Telegram Web Link
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነሥቷል በዚህ የለም😍

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
#ፋሲካ
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው
በሰላም አደረሳችሁ!

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
#ተነሥቷል
❝ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ ይደሰቱ  ተራሮችና ኮረብቶችም ነገሥታት መኳንንት ይጩኹ ይደሰቱ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ደስታን ታደርጋለች።❞

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
❝የሞትን ቁራኝነት አጠፋ ሲኦል በብርሃን ተጥለቀለቀች ነፍሳት በደስታ ከሲኦል ተፈተለኩ ከቁራኝነት ነፃ አውጥቷቸዋልና ዲያቢሎስን ድል መታው ገሀነም ፈራረሰ ሲኦልም ተዘጋ።❞

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ #ተነሣ

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምነዋም
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ

https://www.tg-me.com/MekuriyaM
😢 #ንነጽር_፺፯

አሰሩህ፣ በጥፊ መቱህ፣ ደበደቡህ፣ ተዘባበቱብህ፣ ምራቃቸውን ተፉብህ፣ አዳፉህ፣ ሰቀሉህ... ነገር ግን ይቅር አልካቸው።
የተነሣሁብህ ሆይ፥ የሰቀሉህ እነ'ሱ ትንሣኤህን ባዩ ጊዜ ምን ብለው ተረቱ?

እኔስ እንደ ምርጥ ዕቃህ እንደ ጳውሎስ እንዲህ አልኩ “ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥55

ከኃጢአት የመመለሻ በዓል ይሁንልን!
ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ


They arrested you, slapped you, beat you, abused you, spat on you, hunted you down, crucified you... but you forgave them.
I have risen from you, what did those who crucified you say when they saw your resurrection?

And I, as your best vessel, said like Paul, “O death, where is your sting? Hell, where is your victory?”
— 1 Corinthians 15:55

Let us celebrate the return from sin!
D/n Mekuria Murashe
😓 #ንነጽር_፺፰

ከሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ድረስ እየሰቀልኩት ነበር፤ አልሰቀል ብሎ አስጨንቆኝ፤ ግን የተሰቀለው ክርስቶስ ረዳኝ መሰለኝ ልክ ዕለተ አርብ ላይ ሰቅዬ ጨረስኩት። በዚያው ዕለት ደግሞ ከጌታዬ ጋር መቃብር ውስጥ ጨመርኩት። ዛሬ በዕለተ እሑድ ክርስቶስ ሲነሣ እኔ ቀብሬው የነበረው ግን አልተነሣም።

ሳስበው ግን እንዳይነሣ ያደረገው ሞቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። ምክንያቱም ስሰቅለውና ስቀብረው ያየው እርሱ ነበራ! ተነሥቶ እንዳይከተለኝ አጥብቄ የለመንኩት ለክርስቶስ ነበራ!

ስሰቅለው ግን በጣም ነበር ያስቸገረኝ። አንዱን ስሰቅለው ሌላ ይመጣል፤ ጨርሼ ሰቀልኩ ብዬ ላርፍ ስል ሌላላ ይታወሰኛል። እያልኩ እያልኩ ከሰኞ እስከ አርብ ደረስኳ። አርብ ከስንት ስቃይ በኋላ ሰቀልኩትና ዕረፍትን አገኘኹ። መሰቀሉን ያረጋገጥኩት ደግሞ በዕለተ አርብ መጨረሻ ላይ እካህኑ ጋር ሄጄ ጠብጠብ... ጠብጠብ...እያደረጉ ቃሌን የሰጠኋቸው ጊዜ ነው።

ጌታዬ ሆይ በዕለተ አርብ የሰቀልኳትን
#ኃጢአቴን ትንሣኤ ስለሌላት በብዙ እባርክሃለው። እኔ እንደሰቀልኳት አንተ ደግሞ ቀብረህ አስቀርተሃታልና አመሰግንሃለው🙏

#ኃጢአቴን_ነው_የቀበርኳት!

መ ል ካ ም የ ት ን ሣ ኤ በ ዓ ል !

@MekuriyaM
ሽልማት አለው የእውነት ተሳተፉ

A) "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እና

B) " #የማያውቁትን_ያደርጋሉና_ይቅር_በላቸው"

ልዩነት አላቸው ወይስ የላቸውም?
ቤተ_ልሔም~Bethelhem
ሽልማት አለው የእውነት ተሳተፉ A) "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እና B) " #የማያውቁትን_ያደርጋሉና_ይቅር_በላቸው" ልዩነት አላቸው ወይስ የላቸውም?
የሚያደርጉት አያውቁምና...
ምን እያደረጉ እንደሆነ አያውቁም። ሊመቱት፣ ሊያዳፉት፣ ሊዘባበቱበት ... ይችላሉ ግን እያደረጉ ያለው ምን እንደሆነ አያውቁም።

የማያውቁትን ያደርጋሉ ሲል ሌላ የሚያውቁት ነገር አለ፤ ነገር ግን አኹን እየሠሩት ያለው የሚያውቁትን አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን አያውቁም።

በደንብ ደጋግማችኹ በሉት ትንሽ ልዩነት አለው።

Tsionawit 👏👏👏
. ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈስም የለም ብለው የሚሉት እነማን ናቸው?
Anonymous Poll
40%
ሰዱቃውያን
19%
ፈሪሳውያን
13%
ሁለቱም
29%
ሁሉም
ቤተ_ልሔም~Bethelhem
. ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈስም የለም ብለው የሚሉት እነማን ናቸው?
“ሰዱቃውያን፦ ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ።”
  — ሐዋርያት 23፥8
#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) (Christ is risen from the dead!)
ስለ ኃጥያቴ ታመምክ፣ሞትክ፣ሞትንም ድል አድርገህ የተነሣህ ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣው ጊዜ አስበኝ።

#በዐቢይ_ኃይል_ወሥልጣን (በገናና ኃይልና ሥልጣን) (By the highest power and authority!)
ትንሣኤህን ሳስብ እጅግ ይደንቀኛል ነገር ግን በዳግም ምጽአት፡ እኔ እንደማዉቀህ ሰውኛ ገፅህ ተለውጦ በአምላካዊ ብርሃን እጅግ በሚያስፈራ በሚያስደነግጥ ግርማህ እንደምትመጣ ሳስብ ልቤ በፍራት ይርዳል።

#አሰሮ_ለሰይጣን (ሰይጣንን አሰረው) (He chained Satan!)
ቀን ከሌሊት ያለ ዕረፍት ሊያስት የሚጥረዉ ጠላቴን በትሩፋት አስተክዘዉ ዘንድ ልቤን በፍቅርህ እሰረዉ።

#አግአዞ_ለአዳም (አዳምን ነጻ አወጣው) (Freed Adam!)
አዳምን ለማዳን ከክብርህ ዝቅ ብለህ በፈጠርካቸዉ እጆች የተገፋህ ነህና ዛሬም ነፍሴ ከስንፍና እስር ትፈታ ዘንድ በትንሣኤህም ትበረታ ዘንድ ፍቃድህ ይሁን።

#ሰላም (ፍቅር አንድነት) (Peace!)
ሰማይ መቀመጫዉ ምድር መረገጫዉ አልፋና ኦሜጋ የጌታዬ፥ የጌታሽ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራቱን ይዞ በመጣ ጊዜ በሰጠሽ ሰላምታ ሰላም እልሻለዉ።

#እም_ይዕዜሰ (ከእንግዲህስ) (Henceforth)
ስፍር በሌለዉ መውደድ ወደኸኝ ልክ በሌለው ሕማም ታመህልኛልና የልቤን መቅበዝበዝ አርግተህ ልቤንም እንደ እግሬ ወደ ቤትህ ጥራው።

#ኮነ (ሆነ) (Is!)
ያለና የነበረ ያለ ፍጻሜ የሚኖር ማብቂያ በሌለው ዘለዓለማዊ መንግሥትህ በፍቅር እቅፍ እየሞቅኩ መኖር እናፍቃለው።

#ፍሥሐ_ወሰላም (ደስታና ሰላም) (Joy and Peace!)
ጌታዬ ከአንተ ዘንድ ያለው የውስጥ ሰላሜን በእንቁም የማልሸምተው ነውና በስስት የሚያዩኝ አይኖችህን ፣ በደስታዬ የሚፈነድቀው ልብህን ሌት ተቀን እኔን በመጠበቅ የማትደክም በመልካም ምግባሬ ደስታህን እውን አደርገው ዘንድ ፤ እኔም አንተን በማግኘት እቦርቅ ዘንድ ፤ በትንሣኤህ እኔም ተሰነካክዬ ከወደቅኩበት ኃጢአት መግነዜን ፈተህ ይዘኸኝ ተነሥ፤ ዘመኔም በፍሥሐ በቤትህ ሰላም ይለቅ!

ረድኤት አሊ / Rediet Ali.

◦◦◉◉Join us on telegram
www.tg-me.com/MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"ኢየሱስ ክርስቶስ " ሞቶ በስንት ቀን ተነሳ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተወለደችልኝ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ከዘላለም ህይወት በኃጥያት ተለይቼ
በመከራ ስኖር እውነትን ጠልቼ
ጌታዬ አምላኬን ዘወትር ሳሳዝነው
ሰላምን አጥቼ ነፍሴን አንገላታው
ድክመቴን ያወቀ የፈጠረኝ እሱ
ሊያድነኝ ወደደ መሀሪ ቅዱሱ
ከሴቶች መሀከል በንጽህና መርጧት
በፍጹሙ ፍቅሩ በልዕልና ወዷት
ዳግም ሰው ሊያደርገኝ በቃል አደረባት

ታድያ እቺ ልዕልት እርሷ የኔ ጸሀይ
ሰንሰለት ሆነችኝ ከእርሱ እንዳልለያይ
ከቅድስት እናቷ ከቅዱስ አባቷ
ለአለም አብርቶ ውበት ደምግባቷ
ወላዲተ አምላክ ድንግል እመቤቴ
ተወለደችልኝ ሆነችኝ ህይወቴ

እናቴ ይህ የአንቺ ብቻ አይደለም የኔም የልደት ቀኔ ነው። ከአንቺ ተለይቶ የሚቆጠር ዘመን የለኝም። አንቺ ባትኖሪልኝ እኔ ምንም ነበርኩ። ሰው የሆንኩት፣ አምላኬን ያወቅኩትና ነፍሴን ያሳረፍኳት በአንቺ ነው።

ዛሬ ነፍሴ ልደቷ ነው። ከአንቺ ተወልዳለችና። ያደረግሽልኝን ለመናገር ቃል አጥቻለሁ። ደግሞስ ከየት ጀምሬ የት አቆመዋለሁ። ብቻ በምድር አብሬሽ መኖሬ አይደለም በሰማይም ከእግርሽ ስር መኖሬ እጅጉን ደስተኛ ያደርገኛል።

ደስተኛይቲ ሆይ ደስ ይበልሽ

◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል

     🔐ከስር ክፈት የሚለውን
     በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
2024/06/15 23:44:15
Back to Top
HTML Embed Code: