Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (Ms MN)
ስለፎቻችን ከቁርአን እና ከዚክር ለአንዲትም ቀን ቢሆን የማይታለፍ ዕለታዊ ልምድ ነበራቸው ። ቀኑ በነሱ ላይ ነግቶ አይመሽም የልምዳቸውን ያህል ቁርአንን ያነበቡና አሏህን ያወሱ ቢሆን እንጂ ! በ3 ቀን .... በሳምንት .... በ10 ቀን ..... ቁርአንን ያኸትሙ ነበር ።
ዛሬ ... በመካከላችን ረመዷን ሲገባ እንጂ ቁርአንን የማያስታውስ አለ ! ጁሙዓ ሲመጣ እንጂ ግማሽ ጁዝእ እንኳን ቁርአን ሳይቀራ የሚከርም አለ !
ኧረ አሏህን እንፍራ !
የማይታለፍ እለታዊ የቁርአን መቅራት ልምድ ይኑረን - የዚክርም እንደዚሁ ።
https://www.tg-me.com/msirage4

Telegram
MuhammedSirage M.Noor
اتق الله حيثما كنت
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ከአገር መፍረስ ባሻገር
~
አገር እንድትፈርስ የሚመኙ፣ አገር ለማፍረስ በተግባር የሚጥሩ፣ ለአገር አፍራሾች ድጋፍ የሚሰጡ ብዙ አካላት አሉ። ወንድሜ ሆይ! እውነት በሃገር መፍረስ የምታተርፍ መስሎህ ነው? ለመሆኑ አገር ሲፈርስ ምን ምን ሊከሰት እንደሚችል አሻግረህ ተመልክተሃል? ወይስ በሆኑ አካላት ላይ ያለህ ጥላቻና ቁጭት በሩቅ እንዳትመለከት ሸፍኖብሃል? ወንድሜ አገር ዳቦ አይደለም፤ እንደዋዛ ቆራርሰህ በመካፈል አትገላገልም።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ይፈናቀላሉ። እንኳን አገር ፈርሶ በብሄር ግጭትና ጥቃት ብቻ የሚሊዮኖች ህይወት ተመሰቃቅሏል። ምናልባት አንተ ከሚፈናቀሉት ባትሆን እንኳ ራስህን በነሱ ጫማ ላይ አድርገህ ተመልከት።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ትዳር ይፈርሳል። ከሌላ ብሄር ጋር የተጋቡ ወገኖቻችን እጅግ ብዙ ናቸው። ይሄ ዘር እየለየ የሚገድል ትውልድ የሚተዋቸው እንዳይመስልህ። ስንት ቤተሰብ እንደሚበተን ተመልከት።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ንብረት ይወረሳል። እንኳን አገር ፈርሶ ሰላም በመጥፋቱ ብቻ የስንቱ ምስኪን ንብረት በተለያዩ ክልሎች በጉልበተኛ ተነጥቋል!
* ሃገር ሲፈርስ እዚህም እዚያም መቋጫ የሌለው የድንበር ግጭት ይነሳል። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በሶማሊና በኦሮሞ የድንበር ግጭት ከሚሊየን በላይ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው አፋርና ዒሳ በየጊዜው የሚጋደለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው ዘጠኝ መቶ ሺ አካባቢ የጌዲዎ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው የወሎ ኦሮሞና የሸዋ አማራ የሚጋጨው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በደቡብ ክልል የተለያዩ ህዝቦች መካከል ግጭት የሚቀሰቀሰው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው "ወሎ ኦሮሞ ነው"፣ "ወልቃይት፣ ደራ፣ በረራ፣ መተከል አማራ ነው" የሚል ጩኸት የምንሰማው፡፡ ሃገር ከፈረሰ እነዚህ ጩኸቶች ዛሬ ከምናየው በላይ ሚሊዮኖችን የሚበላ እሳት ይቀሰቅሳሉ።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ነፍስ ይጠፋል። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ መጨረሻቸው እልቂት ነው።
* ምናልባት መልኩ ይቀየር ካልሆነ በስተቀር በሃገር መፍረስ ጭቆና የሚቀር፣ ለድሃ ቀን የሚወጣ እንዳይመስልህ። ወላሂ! ዘር እየለየ፣ ሃይማኖት እየመረጠ በሚገድል ቡድን፣ ከርሱን በሚያስቀድም ፖለቲከኛ መቼም ፍትህና ነፃነት አታገኝም።
የሚሻለው በጋራ ለሰላምና ለፍትህ መጣር ነው። መፍትሄው እንደ ህዝብ ከገጠመን የስነ ምግባር ዝቅጠት ለመውጣት ተባብሮ መሥራት ነው። ችግራችን ስር የሰደደ ነው። ችግራችን በማህበረሰብ ደረጃ የተንሰራፋ ነው። ስለ መንግስት ችግር ጧት ማታ ማውራቱን እንደ ንቃት ቆጥረን እራሳችንን እየሸወድን እንጂ ከመንግስት አልፎ እንደ ህዝብ መተዛዘናችን ሳስቶ መጨካከን ነግሶብናልኮ።
~ በየገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየተቋሙ ህዝብ የሚያጉላላው፣ ... ሁሉ ምንም ስቅ ሳይለው ስለ ፍትህ እየወሸከተ ነው።
~ ለብዙዎች ከትምህርት ገበታ መራቅ ሰበብ የሚሆነው፣ ዘርና ሃይማኖት እየለየ ተማሪዎቹን የሚያከላፍተው አስተማሪ ምንም ሳያፍር ስለ ፍትህና ርትእ እየጮኸ ነው።
~ ታካሚዎቹን ፊቱን አጨፍግጎ የሚያስተናግደው፣ በግዴለሽነት የሰው ነፍስ ላይ የሚቀልደው፣ ለርካሽ ጥቅም ሲል የማይገናኝ ምርመራ እያዘዘ ደካማ ወገኑ ላይ ጭካኔ የሚፈፅመው ሃኪም እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚጮኸው!
~ የተበላሸ ምግብ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት፣ ፎርጂድ እቃ፣ የተጭበረበረ ምርት፣ ... የሚሸጠው ነጋዴ እኮ ነው "መስራት አቃተን" እያለ የሚያለቅሰው። አዎ አቅቶታል። ግን እሱስ መቼ ከግፍ እጁን ሰበሰበ?
~ ፍትህ በገንዘብ የሚሸጠው፣ ከሌባ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው፣ እምነትና ብሄር እየመረጠ ፍትህ የሚቀብረው ዳኛና ፖሊስ እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚዘፍነው።
~ ሚሊዮኖች የወጡበትን መሬት ሶስት አራት ካርታ ሰርቶ የሚቸበችበው ሰራተኛ፣ የሚሊዮኖችን ውሃና መብራት እየቆረጠ ሺ ጊዜ ብር እየተቀበለ የሚቀጥለው ሌ ^ባ እኮ ነው ስለ ፍትህና ስለ ነፃነት የሚለፍፈው።
~ መንገዶችንና ህዝባዊ ተቋማትን ከደረጃ በታች እየሰራ በሀገር በወገኑ ላይ የሚቆምረው እኮ ነው ለሀገር ለወገኑ ተቆርቋሪ መስሎ የሚፈተፍተው።
~ መኪናና ሞተር ሳይክል አዘጋጅቶ፣ አንድ ላምስት ተደራጅቶ የሚዘርፈው፣ ህፃናት እያፈነ የሚወስደውኮ ነው እኩል ስለ ፍትህ የሚያወራው!
~ የሁለት ቀን ጨቅላ፣ የ70 አመት አዛውንት፣ አቅመ ደካማ ሴቶችን ሳይቀር የሚገድለው እኮ ነው የነፃነት ታጋይ የሚባለው።
እስኪ በየትኛው ዘርፍ ነው የሚነሳ ጥሩ ነገር ያለን? ፖለቲከኞቹ የኛው ነፀብራቆች ናቸው። እኛኑ ነው የሚመስሉት። ከኛው የወጡ እንጂ ከሌላ ፕላኔት የመጡ አይደሉም። ክፋታቸው ክፍታችን፣ ንቅዘታቸው ንቅዘታችን ነው።
እንደ ህዝብ በዚህ ደረጃ መልካሞች የመነመኑ ከሆኑ እንዴት ነው ፍትህና እፎይታ የምናገኘው? በቅድሚያ በራሳችን ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ወደተነሳሁበት ስመለስ፣ ስግብግብ ስሜታችን እየጋረደን፣ ቁንፅል አመልካከታችን እየሸወደን እንጂ በርግጠኝነት በሃገር መፍረስ እንደ ህዝብ ከሳሪዎች እንጂ አትራፊዎች አይደለንም። ስለዚህ ደግመን ደጋግመን ልንመለከት፣ ሰላምን ከሚያደፈርስ ድርጊቶች ልንርቅ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለአገር አፍራሾች ድጋፍ ከመሆን ልንጠነቀቅ ይገባል። ጥፋትን ማስቆም ባንችል እንኳ ቢያንስ ተጋሪ ባለመሆን የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 11/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ሰው ውሎውን ይመስላል
~
ሰው ወደሚያዘወትረው ነገር ልቡ ያዘነብላል። ሙዚቃ የሚያዘወትር ወደ ሙዚቃ፣ ፊልምና ድራማ ላይ የሚጣድ ወደ ፊልምና ድራማ፣ ዜና የሚያሳድድ ወደ ዜና፣ ፖለቲካ የሚያነፈንፍ ወደ ፖለቲካ፣ ሚምና ፕራንክ ባየ ቁጥር የሚቆም ወደዚያው፣ ቁም ነገር ላይ የሚያተኩርም እንዲሁ ወደ ቁምነገር ይሳባል። ይሄ የሰው ልጅ ልቦና ስሪት ነው። ለዚያም ነው የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች አልጎሪዝም አጠቃቀማችንን የሚያነፈንፈው። ደጋግመን የምናየውን ወይም ትክ ብለን የምንቆይበትን ይዘት እያጤነ ተመሳሳይ ይዘቶችን ያቀርብልናል።
ይህንን እንያዝና እራሳችንን እንታዘብ። ቁርኣን መቅራትና ማዳመጥ ላይ እንዴት ነን? ንባብ ላይስ? ደዕዋዎችን፣ ዱሩሶችን፣ ጠቃሚ ፕሮግራሞችን ለመከታተል ሶብር አለን ወይ? እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ስናስብ ብዙዎቻችን በጣም እንደተዘናጋን የምንግባባ ይመስለኛል። መፍትሄው አጭር ነው። ባይሆን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ዛሬ ነገ ሳንል ወደ መስመር መግባት። ቁርኣን እንቅራ፣ እናዳምጥ፣ ቋሚ የደርስ ፕሮግራም ይኑረን፣ ቁም ነገር የያዙ ኪታቦችንና መፅሀፎችን እናንብብ። ወደ መስመር ለመግባት ትንሽ ጊዜ ነው የሚጠይቀን። ስንቆይበት ጣእሙን እናገኘዋለን። ያኔ ስላለፈው ጊዜ እንቆጫለን። የልብ እርካታ፣ የአእምሮ ሰላም ይመጣል።
ሌሎችም ኸይር ስራዎች ላይ እንዲሁ ነው። ገንዘቡ እያላቸው ከሶደቃ፣ ከዘካ የራቁ ሰዎች ወደ መስመር የመግባት እድላቸው እየራቀ ነው የሚሄደው። መስጠትን ሲዳፈሩ፣ በመስጠት ውስጥ ያለውን ደስታ ሲያዩት እየለመዱት ይሄዳሉ። አመት ጠብቀው ዘካቸውን አስበው ለመስጠት ተራራ አይሆንባቸውም። ኸይር ስራዎችም ላይ አይታጡም።
ሸሩም ላይ እንዲሁ ነው። ዝሙቱ፣ ስርቆቱ፣ ነፍስ ማጥፋቱ፣ ዘረኝነቱ፣ ማጭበርበሩ፣ ወዘተ. የሚጨንቀው መጀመሪያ አካባቢ ነው። አንዴ ከተለመደ ሁሉም ኖርማል ይሆናል። እንዲያውም ጀብድ ይሆናል። ጨዋነት ፋራ መሆን ይመስለዋል። ጥንቡ ዘረኝነት ለሱ ልዩ መአዛ አለው። መቼስ ከዚያ በኋላ ዘረኝነት ብሎ አይገልፀውም። የራስ ምን አይገማም ይባላል። ስለዚህ? እያሸሞነሞነ ይገልፀዋል። ከወሮ በላ ጋር ተሰልፎ መዝረፍ፣ ማገትና ነፍስ ማጥፋት ዘመኑን የቀደመ ንቃት ይሆንና ይህንን መፀየፍ ደግሞ ማንቀላፋት፣ ወደ ኋላ መቅረት ተደርጎ ይያዛል። ሰው አንዴ ጥፋትን ከተላመደ መነፅሩ ይንሸዋረራል፣ መለኪያው ይዛባል። ተሳስተሃል ብትለው የስድብ ያህል ነው የሚቆጥረው።
ባጭሩ የኸይር ስራ አንዱ ሽልማቱ ወደ ኸይር ማሻገሩ ሲሆን የጥፋት አንዱ ቅጣቱ ይበልጥ ወደሚያስቀጣ የከፋ ጥፋት ማሻገሩ ነው። የኑሮ ዘይቤያችንን፣ የጊዜ አጠቃቀማችንን ወደተሻለ መቀየር ከፈለግን ቅድሚያ ከልባችን፣ ከራሳችን ጋር እንስማማ። ወደዚያም ወደዚህም የምትጎትተን ነፍሲያችን ላይ እናምፅ። እምቢ በቃሽ እንበላት። ለውጥ ከውስጥ ነው የሚጀምረው። ውስጣችን ካላመነ ለውጥ በምኞት አይመጣም።

ኡስታዝ ሆይ! ከምትጠበቁበት ተገኙ
~
ኡስታዝ ሆይ! አደራህን በየትኛውም መልኩ እጅህ ላይ የደረሰን አማና አትብላ! ከሙናፊق ምልክቶች ውስጥ አንዱ ሲታመኑ መክዳት እንደሆነ የምታውቀው ነው። የሰዎችን አማና መክዳት፣ በደዕዋ ስም ሰብስቦ ለግል ጥቅም ማዋል አንዳንድ ኡስታዞች የሚከሰሱበት ወንጀል ነው። ፅሁፌ በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው።
በዚህ ዘመን አላህን ከመፍራት የራቁ፣ ያለ አንድ መረጃ እንዲሁ ቡድናዊ ጥላቻ የወለዳቸው የስም ማጥፋት ውንጀላዎች በስፋት እንዳሉ ይታወቃል። ይሄ ቡድንተኝነት ያመጣብን ልክፍት ነው። ይሁን እንጂ ይሄ ማለት የተረጋገጡ ጥፋቶች የሉም ማለት አይደለም። በተለያየ መልኩ እጃቸው የገባን አማና የካዱ፣ በተደጋጋሚ በደዕዋ ስም ገንዘብ እየሰበሰቡ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ፣ ወዘተ. አካላት አሉ። እነዚህ ጥፋቶች ሲደጋገሙ፡
* የሌሎችንም ዱዓት ስም የሚያጠፉ፣ ተአማኒነትን የሚያሳጡ ስለሚሆኑ አጠቃላይ ደዕዋው ላይ የሚኖራቸው ጠባሳ ከባድ ነው የሚሆነው።
* በዱዓት መካከል መራራቅን ስለሚያስከትሉ እና የትብብር መንፈስን ስለሚጎዱ በዚህም በኩል ደዕዋው ላይ ትልቅ ጉዳት ይኖራቸዋል።
* ከዚህም ባለፈ እንዲህ አይነት አመሎች ሌሎችም ዱዓት ተመሳሳይ ጥፋት ላይ እንዲወድቁ በር ሊከፍቱ ይችላሉ።
ስለዚህ በየትኛውም ባልተፈቀደ መልኩ የሰዎችን ሐቅ ወደራስ ኪስ ማድረግ እና ዲን በማስተማር ያገኘነውን መልካም ስም ላልተገባ ነገር ማዋል አላህን ልንፈራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ስንቶች አሉ በኡስታዞች አማናቸውን ተክደው "አሁን ብናገርስ ማን ያምነኛል?" ብለው እያለቀሱ ዝም ያሉ። እንዲህ አይነት ነገር ሁሌ ተሸፍኖ አይቀርም። በሂደት ውርደትን ያከናንባል፣ መንናቅንም ያመጣል።
እዚህ ላይ ልጅ እያለሁ የገጠመኝ አንድ የማይረሳኝ ክስተት ላንሳ። አንድ ከወረዳችን አልፎ በጣም ብዙ የወሎ አካባቢዎች ዘንድ ስሙ የገነነ፣ የተናገረው መሬት ጠብ አይልም ተብሎ በወልይነት የሚታምንበት ሸይኽ ነው ባለ ታሪኩ። ስሙን ብጠቅስ ብዙዎች ያውቁታል። በዙሪያው የነበሩ ሰዎች እንዴት እንደሚሽቆጠቆጡለት ልነግራችሁ አልችልም። በአቅራቢያ ፍርድ ቤት ስለሌለ ለቀበሌ ሸንጎ ሁለት ሰዎችን በመሬት ጉዳይ ከሶ ነው የቀረበው። ተከሳሾች አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ ናቸው።
ሴቷ ፡ "ጭራሽ ወልይ ነኝ እያለ እያስፈራራ ንብረታችንን ሊነጥቀን ነው የተነሳው! ይሄ ወንበዴ ነው!" እያለች ታዳሚው ለመስማት እስከሚሳቀቅ ድረስ እየጮኸች ትናገራለች። ወላጅ አባቴ ተሸማቆ ጥግ ሲይዝ አየሁት።
ወንዱ ተከሳሽ በጣም የተረጋጋ ነው። ለሽህየው ያለው ፍራቻና አክብሮት አሁንም እንዳለ ያስታውቃል። ድምፁን ዝቅ አድርጎ፡ ''ወላሂ አሕመድ! በ1980 (?) የመስኖ መሬቴን ወስደውብኝ ፈርቻቸው ዝም ብያለሁ። አሁን ደግሞ የእርሻ መሬቴ ላይ ነው የመጡብኝ" አለው ለአባቴ።
ችሎቱን የሚያዩት የቀበሌ ሰዎች ለነዚያ ሁለት ሰዎች ፈርደዋል። የሽሁን ክስ አልተቀበሉም። እንዲያውም በሽሁ ተደጋጋሚ ክስ እንደተሰላቹና ከዚህ በኋላ ይህንን የመሬቱን ጉዳይ ደግመው እንደማያዩ ተናገሩ። ሸህየው "እና እናንተ የሰማዩን ጉዳይ ነው የምታዩት?" ብሎ ሲሳለቅ አጃቢዎቹ ሳቁ። ከዚህም ውጭ ደስ የማይሉ ንግግሮች ከሸሁ ይወጡ ነበር። ብዙው ታዳሚ ፍርሃት ባረበበበት ዝምታ ቢያሳልፍም ያንገሸገሻቸው ሰዎችም ነበሩ። "መከበር በከንፈር" ነው ነገሩ።
የፈለገ የማይደፈር የሚመስል ስም ቢኖርህ እንኳ በክፉ ግብርህ ክብርህን ታጣለህ ልልህ ነው ምሳሌውን ያመጣሁት። መቼስ የሱፍያ ወልዮች ህዝብ ዘንድ ያላቸው አይነት ቦታ እንደማይኖርህ አታጣውም። ልብ በል! ጥፋትህ ሲደጋገም የሚያምንህ እየቀነሰ፣ የሚንቅህ እየበዛ ነው የሚሄደው። ይሄ ስለ ዱንያው ስናወራ ነው። ነገ በቂያማ ቀን በፍጥረታት ሁሉ መሀል ከመዋረድ አላህ ይጠብቀን።
ፅሁፌን በአንድ ነጥብ ልቋጭ! የሰዎችን አማና ለግል ጥቅም በማዋል ስማችሁ በተደጋጋሚ የተነሳባችሁ ኡስታዞች! ለመስጂድ፣ ለመድረሳ፣ ለደዕዋ #በስማችሁ ገንዘብ ለመሰብሰብ አትሞክሩ። ይቅርባችሁ። ክብራችሁንም ጠብቁ፣ ሰውንም አታስወንጅሉ። አስፈላጊ ሆኖ ካገኛችሁት ስራውን ሌሎች ይስሩት። እናንተ ስማችሁን አርቃችሁ እንዲሁ በቅስቀሳ ብቻ አግዙ። አንዳንዴ ሰው ይሳሳታል። ጥፋትን መታወቂያ ልማድ ማድረግ ግን ያስንቃል። እወቁበት። ወላሁ አዕለም።
ማሳሰቢያ፦
* ህዝብ ዘንድ የምትታመኑ እና አማናችሁን የምትወጡትን እየነካሁ አይደለም። እናንተ መታመናችሁን ለበለጠ ኸይር ስራ ልትጠቀሙበት ነው የሚገባው። ውለታችሁም ለብዙ ሰው ነው። አንዳንዴ በአጥፊዎች ላይ የሚሰነዘረው ወቀሳ ጤነኞችን እንዳያሸማቅቅና እንዳያስበረግግ ያስፈራል።

የገዝዛ ጉዳይ
~
የገዝዛ ጉዳይ ለጊዜውም ቢሆን ትልቅ ደስታ ይሰጣል። ከሰሞኑ ጦርነቱ ቆሞ ገዝዛውያን አንፃራዊ ሰላም ማግኘታቸው ከዚህም በተጨማሪ እርዳታ መግባቱ ትልቅ ነገር ነው። ስምምነቱ አሁንም ስጋት ያጠላበት ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት ይሄ በትራምፕ የቀረበው ስምምነት አንዳንድ አንቀፆቹና እና አፈፃፀማቸው ግልፅነት የሚጎድላቸው መሆናቸው ነው። ያንን ተከትሎም በተለይ ሶስት ነጥቦች መግባባት ላይ የሚደረስባቸው ይሆናሉ ወይ የሚለው አሁንም አጠራጣሪ ነው።
1ኛ፦ ጊዜያዊ ስምምነቱን ተከትሎ ኢ $ ራኤል ከያዘቻቸው የገዝዛ አካባቢዎች ቢጫ ወደተቀለመው አፈግፈጋለች። ነገር ግን ይሄ በቢጫ የተቀለመው ክፍል ከጠቅላላው የገዝዛ ስፋት 58% የሚሸፍን ነው። ከስምምነቱ ፍፃሜ ላይ የእውነት ይህንን ክፍል ለቃ ትወጣለች ወይ? ሃገሪቱ ከበፊት ጀምሮ የሚከሰቱ ጦርነቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ግዛቷን እያሰፋች ነው የመጣችው።
2ኛ፦ በስምምነቱ ሃማS ሙሉ ትጥቁን እንዲፈታ ይጠበቃል። የእውነት ይሄ ጉዳይ ይፈፀማል ወይ? አጠያያቂ ነው። አሁንም ቡድኑ በዚህ ነጥብ ላይ ፈቃደኛ እንዳልሆነ እየገለፀ ነው።
3ኛ፦ በስምምነቱ ፍፃሜ ላይ ገዝዛን በሚያስተዳድረው አካል ውስጥ ሐማS ምንም ቦታ እንደማይኖረው ተገልጿል። ይልቁንም ተዋጊዎቹ ወይ ጠቅልሎ ወደ ውጭ መውጣት፣ አለያ ደግሞ ምህረት ተደርጎላቸው በሰላም መኖር ብቻ ነው የቀረበላቸው አማራጭ። ይህ ራሱ ለቀረበው ስምምነት ሌላ ማነቆ የሚሆን ይመስላል።
እነዚህ ሶስት ነጥቦች ላይ አለመግባባት ችግሩን ወደነበረበት እንዳይመልሰው ያሰጋል። ለጊዜው የኢ $ ራኤል ድብደባ ቆማል። የእርዳታ እህሎችና ቁሳቁሶች እየገቡ ናቸው። ከፊል ተፈናቃዮች ወደ ወደሙ መኖሪያ ሰፈሮቻቸው እየተመለሱ ነው። ከፊሎቹ አካባቢዎቻቸው አሁንም በኢ $ራኤል የተያዙ በመሆናቸው መመለስ አልቻሉም።

ከሃኪም ቤቶች በስርቆት እየወጣ ሱቅ ላይ የሚሸጠውን ፕላምፒ ነት (Plumpy nut) መግዛት አይፈቀድም። የተሰረቁ እቃዎችን መግዛት ማለት የሌሎችን ሐቅ ያላግባብ መጠቀም እና አጥፊዎችንም መተባበር ነው የሚሆነው። ከተቻለ ይህንን ተግባር የሚፈጽሙ ሻጮችንና ባለ ሱቆችን አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ይገባል። እምቢ ካሉ ሊርቋቸው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዉድና የተከበራችሁ ኢትጵያዉያን እህት ወድሞቸ
ይሄ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወድማችን
ከጠፋ 1 አመት ከ4ወር ወይም 5ወር ይሆነዋል
ስሙ አረቡ ከበደ ፋሪስ ይባላል እና እደማንኛዉም
ሰዉ ሰርቸ እለወጣለሁ ኑሬየን አሻሽላለሁ ብሎ
በበሀር መቶ ድበርን አልፎ ሳኡድ ዉስጥ ገብቶ
ጓደኞቹ ሲጠየቁ ደርብ የሚባል ቦታ እደተጠፋፉ
ተናግረዋል እናም ይሄን ልጅ የሚታዉቁ ስለዚህ
ልጅ አክባሩን የምታዉቁ እባካችሁ ተባበሩን
እናት አባት ከዛሬ ከነገ ይመጣል እያሉ ደጅ
ደጅ እያዩ ጧት ማታ እያነቡ ስለሆነ እባካችሁ
ሁላችሁም በየ ቻናሎች ሸር በማድረግ ተባበሩን
ወድማችን አረቡ የትዉልድ ቦታዉ ቦረና መካነ
ሰላም ልዩ ቦታዉ ኮሸሚ ይባላል
እናም ያያችሁ የሰማችሁ እታች ባለዉ ስልክ ቁጥር
ለአሏህ ብላችሁ አሳዉቁን ጀዛኩሙላሁ ኸይሯ
ስልክ ቁጥር
0535871953
ኩብራ ከበደ ፋሪስ
00251914066991
መለሰ ከበደ ፋሪስ
0566148196
ሙሀመድ ከበደ ፍሪስ
ዉድና የተከበራችሁ ኢትጵያዉያን እህት ወድሞቸ
ይሄ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወድማችን
ከጠፋ 1 አመት ከ4ወር ወይም 5ወር ይሆነዋል
ስሙ አረቡ ከበደ ፋሪስ ይባላል እና እደማንኛዉም
ሰዉ ሰርቸ እለወጣለሁ ኑሬየን አሻሽላለሁ ብሎ
በበሀር መቶ ድበርን አልፎ ሳኡድ ዉስጥ ገብቶ
ጓደኞቹ ሲጠየቁ ደርብ የሚባል ቦታ እደተጠፋፉ
ተናግረዋል እናም ይሄን ልጅ የሚታዉቁ ስለዚህ
ልጅ አክባሩን የምታዉቁ እባካችሁ ተባበሩን
እናት አባት ከዛሬ ከነገ ይመጣል እያሉ ደጅ
ደጅ እያዩ ጧት ማታ እያነቡ ስለሆነ እባካችሁ
ሁላችሁም በየ ቻናሎች ሸር በማድረግ ተባበሩን
ወድማችን አረቡ የትዉልድ ቦታዉ ቦረና መካነ
ሰላም ልዩ ቦታዉ ኮሸሚ ይባላል
እናም ያያችሁ የሰማችሁ እታች ባለዉ ስልክ ቁጥር
ለአሏህ ብላችሁ አሳዉቁን ጀዛኩሙላሁ ኸይሯ
ስልክ ቁጥር
0535871953
ኩብራ ከበደ ፋሪስ
00251914066991
መለሰ ከበደ ፋሪስ
0566148196
ሙሀመድ ከበደ ፍሪስ
Ahbash #08
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ
• ክፍል:- 8️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8025
• የእለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 23፦ الفصل السابع

የኪታብ ጥቆማ #27
~
* የኪታቡ ስም፦ الزنادقة عقائدهم وفرقهم ...
* አዘጋጅ፦ ሰዒድ ብኑ ፈላሕ አልዐሪፊ
* መጠን ፡ ሁለት ሙጀለድ
* ሰሞኑን ነው ያነበብኩት። በጣም ምርጥ ስራ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ ኢንሻአላህ።
* pdf ፋይል ቀጥሎ አያይዣለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
* የኪታቡ ስም፦ الزنادقة عقائدهم وفرقهم ...
* አዘጋጅ፦ ሰዒድ ብኑ ፈላሕ አልዐሪፊ
* መጠን ፡ ሁለት ሙጀለድ
* ሰሞኑን ነው ያነበብኩት። በጣም ምርጥ ስራ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ ኢንሻአላህ።
* pdf ፋይል ቀጥሎ አያይዣለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ahbash #09
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ
• ክፍል:- 9️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8025
• የእለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 27፦ الفصل التاسع

ዐረብ አገር ስትሄዱ ህጉን አክብራችሁ ኑሩ። ዐረብ አገር ውስጥ አስካሪ መጠጥ ማከፋፈል፣ አደንዛዥ እጾችን ማዘዋወር፣ የሴት ድለላ የመሳሰሉ ከባባድ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ ብዙ ሐበሾች አሉ። ከፊሎቹ በተራራዎችና ጠረፍ አካባቢ መሳሪያ ታጥቀው ሁሉ የሚንቀሳቀሱ ናቸው። በሚገርም ሁኔታ የመን ውስጥ ከሑሢዮች ጋር ጭምር ተሰልፈው የሚዋጉ አሉ። እዚህ የራሳቸውን አገር ለማፍረስ የሚጥሩት አልበቃ ብሎ ባህር ተሻግረው የሰው ሃገር ሊያፈርሱ ተሰልፈዋል። ስርቆትማ ዐረብ አገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን አበሻ የሚበዛበት ሁሉ የተለመደ ነው።
እነዚህ ወንጀለኞች በመብዛታቸው የተነሳ ሰርቶ ለመለወጥ የሚወጣው ምስኪን ወገን በስመ ሐበሻ ፍዳውን ይበላል፣ ይታፈሳል፣ ይሳቀቃል። ያሳዝናል። እንዲህ አይነት ወንጀለኞችን አትቅረቡ። እንዲያውም የተረጋገጠ መረጃ ካላችሁ አሳልፋችሁ ስጧቸው። አሽቃባጭ ይበሏችሁ። ለወንጀለኞች ከማሽቃበጥ ይሻላል። እዚህ በዘር እየተቧደነ እንደሚሸፋፈነው እዚያም እንድትሸፍኑለት ለሚፈልግ ገLቱ ቦታ አትስጡት። እዚህ መስጂድ እያቃጠለ ቢጨፍር፣ መስጂድ ውስጥ እየገባ ቢገድል የሚነካው የለም። ህግ አይጠይቀው፣ ህሊና አይወቅሰው፣ አባት አይቆጣው፣ አዋቂ አይመክረው፣ ባህል አይገታው። ሁሉም የለማ!! እዚያም እንዲሁ ሊሆን ያምረዋል። ከወንጀለኞቹ የሚከላከሉት ናቸው የሚገርሙት። ይሄ ያገራችንን ገፅታ ያጠለሻል ተው እንደማለት እዚህ የለመደውን ውንብድና ውጭም እንዲቀጥል ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፦
~
በግdያ ወንጀል ተጠርጥሮ ፎቶው እየተዘዋወረ ስላለው ኢትዮጵያዊ አይደለም ትኩረቴ። ይሄ እውነተኛ ይሁን አይሁን አላውቅም። ነገር ግን በተለመደው የዘር ውግንና እየተጠራሩ ሸፍኑ ማለት ነውረኛ አካሄድ ነው። ልክ ከነሱ ውስጥ በጅምላ ሁሉንም ሐበሻ መወንጀላቸው ጥፋት እንደሆነው ሁሉ ማለት ነው።

መመላሻዎቻችን እነማን ናቸው?
~
ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በድምፅም ሆነ በፅሁፍ ብዙ አይነት ብዥታዎች ይሰራጫሉ። እነዚህ ብዥታዎች ጥንቃቄ ካላደረግን መሰረታዊ ኢማናችን ላይ፣ የዐቂዳ ነጥቦች ላይ እና ሌሎችም ወሳኝ ርእሶች ላይ ያለንን የፀና አቋም ሊያናውጡት ይችላሉ። ለዚህ አደጋ አንዱ ሰበብ በእንዲህ አይነት የዲን ጉዳዮች ላይ ታማኝ መመለሻ አለመኖር ነው። አለመኖር ስል አለመለየት ማለቴ ነው። በትልልቅ የዲን ጉዳዮች ላይ ግርታ ቢኖር መመለሻ የሚሆኑ የሸሪዐ መረጃዎችን ትንታኔ አብጠርጥረው የሚያውቁ፣ በዒልምም በተቅዋ የተመሰከረላቸው ትልልቅ እና ታማኝ ዑለማኦች ዛሬም አሉ። ነገር ግን ብዙው ሰው ታማኝ የሆኑ እና ታማኝ ያልሆኑ የዲን መመለሻዎችን አይለይም። ያም ቢጮህ ይህም ቢጮህ ይወዘውዘዋል። ይሄ ግልፅ መስመር ሊበጅለት የሚገባ ጉዳይ ነው። ታማኝ የዲን መመለሻዎችን መለየት ከዚያም በሆነ ርእሰ ጉዳይ ላይ ግርግር ቢፈጠር ወደነዚያ የዲን መመለሻዎች ትንታኔና ፈትዋ መመለስ ሁነኛ መድሃኒት ነው። አላህ እንዲህ ይላል :-
{ فَسۡـَٔلُوۤا۟ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ }
"የማታውቁም ብትሆኑ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ።" [አነሕል፡ 43]
እንደምናየው ዛሬ ዛሬ ሁሉም ይናገር ዘንድ መድረኩ ክፍትና የተመቻቸ ነው። ቀድመን አወቅነውም አላወቅነውም፣ በተባ ብእር እና በሰላ አንደበት የተናገረ ሁሉ ትኩረታችንን የሚወስድ ከሆነ ውጤቱ ከባድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ታማኝ የሆኑ መመለሻዎቻችንን እንለይ። ልባችንን ለአልፎ ሂያጅ መንገደኛ ሁሉ እየከፈትን እንዳንጎዳ ጥንቃቄ እናድርግ።

የዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ ኪታብ ደርስ ወደ መጠናቀቂያው እየተቃረበ ነው። ቀጣይ ደርስ የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ይሆናል ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8025
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 30
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦