Telegram Web Link
አንተ መሆን ማድረግ መድረስ የምትፈልገውን ሁሉ ለማግኘት የሚያስችልህ ሀይልና አቅም አለህ፡፡

ሰው በመሆንህና አእምሮ ስላለህ ብቻ የፈለከውን ለመሆንና ለማግኘት የምትፈልገውን ህይወትና ኑሮ ለመቅረጽ የምትችል ድንቅ ፍጥረት ነህ፡፡

ካንተ የሚጠበቀው ምትፈልገውን መምረጥና መወስን፣ ሃሳብህን መግዛትና የምታስበውን ሀሳብ እና ውስጣዊ አለምህን ገዝተህ ለአእምሮህን መሆን ስለምትፈልገው ነገርና ሃሳብ መሙላት ብቻ ነው፡፡ እናም አእምሮህ በመገብከው ሀሳብ መሰረት ማንነትህን ስሜትህን ድርጊትህን ተቆጣጥሮ የፈለክበት ቦታ እጅህን ይዞ ያደርስሃል፡፡

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ልብ ይበሉ አልተሳካም ማለት አይሆንም ማለት አይደለም ግዜና ሂደት ብቻ ነው ሚፈልገው

ውጫዊ ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን ሃሳቦን ይቆጣጠሩና በህይወቶ ውስጥ እርሶ በመረጡትና በሚያልሙት የህይወቶ ግቦችና እሴቶች ሃሳብ ላይ ይጽኑ። እናም ነገን አሻግረው በማለም በውስጦ ከፍ ብለው አሁን ላይ የያዙትን የተሰማሩበትን የሚሰሩትን ማንኛወም ነገር ምንም ይሁን ምን የተቻሎትን ያህል በጥራት ይስሩ።

ሃሳቦን መምረጥ ለእርሶ የተሰጦት ጥግ ነጻነት ነው። እራሶን ነጻ ያውጡ።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በየትኛው የሃሳብ ማዕበል ነውጥ ውስጥ ነህ?

እስቲ አስቡት አንዳንዴ በህይወቶ በሚያብሰለስሉት ሃሳቦች ምን ያህል ደስታ ምን ያህል ሰላም በህይወቶ እንዳመጡ እና ሌላ ግዜ ደግሞ በስሜትህ ውስጥ በአሉታዊ ስሜቶች ጥርጣሬ ጭንቀት እና ገደብ ሁላ ተብሰልስለህ ምን ያህል ህመም ወደ ህይወቶ እንዳመጡ።

ተው ተይ ይብቃህ ይብቃሽ! ባለንበት ቦታ ቆመን አንቆዝም። ዛሬ ላይ ካለንብት በላይ ከፍ ብለን እናስብ እናልም።

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አሁን ያለህበት ሁኔታና ደረጃ አልያም የገጠመህ እንቅፋትና ችግር አልያም የሌለህና ያጣህው ነገር ሊያሳስብህና ሊያሳዝንህ አይገባም፡፡ ይልቁንም በአውነተኛ አፈጣጠርህና ማንነትህ ይበልጥ ደስ ይበልህ ምክንያቱም አንተ ሰው በመሆንህ የተፈጠርከው መሆንና ማድረግ መለወጥና መቀየር የምትፈልገውን ነገር መፍጠርና መለወጥ የምትችል ፍጥረት ነህ፡፡

ወደፊት እንራመድ፡፡ ለውጤት እናስብ ለውጤት እንስራ!መልካም ሀሳብ፣ መልካም ቀን ይሁንሎ!

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ታላቅ ሰው መሆን ትችላለህ! እረ ግን እንዴት? ታላቅ ሰው ቢሆኑስ ግን?

እራሶን በታላላቅ ሰዎች ውስጥ አስቀምጠው ሊሆኑ የሚችሉትንና ሊሰማዎት የሚችለውን ስሜትና ሊያረጉት የሚችሉትን ነገር አስበው ያውቃሉ? ባጭሩ የታላላቅ ሰዎች ታላቅነት የመሆን ሚስጥሩ ምንጩ ይህ ነው፡፡ ከታላቅ ሀሳብና ስሜት የሚመነጭ ነው። ታላቅ ነገር የማድረግ እና ታላቅ ከመሆን ሀሳብና ስሜት የሚመነጭ ነው፡፡ እርሶ በዚህ ሀሳብና ስሜት ሲዘፈቁ ነገሮች በእርሶ ዙርያ ይወለዳሉ፡፡ ብልሀቱና መንገዶቹ ከውስጦ ይመነጫሉ ሀይልና ጉልበት ከውስጦ ይወጣሉ የታላቅነት ባህሪና ድርጊቶች ከውስጦ ይወለዳሉ፡፡

ታላቅነት ብልህነትና ጥበብ ከውስጦ ታላቅ ሀሳብ የሚመጣ ነው

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ከሁኔታዎቻችን በላይ ክፍ እንበል።

እውነተኛ ነጻነት የሚገኘው ከውስጥ ነው። ከምናየው ከምንሰማውና ከሚደርሱብን ነገሮች ውስጡን ያላጠራ እንዲሁም መንፋሳችንን እና አእምሮዎችንን ያላጸዳን እንደሆነ ከሁሉ ይበልጥ ተጎጂው ሰው እሱ እራሱ ነው። ውስጣችንን በውጭ ሁኔታችን በምናየውና በሚደርስብን ነገሮች እየተብሰለሰለ የምናማርር ከሆነና በምሬትና በጥላቻ ከሞላንው እውን ያኔ እኛ እውነተኛ ነጻነታችንን ለሌሎችና ለነገሮች አሳልፋን ሰተናል። ሰው ምንም ነጻነት ቢሰጠው ውስጡና ሃሳቡ መንፈሱ ነጻ እስካልሆነ ድረስ በነጻነት ሊኖር አይችልም።

እነዛ ከውጭ በሚገጥሙህ ሁኔታዎችና ነገሮች በውስጥህ የምታብሰለስላቸው መራራ ሃሳቦች ናቸው አንተ ምትጠጣቸው የምሬት ጽዋዎች ማለት።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ውስጣዊ ሃሳቦቻችን ብቻ ምን ያህል የህይወት ቆያታ ግዜያችንን ነፍገውን ይሆን ግን?

ወደፊት ከመራመድና በህይወት ውስጥ ከመኖር ይልቅ አብዛኛወን ግዜ በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የምንሰማው፤ የምንባለውና የሚነገረን፣ የምናየውና የምንመለከተው የውጭው አለም ነው ብዙውን ግዜ እኛነታችንን እና ህይወታችንን የተቆጣጠረው።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በራስ ማሰብና በራስ ተነሳሽነት መኖር

በውስጥህ ያለው እውነተኛ ፍላጎትና መልክት ምን እያለህ ነው። አብዛኛውን ግዜ ከልጅነታችን ጀምሮ እውነተኛ ፍላጎታችንና ስሜታችን በተለያዩ ምክንያት ተዳፍኖና ተገድበው ቆይተናል እናም አብዛኛውን ህይወታችንን ዛሬም ድረስ ውስጣችንን ከማዳመጥና ለእውነተኛ ፍላጎታችንና ስሜታችን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በሰዎች አመለካከትና በብዙሃኑ እይታና ምልከታ ልክ ብቻ በመኖር እኛነታችንን አጥተን ማንነታችንንና ህይወታችንን ለነገሮችና ለሰዎች አሳልፈን በመስጠት ሰዎች ለኛ በሚሰጡን ልክ ብቻ በህይወት እንባክናለን።

አንተ በራስህ ከውስጥህ ከማሰብና በራስህ ከውስጥህ ባለው ተነሳሽነት ከመኖር የበለጠ ምንም ታላቅ ነገር ካንተ ሊገኝ አይችልም።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በህይወት ካሉበት የተሻለ ለውጥና እድገት ማምጣት ይችላሉ

ዛሬ በህይወት ያሉበት ሁኔታና ደረጃ እውቀትና ክህሎቱ አልያም ልምድ የሚፈልጉት ልክ ባይሆንም እንኮን ሰው በመሆኖ ብቻ እርሶ በህይወቶ ማድረግና ማግኘት እንዲሁም መለወጥና መድረስ የሚፈልጉበት ቦታ ለመድረስ የሚያስችሎት የተሰጦት ተፈጥሮዎዊ የሆነ ድንቅ ማንነት አሎት። ታድያ አንተ በእውነት ምን ትፈልጋለህ? እንዴት መኖር ትፈልጋለህ? አንት ማን መሆን ትፈልጋለህ? ይህ በህይወትህ ውስጥ እውነተኛ ለውጥ ለማድረግ የሚጀምሩበት ቦታ እና በውስጥህ ያለውን እውነተኛ ማንነትና እምቅ አቅም የሚያወጡትበት መንገድ ነው።

ሁሉም ነገር የሚሆነውና የሚወሰነው እንደርሶ አስተሳሰብ ነው። እርሶ በህይወት ትኩረት የሚሰጡት ሃሳቦ ሲለወጥ አስተሳሰቦ ማንነቶ ህይወቶ አለሞ ይለወጣል።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አንተ ውስጥ ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

በእያንዳንዳችን የእለት ተእለት መደበኛ ህይወት ውስጥ ብዙ ያልታለሙ አጋጣሚዎችና ህልሞች አሉ። እኛ በተለምዶ ቸል ብለን የምናልፈው የሆነና በእያንዳንዳችን ውስጥ በእኛ ለመጠራት ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ያለ ውስጣዊ የሆነ እምቅ አቅም አለ። እናስባቸው። እናልማቸው! አንተ ከውስጥ በራስህ ምርጫ ከማሰብ እና ከውስጥህ ባለው እውነተኛ ፍላጎትና ስሜት በራስ ተነሳሽነት በራስህ ከማሰብ የበለጠ ካንተ ውስጥ ሊወጣና ሊገኝ የሚችል ሃይልና ታላቅ ጥበብ የለም።

የእርሶን ነጻ ፍቃድና ምርጫ የሆነውን ሃሳቦን በመቆጣጠርና በመምራት የግል አለሞንና የህይወቶን እጣ ፋንታ ይምረጡ።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ይህንን አስበውት ያውቃሉ ግን?

አብዛኛው ሰው ብዙውን ግዜ ሌሎችን በማየት ሌሎች የሚናገሩትን በመስማት ብቻ እራሱን አሳንሶ ይመለከታል እራሱን ብዙ ግዜ የሚያየው ያለፉ ድክመቱና ጉድለቱን ብቻ በማሰላሰል ሌሎችን በጭፍን በመከተል ብቻ ይኖራል። አንተ ማድረግና ማሳካት መድረስ የማትችልበትን ቦታና ደረጃ ሌሎችን በጭፍን በመስማትና በማየት ብቻ የሌሎች ቦታና ደረጃ አርገህ ለምን ታስባለህ? አንት ሰው በመሆንህ ብቻ በአእምሮዎዊ ማንነትህ ውስጥ የምትፈልገውን ነገር መቅረጽና መፍጠር የምትችል (creative beign) የሆንክ መንፈሳዊ ፍጡር ነህ።ባንተ ውስጥ ሰው የመሆንህ አቀም አለ። እናስብበት!ግዜው አሁን ነው።

ሃሳቦን በመቆጣጠርና በመምራት የግሎን ህይወትና አለሞን ይምሩ።


ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ነጻ ፍቃድና ምርጫህ

ሁል ጊዜ አስታውስ በህይወትህ ውስጥ አንተ ውጤቱን (Effect) መቆጣጠርና መምራት ሳይሆን ያንተ ነጻ ፍቃድና ምርጫ መንስኤዎቹን (Cause) የመፍጠርና የማምረት ነጻነትና ሃላፊነት ብቻ ነው ያለህ። ሀሳቦቻችን፣ ንግግሮቻችን እና ተግባሮቻችን በህይወታችን የምናመርታቸው መንስኤዎች ሲሆኑ በህይወት የምናገኛቸው ውጤቶቻችን፣ ሁኔታዎች እና አካባቢያችን በውስጣችን በፈጠርናቸው ሃሳቦቻችን መንሳኤ ልክ በተፈጥሮ ህግ የሚመነጩ ውጤቶች (Effect) ናቸው።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ለውጥ የሚጀምረው ከኛ ነው - ከውስጥ።

በአለም ላይ ያምናየው እድገትና ለውጥ እንደ ኢንተርኔት፣ መኪና፣ አውሮፕላን የአምፖል መብራት ሁሉም ከመፈጠራቸው በፊት በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ሃሳብ ብቻ ነበሩ። ሁሉም ነገር በመጀመሪያ በአካልና ተጨባጭ ውጫዎ ሁኔታዎች ከመገለጹና ከመፈጠሩ በፊት በአንተ ውስጥ በአእምሮህ ውስጥ ነው የሚፈጠረው። በህይወታችን መፍጠርና ማግኘት መድረስ የሚፈልጉትን ማንኛውም ለውጥና እድገት መጀመር ያለብን እዚህ ነው። ከውስጣችን። ውስጣችን እና መንፈሳችን ሳይለወጥ ለውጥ አይመጣም።

ሁሉም ነገር የሚወሰነው እና የሚሆነው እንዳ አንተ አስተሳሰብ ልክ ነው። አንተ መሆንና መድረስ ይምትችለው የሃሳብህን ልክ ብቻ ነው።

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አስተሳሰብህን የሚመራው ማነው?

አንደንድ ሰዎች አስተሳሰባቸውን የሚመሩት ባሉበት ሁኔታና ደረጃ በሚያዩትና በሚሰሙት በጭፍን በሌሎች ሰዎች ብቻ በመመራት ነው እናም አንተ በቃ በሁኔታዎችና በአካባቢህ ቁጥጥር ስር ትሆናለህ ። እጣ ፋንታህ የሚወሰነው ካንተ ውጭ በሆኑ ውጫዊ ነገሮች ይሆናል። ባንተ ውስጥ ያለ ሃይል በጭራሽ ንቁ አይሆንም። በቃ ያኔ ምን አለፋህ አንተ ከውስጥ አትናገርም አንተ በቃ ከውስጥ አትኖርም። ሃሳቦን በመቆጣጠርና በመምራት የግሎን ህይወትና አለሞን ይምሩ። ሃሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
በህይወታችን እና በነጻነታችን ውስጥ እንኑርበት።

እራሳችንን እና ህይወታችንን የምናየው ባለንበት ደረጃና ሁኔታ በገጠመን ክስተትና ችግሮቻችን ልክ ከሆነ እኛ በውጫዊ ሁኔታዎች እና በአካባቢያችን ቁጥጥር ስር እንወድቃለን እናም እኛ እንዲኖረን የምንፈልገውን የራሳችንን ሁኔታና አካባቢ ከመፍጠር ይልቅ ውጫዊ ሁኔታዎችና አከባቢያችን የእኛን አለም የእኛን ማንነትና ህይወት ይፈጥራሉ።

ይህ በውጫዊ ሁኔታዎች ስር በባርነት (Bondage) ውስጥ መኖር ነው። የራሳችሁን ነፃነትና ነፃ ምርጫችሁን ለዉጭ ሁኔታዎችዎ እና አካባቢዎ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው። ካሉበት ውጫዊ ሁኔታዎችና ክስተቶች የግሎን ሃሳቦን ነጻ በማውጣት በነጻነት ወደፊት ይራመዱ።

ሃሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙና እራሶንና ህይወቶን ነጻ ያውጡ።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
እርሶ ሰው በመሆኖ ብቻ ብቁ ኖት።

የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ በአእምሮዎዊና መንፈሳዊ ማንነቱ ውስጥ የሚያስባቸውን ቅርጽ አልባ (Formless substance) የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች በማስረጽና በምምራት የሚፈልገውን ማንኛውም ለውጥና ነገሮች መፍጠር ይሚችል (Creative Beign) የሆነ መንፈሳዊ ፍጥረት ነው። ሀሳቦን የመቆጣጠርና የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ እናም ማንነቶንና ስሜቶን ህይወቶንና ኑሮዎን ይለውጡ፡፡ ይህ ለእርሶ የተሰጦት ታላቅ ጸጋ እና እምቅ አቅሞ ነው፡፡

ሀሳቦን የመግዛትና የምምራት ጥበብን ይማሩ፡፡ በህይወቷ እና በራሷ ላይ ይሰልጥኑ! እርሶ በራሶ ከጫኑት ውስንንት ሀሳቦች በቀር ድንቅ ፍጥረት ነዎት፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ምን አሰብክ ታድያ?

የምንኖርባት (Gravity Law) ወደታች እንጂ ፍጹም ወደላይ ሊሆን አይችልም። የእርሶ ምርጫና ፈቃድ ከክፍታ ላይ መዝለል ወይ አለመዝለል ብቻ ነው እንጂ አንዴ ከዘለሉ ቡሆላ ምርጫው የሚወሰነው በተፈጥሮ ህግ በቻ ነው። ንፋስና አየሩ፣ ተራራውና ግንቡ እየገፈታተሩ ወዳሻቸው ቦታ እንደየሁኔታው gravity law ወደታች መፈጥፈጦ የማይቀር ነው። እርሶም ዛሬ በህይወቶና በንሮዎ ውስጥ የሚኖሩት ህይወትም ልክ እንደዛው በተፈጥሮ ህግ የሚመራ ሲሆን እሱም በሃሳቦ ልክ ነው። በአስተሳሰቦ አይነት ልክ የሚወስን ነው። ሃሳቦን የመምረጥ ነጻነቶንና አቅሞን ይጠቀሙ

ለውጤት እናስብ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ክረምቱ እየገባ ነው ዘንድሮስ ምን ልትዘራ እያሰብክ ነው?

በአእምሮዎዊና መንፈሳዊ ማንነቶ ውስጥ የሚዘሩትና የሚቀርጹት ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች ስለራሶ ማንነትና ህይወት ውድቀት ከሆነ፣ ስላሉበት ሁኔታና ደረጃ ማማረር፣ ድክመቶንና ችግሮን፣ ጥላቻና ምሬት ከሆነ የሚያብሰለስሉት እጣ ፋንታዎም ጭንቀትና ሃዘን፣ መከራና ችግር ውስጥ የሚኖር ደካማና ተሸናፊ ሰው መሆን ይሆናል።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አንተን የሚመራህና የሚቆጣጠርህ አእምሮህ ነው፡፡

አንተ ለገጠመህ ነገር ለሆነውና ለደረሰው አልያም ለሁኔታዎቸወና ለነገሮች ምላሽ የምትሰጥበት መንገድ የሚወሰነው ባለህ የአእምሮህ ዝንባሌህ (Mental Attitude) ነው::

የደረሰቦትና የሆነው ነገር ሳይሆን አእምሮ የደረሰውንና የሆነውን ነገር በሚያይበት መንገድ ነው የእርሶ ሕይወትና ኑሮ የሚገዛው፡፡ ሃሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ፡፡ የመረጡትና የሚያብሰለስሉት ሀሳቦች እርሶንና ኑሮዎን ይገዛሉና፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
የፈለጉትን ለመሆንና ለማድረግ የሚፈልጉበት ለመድረስ ትኩረት ተስኖታል?

ስላለፈው ስለትላንቱ ስለሆነው ስለሄደውና ስለመጣው መንገድ ላይ ሰው ስለተናገሮት ነገር ስላዩት ፊልም ስለሰሙት ሰበር ዜና ስንቱን አስበው ይችሉታል ግን?

ለእርሶ ለማይረባዎት ውስጦን ለሚያደማዎት ውስጦንና ስሜቶን ለሚረብሽና ለሚያቆሽሽ የእርሶን ማንነትና አቅም ጥያቄ ውስጥ ከሚከትቦትና እርሶንና ማንነቶን ለሚያጎድፍ ሀሳቦች አያብሰልስሉ፡፡ እርሶ ሰው በመሆኖ ብቻ ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ብቁ ፍጥረት ነዎት፡፡

መሆንና ማድረግ መድረስ ከሚፈልጉት ለመድረስ እርሶን ሊያቆምና ሊገታ የሚችል አንድም የለም ከሃሳቦ በቀር፡፡ ሃሳቦን ይምረጡ!

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
2025/07/04 18:07:04
Back to Top
HTML Embed Code: