Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
ጥቂት ማስታወሻ!
☞በተለይ ለሙስሊም ወገኖቻችን አድርሱልኝ!
"በጩኸት ብዛት ሐሰትን እውነት ማድረግ አይቻልም!"
"#በኦርቶዶክሳውያን_እያሳበቡ_ግጭት_መቀስቀስ_ይቁም!"
➊ጎንደር በተፈጠረው ነገር ከማዘኔም በላይ፥ ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እንኳ በእጅጉ ተችግሬ ነበር፡፡ (በዕለቱ) እኔ መደበኛ ሥራዬ ፈጣሪየን ማገልገል ነውና የነበርኩትም እዚያው ነው፡፡
ነገሩን አስቀድመው ተዘጋጅተውበት የቆዩ ጽንፈኛ አካላት ግን፥ የነርኩ ክፋትና ድርጊት እንዳይጋለጥ "የጦስ ዶሮ" ሊያደርጉን ሞክረዋል፡፡ አሁንም ቀጥለውበታል፡፡
እውነቱ ግን እኔ (ክርስቲያን ነኝና፥ ጠላትህን ውደድ የሚል ፈጣሪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና) ጽንፈኛ ግለሰቦች የሚሉትን አላደረግሁትም፥ ለወደፊቱም ጨርሶ ላደርገው አልችልም። (ምክንያቱም ከሃይማኖቴ ተቃራኒ ነውና)
➋የፋና ጋዜጠኛ ስለሚሉት፦
በመጀመሪያ የፋና Tv ጋዜጠኛ አልነበርኩምም፤ አይደለሁምም። የሬዲዮ ጋዜጠኝነቱን ካቆምኩም ከአንድ ዓመት በላይ አልፎኛል፡፡ (ሰዎቹ ግን ከምን እንዳመጡት አላውቅም ፥ አሁንም የፋና Tv ጋዜጠኛ እያሉ መለፈፋቸውን ቀጥለዋል)
በነገራችሁ ላይ ጽንፈኞቹ በሚከሱት ልክ አለመሆኔን የሚመሰክርልኝ እግዚአብሔር ቢሆንም፥ ለዘጠኝ ዓመታት በሠራሁበት የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ሥራ ላይ፥ አንድም ቀን ሙስሊምም ሆነ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቼን የሚያሳዝን ፕሮግራምም ሆነ ዜና ሠርቼ እንደማላውቅ ምስክሩ አድማጭ ነው፡፡
➌ስለሚዘዋወረው ድምጽ፦
በመጀመሪያ ደረጃ (ባለፈውም እንደተናገርኩት) አብዛኛው ጽንፈኞቹ የሚያዘዋውሩት ድምጽ፦
1፡ ተቆራርጦ ለፍላጎታቸው የዋለ ነው፤
2፡ ጽንፈኛ ግለሰቦች ለሚናገሩት የተሰጠ ምላሽ ነው፤ (እርሱም ቢሆን የአንዱን ቀን ትምህርት ከሌላኛው ቀን በመቀጠል መደበኛ መልእክቱን ለቋል)
3፡ አሁን እየቀሰቀሰ ነው ብለው የሚጠቀሙበት አምና የተነገረ ነው፤ (እሱም ከአውዱ ውጭ ተወስዷል)
4፡ በሚስጥር አገኘነው የሚሉት ሁሉ እኔው ራሴ በአደባባይ ያስተማርኩትና በyoutube የተለጠፈ ነው፡፡
➍ሙስሊሙን ይጠላል ስለሚሉት፦
እኔ ተወልጄ ያደግሁት ጎንደር ነው፤ ከልጅነት እስከ እውቀት የልብ ጓደኞቼ ሙስሊሞቹ ናቸው፡፡ የኢድ፥ የአረፋና የጳጉሜን ትዝታወቼ ዛሬም በልቤ ውስጥ አሉ፡፡ የቁርአን መግቢያ የአረብኛ ቋንቋ ያስጠኑኝ "ሻሒያችን" የምንላቸው አባትም ታላቅ ነበሩ፡፡ (ነፍሳቸውን ይማርና)
ዛሬም ድረስ ሙስሊም ወዳጆች አሉኝ፡፡ ጽንፈኞቹ ለክፋት ድምጽ እየቆራረጡ ከሚያጋጩ ይልቅስ ስለሙስሊም-ክርስቲያን ወንድማማችነት ያስተማርሁት ስንት ነበረ፡፡ በዚያውም ላይ (መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም) በማኅበራችን በየወሩ ከምናግዛቸው ወገኖቻችን መካከል ጥቂት የማይባሉት ሙስሊም ናቸው፡፡
ዋናው ነገር ግን ደጋግሜ እላለሁ፤ እኔ ክርስቲያን ነኝ። ሰዎችን ልቆጣ ልገስጽ እችላለሁ፡፡ ማንንም ግን መጥላት አልችልም፡፡ ይህ ከሃይማኖቴ ይጋጫል፡፡ ገሃነመ እሳትም ያስጥለኛል፡፡ ከሁሉ ይልቅ የምፈራው እግዚአብሔርን ነውና!
➎ወጣቶችን አደራጅቷል ስለሚባለው፦
የዚህ ወሬ መነሻው በ2013 ኅዳር ላይ ወጣቶችን ቅርሶቻቸውን ካስጎበኘሁ በኋላ የተናገርኩት ነው፡፡ ምንም እንኳ መደጀራች (በሕግም በሃይማኖትም) ስህተትነት ባይኖረውም፥ እኔ ግን ተደራጁ ያልኳቸው ልጆች ሥራቸው ጓደኞቻቸውን (ቤተሰቦቻቸውን) ለንስሃ እንዲያበቁ ነበር፡፡ (እርሱም ወዲያው የቆመ ተግባር ነው)
ከዚህ ውጪ ግን በቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ወጥቼ ከማስተማሬ በቀር ያደራጀሁትም፥ ያስከተልሁትም ሰው የለም! (ምንስ ሊያረግልኝ)
➏እኔ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በአጋጣሚ ትናንት በተፈጠረው ችግር አይደለም። የግድያ ዛቻ ሊደርሰኝ ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት አልፏል፡ ፡ ላለፉት 13 ወራት ተወልጄ ባደግሁባት ከተማ እንኳ በጎዳና ላይ እንደልብ መንቀሳቀስ ሳልችል ነው የቆየሁት። ጽንፈኞቹ መልካቸውን ቀይረው የመጡት ደግሞ በራሳቸው ያልተሳካላቸውን (በአጋጣሚው) መንግሥት ያሳካልናል ብለው ነው፡፡
➐እኛ (ኦርቶዶክሳውያን) እንደ ጽንፈኞቹ አይደለንም እንጂ፥ እግረ መንገዱንም እነዚህ ግለሰቦች መደበኛውን ሙስሊም አይወክሉም በሚል እሳቤ እንጂ ብዙ የምናውቀው ነገር ነበር። ከሃገር ውጪ እስከ ውስጥ ድረስ ኢትዮጵያን ለማፍረስና የሚጠሏት ሃገራት ሲሣይ ለማድረግ እነማን ምን እንደሚሠሩ ይታወቃል፡፡
እስኪ ተመልከቱት ፥ ፍልስጤም ውስጥ የተገደለችውን ጋዜጠኛ ፎቶ እንኳ እኛን ለመክሰስ ሲጠቀሙበት! (በነገራችሁ ላይ ጋዜጠኛዋ ክርስቲያን ናት!)
☞በዚያውስ ላይ ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብያተክርስቲያናት እንደ ችቦ ሲነዱ፥ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ሲገደሉ ዝም ያልነው ስለሃገርና ስለአብሮነታችን ነውኮ! (እንተዛዘን እንጂ) ለሚያልፍ ቀን ስለምን የግል ክፋታቸውን በእምነት በሚያላክኩ ሰዎች እንባላለን?
ሃገራችንስ አንድነታችንን እንጂ መለያየታችን አይጠቅማትም፤ በግለሰቦች ትርክት መሳቡን ትተን በአንድነት (እንደ ቀድሞው) ብንኖር ደግ ነው፡፡
ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤ ሙስሊም ወገኖቼ አብረን እንቁም! (ጥላቻ የለኝም፥ ለወደፊቱም እንዲኖረኝ አልሻም)
☞መንግሥትም በውጪ ሃገር ሆነው የግጭት ቅስቀሳ የሚያደርጉትን ባይደርስባቸው እንኳ፥ በሃገር ውስጥ ያሉትን አድቡ ይበልልን!
የእውነት አምላክ እውነቱን ለሁላችንም ይግለጥልን!
አሜን!
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

Forwarded from ኦርቶprofile⛪️✟🏞
ወልቂጤ የተዋህዶን የትግል ችቦ ልትከኩሰው ቆርጣ ተነስታለች
የፊታችን ቅዳሜ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል ፡፡ እንደ ሀገር አቀፍ እና በዞኑ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለአለም እናጋልጣለን፡፡
የቤተክርስቲያንን ጥሪ ላልሰሙት Share እናድርግ🙏🙏🙏

@የኢየሱስ እናት ማርያም እና የኦርቶዶክሷ ማርያም ልዩነት! Tizitaw Samuel LIVE 'ማርያም አዳነችኝ፥ ፈወሰችኝ የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ የለም' ላልከው...
፩. ፈጣሪ እግዚአብሔር ፍጡራንን ያድናል፥ ይፈውሳል።
✍️ፈጣሬ ዓለማት አምላካችን ቅድስት ሥላሴ ያድናሉ፥ ይፈውሳሉ። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ፦ "አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።" ኤር. 17፥14 እንዲል።
➜እግዚአብሔር ማዳንም፥ መግደልም ይችላል። "እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።" 1ኛ.ሳሙ. 2፥6።
➺"አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥
ስለ ቸርነትህም አድነኝ።" መዝ.5፥4።
➾"ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።" መዝ.33፥6።
➜"ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ፡ ብሎ ጮኸ።" ማቴ.14፥30።
➱ስለሆነም ፍጡራን ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔር አድነን ማለታቸው የተገባ ነው።
➥ ያዕቆብ እግዚአብሔርን ከዔሳው እጅ አድነኝ እንዳለው...
➔"ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።" ዘፍ.32፥11 እንዲል።
✍️መጽሐፍ ቅዱስ ፍጡር ፍጡርን እንደሚታደገው፥ እንደሚያድነው ገልጿል።
፪. የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል ወንድሙን ዮሴፍን ከወንድሞቹ የሞት ምክር ስለታደገው፦ "ከእጃቸውም አዳነው፥" ይላል።
➔"ሮቤልም ይህን ሰማ፥ ከእጃቸውም አዳነው፥ እንዲህም አለ፦ ሕይወቱን አናጥፋ።" ዘፍ.37፥21 እንዲል።
➣'ትዝታው ሳሙኤል'፦ ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ሮቤልን ዮሴፍን "አዳነው" ስላለ የእግዚአብሔርን ማዳን ጋረደ??? ጸረ ወንጌል ነው???
➲ "ሮቤል ታናሹ ወንድሙን ዮሴፍን አዳነው" ማለቱ ፈቃደ እግዚአብሔር ያለበት ማዳን አይደለምን??? ረድኤተ እግዚአብሔር የሌለበት የሮቤል ዮሴፍን መታደግ(ማዳን) አለ??? "እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።" ዘፍ. 39፥21 ይሏል።
➺የአባቱን ሚስት ሀፍረተ ሥጋ የገለጠው የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል ታናሽ ወንድሙን ዮሴፍን ፈቃደ እግዚአብሔር ባለበት ሁናቴ፦ "አዳነው" ከተባለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምማ በፈቃደ እግዚአብሔር ከአዳኞቻችን የሞት ወጥመድ "አዳነችን" ብንል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው።
➱መቼስ ሮቤል ዮሴፍን የታደገበት፦ ትድግና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የቅድስና ሕይወት አንጻር ስናየው ኢምንት ነው።
➜ ከሮቤል ደግነት የእመቤታችን ደግነት እጅጉን ይሻላል፤ ይበልጣልም።
➱ አባ ጽጌ ድንግልም "አድኅንኒ በተአምርኪ ዳግመ ኢያስቆቁ።..."[ማኅሌተ ጽጌ] ይላታል።
➔ዮሴፍን "አዳነው" ያለው ለሮቤል ብቻ ነው፤ ማርያም አዳነች የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቃል በቃል አለመጥቀሱ ባታድን ነው አያሰኝም። ለምሳሌ፦
➱"እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥..."ሐዋ.19፥11 ስለሚል እግዚአብሔር የሚያስገርም ተኣምር ያደርግ የነበረው በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እጅ ብቻ ነው??? በስም ስላልተጠቀሱ ቅዱሳን ሐዋርያት እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የሚያስገርም ተኣምር አያደርጉም ማለት ነው??? አይደለም።
➺ ለቅዱስ ጳውሎስ የተሰጠ "የሚያስገርም" ገቢረ ተኣምራት በስም ቃል በቃል ባይጠቀሱም ለቅዱስ ጴጥሮስም፥ ለቅዱስ ዮሐንስም... ለቅዱሳን ኹሉ ተሰጥቷልና።
➔ስለሆነም ትዝታው "እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤" የሚለውን ይዘህ ለቅዱስ ጳውሎስ ብቻ እንጂ በእነቅዱስ ጴጥሮስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ቢያደርግ ኖሮ የእያንዳንዱን ስም ዘርዝሮ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረን ነበረ ብትል ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትሆናለህ።
➥አሳዳጅ በነበረው ኋላ በተመለሰው በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተኣምራትን ያደረገ የሚያደርግም እግዚአብሔር፤ ጌታችንን አሳዳ ሳይሆን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተሰዳ የተገኘች በወላዲተ አምላክ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እጅ እንዴት አብልጦ የሚያስገርም ተኣምር አያደርግ????
➺"አድኅንኒ ሊተ እስመ ኀልቀ ኄር ወውኅደ ሃይማኖት እምገጸ ምድር ማርያም እሙ ለክቡር። ሰአሊ ለነ ማርያም ኀበ ወልድኪ ኄር መድኃኔዓለም።"[ስብሐተ ፍቁር ዘእግዝእትነ ማርያም]
፫. እንኳን እመቤታችን ሕዝበ እስራኤል የሳኦልን ልጅ ዮናታን ከሞት አድነውታል።
➜"ሕዝቡም ሳኦልን፦ በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኃኒት ያደረገ ዮናታን ይሞታልን?.... ሕዝቡም እንዳይሞት ዮናታንን አዳነው።" 1ኛ ሳሙ.14፥45 እንዲል።
➾እስራኤላውያን ሞት የሚገባው ዮናታንን አባቱ ሳኦል ጋር አማልደው(ለምነው) ከሞት ከታደጉት(ካዳኑት) እመቤታችን በኃጢኣታችን ምክንያት ሞት የሚገባን ሰዎች በቃል ኪዳኗ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ዘንድ አማልዳ ማዳኗ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው።
➜ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ "አድኅንኒ እምዜና ኀዘን መደንግጽ ወእምድድቀ ነገር መፍርህ። ለዓለመ ዓለም አሜን።"[እንዚራ ስብሐት ዘሰኑይ] እንዲል።
፬. 'ትዝታው' አላስተዋልከው ይኾናል እንጂ ሰው በጥበቡ በብልሃት ከተካነ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ከመፍረስ ያድናታል።
➱"ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።" መክ.9፥15 እንዳለ።
➥ጥበብ የተባለውን መደኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምማ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ከመፍረስ ታድናታለች።
➺ለሰሎሞን የሰጠው ሀብተ ጥበብ ከተደነቀ ለእመቤታችን የተሰጣትን ሀብተ ጥበብ አስበው?!....."ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል..." እንዲል ሥርዐተ ቅዳሴ።
፭. እግዚአብሔር ራሱ ማዳን እየቻለ በሰዎች እጅ ማዳኑም፦ "አድን" ማለቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው።
➜"እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፦ በዚህ በጕልበትህ ሂድ፥ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን፤ እነሆ፥ ልኬሃለሁ፡ አለው።" መሳ. 6፥14።
➱በዘመነ ብሉይ የነበረ ጌዴዎንን እግዚአብሔር "እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን" ብሎ ከላከው እመቤታችን "በስምሽ የሚማጸኑትን ከአጋንንት አሽክላ አድኚ፤" ብሎ ቃል ኪዳን መግባቱ ቢያንስባት እንጂ አይበዛባትም። ከጌዴዎን የሚበልጥ ከዚህ አለ...."ስምሽም በእግዚአብሔር ዘንድ የሰለጠነ ነው" እንዲል....
➾በጌዴዎን እጅ የሚያድን እግዚአብሔር በእመቤታችን እጅ አያድንምን?.....
➔"...አድኅንኒ እግዝእትየ እማየ ሙስና መፍርህ። ከመ አድኃንኪይዮ ቀዳሚ ኖኅ።" [መልክአ ውዳሴ ዘሰንበተ ክርስቲያን] ይላል።
➜"እግዚአብሔርም የእስራኤልን ስም ከሰማይ በታች ይደመስስ ዘንድ አልተናገረም፤ ነገር ግን በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም እጅ አዳናቸው።" 2ኛ.ነገ. 14፥27
➔"ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውንም መልክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው፤ እርስዋም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።" ኢያሱ 6፥25
➔"ወአድኀኖሙ ኢያሱ በይእቲ ዕለት፤ ወረሰዮሙ ከማሁ ወፋርያነ ዕፀው ወሐዋርያነ ማይ ለኵሉ ተዓይን ወለምሥዋዐ እግዚአብሔር።" ኢያሱ 9፥26
➾"እንዲሁም አደረገባቸው፥ ከእስራኤልም ልጆች እጅ አዳናቸው፥ አልገደሉአቸውምም።" ኢያ. 9፥26

፮. ሰው በሚናገረው ቅን ነገር ሰውን ማዳን(መታደግ) ይችላል።
➱"ነገረ ረሲዓን ተሳትፎ ደም ወአፉሆምስ ለራትዓን ታድኅኖሙ፦ የኃጥኣን ቃል ደምን ለማፍሰስ ትሸምቃለች፤ የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።" ምሳሌ 12፥6።
➾ትህትናዋ ግሩም የሆነ እመቤታችንም በመልካምና ቅን ንግግሯም ትታደገናለች።
፯. በሐዲስ ኪዳንም ቅዱስ ጳውሎስ ሚስትምኮ ለባሏ ባልም ሚስቱን ለማዳን ምክንያት መሆን ይችላሉ ብሏል።
➔"እስመ ኢታአምር ብእሲት ለእመ ታድኅኖ ለምታ? ወኢያአምር ብእሲ ለእመ ያድኅና ለብእሲቱ?፦ አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?" 1ኛ.ቆሮ.7፥16 አለ።
➦ስለሆነም ሚስት ለባሏ፤ ባልም ለሚስቱ የመዳን ምክንያት መሆን ከቻሉ እመቤታችንም ምክንያተ ድኂን(የመዳን ምክንያት ናት) ማለታችን የተገባ ነው።
➲አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ፦ "...ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ። ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኲሎ።" እንዳለ።
➥ትዝታው🤔 የሚከተለውን ኅብረ ቃሉን፥ ሰሙንና ወርቁን አውጥተህ ተገልገልበት።
✍️ልትገለብጠኝ የሔዋን መኪና፥
ማርያም አዳነችኝ ፍሬን ያዘችና።

ዓለምን ያነጋገረው ይህ ማነው
<unknown>
*⛪ዓለምን ያስጨነቀው ጥያቄ ይህ ማነው?*
🎙️ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ
ማቴዎስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ *እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።*
²⁷ *ሰዎቹም፦ ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ።*
@KIRSTOSIYESUS

Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (ካልባረከኝ አለቅህም")
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የጃንደረባው ልጅ በጃንደረባው ሥር"
"ወኮነ በውእቱ መዋዕል ወአስተጋብኦሙ ባኮስ ዘተሰምየ አቤላክ ለኵሎሙ ሰብአ ብሔር ወገብረ ከብካበ ለወልዱ ሔኖክ "
የነገር ጥንት የንባብ አርእስት ይሉታል "ኮነ" የሚለውን፤ ያለፈን ታሪክ ለመጻፍ መነሻ መንገድ ይኽ ነው።
"በዚያ ዘመን እንዲህ ሆነ አቤላክ የተባለ ባኮስም በሀገሩ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ሰብስቦ ለልጁ ሰርግ አደረገ"
ከሰሙኑ የየማህበራዊ ገጸ–ድር አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል የጃንደረባው ልጅ ሰርግ (እኔ እንኳ አልነበርኩም የዘገየ ዜና የከረመ ወሬ ፍለጋ ስገባ ሁለነገሬ ሔኖክ ሔኖክ ሔኖክ ይላል) በዚያ ላይ ወሬ አቀባዩ እየተፈራረቀ "የሔኖኬ ሰርግ ታሪክ ነበር አመለጠህ…" ይሉኛል ሊያስቀኑኝ። በአንዳንድ የድል ታሪክ ውስጥ የታሪኩ አካል ለመሆን ተመኝቶ ያልተሳካለት ሰው በሠመረላቸው ካልቀና ለድል ደንታ የለውም ማለት ነው። ለነገሩ "ልጁ" ድሮም ታሪከኛ ነው ሳይሰረግ ስለሰርግ ይጽፋል ያስተምራል (ቃና ዘገሊላ) ያው ሳይቀስስ ስለቅስና እንደጻፈው እንደሰበከው ማለት ነው (ክብረ ክህነት) ።
በውስጥ መስመር ይቅርታውን ለመጠየቅ በሰርጉ ማግስት ለሙሽራው ይሔን ላኩለት።
"ቆይ ግን ምን አጥፍቼ ነው ይሔ ሁሉ ሰው ደስታህን ለመካፈል ወደ ሀገር ሲገባ እኔ ከሀገር የወጣሁት? እድለቢስ ነኝ የምር 😢 ሔኒዬ የምደርስ መስሎኝ ነበር ከኢየሩሳሌም በዚያው ወደ ግብፅ አለፍኩ። ብዙ ሰው በጣም አብዝቶ ጠየቀኝ አለመኖሬንና ደስታዬን እንኳ ተረጋግቼ መግለጽ አቃተኝ። የቅዱሳን አምላክ ልቤን ያውቀዋል ምን ያህል እንዳኮራኸኝ እንደተደሰትኩብህ?! ከዓይን ያውጣህ እንዳልል ከዐይን ገብተሃል 😃 ትዳራችሁን ይባርከው እንዳልል የተባረከው ትዳር ተባርኮ ተሰጥቶኃል! በቃ ምንም አልልም አልኩና ይኼ ደግሞ ቅናት ያስመስልብኛል… ነገ ስመጣ እየጻፍኩ እመጣለሁ እስከዛው ግን ይቅርታህን ደጅ መጥኛ ትሁነኝ! እንኳን ደስ ያለህ!"
ይቅርታዬ ተቀባይነት አግኝቷል ገና የካሳ ቀብድ ቢኖርብኝም።
"ወሰብሳብ ንጹሕ ወባረኮ እግዚአብሔር ለትድምርተ ብእሲ ወብእሲት ☞ ጋብቻ ንጹሕ ነው ፣ የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል " 【ድድስቅልያ ፴፫፡ ፪፻፳፬ 】
ሰርጉ ለምን እንዲህ መነጋገርያ ሆነ ካላችሁ የጃንደረባ ልጅ ስለሆነ ነዋ!
ጃንደረባ የሚለው (סָרִיס) ባለሥልጣኑን ፣ ሀገረ ገዢውን፣ መስፍነ ብሔሩን፣ የሹማምንቱን አለቃ፣ መጋቢውን የሚወክል ነው። (A minister of state / chamberlain)
ሔኖክ Deacon Henok Haile ማለት ሐዲስ ቅዱስ ማለት ነው ፤ በተቀደሰው የተለመደ ጋብቻ አዲስ የሰርግ መንገድ አስተምሮ አልፏል።
ጥንቱንም ሔኖክ የአዳዲስ መንገዶች ጀማሪ ነው። ይህም በቀደመው ሔኖክ ታውቋል!
ሊቃውንቱ "በአቤል አፍርሆሙ ወበሔኖክ አሰፈዎሙ /አንቅሆሙ ☞ በአቤል ሞትን ቀምሶ የደነገጠው የሥጋ ባህሪ በሔኖክ ዕርገት ተስፋ ትንሣኤን አገኘ"
ለዛሬው ደግሞ አቤል Dn Abel Kassahun Mekuria (ትንሹ ኄኖክ) ሚዜው ኖሯል። መጽሐፍ አስቀድሞ ስለሁለቱ እንዲህ ብሏል ፦
"ወእኩያንሰ እለ ይገብሩ ዐመፃ ወጽልአ ወሀከከ ይከውኑ ርኁቃነ እምእግዚአብሔር፤ እስመ እግዚአብሔር አምላከ ምሕረት ይፈቅድ ያስተጋብኦሙ ለኵሎሙ ትውልድ ውስተ ንስሐ በትምህርተ መንፈስ ቅዱስ ወጻድቃን ወነቢያት መሀሮሙ ለእለ እምቅድመ አይኅ ነበሩ አሕዛብ በትምህርተ አቤል …†… ወኄኖክ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ⇨ ዐመፅን ጥላቻንና ክርክርን የሚያደርጉ ክፉዎች ግን ከእግዚአብሔር የተለዩ ይሆናሉ ፤ የምሕረት አምላክ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ትምህርት በጻድቃን በነቢያት ፍጥረቱን ሁሉ ወደ ንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ይወዳልና ፤ ከማየ አይኅ አስቀድመው የነበሩትን በአቤልና … † … በኄኖክ ትምህርትና ተግሣጽ አስተማራቸው"【 ድድስቅልያ ፲፩፥፲፫】
☞ ኢጃቶች ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የ አንባብያን ኅብረት Book Club ሕንክሙ ሔኖክክሙ (ሔኖካችሁን እንካችሁ) በቃልም በሥራም ተማሩ። ዛሬ ደግሞ ይኸው "የጃንደረባው ልጅ በጃንደረባው ሥር" ከአባቱ ሥር በአባቱ ቡራኬ ተቀበለ። በድጋሚ እንኳን ደስ አለህ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሁሉ ርካሽ ነገር የሰው ነፍስ ነው። እጅግ በጣም ውድ፣ የተከበረና ፍፁም መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ህይወት ሲበዛ ውዳቂ ነው።
የኑሮና የመሠረታዊ ሸቀጦች ውድነት ግን ሰማያትን እየታከከ ነው።
እንደ ነፍሳት በከንቱ ለተገደላችሁና እንደ ጉድፍ ለተጣላችሁ ወገኖቼ የልቤ ሀዘን ጥልቅ ነው።
የርኅራኄ አምላክ በምህረት ይቀበላችሁ፣ ብድራታችሁም አይዘግይ..!

Forwarded from ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media) (Ethio Beteseb Media)
✏በሲያትል ስቴት ለምትኖሩ በሙሉ የቀረበ ጥሪ