Telegram Web Link
ስለራስህ ስታስብና ስትጠይቅ ምንድን ነው ምታየው?

ብዙ ሰዎች ስለራሳቸው ሲያስቡ እራሳቸውን የሚያዩት በት/ቤትና በዩኒቨርስቲ ባላቸው ውጤትና ደረጃ፣ ባለቸው ስራና ደረጃ፣ ሰዎች በሚሰጧቸው ተራ ግምገማና ትችት፣ ባላቸው የገንዘብ እና የኑሮ ደረጃ መጠን፣ ባጠቃላይ ውጫዊ በሆኑ ነገሮችና ሁኔታዎች እራሳቸውን አይተውና ገምተው ስለራሳቸው ምንነትና ማንነት የሚያስቀምጡት፡፡ ለምን ቢባል ስለራሳችን ማንነት ግንዛቤውና እውቀቱ ስለሌለን በውጫዊ ሁኔታዎች እራሳችንን አጥረንና አሳንሰን እንቀመጣለን፡፡

አእምሮዎዊ ህይወትህ አስተሳሰብህ ሲለወጥ አለማዊ አካላዊ ህይወትህ ኑሮህ ይለወጣል፡፡

ይከታተሉን እርሶ ሊጠቀሙበት የሚችሉተ የተለያዩ የሃገር ውስጥ ስልጠና መርሃ ግብሮች ሲኖሩ በዚሁ ቻናል እናሳውቆታለን።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በማይሆነው በማይቻለው ሃሳብ ተጠምዷዎልን?

ሀሳቦን ይለውጡ እና ለግቦና ለስኬቶ የሚያስፈልጎት ትክክለኛዎቹ ሰዎች፣ ገንዘቡ እና ሀብቶች ወደ እርሶ እየመጡ መሆኑን ማሰቦን ለራሶ ማውሳቶን ይቀጥሉ፡፡ በእምነት ወደፊት ይራመዱ በጭራሽ ወደሆላ አይመልከቱ እና ስለማይቻለው መንገድ አይብሰልሰሉ፡፡

እናም በመጨረሻ ውድቀት ለእርሶ የማይታሰብና የማይቻል እንደሆነ አርጎ እርምጃዎን ይቀጥሉ፡፡ ለራሶ ደጋግሞ ያስታውሱ ፤ ለራሶ እችላለው አደርገዋለው ይበሉ፡። ያስታውሱ ልብ ይበሉ እምነትና ፍርሃቻ ብዙ ሚያመሳስላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሁለቱም ባላወቁትና ባላዩት ነገር ላይ እንድታምኑ/እንድትቀበል ይጠይቆታል፡፡ ፍርሃቻ ወይስ እምነት ይመርጣሉ ምርጫው ያንተ ነው እሱም ሀሳበህ ብቻ ነው!

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
የሚሆነውና የሚወሰነው እንደአስተሳሰቦ ነው፡፡

“የእርሶ አለም አእምሯዎን እንዴት እንደሚጠቀሙበት እና እንዴት እየተጠቀሙበት እንደመጡ ያሚያሳይ ሕያው መገለጫ ነው፡፡” አርል ናይቲንጌል

እርሶ የሚኖሩት በአለማዊ ሕይወቶ እና በአእምሯዊ ህይወቶ ውስጥ ነው፡፡ አለማዊ ሕይወቶ፤ የእርሶ አካላዊ ህይወት፣ያሉበት ሁኔታና ደረጃ የሚያሳይ ሲሆን አእምሯዊ ሕይወቶ ደግሞ በውስጣዊ አለሞ የሚያስቡትና የሚያብሰለስሉት ሃሳቦች ናቸው፡፡ እናም አለማዊ ሕይወቶ የአእምሯዊ ሕይወቶ መገለጫ ነው፡፡

አለማዊ አካላዊና ውጫዊ ህይወቶን ለመምራት በውስጦ የሚያስቡትን ሀሳቦን ይምረጡ፡፡ ሀሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ።
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ስለማይወዱት ሁኔታና ደረጃ እያብስለሰሉ ነው እንዴ?

ዛሬ ላይ፣ ነገ፣ ሳምንት፣ ወር የሚያስቡትና የሚያብስለስሉት ሀሳቦት የእርሶን ህይወት ይቀርጻሉ እናም የወደፊት ሕይወቶን እና ማንነቶን ይወስናሉ፡፡

ያለፈውን ሁላ ድክመትና ጉድለትህን፣ ያጣህውንና የሌለህን ስላለፈውና ስለመጡበት አልያም ስላሉበት በስሜት ሲዳክሩ የወደፊት ሕይወቶን አያበላሹ፡፡ ስለመጪው አይጨነቁ የወደፊቱ በእርሶ እጅ አይደለም ወደፊት የሚቀሮትን ግዜ አያውቁም፡፡ ለእርሶ ያሎት ዛሬ ብቻ ነው፡፡

ዛሬ ላይ የሚያስቡት የሚያብሰለስሉት ሀሳብ ስሜቶን ይቆጣጠራል፡፡ ስሜቶ ደግሞ ዛሬ ላይ የሚኖሮትን ድርጊቶን ይቆጣጠራል፡፡ ዛሬ ላይ የሚያረጉት ድርጊቶ ደግሞ ኑሮዎን ሕይወቶን የመጪውን ውጤቶን ይቆጣጠራል፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ።
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በውስጥህ ስላንተ ያለህ ምስል ምን እያለህ ነው?

በእያንዳንዳችን ውስጥ ስለራሳችን የሚሰማን ስሜትና የማንነት ጽንሰ ሃሳብ የራሳችን ምልከታና እይታ በአጠቃላይ የራስችን ምስል (Self-Image) በጥልቁ ውስጣዊ አእምሯዋችን ውስጥ ተቀርቅሯዋል፡፡ እናም የሲኬቶቻችን ወሰን ድንበሮች በዚህ ምስል አጥር ስር ይወሰናሉ፡፡ ስላራስህና ሰለማንነትህ የምታሰባቸው ሃሳብ ድምር ውጤቶች ሰላንተ ያለህን ሰሜት ምልከታና እይታ በመቆጣጠር በጥልቁ አእምሮህ ውስጥ ያንተን ምስል (Self-Image) ይቀርጻሉ፡፡

ውጫዊ ማንነትህ ለመቀየር በውስጣዊ አእምሮህ ያለው የራስ ምስል (Self-Image) መቀየር ቅድሚያ መስፈርት ነው፡፡

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ምን እያሰብክ ነው?

መቼም የዚህ ቻናል ታዳሚዎች ሆነው የሀሳብ ሀያልነት ሀሳቧ በእርሷና በህይወቶ ላይ ያለውን ተጽኖ ግንዛቤ አዳብረዎል፡፡ አይደል? ታዲያ እስቲ ዛሬና ትላንተ ቀኑን ሙሉ በውስጦ ሲያብሰለስሉ የዋሉት ሀሳብ እንዴት ነበር?አብዛኛው ሰው በውስጡ ሚያብሰለስላው ሀሳቦች እራሱንና ስሜቱን ዝቅ ስለሚያረገው፣ ስለማይፈልገው፣ በህይወቱ ስላጣውና ስላልሆነለት ጉዳይ እና ስላላረገው ነገር፣ በራስ ወቀሳና ትችት ላይ ነው ሲብሰለሰል ቀኑን ሚያሳልፈው፡፡ ቆይ ቆይ ግን እስቲ ዛሬ የሚሰማዎት ስሜት ደስ የሚል ወይስ የማያስደስት ስሜት ላይ ነዎት? ስሜቶን ለመቀየር የሚያብሰለስሉትን ሀሳቦን ይለውጡ እናም ውሎዎን ያሳምሩ፡፡

ከምርጥ ሀሳብ ምርጥ ቀን ለእርሷ!

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ጥርጣሬ ጭንቀት ፍርሃቻ ሀሳቦች ወደሆላ እንጂ ወደፊት አያራምዶትም፡፡

እየገጠመህ ያለው ፈተናዎች የእርሶ መጨረሻና መዳረሻዎ አልያም እጣ ፋንታዎ አለመሆኑን ያስታውሱ፡፡ ይልቁንም ወደ ስኬት ውጤት መንገድ ላይ አንድ እርምጃ ናቸው፡፡

እናም ሀሳቦን እና ትኩረቶን አሁን ስላሉበት ሳይሆን ወደሚሄዱበት ነገር ላይ ያተኩሩ፡፡ ልብ ይበሉ የማይቻልበትን ነገርና የማይሆንበትን መንገድ ማሰብ ማብሰልሰሎ ለእርሶ አንድም ፋይዳ የለውም ከጥርጣሬ ጭንቀት ፍርሃቻ እናም እርሶን አሽመድምዷ ከሚሄዱበት እርምጃ ከማስቀረት በቀር እንድም ጥቅምና ወጤት አያስገኝሎትም፡፡

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አዲስ የባህሪ ለውጥ ማዝለቅና ማጽናት ተስኖታልን?

ባህሪዎን የሚገዛው ውስጣዊ ስሜቶ ነው፡፡ ስሜቶ ሳይቀየር ባህሪዎ አይቀየርም፡፡ ፍርሃቻ ጭንቀት ቁጭትና የንዴት ስሜት በውስጦ አዝለው የተረጋጋና ሰላማዊ ማንነትን ባህሪዎችን ሊላበሱ አይችሉም፡፡

ዋናው ነገር ግን ስሜቶን የሚገዛው መንስኤው ሀሳቧ ነው፡፡ የሚያብሰለስሉት የሚያስቡት ሀሳብ ፍርሃቻ ጭንቀት ቁጭትና ንዴት ከሆነ ስሜቶ የተረበሸ እናም ባህሪዎ ተናዳጅ ነው የሚሆነው፡፡

ለሁሉም ዋናው ነገር ለውጤት ማሰብን ይማሩ፡፡ በህይወቶ በማንነቷ እና በስብዕናዎ ላይ ይሰልጥኑ! ይቀላቀሉን፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አሁን ያለህበት ሁኔታና ደረጃ ያንተን ማንነተና አቅም ወሰን አይደሉም፡፡

አንተ እኔ ነኝ ብለህ ልትገምተው ከምትችለው በላይ ነህ፡፡ እኔነኝ የተባለ ሳይንቲስት እንኮን ያንተን አቅም ጥግ ሊገምተው ከሚችለው በላይ ነህ፡፡

የአንተ ማንነትና አቅም ጥግ አሁን ያለህበት ሁኔታ ችግሮችህ አልያም ባለህ የገንዘብ አቅም እና የትምህር ደረጃ ወይንም ስላንተ ሰዎች የሚሰጡህ ተራ አስተያት ትችት ጋጋታ ሁሉ በጭራሽ ስላንተ ማንነትና አቅም ጥግ አይገልጹም፡፡ ይልቁንም እነዚህ ሁሉ በአንተ ጥልቅ አእምሮ ውስጥ በተደጋጋሚ የተጻፉና የተቀረቀሩ ሃሳቦች ጥርቅም መገለጫ ብቻ ናቸው። ስለራስህ ብዙ አጥና። ስለራስህ ብዙ ስታውቅና ስትረዳ ስላንተ ያለህ እምነትና ስሜት ለራስህ ያለህ ምልከታ ይለወጣል፡፡

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ለውጥ ከፈለክ መለወጥ የምትችለው አንተን ብቻ ነው፡፡

ያንተ ህይወት ኑሮህ አለምህ እንዲቀየር መንግስትን አትጠብቅ፡፡ ትዳሮ ደስተኛ እዲሆን ለመለወጥ ባለቤቶ እንዲለወጡሎት አይጠብቁ፡፡ ከልጆቾ ጋር ያሎት ግንኙነት እንዲለወጥና እንዲዳብር ልጆቾ እንዲለወጡሎት አይጠብቁ፡፡

እርሶ ሲለወጡ አገር ይለወጣል መንግስት ይለወጣል፡፡ እርሶ ሲለወጡ ትዳሮ ይለወጣል፡፡ እርሶ ለልጆቾ ያሎት ምልከታና እይታ ሲለወጥ ልጆቾ ከርሶ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይለወጣል፡፡ ልብ ይበሉ እርሷ መለወጥ የሚችሉት እርሷን ብቻ ነው፡፡ እናም ያኔ ሌሎች ባይለወጡ እንኮን የእርሷ አለምና የውስጥ ሰለሞ ግን ይለመልማል

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ግዜው አሁን ነው! ዛሬ።

ልብ ይበሉ ሁሉም ነገር ለአእምሮዎ አሁን ብቻ ነው። ለእርሶ አእምሮዎ ትላንት ወደፊት አልያም ያለፋና የመጪው ሚባል ነገር የለም እርሶ በትኩረት በሃሳብ የሚያስቡት ምስሎችና ማንኛውም ነገሮች አእምሮዎ ልክ እውን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን አሁን እየተከናወነ እንደሆነ ጭምር ነው የሚያውቀው። ታድያ በህይወቶ ዛሬን ለመኖር ትኩረቶንና የሚያብሰለስሉትን ሃሳቦችና በውስጦ የሚቀርጹትን ምስሎት በህይወት እሴቶችና ግቦች ላይ በማዎል እውነተኛ ፍላጎቶንና ስሜቶን በማዳመጥና ምላሽ በመስጠት ዛሬን መኖር ይጀምሩ። ግዜው አሁን ነው!

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በነጻነታችንና በህይወታችን ውስጥ መኖር እንጀምር

ወደሆላ በቁጭት ወደፊት ደግሞ በስጋት ሃሳብ ውስጥ በመጠመድ በህይወታችን ውስጥ ከመኖር ይልቅ ነጻነታችንን ለነገሮችና ለሁኔታዎች አሳልፈን በመስጠት ዛሬን ከመኖር ይልቅ ባክነን እንቀራለን። በህይወት የራሳችንን የህይወት እሴቶችና ግቦች በመመስረት የሃሳባችንን ትኩረት ተግባራችንና እርምጃችን በህይወታችን እሴቶቻችንና ግቦች ስር እውነተኛ ፍላጎታችንና ስሜታችን ከማዳመጥና ምላሽ በመስጠት በህይወት ውስጥ ከመኖር ይልቅ በውጫዊ ነገሮችና ሁኔታዎች ብቻ በሃሳብ እንባክናለን።

ለውጤት እናስብ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ችግርና ድክመትን ከማብሰልሰል ይልቅ እስቲ ለውጤት እናስብ

እውነተኛ ስሜቶንና ፍላጎቶን በማዳመጥና ምላሽ በመስጠት ለመኖር ሃሳቦን በህይወቶ ወደሚፈልጉት እሴቶች ለማሳካትና ለመተግበር በሚያስፈልጎት ሃሳብ ላይ ባተኮሩ ቁጥር ውስጣዊ ንቁ-ግንዛቤዎ በአእምሮዎዊና መንፈሳዊ ማንነት ክፍሎ እየተገለጸሎት ወደ መፍትሄ መንገድ በውስጣዊ ጥበብ እየተመሩ ይበለጽጋሉ። ያለፉትን ድክመቶንና ጉድለቶን፣ ችግሮን አልያም በውጫዊ ሁኔታዎችና ክስተቶች ልክ የሃሳቦን ትኩረት ባደረጉ ቁጥር ወደፊት ከመራመድና በህይወት ከመኖር ይልቀ በችግሮችና ድክመቶቻችን ስር ማብቅያና ማቆሚያ በሌለው የትንታኔ ሃሳብና ውጫዊ ምክንያት በህይወቶ ይባክናሉ። አስተሳሰቦ ሳይለወጥ ህይወቶና ችግሮ አይለወጥም።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ህይወት ኑሮ ሃሳብ

አብዛኛው ሰው ብዙ ግዜ ህይወቱን የሚኖረው ለራሱ ባለው ጽንሰ-ሃሳብ ውጫዊ በሚገጥሙት ሁኔታዎች ስሜቱን ሃሳቡን ትኩረቱን አእምሮውን ግዜውን እና ማንነቱን በተቀረጸበት ጽንሰ-ሃሳብ መነጸር ስር በሚፈጠር ውስጣዊ ስሜት ምላሽ በመስጠትና በመጠመድ ከራሱ ጋር በውስጡ በመታገል በሃሳብ ይባክናል። እናም አየህ እውነተኛ ማንነታችን ውስጥ ለእውነተኛ ፍላጎታችንና ስሜታችን ምላሽ በመስጠት በህይወት ከመኖር ይልቅ በውጫዊ ነገሮችና ሁኔታዎች ከውስጥ በተቀረጽንባቸው ጽንሰ-ሃሳብ ውስጥ በሚመነጩ ሃሳቦችና ስሜቶች በመታገልና ምላሽ በመስጠት በህይወት እንባክናለን።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በህይወት መንገድ በህይወት ውስጥ በእርጋታና በሰከነ መንፋስ ለመራመድ ሁሌም ጥረትን ከትግስት ጋር በማጣመር የህይወት መንገድ አድርገህ ያዝ። ያለህበት ደረጃ ሁኔታዎችና ነገሮች በፈለከው መንገድና ፍጥነት አለመሆን በጭራሽ በቻልከው አቅም ከመጣር እንዳትቆጠብ ሁሌም ትግስትን እንደ መንገድ ተጠቀም። በትግስ ውስጥ ነገሮችንና ሁኔታዎችን በመቀበል ጉዞህን መቀጠል እንድትችል ስለሚያረግህ መረጋጋትና ውስጥህ በመስከን ጽናትን እየተለማመድክ ትመጣለህ። አየህ ጽናት ስታደርግና የሃሳብህን ትኩረት ሁላ በየቀኑ ውስጣዊ ስሜትህንና ፍላጎትህን በማዳመጥና ምላሽ በመስጠት ላይ ስትጠመድ አእምሮህ በሃሳብህ ትኩረት ልክ እምነትን በውስጥህ እየገነባ ይመጣል። በቃ ያኔ አንተ ዛሬን መኖር ጀመርክ ማላት ነው።

በህይወት መንገድ ውስጥ ህይወትን መኖር በቃ ይህ ነው እኮ መኖር፣ ስኬት በቃ ይህ ነው ያለማቆረጥ በህይወት መንገድ በየቀኑ ወደፊት መጎዝ እናም አስተውል በየቀኑ በህይወት ስኬት ላይ ነህ።

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በህይወትህ ስለሚቆጩህ ነገሮች፣ እና ይህንን አላረኩም ያንን ባደርግ ኖሮ እያልክ ምታብሰለስላቸው ሀሳቦች ሁላ ያንን ያለፍክበትን ህይወት ደጋግመህ እንድተኖረውና ካንታ ጋር አብሮህ እንዲቆዩ እንጂ የአንተን አዲስ ህይወትና ስብእና ሊገነቡልህ በጭራሽ አይችሉም፡፡

“አንዳንድ ሰዎች ህይወታቸውን በሙሉ ያጠናሉ እናም ሲሞቱ ሁሉንም ነገር ተምረዎል፣ ከማሰብ በስተቀር፡፡” Domergue

ህይወትህን በሙሉ ስለራስህና ስላለፈው ስታጤን ከርመህ የሞትህ ቀን ስለራስህ ሁሉንም ነገር አውቀህ ምንነው እቴ አንድ ቀን ቆም ብዪ የምፈልገውን ነገር ለማድረግ ባስብ ኖሮ ትላለህ፡፡ እናም ከማሰብ በስተቀር ሁሉንም አውቀህ ሁሉም ነገር ያመለጠህ ሰው አትሁን! እናስብበት፡፡ ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በገዛ በራስህ ሃሳብ ነኝ ብለህ ስለራስህ ደጋግምህ የምታስበውና በተለያዩ በህይወት ባለፍክባቸው ውጫዊ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች አንተ ስላራስህ ለራስህ ደጋግምህ የምትነግረውን ሃሳቦች ሁላ እየወሰድ አእምሮህ በምላሹ ያንተን የራስ ምስል (Self-Image) በአንተ በራስህ ውስጥ ይቀርጽልሃል።

እንግዲህ ይሄውልህ ያንተ ማንነትና ህይወት ደራጃ ታዲያ በዚሁ በራስህ ውስጥ በተቀረጸው የራስ ምስል አጥር ልክ ነው። አንተ በውስጥህ ከተቀረጸው ያራስ ምስል በላይ በጭራሽ ልትሆን አትችልም ሌላ አዲስ የራስ ምስል እስካልቀረጽክ ድረስ።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ዛሬ ላይ ሆነው እርሷንና ሕይወቶን የሚቆጣጠሯት ከልጅነቶ ቡሆላ ያገኙት እውቀቶች ሳይሆኑ ዛሬም ድረስ የሚቆጣጠሯትና የሚገዛዎት በህይወቶ ውስጥ አልያም በልጅነቶ በቅድሚያ በውስጧ የተቀረቀረቧት ውስጣዊ ማንነቶ እና ሃሳቧ ነው፡፡

እራሶንና ሕይወቶን ለመቀየር በቅድሚያ በውስጧ የተቀረቀሩትን ውስጣዊ ማንነቶን እና ሃሳቦን ይለውጡ፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በህይወቶ ሊያገኙ ከሚገባው ከእውቀቶች ሁሉ በላጩና ትልቁ ጥበብ ሀሳቦን በመግዛትና በመምራት ህይወቷንና አለሟን የመግዛት ጥበብ ነው፡፡

ሀሳቦን የመግዛትና የምምራት ጥበብን ይማሩ፡፡ በህይወቷ እና በራሷ ላይ ይሰልጥኑ!

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
የምታስበው ሀሳብ ምንድን ነው?

የምታስበው ሀሳብ ጭንቀት፣ ፍርሃቻ፣ ስለሰማህው መጥፎ ዜና፣ ግራ መጋባት ከሆነ ህይወትህ ግራ የተጋባና በሽብር የተሞላ ይሁናል፡፡ የምታስበው ምንም ከሆነ ደግሞ ህይወትህ ምንም ይሆናል፡፡ በህይወትህ ግብ ካለህና የምትስበውና የምታብሰለስለው ግብህ ላይ ከሆነ ደግሞ ግብህን ትኖረዋለህ፡፡

የሰው ልጅ የሚሆነው የሚያስበውን የሚያብሰለስለውን ሃሳብ ነው፡፡

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
2025/07/06 12:35:06
Back to Top
HTML Embed Code: