Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ሁድሁድ፡ ተአምረኛው ወፍ!
~
ነብዩ ሱለይማን ብኑ ዳውድ ﷺ እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ አላህ ሁሉን ነገር የገራላቸው ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡ ከቁርኣን ጥቂት ቀንጨብ ላድርግማ፡-
وَلَقَدْ آتَيْنَا دَاوُودَ وَسُلَيْمَانَ عِلْمًا ۖ وَقَالَا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي فَضَّلَنَا عَلَىٰ كَثِيرٍ مِنْ عِبَادِهِ الْمُؤْمِنِينَ
{ለዳውድና ለሱለይማንም እውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ አሉም፡- “ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ ለዚያ ከምእምናን ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን፡፡”}
وَوَرِثَ سُلَيْمَانُ دَاوُودَ ۖ وَقَالَ يَا أَيُّهَا النَّاسُ عُلِّمْنَا مَنْطِقَ الطَّيْرِ وَأُوتِينَا مِنْ كُلِّ شَيْءٍ ۖ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَضْلُ الْمُبِينُ
{ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፡፡ አለም፡ “ሰዎች ሆይ! የወፍን ቋንቋ ተስተማርን፡፡ ከነገሩ ሁሉም ተሰጠን፡፡ ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው!”}
وَحُشِرَ لِسُلَيْمَانَ جُنُودُهُ مِنَ الْجِنِّ وَالْإِنْسِ وَالطَّيْرِ فَهُمْ يُوزَعُونَ
{ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጂን፣ ከሰውም፣ ከወፍም የሆኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም በስርኣት ይደራጃሉ፡፡}
حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ
{በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን “እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ እንዳይሰባብሩዋችሁ” አለች፡፡}

فَتَبَسَّمَ ضَاحِكًا مِنْ قَوْلِهَا وَقَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ الَّتِي أَنْعَمْتَ عَلَيَّ وَعَلَىٰ وَالِدَيَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَالِحًا تَرْضَاهُ وَأَدْخِلْنِي بِرَحْمَتِكَ فِي عِبَادِكَ الصَّالِحِينَ
{(ሱለይማን) ከንግግርዋም እየሳቀ ፈገግ አለ፡፡ “ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን፣ የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሰራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ” አለ፡፡}
وَتَفَقَّدَ الطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِيَ لَا أَرَى الْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ الْغَائِبِينَ
{ወፎቹንም ተመለከተ፤ አለም፡ “ምነው ሁድሁድን አላየውም?! ወይስ (በቦታው) ከሌሉት ሆኗልን?”}
لَأُعَذِّبَنَّهُ عَذَابًا شَدِيدًا أَوْ لَأَذْبَحَنَّهُ أَوْ لَيَأْتِيَنِّي بِسُلْطَانٍ مُبِينٍ
{“በእርግጥ ብርቱ ቅጣትን እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ አርደዋለሁ!! ወይም (ለመጥፋቱ አሳማኝ የሆነ) ግልፅ የሆነን ማስረጃ ያመጣልኛል” (አለ፡፡)}

فَمَكَثَ غَيْرَ بَعِيدٍ فَقَالَ أَحَطْتُ بِمَا لَمْ تُحِطْ بِهِ وَجِئْتُكَ مِنْ سَبَإٍ بِنَبَإٍ يَقِينٍ
{(ሁድሁድ ግን) ሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም፡ “ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡”}
إِنِّي وَجَدْتُ امْرَأَةً تَمْلِكُهُمْ وَأُوتِيَتْ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ وَلَهَا عَرْشٌ عَظِيمٌ
{“እኔ የምትገዛቸው (ሰዎች ያሏት) የሆነችን፣ ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን ሴት አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡}
وَجَدْتُهَا وَقَوْمَهَا يَسْجُدُونَ لِلشَّمْسِ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ الشَّيْطَانُ أَعْمَالَهُمْ فَصَدَّهُمْ عَنِ السَّبِيلِ فَهُمْ لَا يَهْتَدُونَ
{“እርሷንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ (መጥፎ) ስራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡”}

أَلَّا يَسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي يُخْرِجُ الْخَبْءَ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُخْفُونَ وَمَا تُعْلِنُونَ
{“ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገልፁትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)፡፡”}
اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ
{“አላህ ከርሱ ሌላ (የእውነት) አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው፡፡”}
قَالَ سَنَنْظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنْتَ مِنَ الْكَاذِبِينَ
{(ሱለይማንም) አለ፡- “እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ሆንክ ወደፊት እናያለን፡፡”}
اذْهَبْ بِكِتَابِي هَٰذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ ثُمَّ تَوَلَّ عَنْهُمْ فَانْظُرْ مَاذَا يَرْجِعُونَ
{“ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ፡፡ ወደ እነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ ምን አንደሚመልሱም ተመልከት፡፡”}

ሁድሁድ የታዘዘውን ፈፀመ፡፡ ደብዳቤውንም ከሱለይማን ወስዶ የመን ደርሶ የሰበእ (ሳባ) ንግስት ከምትገኝበት ስፍራ ጣለው፡፡ ተልእኮው ግቡን መቷል፡፡ ደብዳቤው ከንግስቲቷ እጅ ገባ፡፡ ይህኔም፡
قَالَتْ يَا أَيُّهَا الْمَلَأُ إِنِّي أُلْقِيَ إِلَيَّ كِتَابٌ كَرِيمٌ
{አለች፡ “እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ የተከበረ ደብዳቤ ወደኔ ተጣለ፡፡”}
إِنَّهُ مِنْ سُلَيْمَانَ وَإِنَّهُ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
{“እነሆ እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” (የሚል መክፈቻ አለው፡፡)}
أَلَّا تَعْلُوا عَلَيَّ وَأْتُونِي مُسْلِمِينَ
{“በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ሆናችሁ ወደኔ ኑ” (የሚል ነው)፡፡} [አነምል፡ 15 - 31]

ይህን ልብ አንጠልጣይ ታሪክ መጨረስ የፈለገ ጥሩ የሆነ ተፍሲር ይዞ እስከመጨረሻው መከታተል ይችላል፡፡ እኔ ግን አንድ ጥያቄ ጠይቄ ፅሁፌን ልቋጭ፡፡ ሁድሁድ፡ ንግስተ-ሳባ የታደለችውን ሀብትና ድሎት ከገለፀ በኋላ ፀሀይ አምላኪ የሆኑትን ንግስቷን እና ህዝቦቿን ከእውነተኛው የተውሒድ መስመር ያፈነገጡ እንደሆኑ በሚደንቅ ሁኔታ እንዲህ ሲል ገልፁዋቸዋል፡-

“እርሷንም ሕዝቦቿንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ (መጥፎ) ስራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም!”

አላሁ አክበር! ዛሬም ልክ እንዲሁ ሸይጧን ጥፋታቸውን አስውቦላቸው በአላህ ላይ ማጋራታቸውን እንደ ተውሒድ፣ እንደ ፅድቅ የሚቆጥሩት ስንትና ስንት ናቸው?! ህሊና ያላችሁ አስተውሉ! ሁድሁድ ቀጠለ፣ የሰዎቹ ምግባር ማስተዋሉን ላልተነፈገ ከህሊና ጋር የሚጋጭ እንደሆነ እንዲህ ገለፀው፡-
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
“ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገልፁትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል።)”

ዛሬ ግን የተደበቀውን ስውሩን ሁሉ ከዘመናት በፊት የሞቱ ሰዎች ያውቃሉ በሚል በጥፋት ላይ የሚዋልሉት ስንቶች ናቸው?! ከዚያም እንዲህ ሲል ንግግሩን በተውሒድ አሳረገው፡

“አላህ ከርሱ ሌላ (የእውነት) አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው፡፡”

ሱብሓነላህ! ምንኛ የሚደንቅ ነው። ሁድሁድ (hoopoe)፣ እንድር ማርዬ፣ ሽንብር ጉትያ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 11/2008)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Hisnul Muslim #02
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣2️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 10፣ أذكار الاستيقاظ من النوم
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በተውሒድ ደዕዋ ላይ አደራ
~
* አስተማሪዎች ከተውሒድ / ዐቂዳ ኪታቦች አትራቁ። የተለያየ ፈን እያስተማራችሁ ባጠናቀቃችሁ ቁጥር በየ መሀሉ የተውሒድ / የዐቂዳ ኪታቦችን አስገቡ። የቃል በቃል ትርጉም ሳይሆን በሚገባ ሸርሕ አይታችሁ በመቅረብ አብጠርጥራችሁ አድምታችሁ አስተምሩ።

* ለመስጂድ ኮሚቴዎች ወይም ሌሎች የሚመለከታችሁ ሁሉ የተውሒድ ትምህርት ተጠናክሮ ለህዝባችን እንዲስሰጥ የድርሻችሁን ተወጡ።

* ነጋዴዎች፣ ባለ ሀብቶች ብትሞቱ እንኳ የማይቋረጥ እጅግ የገዘፈ ሶደቀቱን ጃሪያ እንዲኖራችሁ ተውሒድን በማሰራጨት ላይ ድርሻ ይኑራችሁ። የተውሒድ ኪታቦችን፣ ሹሩሓትን በመግዛት በተለይም ወደ ገጠር አሰራጩ። ደረሶችን አግዙ። ተውሒድ ላይ ትኩረት የሚሰጡ መሻይኾችን፣ ዱዓቶችን ከጎናቸው ቁሙ።

* ሁሉም በየዘርፉ የተውሒድን ደዕዋ በማገዝ ላይ ሊረባረብ ይገባል። አደራ አደራ! ለወገናችን ከዚህ በላይ የምንውለው ውለታ የለም። አላህ ያበርታችሁ፣ ልፋታችሁንም ይቀበላችሁ።

ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Video
"ወሃBያ ተከትሎ መስገድ አይቻልም፣ ያረ ^ዱት ስጋ አይብበላም፣ ኒካሕ የላቸውም"

#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_2
~
ሰሞኑን ኢኽዋንና አሕ ^ ባሽ በሰለፊያ ደዕዋ ላይ የጋራ ዘመቻ እንደከፈቱ እያየን ነው። በቀዳሚነት እያራገቡት ያለው ነጥብ ተKፊሪዮች ናቸው የሚል ነው። ሙስሊሞችን በጅምላ ከኢስላም በማውጣት ላይ የተሰማራው ማን እንደሆነ በተከታታይ በማስረጃ አቀርባለሁ። ክፍል አንድን አሳልፌያለሁ።

በዚህኛው ክፍል ያቀረብኩት መረጃ የአሕ ^ ባሹን ዑመር ይማምን ንግግር ነው። በቅድሚያ አንድ ነጥብ ላስቀድም። አላህ ከፍጡራን በላይ ነው የሚለው እምነት በቁርኣንም፣ በሐዲሥም የተረጋገጠ የሰለፎች ኢጅማዕ ያለበት ጉዳይ ነው። በዚህ ላይ ተደጋጋሚ መረጃዎችን ያቀረብኩ ቢሆንም ለቅምሻ ያክል ብቻ ጠቆም ላድርግ፦

1. ታላቁ ዓሊም ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ (181 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-

فَإِنَّ أَهْلَ الْإِثْبَاتِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ يُجْمِعُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ

“የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁት የሱና ሰዎች … አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ኢጅማዕ አድርገዋል።” [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 694]

2. አቡ ዙርዐ አራዚይ (264 ሂ.) እና ሓቲም አራዚይ (277 ሂ.) የአህሉ ሱናን ዐቂዳ ሲተነትኑ እንዲህ ብለዋል፡-

أَدْرَكْنَا الْعُلَمَاءَ فِي جَمِيعِ الْأَمْصَارِ حِجَازًا وَعِرَاقًا وَشَامًا وَيَمَنًا فَكَانَ مِنْ مَذْهَبِهِمُ: … وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ كَمَا وَصَفَ نَفْسَهُ فِي كِتَابِهِ , وَعَلَى لِسَانِ رَسُولِهِ ﷺ بِلَا كَيْفٍ

“በሁሉም ሃገራት - በሒጃዝ፣ በዒራቅ፣ በሻም፣ በየመን፣… ያሉ ዑለማዎችን አግኝተናል። ከመዝሀባቸው ውስጥ … አላህ - ዐዘ ወጀል - እራሱን በቁርኣኑ፣ እንዲሁም በመልእክተኛው ﷺ አንደበት እንደተገለፀው - ያለ እንዴት - ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ማመን ነው። [ላለካኢ፡ ቁ. 321]

3. ታላቁ ኢማም ኢብኑ ቁተይባህ (276 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-

وَالْأُمَمُ كُلُّهَا - عَرَبِيُّهَا وَعَجَمِيُّهَا - تَقُولُ: إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى فِي السَّمَاءِ مَا تُرِكَتْ عَلَى فِطَرِهَا وَلَمْ تُنْقَلْ عَنْ ذَلِكَ بِالتَّعْلِيمِ

“ህዝቦች በሙሉ ዐረቡም ሌላውም አላህ በሰማይ ነው ይላሉ። በተፈጥሯቸው ላይ እስከተተውና ከዚህ ላይ በስብከት እስካልተወሰዱ ድረስ።” [ተእዊሉ ሙኽተሊፊል ሐዲሥ፡ 395]


በዚህ ላይ ያሉ የሰለፎች ንግግሮች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ድምፁን ያያያዝኩት ዑመር ይማም የተባለው አሕ ^ባሽስ ምን ይላል?

አላህን ከፍጡራን በላይ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን በሙሉ ከኢስላም ያስወጣል። ሙስሊሞች አይደሉም፣ እነሱን በሶላት ተከትሎ መስገድ አይቻልም፣ ያረ ^ዱት ስጋ አይብበላም፣ ኒካሕም የላቸውም ይላል። ይሄ የሱ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የአሕ ^ባሽ ቡድን አቋም ነው። ዛሬ ያሉ ሙስሊሞችን ከተራው ህዝብ አልፈው እስከ ዑለማእ ከእስልምና ያስወጣሉ። ለሐጅ እና ለዑምራ ወደ ሳዑዲ ሲሄዱ ኢማሞቹ ሙስሊሞች አይደሉም በሚል አብረው አይሰግዱም።

እንደ ዑመር ይማም ሃይማኖት አላህ ከዐርሹ በላይ ነው በማለት ከሶሐቦች ጀምሮ ያለፉ የጥንት ሰለፎች በሙሉ ሙስሊሞች አይደሉም ማለት ነው። እንግዲህ ተመልከቱ! ከዚህ በላይ ተKፊነት ኖሮ አይናቸውን በጨው አጥበው ሌሎችን በተK ፊርነት እየከሰሱ ነው። በሺርክ እየጨፈሩ ሌሎችን ከኢስላም ሲያስወጡ ማየት ስላቅ ነው መቼም። እኮ ማነው ተKፊሩ ?

በደንብ "ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 10፣ 4ኛ ሐዲሥ
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (55 minutes)
Hisnul Muslim #03
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣3️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 10፣ إن في خلق السماوات
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ደስ ይላል!
~
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ብኑ ፈውዛን አልፈውዛን - አላህ ይጠብቃቸው - የሳዑዲ አረቢያ ሙፍቲ ሆነው ተመድበዋል። ላማረ ቀደምት ያማረ ምትክ! አልሐምዱ ሊላህ ቢኒዕመተሂ ተቲሙ ሷሊሓት!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአማላጅ ሰበብ ሙታኖችን መጣራት
~
"የሁዳውንም፣ ነሷራውንም፣ መጁሳውንም እንቀበላለን" ብሏል ዑመር ይማም። ይሄው ከነሷራው ጋር ያላቸው አንድነት። ከሰሞኑም እርስ በርስ ሲሞጋገሱ፣ በጋራ "ወሃ ^ ብያ " በሚሉት ላይ ሲዘምቱ ነበር። የእውነትም ቀላል የማይባል የጋራ እምነት አላቸው። ለምሳሌ ያክል ሁለቱም ደጋጎች ወይም ፃድቃኖች የሚሏቸውን በመማፀን፣ በመጣራት ላይ ይመሳሰላሉ። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ሲፋጠጡ የነበሩት አጋሪዎችም የማሻረካቸው ሰበብ ይሄው ነበር። አላህ እንዲህ ይላል :-

{ وَیَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَضُرُّهُمۡ وَلَا یَنفَعُهُمۡ وَیَقُولُونَ هَـٰۤؤُلَاۤءِ شُفَعَـٰۤؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا یَعۡلَمُ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَلَا فِی ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَـٰنَهُۥ وَتَعَـٰلَىٰ عَمَّا یُشۡرِكُونَ }

"ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ 'እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው' ይላሉ፡፡ 'አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን' በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።" [ዩኑስ፡ 18]

{ وَٱلَّذِینَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦۤ أَوۡلِیَاۤءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِیُقَرِّبُونَاۤ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰۤ }
"እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት 'ወደ አላህ ማቃረብን #እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም' (ይላሉ)።" [አዝዙመር፡ 3]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን ነብያችን ﷺ ሺርክ ተመልሶ አይመጣም ብለዋልን?
~
ነብያችን ﷺ እንደ ሺርክ የሚጎረብጣቸው ነገር አልነበረም። ለዚያም ነበር ሶሐባቸው ጀሪር ብኑ ዐብዲላህን "ምነው ከዚህ ከዘል ኸለሷ አታሳርፈኝም?" ብለው መጠየቃቸው። ዘል ኸለሳ የመን ውስጥ የነበረ ጣኦት ነው። “እንዴታ አሳርፈዎታለሁ እንጂ!” ነበር የጀሪር ምላሽ። ከዚያም ለዚሁ የተዘጋጀ ሰራዊት እየመሩ የመን ድረስ በማቅናት ዘል ኸለሷን ዶግ አመድ አደረጉት። ዜናው ለነብዩ ﷺ ሲደርሳቸው ሌላ ጊዜ ሲደሰቱ ያደርጉት ከነበረው የሶስት ጊዜ ዱዓእ በተለየ አምስት ጊዜ እየደጋገሙ ዱዓእ አደረጉላቸው። [ቡኻሪ፡ 3020] [ሙስሊም፡ 2476]

ብዥታ!
=
ዑቅበቱ ብኑ ዓሚር ባስተላለፉት ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"وإِنَّي قد أُعْطيتُ مفاتيحَ خزائِنِ الأرضِ ، وإِنَّي واللهِ ما أخافُ عليكم أنْ تُشْرِكوا بعدي ، ولكني أخافُ عليكم الدنيا أنْ تَنَافَسُوا فيها
"​እኔም የምድርን ድልብ ሀብቶች ቁልፎች በእርግጥ ተሰጥቻለሁ። በአላህም እምላለሁ! ከኔ በኋላ ታጋራላችሁ ብዬ አልሰጋም። ነገር ግን በሷ (በዱንያ) መሽቀዳደማችሁን ነው ነው የምፈራላችሁ።" [ቡኻሪ፡ 1344] [ሙስሊም፡ 2296]

ይህንንና መሰል መልእክት ያላቸውን ሐዲሦች መነሻ በማድረግ ሺርክ ዳግም ወደ ነብዩ ﷺ ኡመት ስለማይመለስ ከሺርክ ማስጠንቀቅን እና ስለ ሺርክ አደጋ ማስተማርን የሚቃወሙ ሱፍዮች አሉ። ይሄ ሙግት ውድቅ እንደሆነ ሶስት አይነት ምላሾችን መስጠት ይቻላል።

#ምላሽ_አንድ:- የሐዲሡ መልእክት እናንተ እንደምትሉት አይደለም!

የተጠቀሰው ሐዲሥ መልእክት በህዝባቸው ውስጥ ሺርክ አይከሰትም ማለት ሳይሆን ኡመታቸው ሙሉ በሙሉ ከኢስላም ወጥቶ የሺርክ ተከታይ አይሆንም ማለት ነው። ለዚህም እነዚህ ሱፍዮች እራሳቸው የሚከተሏቸውን ሁለት ኢማሞችን አጣቅሳለሁ።

1. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦
"وفي هذا الحديث معجزات لرسول الله صلى الله عليه سلم ؛ فإن معناه الإخبار بأن أمته تملك خزائن الأرض وقد وقع ذلك ، وأنها لا ترتد جملة وقد عصمها الله تعالى من ذلك ، وأنها تتنافس في الدنيا وقد وقع كل ذلك"
"በዚህ ሐዲስ ውስጥ የመልእክተኛው ﷺ ተዓምራት አሉ። ምክንያቱም ትርጉሙ፡ ኡመታቸው የምድርን ሀብቶች እንደሚቆጣጠሩ መናገር ነው። ይህም በእርግጥ ተከስቷል። እንዲሁም #በአጠቃላይ ከሃይማኖት እንደማይወጡ (እንደማይመለሱ)፤ የላቀው አላህ ከዚህ ጠብቋቸዋል። እንዲሁም በዱንያ (በዚህ ዓለም) ነገሮች እንደሚወዳደሩ፤ ይህ ሁሉ በእርግጥም ተከስቷልና።" [ሸርሑ ሙስሊም፡ 15/59]

2. ኢብኑ ሐጀርም እንዲህ ብለዋል፡-
"قوله: (ما أخاف عليكم أن تشركوا) أي على مجموعكم لأن ذلك قد وقع من البعض أعاذنا الله تعالى"
" 'ታጋራላችሁ ብዬ አልሰጋም' የሚለው #ባጠቃላይ ሁላችሁም ማለት ነው። ምክንያቱም ይሄ በአንዳንድ ክፍሎች ላይ #ተከስቷልና፤ የላቀው አላህ ይጠብቀን።" [ፈትሑል ባሪ፡ 3/211]

#ምላሽ_ሁለት፦ ሺርክ እንደሚከሰት የሚጠቁሙ ግልፅ ሐዲሦች አሉ።

1. አቡ ሁረይረህ ባስተላለፉት ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تَقُومُ السَّاعَةُ حتَّى تَضْطَرِبَ ألَياتُ نِساءِ دَوْسٍ، حَوْلَ ذِي الخَلَصَةِ
"የደውስ ጎሳ ሴቶች በዘልኸለሷ ጣኦት ዙሪያ መቀመጫቸው ሳይባለጥ (ጠዋፍ ሳያደርጉ) ቂያማ አይቆምም።" [ቡኻሪ፡ 7116] [ሙስሊም፡ 2906]

2. ሠውባን ባስተላለፉትም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تقومُ الساعةَ حتى تلحق قبائلٌ من أمّتي بالمشركينَ ، وحتى يُعْبَدَوا الأوثانُ
"ከህዝቦቼ የተወሰኑ ጎሳዎች ወደ ሙሽሪኮች ሳይጠጉ፣ የተወሰኑትም ጣኦቶችን ሳያመልኩ ቂያማ አትቆምም!" [ቲርሚዚይ፡ 2219]

#ምላሽ_ሶስት:- ሺርክ ዳግም ተመልሶ በተግባር ተከስቷል።

ለዚህ ማረጋገጫ ማንም ሊያስተባብለው የማይችላቸው ታሪካዊ መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ፦

1. የነብዩን ﷺ ሞት ተከትሎ በርካታ የዐረብ ጎሳዎች ወደ ሺርካቸው ተመልሰው ነበር። [ፈትሑል ባሪ፡ 12/276]
2. ዐሊይን ጌታ ነው የሚሉ ሺ0ዎች ተነስተው ዐሊይ ራሳቸው እርምጃ ወስደውባቸዋል። [ቡኻሪ፡ 3013]
ኋላም ላይ ዐሊይን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያመልኩ በርካታ የሺ0 ቡድኖች ተፈልፍለው ነበር። ዛሬም ኑሶይሪያ ሺዐዎች 0ሊይን የሚያመልኩ መሆናቸው የዚህ ሺርክ አንድ ማሳያ ናቸው።
3. ቀራሚጧዎችም እንዲሁ ከዛሬዋ በሕረይን የተነሱ የታወቁ የሺ0 ቡድኖች ሲሆኑ በሐጅ ወቅት ጥቃት ፈጽመው፣ ሑጃጆችን ጨፍ ^ ጭፈው፣ ሐጀረል አስወድን ወስደው ለ20 ምናምን አመታት አቆይተውታል። ሙሽሪኮች ነበሩ። [ሚርኣቱል ጂናን፣ አልያፊዒይ፡ 2/272]

4. ከላይ የተጠቀሰው የዘልኸለሷ ጣኦት ነብዩ ﷺ ዳግም ይመለካል ብለው እንደተነበዩት በደውስና በዙሪያው ያሉ የዐረብ ጎሳዎች እንደገና እየተመለከ ነበር። የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ደዕዋ ፍሬ አፍርቶ በጊዜው የነበረው ንጉስ አልኢማም ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ሰዑድ ረሒመሁላህ ተነስቶ የተወሰኑ ዳዒያዎችን ወደ ዘልኸለሷ በመላክ እንዲያፈርሷት አደረገ። የመጀመሪያው የሰዑድ ቤተሰቦች አገዛዝ በቱርኮች ሲወድቅ መሀይማን ዳግም ዘል ኸለሷን ማምለካቸውን ተያያዙት። እንደገና ንጉስ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ዐብዲረሕማን ኣለ ሰዑድ ሒጃዝን ሲቆጣጠር በዚያ አካባቢ ያለውን አሚር በማዘዝ ከሰራዊቱም የተወሰነው ወደዚያው አቅንቶ አፈራረሷት። ቅሪቷንም አስወገዱት።” [ፈዋኢዱን ሚን መዓኒ ሚን ኩቱቢል አልባኒይ፡ 1/14]

በተረፈ "ሸይጧን በዐረቢያ ልሳነ-ምድር ላይ ሰጋጆች እንደማያመልኩት ተስፋ ቆርጧል" የሚለው ሐዲሥ መልእክቱ በጊዜው በነበረው የተውሒድ መስፋፋት ምክንያት የነበረውን ተጨባጭ መግለፃቸው እንጂ ሺርክ ዳግም አይመለስም ማለት አይደለም። ሲጀመር ሐዲሡ የሚለው በዐረቢያ ልሳነ-ምድር ነው። እናንተ ምን ቤት ናችሁ? በዚያ ላይ ከላይ እንዳሰፈርኩት በ0ረቢያ ምድር ጨምር ሺርክ እንደሚከሰት የሚገልፁ ሐዲሦች፣ በተጨባጭ እንደተከስተም የሚያሳዩ ታሪካዊ መረጃዎች ባሉበት እውነታውን መሸምጠጥ ራስን መሸወድ ነው ። ይልቅ ከሺርካችሁ፣ ከቀብር አምልኮታችሁ ተመለሱ። አንዳንዶቹማ አይናቸውን በጨው አጥበው ከነ ጭራሹ ቀብር የሚያመልክ አካል የለም እያሉ ነው። የቀብር አምልኮ፣ የሙታን አምልኮ ማለት ቀጥታ የናንተ ተግባር ነው። ለዚህ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እናንተ ዘንድ በክፉ የማይጠረጠረው ፈኽሩ ራዚይ የተናገረውን ላያይዝ፡-

«أَنَّهُمْ وَضَعُوا هَذِهِ الْأَصْنَامَ وَالْأَوْثَانَ عَلَى صُوَرِ أَنْبِيَائِهِمْ وَأَكَابِرِهِمْ، وَزَعَمُوا أَنَّهُمْ مَتَى اشْتَغَلُوا بِعِبَادَةِ هَذِهِ التَّمَاثِيلِ، فَإِنَّ أُولَئِكَ الْأَكَابِرَ تَكُونُ شُفَعَاءَ لَهُمْ عِنْدَ اللَّه تَعَالَى، وَنَظِيرُهُ فِي هَذَا الزَّمَانِ اشْتِغَالُ كَثِيرٍ مِنَ الْخَلْقِ ‌بِتَعْظِيمِ ‌قُبُورِ الْأَكَابِرِ، عَلَى اعْتِقَادِ أَنَّهُمْ إِذَا عَظَّمُوا
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
قُبُورَهُمْ فَإِنَّهُمْ يَكُونُونَ شُفَعَاءَ لَهُمْ عِنْدَ اللَّه»
“እነዚህን ጣኦቶች በነብዮቻቸውና በታላላቆቻቸው አምሳል ቀረጿቸው። እናም እነዚህን ሃውልቶች በማምለክ እስከተጠመዱ ድረስ እነዚህ ታላላቆች ከላቀው አላህ ዘንድ አማላጅ እንደሚሆኗቸው አሰቡ። በዚህ ዘመን የዚህ ብጤ የሆነው በርካታ ፍጡሮች የታላላቆቻቸውን መቃብር በማላቅ መጠመዳቸው ነው። እነሱ መቃብሮቻቸውን ሲያልቁ ለነሱ ከአላህ ዘንድ አማላጅ እንደሚሆኗቸው ያምናሉ።” [መፋቲሑል ገይብ ወይም አተፍሲሩል ከቢር በመባል የሚታወቀው የራዚ ተፍሲር፡ 17/227]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 1/1447)

"ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓሊ እና " ለሐጅ ፍላጎት የለኝም " ያሉት " ሐጅ " ዑመር ።

ከአምስት አመታት በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅጉን የሚታወቁትና በርካታ አስደናቂ በሆኑ እውቀቶች የታጨቁ መፃህፍቶች ን ለሙስለሙ ማህበረሰብ ያበረከቱት ኢትዮጲያዊው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሞተዋል ... በሃገራችን ሚዲያዎች ይህን ያህል አልተባለላቸውም ነበር .... ከቀናት በፊት ይህ ነው የሚባል ደህና ቅሪትን በመተው የማይታወቁት " ሐጂ " ዑመር ሲሞቱ ፅንፈኛ የሆነ የሙስሊም ጠላቶች ጭምር በጉዳዩ ላይ እጅጉን የረዘመ ስራ ሰርተዋል .... እያጦዙ ፅፈዋል ፣ ተናግረዋል

ከዚህ ሁሉ ጀርባ ያለው ነገር ግልፅ ነው :: ፅንፈኞቹ የሚፈልጉት የቅርቡን ሟች መንገድ አጉኖ ማቅረብ ነው ... አዎ ! የሚመቻቸው
" አሏህ ሽቶት ሄድኩ እንጂ ለሐጅ ፍላጎት የለኝም - ፍላጎቴ ለሸኾቼ ነው " እያለ የኢስላም መሰረቶች ላይ ቸልተኝነትን የሚሰብከው ነው ። የሚፈልጉት ወደ ቀብር አምልኮ የሚጣራውን ሞዴል እያደረጉ ማቅረብ ነው ...

እንዲኖር የሚመኙት ወሃቢያ ፣ አክራሪ እያለ እውነተኛውን የኢስላም ገፅታና ተውሒድን እየተዋጋ የነሱን ግብ የሚያስፈጽም አካል ነው :: የሚወዱት እነሱን እያወደሰና ለነሱ እንቅፋት ሳይሆናቸዉ የተውሒድ ባለቤቱን በማክፈር ላይ አንይኑን የማያሸውን መሪ ነው ።

ሸይኽ ሙሐመድ የቀብር አምልኮና አደንዛዥ የሆኑ መጤ መንገዶችን የሚቃወሙ ታላቅ ዓሊም ነበሩ ። በተለያዩ የሸሪዓ የትምህርት ዘርፎች ላይ በርካታ አስደናቂ ኪታቦችን ትተው ያለፉ ታታሪ የተውሒድ ዓሊም ነበሩ ! ወደ ደህንነት ሰራተኞች በመመላለስ እነ እገሌን እሰሩ ፣ አጥፉ የሚሉ ስራ ፈት እና ሴራ ሸራቢ አልነበሩም :: እናም ስለሳቸው ማውራት ፅንፈኞቹን ትርፍ ያሳጣል !

https://www.tg-me.com/msirage4
የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 16፣ دعاء دخول المسجد
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (55 minutes)
2025/10/23 17:19:00
Back to Top
HTML Embed Code: