Telegram Web Link
Live stream finished (55 minutes)
Hisnul Muslim #03
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣3️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 10፣ إن في خلق السماوات
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ደስ ይላል!
~
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ብኑ ፈውዛን አልፈውዛን - አላህ ይጠብቃቸው - የሳዑዲ አረቢያ ሙፍቲ ሆነው ተመድበዋል። ላማረ ቀደምት ያማረ ምትክ! አልሐምዱ ሊላህ ቢኒዕመተሂ ተቲሙ ሷሊሓት!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአማላጅ ሰበብ ሙታኖችን መጣራት
~
"የሁዳውንም፣ ነሷራውንም፣ መጁሳውንም እንቀበላለን" ብሏል ዑመር ይማም። ይሄው ከነሷራው ጋር ያላቸው አንድነት። ከሰሞኑም እርስ በርስ ሲሞጋገሱ፣ በጋራ "ወሃ ^ ብያ " በሚሉት ላይ ሲዘምቱ ነበር። የእውነትም ቀላል የማይባል የጋራ እምነት አላቸው። ለምሳሌ ያክል ሁለቱም ደጋጎች ወይም ፃድቃኖች የሚሏቸውን በመማፀን፣ በመጣራት ላይ ይመሳሰላሉ። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ሲፋጠጡ የነበሩት አጋሪዎችም የማሻረካቸው ሰበብ ይሄው ነበር። አላህ እንዲህ ይላል :-

{ وَیَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَضُرُّهُمۡ وَلَا یَنفَعُهُمۡ وَیَقُولُونَ هَـٰۤؤُلَاۤءِ شُفَعَـٰۤؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا یَعۡلَمُ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَلَا فِی ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَـٰنَهُۥ وَتَعَـٰلَىٰ عَمَّا یُشۡرِكُونَ }

"ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ 'እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው' ይላሉ፡፡ 'አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን' በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።" [ዩኑስ፡ 18]

{ وَٱلَّذِینَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦۤ أَوۡلِیَاۤءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِیُقَرِّبُونَاۤ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰۤ }
"እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት 'ወደ አላህ ማቃረብን #እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም' (ይላሉ)።" [አዝዙመር፡ 3]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን ነብያችን ﷺ ሺርክ ተመልሶ አይመጣም ብለዋልን?
~
ነብያችን ﷺ እንደ ሺርክ የሚጎረብጣቸው ነገር አልነበረም። ለዚያም ነበር ሶሐባቸው ጀሪር ብኑ ዐብዲላህን "ምነው ከዚህ ከዘል ኸለሷ አታሳርፈኝም?" ብለው መጠየቃቸው። ዘል ኸለሳ የመን ውስጥ የነበረ ጣኦት ነው። “እንዴታ አሳርፈዎታለሁ እንጂ!” ነበር የጀሪር ምላሽ። ከዚያም ለዚሁ የተዘጋጀ ሰራዊት እየመሩ የመን ድረስ በማቅናት ዘል ኸለሷን ዶግ አመድ አደረጉት። ዜናው ለነብዩ ﷺ ሲደርሳቸው ሌላ ጊዜ ሲደሰቱ ያደርጉት ከነበረው የሶስት ጊዜ ዱዓእ በተለየ አምስት ጊዜ እየደጋገሙ ዱዓእ አደረጉላቸው። [ቡኻሪ፡ 3020] [ሙስሊም፡ 2476]

ብዥታ!
=
ዑቅበቱ ብኑ ዓሚር ባስተላለፉት ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"وإِنَّي قد أُعْطيتُ مفاتيحَ خزائِنِ الأرضِ ، وإِنَّي واللهِ ما أخافُ عليكم أنْ تُشْرِكوا بعدي ، ولكني أخافُ عليكم الدنيا أنْ تَنَافَسُوا فيها
"​እኔም የምድርን ድልብ ሀብቶች ቁልፎች በእርግጥ ተሰጥቻለሁ። በአላህም እምላለሁ! ከኔ በኋላ ታጋራላችሁ ብዬ አልሰጋም። ነገር ግን በሷ (በዱንያ) መሽቀዳደማችሁን ነው ነው የምፈራላችሁ።" [ቡኻሪ፡ 1344] [ሙስሊም፡ 2296]

ይህንንና መሰል መልእክት ያላቸውን ሐዲሦች መነሻ በማድረግ ሺርክ ዳግም ወደ ነብዩ ﷺ ኡመት ስለማይመለስ ከሺርክ ማስጠንቀቅን እና ስለ ሺርክ አደጋ ማስተማርን የሚቃወሙ ሱፍዮች አሉ። ይሄ ሙግት ውድቅ እንደሆነ ሶስት አይነት ምላሾችን መስጠት ይቻላል።

#ምላሽ_አንድ:- የሐዲሡ መልእክት እናንተ እንደምትሉት አይደለም!

የተጠቀሰው ሐዲሥ መልእክት በህዝባቸው ውስጥ ሺርክ አይከሰትም ማለት ሳይሆን ኡመታቸው ሙሉ በሙሉ ከኢስላም ወጥቶ የሺርክ ተከታይ አይሆንም ማለት ነው። ለዚህም እነዚህ ሱፍዮች እራሳቸው የሚከተሏቸውን ሁለት ኢማሞችን አጣቅሳለሁ።

1. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦
"وفي هذا الحديث معجزات لرسول الله صلى الله عليه سلم ؛ فإن معناه الإخبار بأن أمته تملك خزائن الأرض وقد وقع ذلك ، وأنها لا ترتد جملة وقد عصمها الله تعالى من ذلك ، وأنها تتنافس في الدنيا وقد وقع كل ذلك"
"በዚህ ሐዲስ ውስጥ የመልእክተኛው ﷺ ተዓምራት አሉ። ምክንያቱም ትርጉሙ፡ ኡመታቸው የምድርን ሀብቶች እንደሚቆጣጠሩ መናገር ነው። ይህም በእርግጥ ተከስቷል። እንዲሁም #በአጠቃላይ ከሃይማኖት እንደማይወጡ (እንደማይመለሱ)፤ የላቀው አላህ ከዚህ ጠብቋቸዋል። እንዲሁም በዱንያ (በዚህ ዓለም) ነገሮች እንደሚወዳደሩ፤ ይህ ሁሉ በእርግጥም ተከስቷልና።" [ሸርሑ ሙስሊም፡ 15/59]

2. ኢብኑ ሐጀርም እንዲህ ብለዋል፡-
"قوله: (ما أخاف عليكم أن تشركوا) أي على مجموعكم لأن ذلك قد وقع من البعض أعاذنا الله تعالى"
" 'ታጋራላችሁ ብዬ አልሰጋም' የሚለው #ባጠቃላይ ሁላችሁም ማለት ነው። ምክንያቱም ይሄ በአንዳንድ ክፍሎች ላይ #ተከስቷልና፤ የላቀው አላህ ይጠብቀን።" [ፈትሑል ባሪ፡ 3/211]

#ምላሽ_ሁለት፦ ሺርክ እንደሚከሰት የሚጠቁሙ ግልፅ ሐዲሦች አሉ።

1. አቡ ሁረይረህ ባስተላለፉት ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تَقُومُ السَّاعَةُ حتَّى تَضْطَرِبَ ألَياتُ نِساءِ دَوْسٍ، حَوْلَ ذِي الخَلَصَةِ
"የደውስ ጎሳ ሴቶች በዘልኸለሷ ጣኦት ዙሪያ መቀመጫቸው ሳይባለጥ (ጠዋፍ ሳያደርጉ) ቂያማ አይቆምም።" [ቡኻሪ፡ 7116] [ሙስሊም፡ 2906]

2. ሠውባን ባስተላለፉትም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تقومُ الساعةَ حتى تلحق قبائلٌ من أمّتي بالمشركينَ ، وحتى يُعْبَدَوا الأوثانُ
"ከህዝቦቼ የተወሰኑ ጎሳዎች ወደ ሙሽሪኮች ሳይጠጉ፣ የተወሰኑትም ጣኦቶችን ሳያመልኩ ቂያማ አትቆምም!" [ቲርሚዚይ፡ 2219]

#ምላሽ_ሶስት:- ሺርክ ዳግም ተመልሶ በተግባር ተከስቷል።

ለዚህ ማረጋገጫ ማንም ሊያስተባብለው የማይችላቸው ታሪካዊ መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ፦

1. የነብዩን ﷺ ሞት ተከትሎ በርካታ የዐረብ ጎሳዎች ወደ ሺርካቸው ተመልሰው ነበር። [ፈትሑል ባሪ፡ 12/276]
2. ዐሊይን ጌታ ነው የሚሉ ሺ0ዎች ተነስተው ዐሊይ ራሳቸው እርምጃ ወስደውባቸዋል። [ቡኻሪ፡ 3013]
ኋላም ላይ ዐሊይን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያመልኩ በርካታ የሺ0 ቡድኖች ተፈልፍለው ነበር። ዛሬም ኑሶይሪያ ሺዐዎች 0ሊይን የሚያመልኩ መሆናቸው የዚህ ሺርክ አንድ ማሳያ ናቸው።
3. ቀራሚጧዎችም እንዲሁ ከዛሬዋ በሕረይን የተነሱ የታወቁ የሺ0 ቡድኖች ሲሆኑ በሐጅ ወቅት ጥቃት ፈጽመው፣ ሑጃጆችን ጨፍ ^ ጭፈው፣ ሐጀረል አስወድን ወስደው ለ20 ምናምን አመታት አቆይተውታል። ሙሽሪኮች ነበሩ። [ሚርኣቱል ጂናን፣ አልያፊዒይ፡ 2/272]

4. ከላይ የተጠቀሰው የዘልኸለሷ ጣኦት ነብዩ ﷺ ዳግም ይመለካል ብለው እንደተነበዩት በደውስና በዙሪያው ያሉ የዐረብ ጎሳዎች እንደገና እየተመለከ ነበር። የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ደዕዋ ፍሬ አፍርቶ በጊዜው የነበረው ንጉስ አልኢማም ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ሰዑድ ረሒመሁላህ ተነስቶ የተወሰኑ ዳዒያዎችን ወደ ዘልኸለሷ በመላክ እንዲያፈርሷት አደረገ። የመጀመሪያው የሰዑድ ቤተሰቦች አገዛዝ በቱርኮች ሲወድቅ መሀይማን ዳግም ዘል ኸለሷን ማምለካቸውን ተያያዙት። እንደገና ንጉስ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ዐብዲረሕማን ኣለ ሰዑድ ሒጃዝን ሲቆጣጠር በዚያ አካባቢ ያለውን አሚር በማዘዝ ከሰራዊቱም የተወሰነው ወደዚያው አቅንቶ አፈራረሷት። ቅሪቷንም አስወገዱት።” [ፈዋኢዱን ሚን መዓኒ ሚን ኩቱቢል አልባኒይ፡ 1/14]

በተረፈ "ሸይጧን በዐረቢያ ልሳነ-ምድር ላይ ሰጋጆች እንደማያመልኩት ተስፋ ቆርጧል" የሚለው ሐዲሥ መልእክቱ በጊዜው በነበረው የተውሒድ መስፋፋት ምክንያት የነበረውን ተጨባጭ መግለፃቸው እንጂ ሺርክ ዳግም አይመለስም ማለት አይደለም። ሲጀመር ሐዲሡ የሚለው በዐረቢያ ልሳነ-ምድር ነው። እናንተ ምን ቤት ናችሁ? በዚያ ላይ ከላይ እንዳሰፈርኩት በ0ረቢያ ምድር ጨምር ሺርክ እንደሚከሰት የሚገልፁ ሐዲሦች፣ በተጨባጭ እንደተከስተም የሚያሳዩ ታሪካዊ መረጃዎች ባሉበት እውነታውን መሸምጠጥ ራስን መሸወድ ነው ። ይልቅ ከሺርካችሁ፣ ከቀብር አምልኮታችሁ ተመለሱ። አንዳንዶቹማ አይናቸውን በጨው አጥበው ከነ ጭራሹ ቀብር የሚያመልክ አካል የለም እያሉ ነው። የቀብር አምልኮ፣ የሙታን አምልኮ ማለት ቀጥታ የናንተ ተግባር ነው። ለዚህ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እናንተ ዘንድ በክፉ የማይጠረጠረው ፈኽሩ ራዚይ የተናገረውን ላያይዝ፡-

«أَنَّهُمْ وَضَعُوا هَذِهِ الْأَصْنَامَ وَالْأَوْثَانَ عَلَى صُوَرِ أَنْبِيَائِهِمْ وَأَكَابِرِهِمْ، وَزَعَمُوا أَنَّهُمْ مَتَى اشْتَغَلُوا بِعِبَادَةِ هَذِهِ التَّمَاثِيلِ، فَإِنَّ أُولَئِكَ الْأَكَابِرَ تَكُونُ شُفَعَاءَ لَهُمْ عِنْدَ اللَّه تَعَالَى، وَنَظِيرُهُ فِي هَذَا الزَّمَانِ اشْتِغَالُ كَثِيرٍ مِنَ الْخَلْقِ ‌بِتَعْظِيمِ ‌قُبُورِ الْأَكَابِرِ، عَلَى اعْتِقَادِ أَنَّهُمْ إِذَا عَظَّمُوا
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
قُبُورَهُمْ فَإِنَّهُمْ يَكُونُونَ شُفَعَاءَ لَهُمْ عِنْدَ اللَّه»
“እነዚህን ጣኦቶች በነብዮቻቸውና በታላላቆቻቸው አምሳል ቀረጿቸው። እናም እነዚህን ሃውልቶች በማምለክ እስከተጠመዱ ድረስ እነዚህ ታላላቆች ከላቀው አላህ ዘንድ አማላጅ እንደሚሆኗቸው አሰቡ። በዚህ ዘመን የዚህ ብጤ የሆነው በርካታ ፍጡሮች የታላላቆቻቸውን መቃብር በማላቅ መጠመዳቸው ነው። እነሱ መቃብሮቻቸውን ሲያልቁ ለነሱ ከአላህ ዘንድ አማላጅ እንደሚሆኗቸው ያምናሉ።” [መፋቲሑል ገይብ ወይም አተፍሲሩል ከቢር በመባል የሚታወቀው የራዚ ተፍሲር፡ 17/227]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 1/1447)

"ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓሊ እና " ለሐጅ ፍላጎት የለኝም " ያሉት " ሐጅ " ዑመር ።

ከአምስት አመታት በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅጉን የሚታወቁትና በርካታ አስደናቂ በሆኑ እውቀቶች የታጨቁ መፃህፍቶች ን ለሙስለሙ ማህበረሰብ ያበረከቱት ኢትዮጲያዊው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሞተዋል ... በሃገራችን ሚዲያዎች ይህን ያህል አልተባለላቸውም ነበር .... ከቀናት በፊት ይህ ነው የሚባል ደህና ቅሪትን በመተው የማይታወቁት " ሐጂ " ዑመር ሲሞቱ ፅንፈኛ የሆነ የሙስሊም ጠላቶች ጭምር በጉዳዩ ላይ እጅጉን የረዘመ ስራ ሰርተዋል .... እያጦዙ ፅፈዋል ፣ ተናግረዋል

ከዚህ ሁሉ ጀርባ ያለው ነገር ግልፅ ነው :: ፅንፈኞቹ የሚፈልጉት የቅርቡን ሟች መንገድ አጉኖ ማቅረብ ነው ... አዎ ! የሚመቻቸው
" አሏህ ሽቶት ሄድኩ እንጂ ለሐጅ ፍላጎት የለኝም - ፍላጎቴ ለሸኾቼ ነው " እያለ የኢስላም መሰረቶች ላይ ቸልተኝነትን የሚሰብከው ነው ። የሚፈልጉት ወደ ቀብር አምልኮ የሚጣራውን ሞዴል እያደረጉ ማቅረብ ነው ...

እንዲኖር የሚመኙት ወሃቢያ ፣ አክራሪ እያለ እውነተኛውን የኢስላም ገፅታና ተውሒድን እየተዋጋ የነሱን ግብ የሚያስፈጽም አካል ነው :: የሚወዱት እነሱን እያወደሰና ለነሱ እንቅፋት ሳይሆናቸዉ የተውሒድ ባለቤቱን በማክፈር ላይ አንይኑን የማያሸውን መሪ ነው ።

ሸይኽ ሙሐመድ የቀብር አምልኮና አደንዛዥ የሆኑ መጤ መንገዶችን የሚቃወሙ ታላቅ ዓሊም ነበሩ ። በተለያዩ የሸሪዓ የትምህርት ዘርፎች ላይ በርካታ አስደናቂ ኪታቦችን ትተው ያለፉ ታታሪ የተውሒድ ዓሊም ነበሩ ! ወደ ደህንነት ሰራተኞች በመመላለስ እነ እገሌን እሰሩ ፣ አጥፉ የሚሉ ስራ ፈት እና ሴራ ሸራቢ አልነበሩም :: እናም ስለሳቸው ማውራት ፅንፈኞቹን ትርፍ ያሳጣል !

https://www.tg-me.com/msirage4
የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 16፣ دعاء دخول المسجد
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (55 minutes)
Hisnul Muslim #04
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣4️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 16፣ دعاء دخول المسجد
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሶሐቦች ጥረት፣ የሰዎችን እምነት ለመጠበቅ
~
እነዚያ የኢስላም አንበሶች፣ የነብዩ ﷺ ድንቅ ሶሐቦች ተውሒድን በመጠበቅ ላይ በነብያቸው ፈለግ ላይ ተጉዘዋል። የተውሒድ ብርሃንን ሊያዳርሱ በየአለማቱ ተበትነዋል። የሙስሊሞችን አቂዳ ለመጠበቅ የሚችሉትን መስዋእትነት ሁሉ ከፍለዋል። ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ በሐጅ ጉዞ መንገድ ላይ የሱብሕን ሶላት ከሰገዱ በኋላ የሆኑ ሰዎች ወደሆነ ቦታ ሲሽቀዳደሙ ተመለከቱና “ምንድን ነው ይሄ?” ሲሉ ጠየቁ። “የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሰገዱበት ቦታ ነው” አሏቸው። የዚህን ጊዜ ዑመር “ልክ በዚህ መልኩ ነው የመፅሐፉ ሰዎች የጠፉት። የነብዮቻቸውን ፋና እየተከተሉ ምኩራቦች አድርገው ይይዟቸዋል። ከናንተ ውስጥ ከዚህ ቦታ ሶላት የደረሰበት ሰው ይስገድበት። ከናንተ ሶላት ከዚህ ቦታ ያልደረሰበት ሰው ግን እዚህ እንዳይሰግድ” አሉ። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 2/185]

እንግዲህ የነብዩን ﷺ ቅሪቶች በተመለከተ እንዲህ ከተባለ ከሳቸው በታች ያሉ ደጋጎችን ቅሪቶች በተመለከተስ ምን ሊባል ነው?
ሶሐቦች ከነብዩ ﷺ ጋር ሆነው ከስሯ “የበይዐተ ሪድዋን” ቃል ኪዳን የፈፀሙባትን ዛፍ ባመቱ ሲመጡ ረስተዋታል። መርሳታቸውንም “የአላህ እዝነት ነው” ይሉናል በተውሒድ ከፍ ያሉት የነብዩ ﷺ ባልደረቦች። [ቡኻሪ፡ 2958] የሚገርመው ግን ኋላ ላይ ገና ሶሐቦች ሳያልቁ “አውቀናታል” የሚሉ ሰዎች መምጣታቸው ነው። ታላቁ ታቢዒይ ሰዒድ ኢብኑል ሙሰዪብ ታዲያ፡ “የሙሐመድ ሶሐቦች አላወቋትም፣ እናንተ ግን አወቃችኋት?¡ እናንተ የበለጠ አዋቂዎች ናችሁን?i” በማለት ተሳልቀውባቸዋል። [ቡኻሪ፡ 4163] ከዚያ በኋላ “አውቀናታል” ያሏትን ዛፍ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስቆረጧት ተዘግቧል። [አልቢደዕ፣ ኢብኑ ወዷሕ፡ 42]

አቡል ዓሊያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ “የቱስተር ከተማን በከፈትን ጊዜ በሁርሙዛን ግምጃ ቤት ውስጥ አስከሬን ያለበት አልጋ አገኘን። … አስራ ሶስት የተበታተኑ ቀብሮችን በቀን ቆፈርንና (ካንዱ) ውስጥ በሌሊት ቀበርነው። ከዚያም ሰዎች እንዳያወጡት በመስጋት እንዳይለይ አድርገን ቀብሮቹን ሁሉንም (በተመሳሳይ ከመሬት) አስተካከልናቸው።”

* “ከሱ ምን ይፈልጋሉ?” ተብለው ሲጠየቁ
∆ “ድርቅ ሲሆንባቸው አልጋውን ይዘውት ይወጡና ዝናብ ይለምኑበታል” አሉ አቡል ዓሊያ።
* “ሰውየው ማነው ብላችሁ ትገምታላችሁ?” ብለው ጠየቋቸው።
∆ “ዳንኤል የሚባል (ነብይ) ነው” አሉ።
* “ስታገኙት ከሞተ ምን ያክል ሆኖታል?” ሲሏቸው
∆ “ሶስት መቶ አመት ሆኖታል” አሉ።
* “ከሱ ምን የተቀየረ አለው?” ሲሏቸው
∆ “ከማጅራቱ አካባቢ ጥቂት ፀጉሮች እንጂ የተቀየረ የለም። የነብያትን ስጋኮ አፈር አይበላውም” አሉ። [አልመጋዚ፣ ኢብኑ ኢስሓቅ፡ 6]

ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ከዚህ ታሪክ ስር እንዲህ ይላሉ፡-

“በዚህ ታሪክ ውስጥ ሙሃጂሮችና አንሷሮች የፈፀሙት ተግባር ሰዎች እንዳይፈተኑበት ቀብሩን እንዳይለይ ማድረግ ነው እንጂ እሱ ዘንድ ዱዓእ እንዲደረግና በረካ እንዲፈልጉበት ግልፅ ማድረግ አይደለም። ዘግይተው የመጡት ሰዎች ቢያገኙት ኖሮ ለሱ ሲሉ በሰይፍ ይሞሻለቁ ነበር። ከአላህ ውጭም ያመልኩት ነበር። በርግጥም ከዚህ ጋር የማይነፃፀሩና የማይቀራረቡ መቃብሮችን ጣኦቶች አድርገው ይዘዋል። አገልጋዮች መድበውላቸዋል። ከመስጂዶች የበለጡ የአምልኮት ቦታዎችም አድርገዋቸዋል።

መቃብር ዘንድ ዱዓእ ማድረግ፣ እዚያም ሶላት መስገድ፣ በነሱም በረከትን መሻት ትሩፋት ቢኖረው ኖሮ ወይም ሱና ቢሆን ኖሮ ወይም የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ሙሃጂሮችና አንሷሮች ይህን ቀብር ለእንዲህ አይነት ተግባር ምሳሌ ያደርጉት ነበር። እሱም ዘንድ ዱዓእ ያደርጉ ነበር። ከኋላቸው ለሚመጣ ትውልድም ፍኖት ያደርጉት ነበር። ነገር ግን ከኋላቸው ከመጡ ክፉ ምትኮች በተሻለ አላህን፣ መልእክተኛውንና እምነቱን የሚያውቁ ነበሩ። እነሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮችም እንደዚያው በዚሁ መንገድ ላይ ነው የተጓዙት። እነሱ በብዛት እያሉ ከነሱ ዘንድ የሶሐቦች መቃብር በየሀገራቱ በብዛት ነበር። ከመሆኑም ጋር ከነሱ ውስጥ አንድም ከሶሐቦች ቀብር ዘንድ ሄዶ እርዳታ የጠየቀ፣ እሱንም የለመነ፣ በሱም የተመጀነ፣ በሱ ፈውስን፣ ዝናብን፣ እገዛን የጠየቀ የለም።” [ኢጋሠቱል ለህፋን፡ 1/202-203]

ከዚያ በኋላ ግን ሺርክን ያነገሱ፣ ተውሒድን ያኮሰሱ፣ ቃላቸውን ያፈረሱ፣ ስሜታቸው ጋር የሚፈሱ ሱፍያ የሚባሉ ክፉ ምትኮች ተተኩ። የሶሐቦችን ግንዛቤ ተመልከቱ። ከዚያም የኛን ዘመን ትውልድ ታዘቡ። የዛሬ ቀብር አምላኪዎችስ ከቀብር ዘንድ ሲቆሙ ማንን ነው የሚያስቡት? የነብዩ ﷺ አስተምህሮት ለእንዲህ አይነት የጣኦት ስርኣት ሰይፍ ነበር፣ የተሰላ ሰይፍ! አቡ ዋቂድ አለይሢይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ወደ ሑነይን ወጣን። ከኩ ^ ፍር ከወጣን ቅርብ ጊዜያችን ነበር። (አዲስ ሰለምቴዎች ነን።) ለሙሽ ^ ሪኮቹ ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት እና መሳሪያዎቻቸውን የሚሰቅሉባት የቁርቁራ ዛፍ አለች። ከዚያ በአንዲት የቁርቁራ ዛፍ አጠገብ አለፍን። ‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኛም ይቺን መስቀያ አድርግልን፣ ለሙሽ ^ሪኮቹ መስቀያ እንዳለቻቸው’ አልን። ነብዩ ﷺ {አላሁ አክበር! ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! የኢ $ራኢል ልጆች ለሙሳ 'ለነሱ (ለሙሽ ^ሪኮቹ) አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክ አድርግልን' ያሉት አይነት ነው የተናገራችሁት!' እሱም 'እናንተ የማታውቁ ህዝቦች ናችሁ' ብሏቸዋል። በውኑ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ልማዶች ትከተላላችሁ!} አሉ።” [ዚላሉል ጀናህ፡ 1/31]

አቡ በክር አጦርጡሺይ በዚህ ሐዲስ ስር እንዲህ ይላሉ፡- “ተመልከቱ እንግዲህ አላህ ይዘንላችሁና። የትም ቦታ ሰዎች የሚያስቧት፣ የሚያከብሯት፣ ፈውስና መድሃኒትነትን የሚያስቧት፣ ሚስማሮችና ቁርጥራጭ ጨርቆች የሚሰቅሉባት ቁርቁራ ወይም ሌላ ዛፍ ካገኛችሁ ዛቱ አንዋጥ ናትና ቁረጧት!!” [አልሐዋዲሥ ወልቢደዕ፡ 38]

በሀገራችንም የስለት ክር የሚተበተብባቸው፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ ለበረካ ታስቦ አላፊ አግዳሚ የሚያርፍባቸው፣ ለዱዓእ የሚሰባሰቡባቸው፣ ከስራቸው እርድ የሚፈፀምባቸው በርካታ ዛፎች - ዛቱ አንዋጦች - ዛሬም ድረስ አሉ። ሺርክ የሚፈፀምባቸው ድንጋዮች፣ መቃብሮች፣ ... እነኚህን ነገሮች የሚስም፣ የሚሳለም፣ የሚተሻሽ፣ ቅቤ የሚቀባ፣ የስለት ክር የሚያስር፣ እርድ የሚያርድ፣ ምንነቱን በውል ከማያውቀው ቦታ ላይ ጠጠር እየወረወረ ድንጋይ የሚከምር፣ ... መአት ነው። እነዚህን ነገሮች ከተቻለ ከመሬት ላይ በእጃችን፣ ከሰው ጭንቅላት ውስጥ ደግሞ በደዕዋችን ልናስወግዳቸው ይገባል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 2/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 18፣ دعاء الاستفتاح
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (56 minutes)
Hisnul Muslim #05
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣5️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 18
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በ2018 ዓ.ል አዲስ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2017 ዓ.ል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ስንድቱን ጨርሶ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::

ስትመጡ የሚቀበሏቹ ወንድሞች እና እህቶች ማንኛውንም አይነት ትብብር የሚያደርጉላችሁ ይሆናል::

በምትመጡ ሰዓት ከዚህ በታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል የሚያስፍልጋቹን ትብብሮች  ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን::

• ፉርቃን ጀሚል  - 0968278025
• ሰለሃዲን ሙዘሚል-0983048814
• ጀማል አህመድ - 0909282436
• ፉአድ ከድር - 0921053417
• ኢብራሂም ጀማል-0976710967


🔴የእህቶችን ስልክ ለማግኘት ወንድሞች ጋር በዚህ 👉 0968278025 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::

ስለ ድሬዳዋ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ማንኛውም አይነት መረጃ ለማግኘት ይህንኑ የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ::

በተጨማሪ 👇
👉 Academic's Dep.t : https://www.tg-me.com/ddumsjaccadamic

DDUMSJ©


https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
2025/10/25 01:01:53
Back to Top
HTML Embed Code: