Telegram Web Link
እውን የኢብኑ ተይሚያ መታሰር የዐቂዳቸውን መበላሸት ያሳያልን?
~
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ በፅንፈኛ ሱፊዮችና አሽዐሪዮች በሃሰት ተከሰው፣ በግፍ ታስረው ወህኒ ቤት እያሉ ነው የሞቱት። የሚደንቀው ታዲያ እነዚህ አካላት እራሳቸው ከስሰው ካሳሰሯቸው በኋላ ወህኒ ቤት ውስጥ መሞታቸውን ዛሬም ድረስ ለትችት መጠቀማቸው ነው። ፊት ለፊት ተከራክሮ መርታት፣ ተናግሮ ማሳመን፣ ፅፎ ፍርድን ለአንባቢ መተው ነበር እንጂ ሹማምንትን ተጠቅሞ ካፈኑ በኋላ መክሰስማ ከፍትህ እልፍ አእላፍ ማይል የራቀ ነው። ጭራሽ እራሳቸው እየከሰሱ እራሳቸው እየፈረዱ ካሳሰሩ በኋላ የትላንት ፍርደ ገምድል ውሳኔያቸውን ዳግም ለማሳጣት ማዋል ግን የሐያእ መቅለልንም የሚያሳይ ነው።
አዎ ትላንት ጠላቶቻቸው ተረባርበው የዘመቱባቸው መረጃን በመረጃ የመሞገት አቅሙ ስላልነበራቸው ነበር። “ማን ይናገር የነበረ” ነውና በዚያው ዘመን የነበሩት ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪይ እንዲህ ይላሉ፡-

“በግብፅም በሻምም የፉቀሃእ እና የቃዲዎች ህብረት ተነስቶ በእግር በፈረስ ዘምቶበታል። ግና ሁሉንም በጣጥሶ ግልፅ በሆኑ ማስረጃዎች ብርቱ አያያዝ ያዛቸው። መቋቋም ሲያቅታቸው ግን መኳንንትና ገዢዎችን ተጠቀሙ።” [አረዱል ዋፊር፡ 84]

በድሩዲን አልዐይኒይም እንዲህ ይላሉ፡- “የታሰረው በግፍና በበደል ነው። ስለዚህ በዚህ ላይ የሚነወርበት ነገር የለም። በርካታ ታላላቅ ታቢዒዮች ላይም ግ ድያ፣ ተጠፍሮ መታሰር፣ ወህኒ መግባትና ባደባባይ መንቋሸሽ ደርሷል። አልኢማም አቡ ሐኒፋ ረዲየላሁ ዐንሁ ታስረዋል፣ የሞቱትም በእስር ላይ እያሉ ነው። ከዑለማእ አንድ እንኳን መታሰራቸው ሐቅ ነው ያለ አለን? ኢማሙ አሕመድም እውነትን በመናገራቸው ሳቢያ ታስረዋል፣ ተጠፍረዋል። ኢማሙ ማሊክም በጂራፍ ከባድ ድብደባ ተደብድበዋል። ኢማሙ ሻፊዕይም ከየመን ባግዳድ ተጠፍረው ታስረው ተወስደዋል። ስለዚህ በነዚያ ታላላቅ ኢማሞች ላይ የደረሰው አይነት በዚህ ኢማም ላይ ቢደርስበት እንግዳ አይደለም።” [አሸሃደቱ ዘኪያህ፡ 76-77]

ስለዚህ መታሰርና መገፋት በኢብኑ ተይሚያ አልተጀመረም። አልዐይኒይ ከጠቀሷቸው ውጭ ሌሎችም በርካታ ዑለማዎች በግፍ ተገ ድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተንገላተዋል። ሰዒድ ብኑ ጁበይር፣ ሰዒድ ብኑል ሙሰይብ፣ ሐሰኑል በስሪ፣ ቡኻሪ፣… ብዙ ግፍ ካስተናገዱ ዑለማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህ ሁሉ ምሁራን በላይም ነቢያት ተንገላተዋል። ለዚህም ነው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው፡-
“ከሰው ሁሉ ፈተና የሚበረታባቸው ነቢያት ናቸው። ከዚያም ታላላቅ ሰዎች እንደ ደረጃቸው። ሰው በዲኑ ልክ ይፈተናል። ዲኑ ጠንካራ ከሆነ ፈተናው ይበረታል። ዲኑ ላይ መሳሳት ካለ በዲኑ ልክ ይፈተናል።” [አሶሒሐህ፡ 143]

አልኢማም ኢብኑል ቀይም ረሑመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በጥንት ዘመን ሰልማኑል ፋሪሲይ የታደሉት ማስረጃ ከአባቶቻቸው የእሳት አምልኮ እምነት ከፍ ቢያደርጋቸው ጊዜ በዚህ የባእድ አምልኮት ላይ አባታቸውን መሞገት ያዙ። በማስረጃ ሲረቱት ጊዜ ግን መልሱ እስራት ነበር የሆነው። ይሄ የሀሰት ተጣሪዎች ከጥንት ጀምሮ የሚቀባበሉት መልስ ነው። ፊርዐውንም ለሙሳ የሰጠው መልስ ይሄው ነበር።
لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ
‘ከኔ ውጭ አምላክን የምትይዝ ከሆነ በርግጥም ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ’ በማለት። ጀህሚያዎች ለኢማሙ አሕመድ የሰጧቸው መልስም ይሄው ነበር፣ ያኔ በአለንጋ የገረፏቸው ጊዜ። የቢድዐ ሰዎች ለሸይኹል ኢስላም የሰጡት መልስም ይሄው ነበር።” [አልፈዋኢድ፡ 53]

ኢብኑል ወርዲ ረሒመሁላህ የኢብኑ ተይሚያን ሞት ተከትሎ ከገጠሙት ረጅም የሃዘን መግለጫ ግጥም (ረሣእ) ውስጥ ጥቂት ልጭለፍ፡-

“ከገድሉ መድረስ ቢያቅታቸው … ከደረሰበት መድረሱ
በሴራ ራሳቸውን አቃጥለው … በምቀኝነት ታመሱ።
ታካች ሰነፎች ቢሆኑም … ከመልካም ፈለጉ የራቁ
እሱን ለመጉዳቱ ግን … የበቁ ናቸው የነቁ!”

“በናንተ የክፋት ስራ … አቤት አይ^ ሁድ ሲደሰት!
የባላጋራው መታወክ … ሰርግ ነውና ለጠ -ላት
ሹመት አልነበር ምኞቱ … ሃብት አልጠየቀ የሰፋ
ቅልቅል የለው ከናንተ … ገንዘብ ፈልጎ አልተጋፋ።
እስኪ ስለምን ጠልታችሁ … ስለምንስ ታሰረ?
እንዲህ ትገፉት ዘንድስ … ምን ክፋት ነበር የፈጠረ?”

“በምን እንዳሰራችሁት … ያኔ እሳቤያችሁ ሲገለጥ
ሳንነግራችሁ አንቀርም … ነገ ሲተከል ሲራጥ።
ይሄው ሞተ እፎይ በሉ … ይሰማችሁ ደስታ
ያሰኛችሁን ለጥጡ … ያለምንም ይሉኝታ።
ፍቱ እሰሩ እንዳሻችሁ … እግር ዘርጉ በሉ ፈታ
ምንጣፉ ተጠቀለለ … ይሄው ያ ጀግና ተረታ።”

[ታሪኹ ኢብኒል ወርዲ፡ 2/275-276]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 8/2013)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ብዙ ልጆች - በተለይም ወጣቶች - በእናቶች መሸፋፈን እና አጉል ውግንና ይበላሻሉ። "ለምን?" የሚል አባታቸውንም ጠላት አድርገው እንዲይዙ ይደረጋሉ። እንዲህ አይነት አያያዝ ልጆቹንም አይጠቅምም። አባትም እንዲጎዳ እና በገዛ ቤቱ ውስጡ ባይተዋር እንዲሆን ያደርጋል። ኋላ ከመፀፀት በጊዜ ማስተካከል ይሻላል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (58 minutes)
Umdetul Ahkam #49
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:- 4️⃣9️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 210፣ ሐዲሥ ቁ. 353
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቤተ ክርስቲያን እንዳይመስላችሁ ፣ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ፣ ገርጂ የሚገኘው ኮሪያ ሆስፒታል። Myung Sung Christian Medical Center .

እስኪ ገልብጠን እንየው። ቤቱ ለታካሚው ኢስላማዊ ትምህርት የሚሰጥበት፣ ኢስላማዊ ጥቅሶች የተለጣጠፉበት፣ ወደ ኢስላም የሚጣሩ በራሪ ወረቀቶች እዚህም እዚያም የተቀመጡበት፣ በሩ ላይ በትልቁ "አላህ አንድ ነው። አይወልድም፤ አይወለድም" የሚል ደማቅ ፅሁፍ ያለበት Islamic Medical Center የሚል ቢሆን ብላችሁ አስቡ። Ministry of Health,Ethiopia ራሱ ዝም አይልም ነበር። በሲዳማ ክልል እና በወላይታ በመንግስት ሆስፒታል ጭምር ተመሳሳይ ነገር አለ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ከኛ ይልቅ ሌሎች ናቸው የሚቀርቧቸው።
በ1ኛው ቪዲዮ ላይ ከነሷራ ጋር ስላላቸው ፍቅር፣ መተሳሰብ እና መተባበር ይገልፃል።
በ2ኛው ቪዲዮስ? ሰለፊያውን አጥፉልን እያለ የኢህአዴግ ሰዎችን የተማፀነበት ነው። እንዲህ ነበር ያለው :-

"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"
.
ያለ ምክንያት አይደለም እንደ ዘመድኩን በቀለ፣ አባይነህ ካሴ፣ ሀብታሙ አያሌው ፣ ወዘተ ያሉ ዲያቆኖችና ጭፍራዎቻቸው ልባቸው ውልቅ እስከሚል ድረስ "ሙፍቲ፣ ሙፍቲ " የሚሉት። እነዚህ አካላት የነ "ሙፍቲ ነባሩ እስልምና" ሙስሊሙን የሚጠላ፣ ነሷራውን ግን የሚያከብር እንደሆነ በሚገባ ለይተዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሙስጠፋ ዐብደላህ የቤት ኪራይ የምትችል ሴት እየተፈለገለት ነው። ግን ሴት ለምን? የቤት ኪራይ ችላ የምታገባው ለማለት ነው? ወይስ ሌላ ነው ሚስጥሩ? ለመስጂድ ግንባታ፣ አቅመ ደካሞችን ለማገዝ፣ የቲሞትን ለመርዳት፣ ለደዕዋ ስራ መዋጮ የሚጠይቁ ሰዎች "ጀምዒዮች ሌቦች ናቸው፣ አላማቸው ገንዘብ ነው፣ ... " እያሉ ላንቃቸው እስከሚበጠስ ይጮሃሉ። ለግል ጥቅማቸው ሲሆን ለኢቃማ፣ ለቤት ኪራይ፣ ... ልመና ውስጥ ይገባሉ።

ደግሞ እየደጋገሙ "አደራ በኔና ባንተ መሀል የሚቀር ሚስጥር ነው" ይባባላሉ። ሚስጥር!

ለማንኛውም ሴቶች ተጠንቀቁ። እንደምትሰሙት በቀዳሚነት ያነጣጠሩት ሴቶችን ለመጥለፍ ነው። ገንዘባችሁን ተጠንቀቁ። ከዚያ በላይ ዲናችሁን እንዳይዘርፏችሁ ተጠንቀቁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ኢብኑ ማጀህ (273 ሂ.)፡-
~
ኢብኑ ማጀህ ከስድስቱ ታዋቂ የሐዲሥ ኪታቦች (ሶሒሕ አልቡኻሪይ፣ ሶሒሕ ሙስሊም፣ ሱነን አቢ ዳውድ፣ ሱነን አነሳኢይ፣ ሱነን ኢቲርሚዚይ እና ሱነን ኢብኒ ማጀህ) ውስጥ የአንዱ ሰብሳቢ ናቸው።

በታዋቂው ሱነናቸው ውስጥ “بَابٌ فِيمَا أَنْكَرَتِ الْجَهْمِيَّةُ” (ጀህሚያዎች ያስተባበሏቸውን ነጥቦች የሚመለከት) የሚል ርእስ ቋጥረዋል። ጀህሚያ ማለት ብዙ ጥመቶችን ያቀፈ አንጃ ሲሆን በሰፊው ከሚታወቁ ጥመቶቹ ውስጥ አንዱ የአላህን ሲፋት (መገለጫዎች) የሚያስተባብል መሆኑ ነው። ለምሳሌ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን፣ በየ ሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ መውረዱን፣ ለአላህ በቁርኣንና በሐዲሥ እንደተገለፀው ፊት፣ እጅ፣ ... መኖሩን አይቀበልም ይሄ ቡድን። ከዚህ ጥፋቱ ውስጥ በብዙዎቹ አሽዐሪዮች (አሕ ^ባሾች) ይጋሩታል። ስለዚህ ኢብኑ ማጀህ ረሒመሁላህ በጀህሚያ ላይ የሰጡት ምላሽ ለአሕ ^ባሽም ይሆናል።

ከላይ በተጠቀሰው ርእሳቸው ኢብኑ ማጀህ የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የያዙ ሐዲሦችን ዘርዝረዋል። ከነዚህ ውስጥ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያመላክቱ ይገኙበታል። ለምሳሌ ያህል ሐዲሥ ቁ. 193፣ 194 መመልከት ይቻላል።

በተጨማሪም ተከታዩን ሐዲሥ አስፍረዋል።

ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

الْمَيِّتُ تَحْضُرُهُ الْمَلَائِكَةُ، فَإِذَا كَانَ الرَّجُلُ صَالِحًا قَالُوا : اخْرُجِي أَيَّتُهَا النَّفْسُ الطَّيِّبَةُ، كَانَتْ فِي الْجَسَدِ الطَّيِّبِ، اخْرُجِي حَمِيدَةً، وَأَبْشِرِي بِرَوْحٍ وَرَيْحَانٍ، وَرَبٍّ غَيْرِ غَضْبَانَ. فَلَا يَزَالُ يُقَالُ لَهَا ذَلِكَ حَتَّى تَخْرُجَ، ثُمَّ يُعْرَجُ بِهَا إِلَى السَّمَاءِ، فَيُفْتَحُ لَهَا، فَيُقَالُ : مَنْ هَذَا ؟ فَيَقُولُونَ : فُلَانٌ. فَيُقَالُ : مَرْحَبًا بِالنَّفْسِ الطَّيِّبَةِ، كَانَتْ فِي الْجَسَدِ الطَّيِّبِ، ادْخُلِي حَمِيدَةً، وَأَبْشِرِي بِرَوْحٍ وَرَيْحَانٍ، وَرَبٍّ غَيْرِ غَضْبَانَ. فَلَا يَزَالُ يُقَالُ لَهَا ذَلِكَ، حَتَّى يُنْتَهَى بِهَا إِلَى السَّمَاءِ الَّتِي فِيهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ
{ሟች ጣእረተ-ሞት ላይ ሲሆን መላእክት ይቀርቡታል። ሰውየው ደግ ከሆነ “አንቺ ከጥሩ አካል ውስጥ የነበርሽዋ ንፁህ ነፍስ ሆይ! ውጪ በእረፍትና በመልካም ሲሳይ ካልተቆጣው ጌታ ዘንድም አብሽሪ” ይሏታል። እስከምትወጣ ድረስ እንዲህ ሲባል ይቆያል። ከዚያም ወደ ሰማይ እንድትወጣ ትደረጋለች። እንዲከፈትላት ፈቃድ ይጠየቃል። “ማነው ይሄ?” ሲባል ይጠየቃል። “እገሌ ነው” ይባላል። “ከጥሩ አካል ውስጥ የነበረሽዋ ጥሩዋ ነፍስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣሽ! ውጪ። በእረፍትና በመልካም ሲሳይ ካልተቆጣው ጌታ ዘንድም አብሽሪ” ይባላል። አላህ - ዐዘ ወጀለ - ወዳለበት ሰማይ እስከሚደረስ ድረስ እንዲሁ እየተባለ ትቀጥላለች።} [ሱነኑ ኢብኒ ማጀህ፡ 4262]

ሐዲሡን በርካታ ሊቃውንት ሶሒሕ እንደሆነ ገልፀዋል።

በአሕ ^ባሽ ሃይማኖት መሰረት ኢብኑ ማጀህ ሙጀሲም እንጂ ሙስሊም አይደሉም። አሕ ^ባሽ ከነብዩ ﷺ ሐዲሥ ያፈነገጠ መንገድ ነው። ከቀደምት የሐዲሥ ሊቃውንት መዝሀብ ያፈነገጠ መንገድ ነው። ይልቁንም ኢብኑ ማጀህ እንዳሉት የጀህሚያ መንገድ ነው። አሕ ^ባሽ ከኸዋ ^ ሪጅ የከፋ ተስፈንጣሪ አንጃ ነው። ኸዋ ^ ሪጅ ከባባድ ወንጀል ላይ የወደቁ፣ ጥፋት የፈፀሙ ሰዎችን ነው ከኢስላም የሚያስወጡት። አሕ ~ ባሽ ግን ራሱ ጥመት ላይ ወድቆ፣ የራሱ መጥመም አልበቃ ብሎ፣ ክህ . ደቴን ካልተቀበላችሁ ብሎ ነው ከሊቅ እስከ ደቂቅ በጅምላ ሙስሊሞችን ከኢስላም የሚያስወጣው። አሕ ^ባሽ ከሙስሊሞች ይልቅ ሌሎችን የሚወድና የሚያቀርብ፣ ከየ ሁድ ከነሷራ ጋር ተባብሮ ሙስሊሞችን ለማጥፋት የሚያሴር እጅግ መ ሰ ^ሪ ቡድን ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Menhaju salikin #49
Ibnu Munewor
ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 4️⃣9️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ደርስ
~
* ኪታቡ፦ አልአርበዑነ ነውዊየህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር
* ቦታ፦ በአሸዋ ሜዳ፣ ዘህራ መስጂድ (ኮንደሚኒየም አጠገብ)
* ጊዜ፦ ሰኞ እና ማክሰኞ
* ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የምትችሉ ኪታቡን ገዝታችሁ ያዙ። የማትችሉ pdf ፋይል በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦ https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/7390
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (43 minutes)
የሰላምታ አደብ
~
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

"ትንሽ በትልቅ ላይ፣ አላፊ በተቀማጭ ላይ፣ ጥቂት በብዙ ላይ ሰላምታ ያቅርብ።" [አልቡኻሪይ ፡ 6231]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
አልኢማም አቡ ዒሳ ሙሐመድ ብኑ ዒሳ አቲርሚዚይ (279 ሂ.) እና አሻዒራ
~
ቲርሚዚይ ረሒመሁላህ ከስድስቱ ታዋቂ የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የአንዱ ማለትም የሱነኑ ቲርሚዚይ ሰብሳቢ ናቸው። በቁርኣን እና በሐዲሥ የተገለፁ የአላህን ሲፋት እንደመጡ ያፀድቃሉ። በዚህ መልኩ በቀጥታ ዟሂር መልእክታቸውን ማፅደቅ ፈፅሞ ማመሳሰል እንዳልሆነ አስረግጠው ይናገራሉ። ለአላህ እጅ እንዳለው፣ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ፣ በየሌሊቱ እንደሚወርድ፣ ... ያፀድቃሉ። ይሄ መረጃዎቹን በቀጥታ መተርጎም ከሳቸው በፊት የነበሩ ዑለማእ አካሄድ እንደሆነ እና ከዚህ በተለየ የመረጃዎችን ጉልህ መልእክት (ዟሂሩን) እየቆለመሙ ሌላ ትርጉም መስጠት የአፈንጋጩ ጀህሚያ አንጃ አካሄድ እንደሆነ በግልፅ አስፍረዋል። ንግግሮቻቸውን ላስፍር :-

#መረጃ_አንድ

{አላህ ሶደቃን ተቀብሎ በቀኙ ይይዛታል…} የሚለውን ሐዲሥ “ሐሰኑን ሶሒሕ” በማለት ደረጃውን ከገለፁ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦

وَقَدْ قَالَ غَيْرُ وَاحِدٍ مِنْ أَهْلِ العِلْمِ فِي هَذَا الحَدِيثِ وَمَا يُشْبِهُ هَذَا مِنَ الرِّوَايَاتِ مِنَ الصِّفَاتِ: وَنُزُولِ الرَّبِّ تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا، قَالُوا: قَدْ تَثْبُتُ الرِّوَايَاتُ فِي هَذَا وَيُؤْمَنُ بِهَا وَلَا يُتَوَهَّمُ وَلَا يُقَالُ: كَيْفَ؟ هَكَذَا رُوِيَ عَنْ مَالِكٍ، وَسُفْيَانَ بْنِ عُيَيْنَةَ، وَعَبْدِ اللهِ بْنِ الْمُبَارَكِ أَنَّهُمْ قَالُوا فِي هَذِهِ الأَحَادِيثِ: أَمِرُّوهَا بِلَا كَيْفٍ، وَهَكَذَا قَوْلُ أَهْلِ العِلْمِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ وَالجَمَاعَةِ، وَأَمَّا الجَهْمِيَّةُ فَأَنْكَرَتْ هَذِهِ الرِّوَايَاتِ وَقَالُوا: هَذَا تَشْبِيهٌ.
“በርካታ የእውቀት ባለቤቶች በዚህና መሰል የአላህን መገለጫዎችና የጌታችንን -ተባረከ ወተዓላ - በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ መውረድ በሚጠቁሙ ሐዲሦች ላይ ‘ዘገባዎቹን በዚህ ላይ ማፅደቅ ይገባል፣ ይታመንባቸዋል እንጂ ግመታ (ወህም) ውስጥ አይገባም፤ እንዴት አይባልም’ ብለዋል። ከማሊክ፣ ከሱፍያን ብን ዑየይናና ከዐብዲላህ ብኒል ሙባረክ፣ ... በዚሁ መልኩ የተዘገበ ሲሆን በነዚህ ሐዲሦች ላይ ‘ያለ እንዴት አሳልፏቸው’ ብለዋል። ከአህለ ሱና ወልጀማዐ የሆኑ የሌሎች የእውቀት ባለቤቶች አቋምም እንዲሁ ነው። ጀህሚያዎች ግን እነዚህን ዘገባዎች የተቃወሙ ሲሆን ‘ይሄ ማመሳሰል ነው’ ብለዋል።

وَقَدْ ذَكَرَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي غَيْرِ مَوْضِعٍ مِنْ كِتَابهِ اليَدَ وَالسَّمْعَ وَالبَصَرَ، فَتَأَوَّلَتِ الجَهْمِيَّةُ هَذِهِ الآيَاتِ فَفَسَّرُوهَا عَلَى غَيْرِ مَا فَسَّرَ أَهْلُ العِلْمِ، وَقَالُوا: إِنَّ اللَّهَ لَمْ يَخْلُقْ آدَمَ بِيَدِهِ، وَقَالُوا: إِنَّ مَعْنَى اليَدِ هَاهُنَا القُوَّةُ.
وقَالَ إِسْحَاقُ بْنُ إِبْرَاهِيمَ: إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ، أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَإِذَا قَالَ: سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَهَذَا التَّشْبِيهُ. وَأَمَّا إِذَا قَالَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلَا يَقُولُ كَيْفَ، وَلَا يَقُولُ مِثْلُ سَمْعٍ، وَلَا كَسَمْعٍ، فَهَذَا لَا يَكُونُ تَشْبِيهًا، وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ}
“በርግጥም አላህ - ዐዘ ወጀል- በቁርኣኑ ብዙ ቦታዎች ላይ እጁን፣ መስማትና ማየቱን ጠቅሷል። ጀህሚያዎች ግን እነዚህን አንቀፆች ቆልምመው (‘ተእዊል’ አድርገው) ዑለማዎች ባልፈሰሩት መልኩ ፈሰሯቸው። ‘አላህ ኣደምን በእጁ አልፈጠረም’ አሉ። ‘እዚህ ላይ የእጅ ትርጓሜ ሃይል (ቁዋ) ነው’ አሉ።

ኢስሓቅ ብኑ ኢብራሂም እንዲህ ብለዋል፦ ‘ማመሳሰል የሚሆነው ‘እጁ እንደ እጄ ወይም የእጅ አምሳያ ነው፤ መስሚያው እንደ መስሚያዬ ወይም የመስሚያ አምሳያ ነው’ ሲል ነው። ‘መስሚያው እንደ (ፍጡር) መስሚያ ወይም አምሳያ ነው’ ካለ፣ ይሄ ነው ማመሳሰል። ያለ አኳኋን (ከይፍያ)፣ ያለ አምሳያ አላህ እንዳለው ብቻ ‘እጅ’፣ ‘መስሚያ’፣ ‘መመልከቻ’ አልለው’ ካለ ግን ይሄ ማመሳሰል አይሆንም። ይህም ከፍ ያለው አላህ በቁርኣኑ እንዲህ እንዳለው ነው፦ {የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው።}” [ሱነኑ ቲርሚዚይ፡ ሐዲሥ ቁ. 662]

ከዚህ ንግግራቸው ምን እንወስዳለን?

1. የአላህን ሲፋት የሚጠቁሙ መረጃዎችን በተመለከተ የቲርሚዚይ እና የቀደምት ሰለፎች አቋም በቀጥታ መተርጎምና ማፅደቅ እንደሆነ።
2. ሲያፅድቁ ማመሳሰልና ከይፊያ መስጠት ውስጥ የሚገቡ እንዳልነበሩ።
3. ሰለፎቹ ዘንድ የአላህን ሲፋት በቀጥታ ማፅደቅ ፈፅሞ ማመሳሰል እንዳልሆነ።
4. በቀጥታ ማፅደቁ ማመሳሰል ይሰጣል እያሉ የሚሞግቱት እና በዚህ ሰበብ ተእዊል እያደረጉ ሌላ ትርጉም የሚሰጡት ጀህሚያዎች እንደሆኑ ተገልፆ እናገኛለን። ይሄ ኢማሙ ቲርሚዚይ የጀህሚያ አቋም ነው ብለው የገለፁት ዛሬ የአሸ ዐ ሪዮች/ የአሕባሾች አቋም ነው። ከዚህም የምንረዳው እነዚህ አካላት መዝሀባቸው የጥንቶቹ ሰለፎች የነ ቲርሚዚይ ሳይሆን የጀህሚያ መዝሀብ እንደሆነ ነው።

#መረጃ_ሁለት

በተጨማሪም አልኢማሙ ቲርሚዚይ አላህ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፡-
وَعِلْمُ اللهِ وَقُدْرَتُهُ وَسُلْطَانُهُ فِي كُلِّ مَكَانٍ، وَهُوَ عَلَى العَرْشِ كَمَا وَصَفَ فِي كِتَابهِ
“የአላህ እውቀቱ፣ ችሎታውና ስልጣኑ በሁሉም ቦታ ነው። እሱ ግን በመፅሐፉ እንደገለፀው ከዐርሹ በላይ ነው።” [ሱነኑ ቲርሚዚይ፣ ሐዲሥ ቁጥር፡ 3298]

እነዚህ የኢማም አቲርሚዚይ ንግግሮች ለአሕ - ባሽ ምቾት የሚነሱ ናቸው። የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የሚያራቁት ሰው ሱነኑ ቲርሚዚይን እቀራለሁ ብሎ ቢነሳ እነዚህ የቲርሚዚይ ንግግሮች ጦር ሆነው ይወጉታል። ሰላም አይሰጡትም። በቀጥታ የአላህን ሲፋት የሚያፀድቁት ቲርሚዚይ አሕ ^ ባሾች ዘንድ ሙጀሲም፣ ሙሸቢህ ካ ^ ፊ r እንጂ ሙስሊም አይደሉም። አስተዋይ ለሆነ አካል የአሕ ^ ባሽ አካሄድ ከጥንቱ፣ ከነባሩ ኢስላም ያፈነገጠ እንደሆነ ለመረዳት ይሄ ብቻውን በቂ ነው። መንገድ የሳቱ ወገኖቻችንን አላህ ልቦናቸውን ለሐቅ ክፍት ያድርግላቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ደርስ
~
* ኪታቡ፦ አልአርበዑነ ነውዊየህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር
* ቦታ፦ በአሸዋ ሜዳ፣ ዘህራ መስጂድ (ኮንደሚኒየም አጠገብ)
* ጊዜ፦ ሰኞ እና ማክሰኞ
* ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የምትችሉ ኪታቡን ገዝታችሁ ያዙ። የማትችሉ pdf ፋይል በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦ https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/7390
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2025/07/13 20:58:41
Back to Top
HTML Embed Code: