ጌታህ ረሺ አይደለም!
~
በበዳይ ሰው ልብ ላይ ቀስት የሆነች፣ በተበዳይ ሰው ልብ ላይ ደግሞ ፈውስ የሆነች አንዲት የቁርኣን አንቀፅ!
{ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِیࣰّا }
"ጌታህም ረሺ አይደለም።" [መርየም፡ 64]
.
ኮፒ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Umdetul Ahkam #50
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-5️⃣ 0️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሙሳ ሰዎች ቂሷ ለዑዝር ቢል ጀህል ማስረጃ
~
አላዋቂ ሰው ጥፋት ቢፈፅም ወንጀለኛ አይደለም። ሰው ወንጀለኛ የሚሆነው ሆነ ብሎ በሚፈፅመው ጥፋት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا}
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ግን ልቦቻችሁ አውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
ይሄ ሁሉንም የዲን ርእሶች የሚያካትት መሰረታዊ የሸሪዐ ህግ ነው። "ዐቂዳ ሲቀር"፣ "ኡሉሂያ ሲቀር" የሚለው የአንዳንዶች 'ኢስቲሥናእ' ጠንካራ መሠረት ላይ ያልቆመ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው።
ስለዚህ አንድ ሙስሊም ባለማወቅ ሺርክ ቢፈፅም ከኢስላም አይወጣም። ይህንን ከሚያስይዙ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ የሙሳ ሰዎች ታሪክ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَجَـٰوَزۡنَا بِبَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتَوۡا۟ عَلَىٰ قَوۡمࣲ یَعۡكُفُونَ عَلَىٰۤ أَصۡنَامࣲ لَّهُمۡۚ قَالُوا۟ یَـٰمُوسَى ٱجۡعَل لَّنَاۤ إِلَـٰهࣰا كَمَا لَهُمۡ ءَالِهَةࣱۚ قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمࣱ تَجۡهَلُونَ﴾
''የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ በጣዖቶቻቸው (ማምለክ) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ዘንድም አለፉ፡፡ 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው።" [አልአዕራፍ ፡ 138]
* ታሪኩ ምን ያስይዛል? እነዚህ የሙሳ ሰዎች፡
1ኛ፦ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ላይ ያዩትን የሺርክ ተግባር ለመፈፀም ጠይቀው እንደነበር፣
2ኛ፦ የጠየቁት ጉዳይ ከኢስላም የሚያስወጣ መሆኑን ባለማወቅ እንደሆነ፣
3ኛ፦ ባለማወቃቸውም የተነሳ ከኢስላም እንዳልወጡ እንወስዳለን።
ስለዚህ ባለማወቅ ሺርክ ወይም ኩ * f ር የፈፀመ ሰው ከኢስላም እንደማይወጣ ከታሪኩ እንረዳለን። ይህንን ሃሳብ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ረሒመሁላህ በከሽፉ ሹቡሃት ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል። የቀረበበት ጭብጥ ምንድነው?
የበኑ ኢስራኢል ሰዎች "አምላክ አድርግልን" ከማለታቸው ጋር ከኢስላም አልወጡም። በተመሳሳይ ሙታን የሚጣሩ ሰዎችም በተግባራቸው ቢቀጥሉም ከኢስላም አይወጡም የሚል ሙግት ለሚያቀርቡ አካላት እነሱ ሲነገራቸው ከመፈፀም ታቅበዋል። ከተነገራቸው በኋላ ቢቀጥሉ ኖሮ ከኢስላም ይወጡ ነበር የሚል ነው ባ'ጭሩ።
ከሽፉ ሹቡሃትን ሸርሕ ያደረጉ ሌሎች ዓሊሞችም የሸይኹን ሃሳብ አርመው ሳይሆን አጠናክረው ነው የፃፉት።
የአንቀጿ አጭር ተፍሲር
-
በቅድሚያ እዚህ ላይ የማቀርባቸው ማብራሪያዎች በሙሉ ከቀደምት የተፍሲር ሊቃውንት የተወሰዱ እንደሆኑ ይሰመርልኝ። የዓሊሞቹን ሙሉ ትንታኔያቸውን የሚፈልግ ሰው ከምጠቅሳቸው ምንጮች ይመልከት። እኔ ለማሳጠር ስል ለማስረጃ በቂ ናቸው የምላቸው ነጥቦች ላይ ብቻ ነው የማነጣጥረው።
1. ኢብኑ ጀሪር አጦበሪይ (310 ሂ.):-
" ... اجعل لنا" يا موسى "إلهًا"، يقول: مثالا نعبده وصنما نتخذُه إلهًا، كما لهؤلاء القوم أصنامٌ يعبدونها. ولا تنبغي العبادة لشيء سوى الله الواحد القهار. وقال موسى صلوات الله عليه: إنكم أيها القوم قوم تجهلون عظمة الله وواجبَ حقه عليكم، ولا تعلمون أنه لا تجوز العبادة لشيء سوى الله الذي له ملك السموات والأرض.
" 'ሙሳ ሆይ! አምላክ አድርግልን' አሉ። 'የምንገዛው ሃውልት፣ አምላክ አድርገን የምን ይዘው ጣዖት። ልክ ለነዚያ ሰዎች የሚያመልኳቸው ጣዖቶች እንዳሏቸው 'ማለታቸው ነው። ከአንድየውና አሸናፊው አላህ ውጭ ለማንም አምልኮት አይገባም። ሙሳ - የአላህ ሶለዋት በሱ ላይ ይሁንና - 'እናንተ የአላህን ልቅና እና በናንተ ላይ ያለውን የግዴታ ሐቁን አታውቁም፤ አምልኮት ለዚያ የሰማያትና የምድር ባለቤት ከሆነው ውጭ ለምንም እንደማይገባም አታውቁም ' አላቸው።" [ተፍሲር አጦበሪ]
2. መኪይ ብኑ አቢ ጧሊብ (437 ሂ.):-
فقال لهم موسى: عليه السلام: ﴿إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ﴾. أي: تجهلون نعمة الله عز وجل، عليكم وحقه، وتجهلون أنه لا تجوز العبادة إلا لله، سبحانه.
"ሙሳ - ዐለይሂ ሰላም - ለነሱ፡ 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው። ማለትም፡ አላህ - ዐዘ ወጀለ - በናንተ ላይ ያለውን ፀጋ እና ሐቁን ትዘነጋላችሁ። ከአላህ - ሱብሓነህ - በስተቀር ለሌላ አምልኮት እንደማይፈቀድ ትዘነጋላችሁ።" [ተፍሲር መኪይ አቢ ጧሊብ]
3. አሰምዓኒይ (489 ሂ.):-
﴿قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لنا إِلَهًا كَمَا لَهُم آلِهَة﴾ وَلم يكن ذَلِك من بني إِسْرَائِيل شكا فِي وحدانية الله - تَعَالَى - وَإِنَّمَا مَعْنَاهُ: اجْعَل لنا شَيْئا نعظمه ونتقرب بتعظيمه إِلَى الله - تَعَالَى - وظنوا أَن ذَلِك لَا يضر الدّيانَة، وَكَانَ ذَلِك من شدَّة جهلهم.
" 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ የበኑ ኢስራኢል ሰዎች ይህን ሲሉ የላቀውን አላህ አንድነት በመጠራጠር አይደለም። ይልቁንም 'ለኛ የምናልቀው እና እሱን በማላቅ ወደ አላህ - ተዓላ - የምንቃረብበት አድርግልን' ማለታቸው ነው። ይሄ እምነትን የማይጎዳ መስሏቸዋል። ይሄ በመሀይምነታቸው ክፋት የተነሳ ነው።" [ተፍሲር አሰምዓኒይ]
4. ኢብኑ ዐጢያ (546 ሂ.):-
ቃዲ አቡ ሙሐመድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦
والظاهِرُ مِن مَقالَةِ بَنِي إسْرائِيلَ لِمُوسى: ﴿اجْعَلْ لَنا إلَهًا كَما لَهم آلِهَةٌ﴾ أنَّهُمُ اسْتَحْسَنُوا ما رَأوهُ مِن آلِهَةِ أُولَئِكَ القَوْمِ، فَأرادُوا أنْ يَكُونَ ذَلِكَ في شَرْعِ مُوسى وفي جُمْلَةِ ما يَتَقَرَّبُ بِهِ إلى اللهِ، وإلّا فَبَعِيدٌ أنْ يَقُولُوا لِمُوسى: اجْعَلْ لَنا صَنَمًا نُفْرِدُهُ بِالعِبادَةِ ونَكْفُرُ بِرَبِّكَ. فَعَرَّفَهم مُوسى عَلَيْهِ السَلامُ أنَّ هَذا جَهْلٌ مِنهم إذْ سَألُوا أمْرًا حَرامًا فِيهِ الإشْراكُ في العِبادَةِ
"የኢስራኢል ልጆች ለሙሳ፡ 'ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' ሲሉ ጉልህ መልእክቱ የሚያስይዘው እነሱ ከነዚያዎቹ ሰዎች አማልኮት ከተመለከቱት በመነሳት መልካም ነገር አድርገው አስበውታል፡፡ በዚህ የተነሳ ይሄ ተግባር በሙሳ ሸሪዐ ውስጥ እንዲካተት እና ወደ አላህ ከሚቃረቡባቸው ተግባራት ውስጥ እንዲሆን ፈልገዋል። እንጂ ለሙሳ 'በጌታህ ክደን በአምልኮት ብቸኛ አድርገን የምን ይዘው ጣዖት አድርግል' ሊሉት አይችሉም። ሙሳ - ዐለይሂ ወሰለም - ይሄ የነሱ

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ነገር አለማወቅ እንደሆነ አሳወቋቸው። በአምልኮ ማጋራት ያለበት ክልክል ነገር ነውና የጠየቁት።" [አልሙሐረሩል ወጂዝ፣ ኢብኑ ዐጢያ]
5. ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ .)
وهذا إخبار عن عظيم جهلهم حيث توهموا جواز عبادة غير الله ، بعد ما رأوا الآيات".
"ይሄ አለማወቃቸው ምንኛ የራቀ እንደሆነ መናገር ነው፤ እነዚያን ሁላ ተአምራት ካዩ በኋላ ከአላህ ውጭ ያለን ማምለክ እንደሚቻል ገምተዋልና።'' [ዛዱል መሲር፡ 2/150]
6. ኢብኑ ከሢር (774 ሂ.):-
يُخْبِرُ تَعَالَى عَمَّا قَالَهُ جَهَلَةُ بَنِي إِسْرَائِيلَ لِمُوسَى، عَلَيْهِ السَّلَامُ، ... فَقَالُوا: ﴿يَا مُوسَى اجْعَلْ لَنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ﴾ أَيْ: تَجْهَلُونَ عَظَمَةَ اللَّهِ وَجَلَالَهُ، وَمَا يَجِبُ أَنْ يُنَزَّهَ عَنْهُ مِنَ الشَّرِيكِ وَالْمَثِيلِ
"የላቀው አላህ መሀይማን በኑ ኢስራኢል ለሙሳ - ዐለይሂ ወሰለም - ያሉትን አስመልክቶ ይነግረናል። ... 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ ይህም 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው። የአላህን ልቅና እና ክብር እንዲሁም ከተጋሪና ከአምሳያ ሊያጠሩት እንደሚገባ የማታወቁ ናችሁ' ማለት ነው።" [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር]
ብዥታዎች
-
ይሄ የሙሳ ሰዎች ቂሷ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ የሚነሱ የተለመዱ ብዥታዎች አሉ። እንያቸው።
#ብዥታ_አንድ፦ "እነሱ ጥያቄ ጠየቁ እንጂ ሺርክ አልሰሩም" የሚሉ አሉ።
°
ምን ማለታቸው ነው? የሙሳ ሰዎች ጥያቄ ነው የጠየቁት። እንደማይቻል ሲነገራቸው ቆመዋል። ሁኔታቸው ሺርክ ከሚፈፅሙ ሰዎች ይለያል የሚል ነው።
ምላሽ፦
ሀ - ጥያቄያቸው'ኮ በራሱ ሺርክ ነው!
የሙሳ ሰዎች ጥያቄያቸው "ይቻላል ወይስ አይቻልም?" ወይም "ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?" የሚል አይደለም። ጥያቄያቸው "ወደ አላህ መቃረቢያ እንዲሆነን የምናመልከው አምላክ አድርግልን" የሚል ነው። ይሄ ግልፅ ሺርክ ነው። ከላይ ያሰፈርኳቸውን የዓሊሞቹን ንግግር ተመልከቱ። ጥያቄያቸው ሺርክ እንደሆነ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ እንዲህ ሲሉ አስረግጠው ይናገራሉ፦
وتفيد أيضا أن المسلم المجتهد إذا تكلم بكلام كفر وهو لا يدري فنبه على ذلك فتاب من ساعته أنه لا يكفر كما فعل بنو إسرائيل
"ታሪኩ በተጨማሪ አንድ ለሐቅ ፍለጋ የሚጥር ሙስሊም ሳያውቅ #የክህደት ንግግር ቢናገር እና በዚያ ላይ ማስገንዘቢያ ተሰጥቶት ወዲያው ከተመለሰ ከኢስላም አይወጣም፤ ልክ በኑ ኢስራኢል እንዳደረጉት ማለት ነው።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]
ልብ በሉ! "የክህ .ደት ንግግር" ብለው ነው የገለፁት። እነዚህ ግን "ጥያቄ" ብለው ያሉታል።
ለ - "ያላወቀ አልገባም" የሚለው ህጋችሁ የት ገባ?
እነዚህ ዑዝር ቢልጀህል የለም የሚሉ ሰዎች "የኡሉሂያ ጉዳይ በዐቅል የሚታወቅ ነው። ላ ኢላሀ ኢለላህን እና አፍራሿን ያላወቀ ሰው ከነጭራሹ ወደ ኢስላም አልገባም" የሚሉ ናቸው። እንዲህ አይነት አቋም የሚያራምድ አካል የሙሳ ሰዎችን "ጠየቁ እንጂ መቼ ፈፀሙት?" ሊል አይገባም። በራሱ ህግ መሰረት ከነ ጭራሹ ወደ ኢስላም አልገቡምና።
#ብዥታ_ሁለት፦ "የሰዎቹ ጥፋት ትንሹ ሺርክ ነው" የሚሉም አሉ።
ምላሽ፦
የነዚህ ሰዎች አላማ በጥፋታቸው ከኢስላም ያልወጡት የፈፀሙት ትንሹ ሺርክ በመሆኑ ነው የሚል ነው። ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። "አምላክ አድርግልን" ማለት በምን ስሌት ነው ትንሹ ሺርክ የሚሆነው? ቀድመው አቋም ይዘው ስለሚዘጉ እንጂ ይሄ ሐቂቃ ለማንም የሚሰወር አልነበረም። ለማንኛውም ከላይ ያሰፈርኳቸውን የሙፈሲሮቹን ትንታኔ አስተውሉ።
* ሰምዓኒይ :- "ለኛ የምናልቀው እና እሱን በማላቅ ወደ አላህ - ተዓላ - የምንቃረብበት አድርግልን" እንዳሉ ገልፀዋል። የመቃረቢያ ሺርክ ጥንት የቁረይሾች ዛሬ ደግሞ የብዙ ሱፊዎች ሺርክ ነው፤ ትልቁ ሺርክ።
* ኢብኑ ዐጢያ፦ "ይሄ ተግባር በሙሳ ሸሪዐ ውስጥ እንዲካተት እና ወደ አላህ ከሚቃረቡባቸው ተግባራት ውስጥ እንዲሆን ፈልገዋል። ... በአምልኮ ማጋራት ያለበት ክልክል ነገር ነው የጠየቁት" ብለዋል።
እና ይሄ ትንሹ ሺርክ ነው? አላህን ፍሩ። ህሊናችሁንም አክብሩ። "አምላክ አድርግልን" የሚለው ንግግር ትልቁ ሺርክ እንደሆነ የማያውቅ ሰው ዑዝር ቢል ጀህል ባይኖር ኖሮ ሙስሊም አይሆንም ነበር።
#ብዥታ_ሶስት፦ "በአንቀጿ ውስጥ የተጠቀሰው ጀህል አለማወቅ ሳይሆን አውቆ ማጥፋት ነው። ሰዎቹ በፈፀሙት ሺርክ ከኢስላም ወጥተዋል" የሚሉም አሉ።
ምላሽ፦
ይሄም የተሳሳተ ድምዳሜ ነው። ምክንያቱም
ሀ - ሰዎቹ አውቆ አጥፊ ሳይሆኑ ባለማወቅ የጠየቁ እንደሆነ ከላይ ያሳለፍኳቸውን ስድስት ተፍሲሮች አስተውሉ። ጉዳዩ ኢንሷፍ ብቻ ነው የሚፈልገው።
ለ - እነዚህ የሙሳ ሰዎች ጥያቄያቸው ባለማወቅ እንደሆነ እና በዚህም የተነሳ ከኢስላም እንዳልወጡ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ደጋግመው ተናግረዋል። ይሄውና፦
1- ومن الدليل على ذلك أيضا ما حكى الله عن بني إسرائيل مع إسلامهم وعلمهم وصلاحهم، أنهم قالوا لموسى: اجعل لنا إلها كما لهم آلهة
"በዚህ ላይ ከሚነሱ ማስረጃዎች ውስጥ ደግሞ ሌላው አላህ ስለ በኑ ኢስራኢል የገለፀው ነው። ሙስሊሞች ከመሆናቸው ጋር፣ ዒልም ያላቸው እና ደጋጎች ከመሆናቸው ጋር ለሙሳ፡ 'ለእነርሱ አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' ብለዋል፡፡" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 43]
ልብ በሉ! ሸይኹ እነዚህን የሙሳን ሰዎች ሙስሊሞች፣ ኧረ እንዲያውም ዓሊሞች፣ አልፎም ደጋጎች ብለው ነው የገለጿቸው። ልጨምር!
2- ولا خلاف أن بني إسرائيل لو فعلوا ذلك لكف .روا.
"የበኑ ኢስራኢል ሰዎች ያንን (የጠየቁትን) ቢሰሩት ኖሮ ከኢስላም ይወጡ እንደነበር በዑሉማእ መካከል ልዩነት የለም።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 44]
ልብ በሉ! ሰዎች ሙስሊሞች ባይሆኑ ኖሮ ከኢስላም ይወጡ ነበር አይሉም። ካ fi ር ከመነሻውም ከኢስላም ውጭ ነውና። ልቀጥል፦
3- هذه القصة تفيد أن المسلم بل العالم قد يقع في أنواع من الشرك لا يدري عنها
"ይህቺ ታሪክ አንድ ሙስሊም ኧረ እንዲያውም ዓሊም የሆነ ሰው ሳያውቀው የሺርክ አይነቶች ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ትጠቁማለች።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]
ልብ በሉ! ሰዎቹን ሙስሊሞች እንደሆኑና የወደቁበትንም ጥፋት ባለማወቅ እንደሆነ እየጠቆሙ ነው። ተጨማሪ!
4- وتفيد أيضا أن المسلم المجتهد إذا تكلم بكلام كف .ر وهو لا يدري فنبه على ذلك فتاب من ساعته أنه لا يكف . ر كما فعل بنو إسرائيل
"ታሪኩ በተጨማሪ አንድ ለሐቅ ፍለጋ የሚጥር ሙስሊም ሳያውቅ የክህደት ንግግር ቢናገር እና በዚያ ላይ ማስገንዘቢያ ተሰጥቶት ወዲያው ከተመለሰ ከኢስላም አይወጣም፤ ልክ በኑ ኢስራኢል እንዳደረጉት ማለት ነው።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]

እዚህም ላይ ሰዎቹ ሙስሊሞች መሆናቸውን እየጠቆሙ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታ ያለው ሰው ከኢስላም እንደማይወጣ የሚገልፀው ንፅፅራቸው ከዚህ ውጭ ሌላ ትርጉም የለውም።
ማሳሰቢያ፦
-
ሃሳብ ወይም እርምት አለኝ ለሚል ሰው በሩ ክፍት ነው። ባይሆን
1. በአደብ ይሁን።
2. ነጥብ ይጠበቅ። ስለ "ዛቱ አንዋጥ" ቂሷ አላወራሁም። የፃፍኩት ስለ ሙሳ ሰዎች ቂሷ ብቻ ነው።
3. ሙሉውን ያላነበበ ሃሳብ እንዳይሰጥ።
4. "ይህን የሚፈፅሙ፣ ያን የሚያደርጉ ሰዎችን ሙስሊሞች ናቸው ልትል ነው ወይ?" አይነት ከደሊል የተራቆተ ስሜት ኮርኳሪ፣ ሽብር ፈጣሪ ሙግት አልቀበልልም። እችላለሁ የሚል ሰው ዒልሚይ የሆነ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል።
ባግባቡ የማይመጣን ሃሳብ ልሰርዝ እችላለሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 15/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ማሳሰቢያ፦
-
ሃሳብ ወይም እርምት አለኝ ለሚል ሰው በሩ ክፍት ነው። ባይሆን
1. በአደብ ይሁን።
2. ነጥብ ይጠበቅ። ስለ "ዛቱ አንዋጥ" ቂሷ አላወራሁም። የፃፍኩት ስለ ሙሳ ሰዎች ቂሷ ብቻ ነው።
3. ሙሉውን ያላነበበ ሃሳብ እንዳይሰጥ።
4. "ይህን የሚፈፅሙ፣ ያን የሚያደርጉ ሰዎችን ሙስሊሞች ናቸው ልትል ነው ወይ?" አይነት ከደሊል የተራቆተ ስሜት ኮርኳሪ፣ ሽብር ፈጣሪ ሙግት አልቀበልልም። እችላለሁ የሚል ሰው ዒልሚይ የሆነ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል።
ባግባቡ የማይመጣን ሃሳብ ልሰርዝ እችላለሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 15/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #51
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-5️⃣ 1️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተውሒድን ወሳኝነት እና ህዝባችን በዚህ በኩል ያለበትን ክፍተት የሚያውቅ ሰው ተውሒድ የደዕዋችን ሁሉ ማዕከል ሊሆን እንደሚገባው አይሰወረውም። ይሄ ሐቂቃ ባለበት ሁኔታ መስጂድ ላይ በሚያስተምረውም ይሁን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚያደርገው ደዕዋ ነክ ተሳትፎው ላይ የተውሒድን ርእስ #ከነጭራሹ የሚገፋ ዳዒያህ እውነተኛ ዳዒያህ ተብሎ ሊቆጠር አይችልም። በዚህ ጉዳይ ላይ ደንታ ቢስ የሆነ ዳዒያህ ለደዕዋው ሸክም ስለሚሆን ወይ ወደ መስመር ይገባ ዘንድ በጥልቀት መስራት ይገባል። መፍትሄ ከሌለው አርግፎ መተው ነው። እንዲህ አይነቱ ካለም አይቆጠርም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ሰዎች ለተውሒድ ትምህርት እንቅፋት ሲሆኑብን በቀላሉ ተሸንፎ እጅ መስጠት አይገባም። እስከ ደም ጠብታ ታገል። ተውሒድ ከሌለ ከዲንህ ምን ቀረህ? ለተውሒድ ካልተቆጨህ ለምን ልትቆጭ ነው? ምከር። ዝከር። ጣር። ታገል። መክፈል ያለበህን መስዋእትነት ሁሉ ክፈል። ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ።
ዙልቀዕዳህ 28/1446
ጅማ አባ ጅፋር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ዙልቀዕዳህ 28/1446
ጅማ አባ ጅፋር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
በነገራችን ላይ ለቻለበት በአርበዑነ ነወዊየህ፣ በሪያዱ ሷሊሒን፣ ... ደርስ ተውሒድን ማስተማር የሚቻልባቸው ብዙ ተያያዥ ሐዲሦች / ርእሶች አሉ። ብቻ የእውነት ትኩረት ይኑርህ! ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም።
ስለዚህ በነፃነት ተውሒድን የምታስተምርበት መድረክ ስታጣ ተውሒድ ከለከሉኝ እያልክ አትነፋረቅ። ሁሉ አልተገኘ ተብሎ ሁሉ አይተውም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ስለዚህ በነፃነት ተውሒድን የምታስተምርበት መድረክ ስታጣ ተውሒድ ከለከሉኝ እያልክ አትነፋረቅ። ሁሉ አልተገኘ ተብሎ ሁሉ አይተውም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ተውሒድን ትተህ ''ሒክማ ገብቶታል"፣ "ሰፋ ያለ ነው"፣ "ፀባዬ ሸጋ ነው"፣ ... ከምትባል ፤ ተውሒድ ላይ ትኩረት አድርገህ ያሰኛቸውን ስም ይለጥፉልህ።
ስለ አቀራረብህ ደንታ ቢስ ሁን ማለቴ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ስለ አቀራረብህ ደንታ ቢስ ሁን ማለቴ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የደዕዋው ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሁሉ!
~
እውቀት ያለው በእውቀቱ፣
ሃብት ያለው በሀብቱ፣
በየትኛውም በምንችለው መንገድ ሁሉ ለደዕዋ አስተዋፅኦ ይኑረን። መስጂዶችን፣ ማህበራዊ መገናኛዎችን፣ ... ለደዕዋ እንደሚገባ እንጠቀማቸው። ካልሆነ የተጋረጡብንን አደጋዎች መቋቋም አንችልም።

የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ጂብሪል ታላላቆችን እንዳስቀድሞ አዞኛል።"
[አሶሒሐ ፡ 1555]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
"ጂብሪል ታላላቆችን እንዳስቀድሞ አዞኛል።"
[አሶሒሐ ፡ 1555]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ከቀናት በፊት ከዑዝር ቢል ጀህል ጋር በተያያዘ የሙሳ ሰዎችን ቂሷ አንስቼ ለፃፍኩት ፅሁፍ በርከት ያሉ ኮመንቶች እንደተሰጡ አየሁኝ። ተረጋግቼ ቁጭ ስል ምላሽ እስከምሰጥበት ድረስ በሚል ትኩረት አላደረግኩበትም ነበር። ሀሳባችሁ ከኔ ድምዳሜ ጋር ገጠመም አልገጠመም በመልካም ኒያ ተሳትፎ ያደረጋችሁን ሁሉ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ልል እወዳለሁ።
በጉዳዩ ላይ ዑለማኦች የተለያየ አቋም የሰነዘሩበት መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ከልብ መቀበል ይገባል። ያ ሲሆን ነው ጉዳዩን በልኩ የምንይዘው። ይሄ ርእስ በምንም መልኩ ለመፈራረጅ የሚደርስ አልነበረም። ይሁን እንጂ እንደ ኢብኑ ተይሚያ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን ያሉ ታላላቅ ዑለማኦችን ሳይቀር ዑዝር በመስጠታቸው የተነሳ አንዴ በማ k ፈ ^ r ሌላ ጊዜ በኢርጃእ በመወረፍ የተጠመደ አካል እስካለ ድረስ ጉዳዩ በቀላል ሊታይ አይችልም። ስለዚህ በስርአት ለመነጋገር ዝግጁ ያልሆነውን እያስገለሉ መወያየቱ እና ብዥታ ማጥራቱ ይቀጥላል፣ ኢንሻአላህ።
መዝዘንጋት የሌለበት ነገር ቢኖር ዑዝር ቢል ጀህል የለም የሚሉ አካላት አይነታቸው ብዙ መሆኑን ነው። ለምሳሌ ያህል፦
- ዑዝር የማይሰጡበትን ርእስ በተመለከተ ከፊሎቹ በኡሉሂያ ጉዳይ ላይ ብቻ ሲገደቡ ፣ ሌሎቹ በአስማእ ወሲፋት ጭምር ያከ f ^ራሉ።
- ዑዝር የሚሰጡ አካላትን ከፊሉ በጅምላ ከኢስላም ሲያስወጡ፣ ከፊሎቹ ደግሞ በኢርጃእ ይወነጅላሉ። ሌሎቹ ችግራቸው እዚህ አይደርስም።
- ከፊሎቹ ለአዲስ ሰለምቴ እና ከእውቀት ርቆ ላለ ዑዝር ሲሰጡ ከፊሎቹ ማንንም አያስተርፉም።
- ከፊሎቹ እነ ፈውዛንን ደጋግመው ሲያጣቅሱ ሌሎቹ ደግሞ ፈውዛንን ጭምር ከኢስላም ያስወጣሉ።
- ከፊሎቹ የሙሳ ሰዎች ከኢስላም ወጥተዋል ብለው በድፍረት ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ "አይ" ይላሉ። በዚህ ነጥብ ብቻ አንድ የነበሩ ግን ለሁለት የተሰነጠቁ አካላት አሉ።
ወዘተ.
ማለት የፈለግኩት ምንድነው? አይነታቸውም ነገሮችን የሚይዙባቸውም መንገዶች የበዛ ስለሆነ ለአንዱ ብዥታ የሚስሰጠው ምላሽ ለሌላው ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ብዥታን ለማጥራት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጉዳዩን መመልከት ያስፈልጋል ማለት ነው። ስለሆነም በየቀኑ ሆኖ እንዳያሰለች አለፍ አለፍ እያልኩ መጠነኛ ዳሰሳ ለማድረግ እሞክራለሁ ኢንሻአላህ።
የተለየ ሀሳብ ላላችሁ!
-
የተለየ ሃሳብ መምጣቱን በቅሬታ አላይም። እንዲያውም በደስታ ነው የምቀበለው። ለቀጣይ ዳሰሳዬ እንደ ግብአት እጠቀመዋለሁ። መነሻ ሃሳብ ወይም ራሱን የቻለ ርእስ እወስድበታለሁ። አመጣጡ ጤነኛ ካልሆነ ግን አስወግደዋለሁ። "ተሳስተሃል" የሚል አካል በማስረጃ እንዲመጣ አደራ እላለሁ። ባይሆን ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም መዘጋጀት ደግ ነው። ለዛሬ ለመነሻ ያህል ይህን ካልኩ ይበቃኛል።