ ጉዳይ ገብተው ያቦካሉ። የሚያጨበጭቡለትን ተመልከቱ። ወይ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ናቸው። ወይ ደግሞ የሸሪዐ እውቀት አካባቢ የሌሉ የሱው ቢጤዎች ናቸው።
በአካዳሚ ትምህርት ፈትዋ አይሰጥም። የፀጉር ንቅለ ተከላ፣ ደም ልገሳ ፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝና፣ ... በሃኪሞች ስለሚተገበሩ ብቻ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለው ሸሪዐዊ ሑክም በሃኪም አይሰጥም። ፈትዋው የሚሰጠው በሸሪዐ ዓሊም ነው። ሃኪሙ "ዓሊሞቹ ስለዚህ ምን ያውቃሉ?" ቢል ይሄ ሞኝነቱን ነው የሚያሳየው። ፋይናንስ እና ኢኮኖሚውም ላይ እንዲሁ ነው። አንተ ስለዚህ ጉዳይ አስኮላ ተምረሃል ማለት በጉዳዩ ላይ የሸሪዐ ሑክም መስጠት ትችላለህ ማለት አይደለም። ያስተማረህ ገብሬ እንጂ የሸሪዐ ዓሊም አይደለም። ፈትዋው የሚሰጠው በዓሊሞች ነው። እነ ጋንጃሞ ግን ሳይነቁ እንደነቁ የሚያስቡ ናቸው። (وَتَحۡسَبُهُمۡ أَیۡقَاظࣰا وَهُمۡ رُقُودࣱۚ)
ጋንጃሞ ራሱን በባዶ እየቆለለ "በዚህ ክፍለ ዘመን በሙስሊም ሊቃውንት የተበየኑና ቀላል የማይባሉ ገንዘብ ነክ ሃይማኖታዊ ብያኔዎቻችን (ፈትዋዎቻችን) ሲታዩ ደግሞ ጥያቄውን ሳይረዳ መልስ እንደሚፅፍ ተማሪ ይመስላሉ" በማለት ከዑለማዎች በላይ አውቃለሁ የሚል ብ^ሽ ^ቅ ፍጡር ነው። ይሄ አነጋገሬ የሚጎረብጣችሁ እንዳላችሁ አውቃለሁ። ዑለማዎችን ጥያቄውን ሳይረዳ መልስ በሚፅፍ አለማወቁን እንኳ በማያውቅ ደ *ደብ ተማሪ እየመሰለ ራሱን የሚቆልልን ግብ ዝ የሚበዛበት ቃል አልተጠቀምኩም። እንዲህ አይነቱ ከንቱ ነው በትልልቅ ሸሪዐዊ ጉዳዮች ገብቶ ዑለማዎችን ገፈታትሮ ብቻውን ሊያቦካ የተነሳው። በርእሱ ላይ ካለው ግድፈቱ በላይ እንዲህ አይነቱ ድፍረቱ ነው ይበልጥ የሚያንገበግበው፡፡

አንድ ሰው "ይህን ላደርግ ምያለሁ!" ቢል የአላህን ስም ባይጠራበትም ልክ "ወላሂ ይህን ላደርግ" እንዳለ ሰው መሀላው ይቆጠራል ይላሉ ኢብኑ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ ኢብራሂም አነኸዒይ፣ ሱፍያን አሠውሪይ እና ሌሎችም። [ሚስኩል ኺታም፡ 5/205]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
በአንድ ጉዳይ ላይ ለምሳሌ "ይህንን ላላደርግ" ብሎ የማለ ሰው ረስቶ ወይም ጉዳዩ የማለበት ጉዳይ መሆኑን ባለማወቅ ቢፈጽም ማካካሻ (ከ * fa ራ) አይጠበቅበትም። አላህ እንዲህ ብሏል :-
{ وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا }
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ነገር ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
{ وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا }
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ነገር ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #48
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-4️⃣ 8️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን አላህ እጅ የለውም?
~
ህሊና ላለው ሰው “አላህ እጅ የለውም” የሚል እምነት አስቀያሚና እጅጉን የሚያሳፍር ነው። ግና አእምሯቸው በእምነት የለሾች ፍልስፍና በመበከሉ የተነሳ ይህንን አጉል እምነት ተውሒድ ያደረጉ፣ ይባስ ብሎም ያልተጋራቸውን በሙሽ^ ሪክነት የሚወነጅሉ አንጃዎች ተፈልፍለዋል። በዘመናችን ይህንን ጥፉ አመለካከት ከሚያራምዱ አንጃዎች ውስጥ “አሕ -ባሽ” ፊታውራሪ ነው። ይህ የአሕ -ባሽ አመለካከት ከሙዕተዚላ የተኮረጀ እምነት ነው። ለዚህም ሁለት አይነት መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።
1ኛ፡- የሙዕተዚላዎችን ስራዎች። ለምሳሌ የቃዲ ዐብዱል ጀባር አልሙዕተዚሊን ስራዎች። [ሸርሑ ኡሱሊል ኸምሳ፡ 228] [ሙተሻቢሁል ቁርኣን፡ 231]
2ኛ፡- አሕ -ባሾች እንከተላቸዋለን የሚሏቸው ኢማሞች ምስክርነት። ለምሳሌ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪና አቡ መንሱር አልበግዳዲ ይህ እምነት የሙዕተዚላ ዐቂዳ እንደሆነ መስክረዋል። [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 157፣ 167] [ኡሱሉዲን፡ 228]
ስለ ራሱም ይሁን ስለሌሎች ከማንም በላይ አዋቂ የሆነው ጌታ ግን እጅ እንዳለው በግልፅ ቋንቋ ይናገራል። መልእክተኛውም ﷺ እንዲሁ። ጥቂት ማስረጃዎችን እንመልከት፡-
#ማስረጃ_አንድ፦
~
(قَالَ یَـٰۤإِبۡلِیسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِیَدَیَّۖ )
{ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ?} [ሷድ፡ 75]
ከዚች አንቀፅ አባታችን ኣደም በአላህ እጆች የተፈጠሩ ክቡር ፍጡር እንደሆኑ ማንም ይርረዳል፡፡ አሕ -ባሽ ሲቀር። እነሱ ግን “እጅ”/ “የድ” የሚለውን “ችሎታ፣ ፀጋ ማለት ነው” ይላሉ።
- ለችሎታማ ሁሉም የተፈጠረው በአላህ ችሎታ ነው። እዚህ ላይ በልዩ ሁኔታ አክብሮ እንደፈጠራቸው ሲናገር ነው “በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት” ማለቱ። የ“እጅ” ትርጓሜው “ችሎታ” ቢሆን ኖሮ ኣደም ከኢብሊስ ልዩነት ባልነበራቸው ነበር። ኢብሊስም በአላህ ችሎታ የተፈጠረ ነውና።
- እጅ ማለት ችሎታ ቢሆን ኖሮ {በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት} ሲለው ኢብሊስ “እኔስ በችሎታህ አይደል የተፈጠርኩት?” ይል ነበር። ግን አላለም። ይህም በዚህ ነጥብ ላይ ኢብሊስ ከነዚህ ሰዎች የተሻለ እምነት እንዳለው ያሳየናል። አዎ የጥፋት ቁንጮው ኢብሊስ በአላህ እጆች አልካደም። “የለም! በእጆችህ አልፈጠርከውም። ሲጀመር አንተ እጅ የት አለህና?!” አላለም! “ከኛ ወዲያ ተውሒድ አዋቂ ላሳር” የሚሉ አሕ -ባሾች ግን “አላህ እጅ የለውም” ሲሉ ኢብሊስ እንኳን ያልደፈረውን ጥፋት እየፈፀሙ ነው ያሉት።
#ማስረጃ_ሁለት፡-
~
(وَقَالَتِ ٱلۡیَهُودُ یَدُ ٱللَّهِ مَغۡلُولَةٌۚ غُلَّتۡ أَیۡدِیهِمۡ وَلُعِنُوا۟ بِمَا قَالُوا۟ۘ بَلۡ یَدَاهُ مَبۡسُوطَتَانِ یُنفِقُ كَیۡفَ یَشَاۤءُۚ)
{አይሁዶችም “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” አሉ። እጆቻቸው ይጠፈሩ! ይልቅ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው። እንደሚሻ ይለግሳል፡፡} [ማኢዳህ፡ 64]
አስተውሉ! አይሁዶቹ የተረ-ገሙት “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” በማለታቸው እንጂ ከነ ጭራሹ “አላህ እጅ የለውም” ብለው አይደለም። አሕ -ባሾችስ? የሁዶች እንኳን ያልተዳፈሩትን በመዳፈር ጭራሽ ለአላህ እጅ መኖሩን አስተባብለዋል። በዚህ ነጥብ ላይ ጥፋታቸው ከየሁዶቹ የከፋ ነው።
#ማስረጃ_ሶስት፡-
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
يُجْمَعُ المُؤْمِنُونَ يَوْمَ القِيَامَةِ فَيَقُولُونَ: لَوِ اسْتَشْفَعْنَا إِلَى رَبِّنَا فَيُرِيحُنَا مِنْ مَكَانِنَا هَذَا، فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ لَهُ: أَنْتَ آدَمُ أَبُو البَشَرِ، خَلَقَكَ اللَّهُ بِيَدِهِ، وَأَسْجَدَ لَكَ المَلاَئِكَةَ، وَعَلَّمَكَ أَسْمَاءَ كُلِّ شَيْءٍ فَاشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّنَا حَتَّى يُرِيحَنَا
{በቂያማ ቀን አማኞች ይሰበሰቡና ‘ወደ ጌታችን አማላጅ ብንልክና ከዚህ ቦታችን ቢያሳርፈን’ ይላሉ። ከዚያም ኣደም ዘንድ ይመጡና፡ ‘አንተ የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆንከው ኣደም ነህ። አላህ #በእጁ ፈጥሮሃል። መላእክትን አሰግዶልሃል። የሁሉን ነገር ስሞችም አስተምሮሃል። ያሳርፈን ዘንድ ጌታችን ዘንድ አማልደን’ ይላሉ። … } [አልቡኻሪይ፡ 7516]
#ማስረጃ_አራት፡-
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
يَأْخُذُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ سَمَاوَاتِهِ وَأَرَضِيهِ بِيَدَيْهِ، فَيَقُولُ: أَنَا اللهُ - وَيَقْبِضُ أَصَابِعَهُ وَيَبْسُطُهَا - أَنَا الْمَلِكُ " …
{አላህ - ዐዘ ወጀል - ሰማያቱንና ምድሮቹን #በሁለት_እጆቹ ይይዝና ‘እኔ ነኝ አላህ! - ጣቶቻቸውን እየጨበጡና እየዘረጉ- እኔ ነኝ ንጉሱ’ ይላል።} … [ሙስሊም፡ 2788]
አያዎችንና ሐዲሦችን በዚህ ላይ ልግታ። ለማሳጠር ስል የሰለፎችን ንግግርም አላካትትም። እውነታው እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ሳለ የሚጨናበሱ ሰዎች መኖራቸው የቢድዐ ዳፍንት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። “አሽዐ ሪዮች እና ወራሾቻቸው አሕ -ባሾችስ ለአቋማቸው ማጠናከሪያ ምን ይጠቅሳሉ?” ካላችሁ “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ከቁርኣንም፣ ከሐዲሥም፣ ከሰለፎች ንግግርም አንዲትም መረጃ መቼም አያመጡም። የሚጠቅሱት ሁለት ማምታቻ ነው።
[ማምታቻ አንድ]፡-
“የሚመስለው የለም” የሚለውንና መሰል አንቀፆችን በመጥቀስ ከሶሐቦች ያልተገኘ የራሳቸውን ትርጉም መስጠት። “ምን አገናኘው?” ካላችሁ እነሱ ዘንድ “እጅ አለው” ማለት ማመሳሰል ነው። በቃ! “እንዲያ ከሆነ ቁርኣኑ የማመሳሰልና የሺርክ ሰነድ ነው ማለት ነው” ብትሏቸው ምንም ሳያፍሩ “አዎ ዟሂሩ ኩ^ f ^ር ነው” ይላሉ። እንዲያ ከሆነ የመጀመሪያ አመሳሳዮች አላህና መልእክተኛው ናቸው ማለት ነው! አዑዙ ቢላህ! ሐቂቃው ግን አላህን እራሱን በገለፀበት፣ ነብዩም ﷺ አላህን በገለፁበት መግለፅ ፈፅሞ ማመሳሰል አለመሆኑ ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኢማም ኑዐይም ብኑ ሐማድ አልኹዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ
“አላህን ከፍጡሩ በየትኛውም ያመሳሰለ በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አደለም።” [ላለካኢይ፡ ቁ. 936]
ይሄ የኑዐይም ንግግር በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ቁልፍ የሆነ ቀመር ነው። ከውስጡ ሶስት ወሳኝ ህጎችን እናገኝበታለን። እነሱም፡-
1ኛ፡- አላህን በፍጡር ማመሳሰል ክህ -ደት ስለሆነ መጠንቀቅ እንደሚገባ።
2ኛ፡- አላህ እራሱን የገለፀበትን ማስተባበል ክህ -ደት እንደሆነ።
3ኛ፡- በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ ፈፅሞ ማመሳሰል እንደሌለ። (አሕ -ባሽ ግን ቁርኣንና ሐዲሥ በማመሳሰል የታጨቀ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።)
[ማምታቻ ሁለት]፡-

ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃቸው” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነሱ “ነወዊይ፣ ኢብኑ ሐጀር፣…” ይላሉ። ከቁርኣንና ሐዲሥ በተቃራኒ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ማጣቀስ ነውር ነው። “እናንተ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከነሱ በላይ ልታውቁት ነወይ?” ይላሉ። መልካም! እነሱስ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከሰለፎች በላይ ሊያውቁት ነውን? እስኪ የሰለፎቹን ተፍሲር መርምሩና አደብ ይኑራችሁ።
የአሕ -ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡-
وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان.
“የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን መስጠት (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290]
ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የአሕ -ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡-
وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان.
“የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን መስጠት (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290]
ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
እውን የኢብኑ ተይሚያ መታሰር የዐቂዳቸውን መበላሸት ያሳያልን?
~
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ በፅንፈኛ ሱፊዮችና አሽዐሪዮች በሃሰት ተከሰው፣ በግፍ ታስረው ወህኒ ቤት እያሉ ነው የሞቱት። የሚደንቀው ታዲያ እነዚህ አካላት እራሳቸው ከስሰው ካሳሰሯቸው በኋላ ወህኒ ቤት ውስጥ መሞታቸውን ዛሬም ድረስ ለትችት መጠቀማቸው ነው። ፊት ለፊት ተከራክሮ መርታት፣ ተናግሮ ማሳመን፣ ፅፎ ፍርድን ለአንባቢ መተው ነበር እንጂ ሹማምንትን ተጠቅሞ ካፈኑ በኋላ መክሰስማ ከፍትህ እልፍ አእላፍ ማይል የራቀ ነው። ጭራሽ እራሳቸው እየከሰሱ እራሳቸው እየፈረዱ ካሳሰሩ በኋላ የትላንት ፍርደ ገምድል ውሳኔያቸውን ዳግም ለማሳጣት ማዋል ግን የሐያእ መቅለልንም የሚያሳይ ነው።
አዎ ትላንት ጠላቶቻቸው ተረባርበው የዘመቱባቸው መረጃን በመረጃ የመሞገት አቅሙ ስላልነበራቸው ነበር። “ማን ይናገር የነበረ” ነውና በዚያው ዘመን የነበሩት ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪይ እንዲህ ይላሉ፡-
“በግብፅም በሻምም የፉቀሃእ እና የቃዲዎች ህብረት ተነስቶ በእግር በፈረስ ዘምቶበታል። ግና ሁሉንም በጣጥሶ ግልፅ በሆኑ ማስረጃዎች ብርቱ አያያዝ ያዛቸው። መቋቋም ሲያቅታቸው ግን መኳንንትና ገዢዎችን ተጠቀሙ።” [አረዱል ዋፊር፡ 84]
በድሩዲን አልዐይኒይም እንዲህ ይላሉ፡- “የታሰረው በግፍና በበደል ነው። ስለዚህ በዚህ ላይ የሚነወርበት ነገር የለም። በርካታ ታላላቅ ታቢዒዮች ላይም ግ ድያ፣ ተጠፍሮ መታሰር፣ ወህኒ መግባትና ባደባባይ መንቋሸሽ ደርሷል። አልኢማም አቡ ሐኒፋ ረዲየላሁ ዐንሁ ታስረዋል፣ የሞቱትም በእስር ላይ እያሉ ነው። ከዑለማእ አንድ እንኳን መታሰራቸው ሐቅ ነው ያለ አለን? ኢማሙ አሕመድም እውነትን በመናገራቸው ሳቢያ ታስረዋል፣ ተጠፍረዋል። ኢማሙ ማሊክም በጂራፍ ከባድ ድብደባ ተደብድበዋል። ኢማሙ ሻፊዕይም ከየመን ባግዳድ ተጠፍረው ታስረው ተወስደዋል። ስለዚህ በነዚያ ታላላቅ ኢማሞች ላይ የደረሰው አይነት በዚህ ኢማም ላይ ቢደርስበት እንግዳ አይደለም።” [አሸሃደቱ ዘኪያህ፡ 76-77]
ስለዚህ መታሰርና መገፋት በኢብኑ ተይሚያ አልተጀመረም። አልዐይኒይ ከጠቀሷቸው ውጭ ሌሎችም በርካታ ዑለማዎች በግፍ ተገ ድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተንገላተዋል። ሰዒድ ብኑ ጁበይር፣ ሰዒድ ብኑል ሙሰይብ፣ ሐሰኑል በስሪ፣ ቡኻሪ፣… ብዙ ግፍ ካስተናገዱ ዑለማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህ ሁሉ ምሁራን በላይም ነቢያት ተንገላተዋል። ለዚህም ነው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው፡-
“ከሰው ሁሉ ፈተና የሚበረታባቸው ነቢያት ናቸው። ከዚያም ታላላቅ ሰዎች እንደ ደረጃቸው። ሰው በዲኑ ልክ ይፈተናል። ዲኑ ጠንካራ ከሆነ ፈተናው ይበረታል። ዲኑ ላይ መሳሳት ካለ በዲኑ ልክ ይፈተናል።” [አሶሒሐህ፡ 143]
አልኢማም ኢብኑል ቀይም ረሑመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በጥንት ዘመን ሰልማኑል ፋሪሲይ የታደሉት ማስረጃ ከአባቶቻቸው የእሳት አምልኮ እምነት ከፍ ቢያደርጋቸው ጊዜ በዚህ የባእድ አምልኮት ላይ አባታቸውን መሞገት ያዙ። በማስረጃ ሲረቱት ጊዜ ግን መልሱ እስራት ነበር የሆነው። ይሄ የሀሰት ተጣሪዎች ከጥንት ጀምሮ የሚቀባበሉት መልስ ነው። ፊርዐውንም ለሙሳ የሰጠው መልስ ይሄው ነበር።
لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ
‘ከኔ ውጭ አምላክን የምትይዝ ከሆነ በርግጥም ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ’ በማለት። ጀህሚያዎች ለኢማሙ አሕመድ የሰጧቸው መልስም ይሄው ነበር፣ ያኔ በአለንጋ የገረፏቸው ጊዜ። የቢድዐ ሰዎች ለሸይኹል ኢስላም የሰጡት መልስም ይሄው ነበር።” [አልፈዋኢድ፡ 53]
ኢብኑል ወርዲ ረሒመሁላህ የኢብኑ ተይሚያን ሞት ተከትሎ ከገጠሙት ረጅም የሃዘን መግለጫ ግጥም (ረሣእ) ውስጥ ጥቂት ልጭለፍ፡-
“ከገድሉ መድረስ ቢያቅታቸው … ከደረሰበት መድረሱ
በሴራ ራሳቸውን አቃጥለው … በምቀኝነት ታመሱ።
ታካች ሰነፎች ቢሆኑም … ከመልካም ፈለጉ የራቁ
እሱን ለመጉዳቱ ግን … የበቁ ናቸው የነቁ!”
“በናንተ የክፋት ስራ … አቤት አይ^ ሁድ ሲደሰት!
የባላጋራው መታወክ … ሰርግ ነውና ለጠ -ላት
ሹመት አልነበር ምኞቱ … ሃብት አልጠየቀ የሰፋ
ቅልቅል የለው ከናንተ … ገንዘብ ፈልጎ አልተጋፋ።
እስኪ ስለምን ጠልታችሁ … ስለምንስ ታሰረ?
እንዲህ ትገፉት ዘንድስ … ምን ክፋት ነበር የፈጠረ?”
“በምን እንዳሰራችሁት … ያኔ እሳቤያችሁ ሲገለጥ
ሳንነግራችሁ አንቀርም … ነገ ሲተከል ሲራጥ።
ይሄው ሞተ እፎይ በሉ … ይሰማችሁ ደስታ
ያሰኛችሁን ለጥጡ … ያለምንም ይሉኝታ።
ፍቱ እሰሩ እንዳሻችሁ … እግር ዘርጉ በሉ ፈታ
ምንጣፉ ተጠቀለለ … ይሄው ያ ጀግና ተረታ።”
[ታሪኹ ኢብኒል ወርዲ፡ 2/275-276]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 8/2013)

• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ብዙ ልጆች - በተለይም ወጣቶች - በእናቶች መሸፋፈን እና አጉል ውግንና ይበላሻሉ። "ለምን?" የሚል አባታቸውንም ጠላት አድርገው እንዲይዙ ይደረጋሉ። እንዲህ አይነት አያያዝ ልጆቹንም አይጠቅምም። አባትም እንዲጎዳ እና በገዛ ቤቱ ውስጡ ባይተዋር እንዲሆን ያደርጋል። ኋላ ከመፀፀት በጊዜ ማስተካከል ይሻላል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Umdetul Ahkam #49
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-4️⃣ 9️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቤተ ክርስቲያን እንዳይመስላችሁ ፣ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ፣ ገርጂ የሚገኘው ኮሪያ ሆስፒታል። Myung Sung Christian Medical Center .
እስኪ ገልብጠን እንየው። ቤቱ ለታካሚው ኢስላማዊ ትምህርት የሚሰጥበት፣ ኢስላማዊ ጥቅሶች የተለጣጠፉበት፣ ወደ ኢስላም የሚጣሩ በራሪ ወረቀቶች እዚህም እዚያም የተቀመጡበት፣ በሩ ላይ በትልቁ "አላህ አንድ ነው። አይወልድም፤ አይወለድም" የሚል ደማቅ ፅሁፍ ያለበት Islamic Medical Center የሚል ቢሆን ብላችሁ አስቡ። Ministry of Health,Ethiopia ራሱ ዝም አይልም ነበር። በሲዳማ ክልል እና በወላይታ በመንግስት ሆስፒታል ጭምር ተመሳሳይ ነገር አለ።