ወሊይ እና አታላይ ይለያያል
~
በሱፊያው ዓለም ሶላት የማይሰግዱ፣ ፆም የማይፆሙ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ በርካታ ወሊዮች አሉ። ለወንጀላቸው ሽፋን ይሆን ዘንድ “ትልቅ ወሊይ ለሰዎች ሲታይ ይወነጅላል። በሐቂቃው ግን ወንጀለኛ አይደለም” በማለት ኪታብ እስከመፃፍ የደረሱ አሉ። [አልኢብሪዝ፡ 2/23] እነዚህ የአላህ ሳይሆን የሸይ - ጧን ወሊዮች ናቸው። የአላህ ወሊዮች በኢማን የደመቁ፣ በተቅዋ ያሸበረቁ ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{أَلَاۤ إِنَّ أَوۡلِیَاۤءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَیۡهِمۡ وَلَا هُمۡ یَحۡزَنُونَ (62) ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ یَتَّقُونَ (63)}
{ንቁ! የአላህ ወሊዮች አይፈሩም አይተክዙም። እነሱም እነዚያ ያመኑትና የሚፈሩ የሆኑት ናቸው።} [ዩኑስ፡ 62-63]
የአላህ ወሊይ ለመሆን የሚያስፈልገው ኢማን እና አላህን መፍራት ነው። ኢማንና ተቅዋ ያለው ሁሉ ወንድ ይሁን ሴት፣ ነጋዴ ይሁን ገበሬ፣ ወታደር ይሁን ወዛደር፣ ሐኪምም ይሁን አስተማሪ፣ ሊስቲሮም ይሁን ተላላኪ ሁሉም የአላህ ወሊይ ነው። “አማኞች በሙሉ የአረሕማን ወሊዮች ናቸው። አላህ ዘንድ ይበልጥ የተከበሩት ይበልጥ ታዛዦቹና ይበልጥ ለቁርኣን ተከታዮቹ ናቸው” ይላሉ ጦሓዊይ ረሒመሁላህ። [አልዐቂደቱ ጦሓዊያህ፡ 64]
1. የአላህ ወሊይ ለመሆን የወሊይ ዘር መሆን አያስፈልግም። ጋርዶ መቀመጥን አይጠይቅም። አጃቢ እንዲኖር አይጠበቅም። ትንቢት መናገር አይደለም መስፈርቱ።
2. ወሊይ ሞቶ ቀርቶ በህይወት እያለም የሰው ልጅ ከሚያደርገው የተሻገረ ምንም ሊያደርግ አይቻለውም። እንዲያውም “ልጅ፣ ዝናብ፣ ሲሳይ፣ ጤና፣ ህይወት እሰጣለሁ፣ እነጥቃለሁ፣ ዱስቱር ያለን እጠቅማለሁ፣ እምቢ ያለን እጎዳለሁ” ብሎ የሚሞግት ካለ ራሱን ለአላህ ባላንጣ ያደረገ ሸይ .ጧን የሸይ .ጧን ወሊይ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
{أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ}
{ወይስ ያ ችግረኛ በለመነው ጊዜ መልስ የሚሰጥ፣ ክፉንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) (ይህን የሚያደርግ) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን?! ጥቂትንም አትገሰፁም!} [ነምል፡ 62]
ወሊይ ይቅርና ነብይም ሌሎችን መጥቀም መጉዳት የሚችልበት ስልጣን የለውም። ሃያሉ ጌታ ነብዩን ﷺ ይህን አዋጅ እንዲያሰሙ አዟቸዋል፦
{قُلۡ إِنِّی لَاۤ أَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا رَشَدࣰا (21) قُلۡ إِنِّی لَن یُجِیرَنِی مِنَ ٱللَّهِ أَحَدࣱ وَلَنۡ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدًا (22)}
{“እኔ ለናንተ መጉዳትንም ማቃናትንም አልችልም” በላቸው። “እኔ ከአላህ ቅጣት ማንም አያድነኝም። ከርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም” በላቸው።} [ጂን፡ 21-22]
3. ወሊይነት በኢማንና በተቅዋ የሚገኝ እንጂ ከአባት፣ ከአያት የሚወረስ ርስት አይደለም። ማንም ቢሆን በኢማኑ ያላገኘውን ደረጃ በዘሩ አይቆናጠጠውም። ነብዩ ﷺ {ስራው ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም} ብለዋል። [ሙስሊም፡ 2699]
4. ወሊይ ፍፁም የሆነ፣ የተናገረው መሬት ጠብ የማይል የሚመስላቸው አሉ። ወሊይ ሰው ነው። እንደማንኛውም ሰው ይሳሳታል። ነብዩ ﷺ {የሰው ልጅ ባጠቃላይ ተሳሳች ነው። ከተሳሳቾች ሁሉ በላጩ ተመላሾቹ ናቸው} ብለዋል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4515] ወሊዮች ሰዎች አይደሉም'ንዴ? ለነገሩ አንዳንዶቹ መላእክት ናቸው ብለው ነው የሚያምኑት። ለምሳሌ ያክል ሸይኽ ጫሊ እንዲህ ብለዋል እየተባለ ይወራል፦
"ኣደም ሲፈጠር - ጭቃው ሲብቦካ
ውሃ አግዘናል - እንደ መለይካ።"
በስሙ የተቀጠፈ ይሁን የራሱ ንግግር ይሁን አላውቅም። በሱፊያ ተረት ጭንቅላቱ የተዘጋ ካልሆነ በስተቀር እንዲህ አይነቱ የብልግና ንግግር ውሸት እንደሆነ ለማስረዳት መድከም የሚያስፈልግ አይደለም። ብቻ መዝዘንጋት የሌለበት ነገር እንኳን እነ ጫሊ፣ አብሬት፣ ወዘተ . ሶሐቦቹም መላእክት አልነበሩም።
5. የአላህ ወሊዮች የራሳቸው መጨረሻ የሚያስጨንቃቸው እንጂ “አብሽሩ እኛ አለንላችሁ”፣ “እኛን ያየ ጀነት ይገባል”፣ “ከቀብራችን የቆመ እሳት አይነካውም” የሚሉ አልነበሩም። “ሰላሳ የሚሆኑ የነብዩ ሶሓቦችን አግኝቻለሁ። ሁሉም በራሳቸው ላይ ን .ፍ ^ ቅ .ናን ይፈሩ ነበር” ይላሉ ታቢዒዩ ኢብኑ አቢ ሙለይካህ። [ፈትሑል ባሪ፡ 1/51]
6. የትኛውም የአላህ ወሊይ ከሸሪዐ አጥር የመውጣት ፍቃድ የለውም። ከነብዩ ﷺ ሸሪዐ የወጣ ሰው ትልቅ ወሊይ ሊሆን ቀርቶ ተራ ሙስሊምም መሆን አይችልም። ከ.ሃ.ዲ ነው። ኢስላም አንድ ነው። ስውር የሚባል ሌላ ሸሪዐ የለም። “ሸሪዐ ሁለት አይነት ነው። ግልፅና ስውር። ግልፁ የመሀይማን ነው። ስውሩ የወሊዮች ነው” የሚሉ ሰዎች ያለጥርጥር ከሃ * ዲዎች ናቸው። አላህ ሶላት የማይሰግድ አጭበርባሪ ወሊይ የለውም።
{فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٌ أَضَاعُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلشَّهَوَ ٰتِۖ فَسَوۡفَ یَلۡقَوۡنَ غَیًّا}]
{ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ፣ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የጀሀነምን ሸለቆ ያገኛሉ።} [መርየም፡ 59]
ታላቁ የአላህ ወሊይ ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ “ሶላት የተወ ሰው በኢስላም ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም” ብለዋል። [ሙወጦእ፡ 2/54] ስለዚህ “ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው”፣ “ሐረም በርሬ ሄጄ ነው የምሰግደው” የሚል ሰው አጭ *በርባሪ ማጅራት መቺ እንጂ የአላህ ወሊይ አይደለም መጠሪያው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 23/1444፣ ግንቦት 05/2015)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

ሃኪሞች የህዝብ ባለ ውለታዎች ናቸው። እንደ ሃገር ያለንበት ሁኔታ አጠቃላይ ግራ ቢሆንም ሁለ ነገራቸውን ለህዝብ የሰጡ ባለሙያዎች ራበን ሲሉ ማየት ያሳዝናል። እንደ ሃገር ከገባንበት ውጥንቅጥ አላህ ያውጣን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 202፣ ሐዲሥ ቁ. 341
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 202፣ ሐዲሥ ቁ. 341
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #47
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-4️⃣ 7️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 202፣ ሐዲሥ ቁ. 341
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 202፣ ሐዲሥ ቁ. 341
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተውሒድ ላይ አደራ
~
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የድሎት (የመልካም ህይወት) ባለቤቶች የሆኑት የተውሒድ ሰዎች ናቸው።"
[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 9/29]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የድሎት (የመልካም ህይወት) ባለቤቶች የሆኑት የተውሒድ ሰዎች ናቸው።"
[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 9/29]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ውሎህ ከማን ጋር ነው? ምን ይመስላል?
~
ሰው በአብዛኛው ውሎውን ይመስላል። ቁርኝቱ ከመጥፎ ሰዎች ጋር የሆነ ሰው ውስጡ ይደፈርሳል። ብዙ መጥፎ ልማዶችን ይወርሳል። በሱስ የተለከፉ ወገኖች በዚህ ወጥመድ ውስጥ የወደቁት በጓደኛ ነው።
- በጓደኛ ብልግና ውስጥ የተነከሩ አሉ።
- በጓደኛ ራሳቸውንም ሌሎችንም የሚጎዳ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ አሉ።
- በጓደኛ ቁማር ያናወዛቸው አሉ።
- በጓደኛ ከሶላት የራቁ አሉ።
- በጓደኛ በጠዋት በማታ በኳስ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ የተጠመዱ አሉ።
- በጓደኛ ሰንካላ ፍልስፍና ውስጥ ገብተው እምነታቸውን ያጡ ወይም አፋፍ ላይ ያሉ አሉ።
- በጓደኛ ስራቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ትዳራቸውን፣ ቤተሰባቸውን ያጡ አሉ።
በተቃራኒው ፡
- በጓደኛ ከሺርክ፣ ከቢድዐ፣ ከተለያዩ ወንጀሎች የወጡ፣ ወደ ዲን የመጡ አሉ።
- በጓደኛ ከወንጀል የራቁ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ትዳር የመሰረቱ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ስራ ያገኙ፣ የተሻለ አቅም የገነቡ አሉ።
- በጓደኛ ዲንም ዱንያም የተማሩ፣ እውቀታቸውን ያሰፉ አሉ።
- በጓደኛ ከነበሩበት ፈተና ወጥተው ተስፋቸውን ያለመለሙ፣ ነፍሳቸውን ያረጋጉ አሉ።
ስለዚህ፡
ጓደኛችን ማነው? ዝንባሌውና ተፅእኖውስ ወዴት ነው? ወደ ኸይር? ወይስ ወደ ሸር? ጓደኝነታችን አትራፊ ነው ወይስ አክሳሪ? የቁም ነገር ነው? ወይስ እንዲሁ መደበሪያ? ሂሳብ መስራትና መወሰን ይገባል።
ከዚያ በፊት እኛ ለጓደኞቻችን ምን አይነት ሰዎች ነን? ሰዎችን ወደ ሱስ፣ ወደ ወንጀል፣ ወደ ክፋት የምንጎትት ከሆንን ወዮ ለኛ! በራሳችን ብቻ ሳይሆን ባጠፋናቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ነን። ጓደኝነታችን የኸይር ሰበብ ከሆነ ግን መታደል ነው።
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ሰውበጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው" ይላሉ።
* አቡበክር ሲዲቅ ህይወታቸውን ሙሉ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ጓደኛ ነበሩ። እንደሳቸው ያተረፈ ማን አለ?
* አቡ ጧሊብ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አጎት ነው። ደጀናቸው፣ መከታቸው ነበር። የሳቸውን እውነተኝነት በሚገባ ያውቃል። መጥፎ ጓደኞቹ ግን ሐቅ እንደሆነ ለሚመሰክርበት ኢስላም እጅ እንዳይሰጥ ይልቁንም በሺርኩ ላይ እንዲሞት አድርገውታል። ከዚህ በላይ የመጥፎ ጓደኛን አደጋ የሚያሳይ ምን አለ?
ስለዚህ፡ ጓደኞችህ/ሽ እነማን ናቸው? ወዴት እየወሰዱህ/ሽ ነው? ወዴትስ እየወስድካቸው /ሻቸው ነው? ከልብ መገምገምና ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ይገባል።

የ "ብያለሁ ንጉስ" - ጋንጃሞ
~
ሰሞኑን ''አንድ እቃ በራሱ የማይገዛ ባንክ / ድርጅት "መኪና ልግዛላችሁ" ብሎ በተጠቃሚው ስም ሂሳብ ከፍሎ ትርፍ የሚጠይቅበት አሰራር የብድር ወለድ እንጂ የሽያጭ ውል አይደለም" የሚል ፅሁፍ ፅፌ ነበር። ስሙን አስሬ በመቀያየር የሚታወቀው ዐብዱልቃዲር ኑረዲን (ምናልባት ይህም እውነተኛ ስሙ ከሆነ) ከ10 ዓመት በፊት ብዬ ነበር እያለ ፅፏል። ልክ ዓለም ፀጥ ብሎ እሱ የጀመረው ሃሳብ ይመስለው ይሆን? ለማንኛውም
1. አንድ ሰው "ንብረት /ሚልክ" ያላደረገውን ነገር መሸጥ የለበትም የሚለው ሃሳብ መሰረቱ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ሲሆን በየ ደርሱ ላይ በስፋት የሚነሳ ነው። እሱ በቅርብ ጊዜ ያቀነቀነው ርእስ የመሰለው ደርስ አካባቢ በቅርብም በሩቅም ባለመኖሩ ነው። እንጂ በየ መሳጂዱ የኪታብ ደርስ ላይ የሚነሳ ነጥብ ነው። እኔ ራሴ የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም ስለዚህ ስናገር። በመንሀጁ ሳሊኪን እና በዑምደቱል አሕካም ደርሶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት አንስቼዋለሁ። የደምፅ ፋይሎች ይኖራሉ። ሰፋፊ ደርሶች ባሉባቸው መስጂዶች ደግሞ በተደጋጋሚ ይነሳል።
2ኛ. "ብዬ ነበር" ማለቱ የተለመደ የሰውየው ውሸት ነው። የሱ ጩኸት ይሄ አይደለም። የሱ ጩኸት "የፊያት መገበያያ ገንዘቦች በሸሪዐ ሚዛን ገንዘብ አይደሉም" የሚል ነው። ስለሆነም {አበላልጦ መዋዋል ወለድ/ አራጣ አይሆንም። በባንክ ቤት ሂሳብ ስትከፍቱ ቀጥታም በወለድ አድርጉትና በየወሩ ወለድ ይታሰብላችሁ} እያሉ መስበክ ነው የሱ "አብዮት"። ዐቅል ቢኖረው ኖሮ ይሄ ሊደብቀው የሚገባ፣ የሚያሳፍር ነውር እንጂ ክሬዲት ይሰጠኝ የሚያስብል ነገር አልነበረም። ግን በምን ዐቅሉ?
ሰውየው ከጫቱ ባልተናነሰ በውሸት ሱስ ተለክፏል።
- ወለድ ነፃ ስለሚባሉት ባንኮች እና ተያያዥ ነጥቦች ሂስ ከተነሳ ዘሎ ይመጣል፣ "ብዬ ነበር" ለማለት።
- "ስለ ዋጋ ግሽበት ሲወራ "ብያለሁኮ!" ይላል።
- ስለ ምንዛሬ ቀውስ ሲነሳ "የሚሰማኝ አጥቼ እንጂ ..." ይላል።
- "ብር ዋጋ እያጣ ስለሆነ ገንዘባችሁን በጥሬ ከምታስቀምጡ ንብረት ግዙበት" የሚል ሲያይ "ይሄው ቀድመው ስንት እንዳላሉኝ እኔ ወዳልኩት እየመጡ ነው፤ ገና መቼ!" እያለ ጮቤ ይረግጣል።
ሰው ዛሬ ከባንክ በወለድ ለመበደር ሰበብ ነው የሚፈልገው። ይሄ ጫት ላይ ተወዝቶ በምርቃና ወደ አራጣ የሚጣራ ሰባኪ ጥሩ ጋሻ ሆኗቸዋል። ሰውየው "የብር ግሽበት"፣ "የዋጋ ንረት"፣ በንዲህ አይነት ቀውስ ጊዜ ሰዎችን ንብረት እንዲይዙ መምከር የሱ የፈጠራ ግኝት ይመስለዋል። ከዚያ ስለነዚህ ጉዳዮች የሚያወራ ባየ ቁጥር "ወደኔ ሃሳብ እየመጡ ነው" ይላል። እነዚህ ቀውሶችና ተያያዥ ጉዳዮች አንተ ሳትፈጠርም በፊት የነበሩ ናቸው። እንዲያውም ወርቅ ከመገበያያነት ሳይጠፋ በፊትም ነበሩ። በ1933 አሜሪካ ላይ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ደግሞ ጀርመን ላይ የገጠመው በታሪክ ጎልተው የሚጠቀሱ ናቸው። በሌሎችም ሃገራት የገጠመ ነው።
ከወለድ ነፃ የሚባሉት ባንኮች ላይ የሚሰነዘሩ ሂሶችም ዛሬ የጀመሩ አይደሉም። እሱ 10 ዓመት ነዋ የሚለው? ከ 26 ዓመታት በፊት የሞቱት ሸይኹል አልባኒይ ስለነዚህ ባንኮች ጠንካራ ሂስ አላቸው። አለማወቅህ ነው ደረትህን ገልብጠህ እንድታወራ የሚያደርግህ።
ለማንኛውም የሸሪዐ ሑክም (ብይን) መሰረቱ ቁርአንና ሐዲሥ ነው። ጉዳዩ ቀድሞ ያልነበረ ወቅታዊ ሆኖ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ቁርአንና ሐዲሥ ውስጥ ምላሹ የማይገኝ ከሆነ ዑለማዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ ካጠኑ በኋላ ከሸሪዐ ማስረጃዎች ጋር አገናዝበው ብይን ይሰጣሉ። ጉዳዮቹ ውስብሰብ በሚሆኑ ጊዜ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎች ጠርተው ዝርዝር ማብራሪያ እና በቂ ግንዛቤ ከያዙ በኋላ ከብዙ አቅጣጫ ገምግመው ፈትዋ የሚሰጡባቸው ተቋማትም አሉ። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ እንደ ጋንጃሞ ያሉ ጥራዝ ነጠቆች ግን ስንዝር የአካዳሚ እውቀታቸው ላይ ተመርኩዘው ምንም በማያውቁት የሸሪዐ ጉዳይ ገብተው ያቦካሉ። የሚያጨበጭቡለትን ተመልከቱ። ወይ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ናቸው። ወይ ደግሞ የሸሪዐ እውቀት አካባቢ የሌሉ የሱው ቢጤዎች ናቸው።
በአካዳሚ ትምህርት ፈትዋ አይሰጥም። የፀጉር ንቅለ ተከላ፣ ደም ልገሳ ፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝና፣ ... በሃኪሞች ስለሚተገበሩ ብቻ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለው ሸሪዐዊ ሑክም በሃኪም አይሰጥም። ፈትዋው የሚሰጠው በሸሪዐ ዓሊም ነው። ሃኪሙ "ዓሊሞቹ ስለዚህ ምን ያውቃሉ?" ቢል ይሄ ሞኝነቱን ነው የሚያሳየው። ፋይናንስ እና ኢኮኖሚውም ላይ እንዲሁ ነው። አንተ ስለዚህ ጉዳይ አስኮላ ተምረሃል ማለት በጉዳዩ ላይ የሸሪዐ ሑክም መስጠት ትችላለህ ማለት አይደለም። ያስተማረህ ገብሬ እንጂ የሸሪዐ ዓሊም አይደለም። ፈትዋው የሚሰጠው በዓሊሞች ነው። እነ ጋንጃሞ ግን ሳይነቁ እንደነቁ የሚያስቡ ናቸው። (وَتَحۡسَبُهُمۡ أَیۡقَاظࣰا وَهُمۡ رُقُودࣱۚ)
ጋንጃሞ ራሱን በባዶ እየቆለለ "በዚህ ክፍለ ዘመን በሙስሊም ሊቃውንት የተበየኑና ቀላል የማይባሉ ገንዘብ ነክ ሃይማኖታዊ ብያኔዎቻችን (ፈትዋዎቻችን) ሲታዩ ደግሞ ጥያቄውን ሳይረዳ መልስ እንደሚፅፍ ተማሪ ይመስላሉ" በማለት ከዑለማዎች በላይ አውቃለሁ የሚል ብ^ሽ ^ቅ ፍጡር ነው። ይሄ አነጋገሬ የሚጎረብጣችሁ እንዳላችሁ አውቃለሁ። ዑለማዎችን ጥያቄውን ሳይረዳ መልስ በሚፅፍ አለማወቁን እንኳ በማያውቅ ደ *ደብ ተማሪ እየመሰለ ራሱን የሚቆልልን ግብ ዝ የሚበዛበት ቃል አልተጠቀምኩም። እንዲህ አይነቱ ከንቱ ነው በትልልቅ ሸሪዐዊ ጉዳዮች ገብቶ ዑለማዎችን ገፈታትሮ ብቻውን ሊያቦካ የተነሳው። በርእሱ ላይ ካለው ግድፈቱ በላይ እንዲህ አይነቱ ድፍረቱ ነው ይበልጥ የሚያንገበግበው፡፡

አንድ ሰው "ይህን ላደርግ ምያለሁ!" ቢል የአላህን ስም ባይጠራበትም ልክ "ወላሂ ይህን ላደርግ" እንዳለ ሰው መሀላው ይቆጠራል ይላሉ ኢብኑ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ ኢብራሂም አነኸዒይ፣ ሱፍያን አሠውሪይ እና ሌሎችም። [ሚስኩል ኺታም፡ 5/205]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
በአንድ ጉዳይ ላይ ለምሳሌ "ይህንን ላላደርግ" ብሎ የማለ ሰው ረስቶ ወይም ጉዳዩ የማለበት ጉዳይ መሆኑን ባለማወቅ ቢፈጽም ማካካሻ (ከ * fa ራ) አይጠበቅበትም። አላህ እንዲህ ብሏል :-
{ وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا }
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ነገር ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
{ وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا }
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ነገር ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #48
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-4️⃣ 8️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 207፣ ሐዲሥ ቁ. 348
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን አላህ እጅ የለውም?
~
ህሊና ላለው ሰው “አላህ እጅ የለውም” የሚል እምነት አስቀያሚና እጅጉን የሚያሳፍር ነው። ግና አእምሯቸው በእምነት የለሾች ፍልስፍና በመበከሉ የተነሳ ይህንን አጉል እምነት ተውሒድ ያደረጉ፣ ይባስ ብሎም ያልተጋራቸውን በሙሽ^ ሪክነት የሚወነጅሉ አንጃዎች ተፈልፍለዋል። በዘመናችን ይህንን ጥፉ አመለካከት ከሚያራምዱ አንጃዎች ውስጥ “አሕ -ባሽ” ፊታውራሪ ነው። ይህ የአሕ -ባሽ አመለካከት ከሙዕተዚላ የተኮረጀ እምነት ነው። ለዚህም ሁለት አይነት መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።
1ኛ፡- የሙዕተዚላዎችን ስራዎች። ለምሳሌ የቃዲ ዐብዱል ጀባር አልሙዕተዚሊን ስራዎች። [ሸርሑ ኡሱሊል ኸምሳ፡ 228] [ሙተሻቢሁል ቁርኣን፡ 231]
2ኛ፡- አሕ -ባሾች እንከተላቸዋለን የሚሏቸው ኢማሞች ምስክርነት። ለምሳሌ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪና አቡ መንሱር አልበግዳዲ ይህ እምነት የሙዕተዚላ ዐቂዳ እንደሆነ መስክረዋል። [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 157፣ 167] [ኡሱሉዲን፡ 228]
ስለ ራሱም ይሁን ስለሌሎች ከማንም በላይ አዋቂ የሆነው ጌታ ግን እጅ እንዳለው በግልፅ ቋንቋ ይናገራል። መልእክተኛውም ﷺ እንዲሁ። ጥቂት ማስረጃዎችን እንመልከት፡-
#ማስረጃ_አንድ፦
~
(قَالَ یَـٰۤإِبۡلِیسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِیَدَیَّۖ )
{ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ?} [ሷድ፡ 75]
ከዚች አንቀፅ አባታችን ኣደም በአላህ እጆች የተፈጠሩ ክቡር ፍጡር እንደሆኑ ማንም ይርረዳል፡፡ አሕ -ባሽ ሲቀር። እነሱ ግን “እጅ”/ “የድ” የሚለውን “ችሎታ፣ ፀጋ ማለት ነው” ይላሉ።
- ለችሎታማ ሁሉም የተፈጠረው በአላህ ችሎታ ነው። እዚህ ላይ በልዩ ሁኔታ አክብሮ እንደፈጠራቸው ሲናገር ነው “በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት” ማለቱ። የ“እጅ” ትርጓሜው “ችሎታ” ቢሆን ኖሮ ኣደም ከኢብሊስ ልዩነት ባልነበራቸው ነበር። ኢብሊስም በአላህ ችሎታ የተፈጠረ ነውና።
- እጅ ማለት ችሎታ ቢሆን ኖሮ {በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት} ሲለው ኢብሊስ “እኔስ በችሎታህ አይደል የተፈጠርኩት?” ይል ነበር። ግን አላለም። ይህም በዚህ ነጥብ ላይ ኢብሊስ ከነዚህ ሰዎች የተሻለ እምነት እንዳለው ያሳየናል። አዎ የጥፋት ቁንጮው ኢብሊስ በአላህ እጆች አልካደም። “የለም! በእጆችህ አልፈጠርከውም። ሲጀመር አንተ እጅ የት አለህና?!” አላለም! “ከኛ ወዲያ ተውሒድ አዋቂ ላሳር” የሚሉ አሕ -ባሾች ግን “አላህ እጅ የለውም” ሲሉ ኢብሊስ እንኳን ያልደፈረውን ጥፋት እየፈፀሙ ነው ያሉት።
#ማስረጃ_ሁለት፡-
~
(وَقَالَتِ ٱلۡیَهُودُ یَدُ ٱللَّهِ مَغۡلُولَةٌۚ غُلَّتۡ أَیۡدِیهِمۡ وَلُعِنُوا۟ بِمَا قَالُوا۟ۘ بَلۡ یَدَاهُ مَبۡسُوطَتَانِ یُنفِقُ كَیۡفَ یَشَاۤءُۚ)
{አይሁዶችም “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” አሉ። እጆቻቸው ይጠፈሩ! ይልቅ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው። እንደሚሻ ይለግሳል፡፡} [ማኢዳህ፡ 64]
አስተውሉ! አይሁዶቹ የተረ-ገሙት “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” በማለታቸው እንጂ ከነ ጭራሹ “አላህ እጅ የለውም” ብለው አይደለም። አሕ -ባሾችስ? የሁዶች እንኳን ያልተዳፈሩትን በመዳፈር ጭራሽ ለአላህ እጅ መኖሩን አስተባብለዋል። በዚህ ነጥብ ላይ ጥፋታቸው ከየሁዶቹ የከፋ ነው።
#ማስረጃ_ሶስት፡-
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
يُجْمَعُ المُؤْمِنُونَ يَوْمَ القِيَامَةِ فَيَقُولُونَ: لَوِ اسْتَشْفَعْنَا إِلَى رَبِّنَا فَيُرِيحُنَا مِنْ مَكَانِنَا هَذَا، فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ لَهُ: أَنْتَ آدَمُ أَبُو البَشَرِ، خَلَقَكَ اللَّهُ بِيَدِهِ، وَأَسْجَدَ لَكَ المَلاَئِكَةَ، وَعَلَّمَكَ أَسْمَاءَ كُلِّ شَيْءٍ فَاشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّنَا حَتَّى يُرِيحَنَا
{በቂያማ ቀን አማኞች ይሰበሰቡና ‘ወደ ጌታችን አማላጅ ብንልክና ከዚህ ቦታችን ቢያሳርፈን’ ይላሉ። ከዚያም ኣደም ዘንድ ይመጡና፡ ‘አንተ የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆንከው ኣደም ነህ። አላህ #በእጁ ፈጥሮሃል። መላእክትን አሰግዶልሃል። የሁሉን ነገር ስሞችም አስተምሮሃል። ያሳርፈን ዘንድ ጌታችን ዘንድ አማልደን’ ይላሉ። … } [አልቡኻሪይ፡ 7516]
#ማስረጃ_አራት፡-
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
يَأْخُذُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ سَمَاوَاتِهِ وَأَرَضِيهِ بِيَدَيْهِ، فَيَقُولُ: أَنَا اللهُ - وَيَقْبِضُ أَصَابِعَهُ وَيَبْسُطُهَا - أَنَا الْمَلِكُ " …
{አላህ - ዐዘ ወጀል - ሰማያቱንና ምድሮቹን #በሁለት_እጆቹ ይይዝና ‘እኔ ነኝ አላህ! - ጣቶቻቸውን እየጨበጡና እየዘረጉ- እኔ ነኝ ንጉሱ’ ይላል።} … [ሙስሊም፡ 2788]
አያዎችንና ሐዲሦችን በዚህ ላይ ልግታ። ለማሳጠር ስል የሰለፎችን ንግግርም አላካትትም። እውነታው እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ሳለ የሚጨናበሱ ሰዎች መኖራቸው የቢድዐ ዳፍንት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። “አሽዐ ሪዮች እና ወራሾቻቸው አሕ -ባሾችስ ለአቋማቸው ማጠናከሪያ ምን ይጠቅሳሉ?” ካላችሁ “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ከቁርኣንም፣ ከሐዲሥም፣ ከሰለፎች ንግግርም አንዲትም መረጃ መቼም አያመጡም። የሚጠቅሱት ሁለት ማምታቻ ነው።
[ማምታቻ አንድ]፡-
“የሚመስለው የለም” የሚለውንና መሰል አንቀፆችን በመጥቀስ ከሶሐቦች ያልተገኘ የራሳቸውን ትርጉም መስጠት። “ምን አገናኘው?” ካላችሁ እነሱ ዘንድ “እጅ አለው” ማለት ማመሳሰል ነው። በቃ! “እንዲያ ከሆነ ቁርኣኑ የማመሳሰልና የሺርክ ሰነድ ነው ማለት ነው” ብትሏቸው ምንም ሳያፍሩ “አዎ ዟሂሩ ኩ^ f ^ር ነው” ይላሉ። እንዲያ ከሆነ የመጀመሪያ አመሳሳዮች አላህና መልእክተኛው ናቸው ማለት ነው! አዑዙ ቢላህ! ሐቂቃው ግን አላህን እራሱን በገለፀበት፣ ነብዩም ﷺ አላህን በገለፁበት መግለፅ ፈፅሞ ማመሳሰል አለመሆኑ ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኢማም ኑዐይም ብኑ ሐማድ አልኹዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ
“አላህን ከፍጡሩ በየትኛውም ያመሳሰለ በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አደለም።” [ላለካኢይ፡ ቁ. 936]
ይሄ የኑዐይም ንግግር በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ቁልፍ የሆነ ቀመር ነው። ከውስጡ ሶስት ወሳኝ ህጎችን እናገኝበታለን። እነሱም፡-
1ኛ፡- አላህን በፍጡር ማመሳሰል ክህ -ደት ስለሆነ መጠንቀቅ እንደሚገባ።
2ኛ፡- አላህ እራሱን የገለፀበትን ማስተባበል ክህ -ደት እንደሆነ።
3ኛ፡- በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ ፈፅሞ ማመሳሰል እንደሌለ። (አሕ -ባሽ ግን ቁርኣንና ሐዲሥ በማመሳሰል የታጨቀ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።)
[ማምታቻ ሁለት]፡-

ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃቸው” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነሱ “ነወዊይ፣ ኢብኑ ሐጀር፣…” ይላሉ። ከቁርኣንና ሐዲሥ በተቃራኒ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ማጣቀስ ነውር ነው። “እናንተ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከነሱ በላይ ልታውቁት ነወይ?” ይላሉ። መልካም! እነሱስ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከሰለፎች በላይ ሊያውቁት ነውን? እስኪ የሰለፎቹን ተፍሲር መርምሩና አደብ ይኑራችሁ።
የአሕ -ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡-
وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان.
“የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን መስጠት (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290]
ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012)
የቴሌግራም ቻናል፦