Telegram Web Link
እኔስ ስለ አርሴማ፥ አለኝ ብዙ ቅኔ፤
ወጥቼ መግባቴ፥ ተባርኮ ነው ቀኔ።
ሰማዕትነቷን፥ ክብሯን ያልዘነጋ፤
አክሊል ሽልማት ነው፥ የድካሙ ዋጋ።
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
+++ #እንኳን_አደረሳችሁ +++

#ፍልሰታ...
ስጋሽ የኖረበት፥የሰማዩ በፍታ፤
ጥር ያሰሩት መግነዝ፥ነሀሴ ተፈታ።
ቶማስ ምስክር ሁን፥ ሰበኗን ያዝና፤
ሄደህ ንገራቸው፥ ለሐዋርያት ዜና።
የጌታችን እናት፥ማርያም ተነስታለች፤
በአንድ ልጇ ስልጣን፥ ድንግል አርጋለች።
+++++++++
“አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።”
መዝሙር ዘ ዳዊት132፥8
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ሕመሜ መሰንቆ፥ ለቅሶዬ በገና፤
ዘመኔ በድንገት፥ ሁለት አለም ሆና።
ያፈስኩት ቢበተን፥ የያዝኩት ቢጠፋ፤
ከእግዚአብሄር በቀር፥ የለም ሌላ ተስፋ።
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፥ አባ ተከለሀይማኖት፤
አገልግለህ የመጣህ፥ በሰማዩ ክህነት።
ከሀያ አራቱ ጋር፥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ስትል።
የሰላምን ፍሬ፥ በልባችን ትከል።

ዛሬም እንዳትረሳኝ፥ አባቴ ትላለች፤
ሰላሟ ጠፍቶባት፥ ኢትዮጵያ ታማለች።
ቆመህ የፀለይከው፥ የፀሎትህ ፍሬ፤
ሰላም ይሰጣት ዘንድ፥ ይድረሳት ሀገሬ፤

አባ ተክለሀይማኖት፥ አደራ አባታችን፤
ፍቅር ይሰጠን ዘንድ፥ ጠይቅ ከአምላካችን።
አንድ ያደርገንም ዘንድ፥ ለምን ለህዝባችን፤
ሰላም ይሰጠን ዘንድ፥ ፀልይ ለሁላችን።

©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ረድቶኛል ምልጃ ፀሎቱ፤
ለእረፍቱ አልቀርም ቤቱ፤
በደብረ አስቦ ያረፈው፤
ተክለሀይማኖት አባቴ ነው፤
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
በዘመናችን ላይ ዘመንን የሰጠ
ጷጉሜን በመስከረም እነሆ ለወጠ
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
መልካም አዲስ አመት
ታዜና
ማርያምን ተረከ…

ጽጋን የተሞላች የጌታዬ እናቱ
የአዳም ተስፋ ናት ኪዳን የምህረቱ፡፡
በደም የነጠቀ ከዘላለም ሲቃ
ማረፊያ ነው ልጇ የሰላም አለቃ፡፡

እርሻችን አሸተ ደመናው ተከፍቶ
እንጀራን ጠገብን ጎተራችን ሞልቶ፡፡
የዘራነው ሁሉ በወቅቱ ደረሰ
የአይኖቻችን እንባ በልጇ ታበሰ፡፡

የወይኑን እንስራ ይሞላል ምልጃዋ
በታሪክ መካከል ያበራል ስራዋ፡፡

ያዘነ ተጽናና ደካማው በረታ
ታላቅ ለታናሹ ለቀቀለት ቦታ፡፡
ትውልድ ተረጋጋ ዘመን ተባረከ
ብራና መጻፉ ማርያምን ተረከ፡፡
++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በአማኑኤል ስምህ
በፈሰሰ ደምህ
በተወጋ ጎንህ
በሰጠኸኝ ነፍስህ
አትተወኝ እልሀለሁ
ነፍሴን ማራት እልሀለሁ

እረኛዬ ሆነህ፥ ያሳጣኸን የለም፤
የችንካርህ ጽሁፍ፥ ፍቅር ነው ዘላለም።
በደሌን ታግሰህ፥ አይዞህ ትለኛለህ፤
በለመለመ መስክ፥ ታሰማራኛለህ።
++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
አለምን የሰራ ሲሆን፥
ከእኛ እንዳንዱ ቢሆን።
እንደ በደለኛ ቆጥረነው፥
በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀልነው።
++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ቅዱስ ሚካኤል፣ ክንፉን ዘርግቶ፤
ያሻግረናል፣ በፀዳል መርቶ፡፡
ህዳር ሚካኤል፣ ህዳር ሲታጠን፤
ፍቅርና ሰላም፣ ጤናውን ይስጠን፡፡
++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (ኩነኔ ሲገባኝ መዳኔ ገረመኝ)
++ምናለ ብታስተምረኝ++
በክብር በሞገስ በመወደስ ፈንታ
መቀመጥ እንድችል ከመዋረድ ተርታ
ስድብን እየሰማሁ ያለ አንዳች ሁካታ
ለመቆም እንድችል ልቤ ሳይረታ
ምናል ብታስተምረኝ ብታስችለኝ ጌታ!?
ለእኔም አስተምረኝ ባላጠፉት ጥፋት
በጸጋ መቀበል የአይሁድን ትፋት
እንዴት እንደሚቻል ሳያጉረመርሙ
ንገረኝ ጌታዬ ይረዳኝ ትርጉሙ!
የመናቅን ጥበብ የውርደትን ዘዴ
እባክህ አስረዳኝ አስተምረኝ አንዴ
ብዔል ዜቡል ተብለህ ያልተበሳጨኸው
የኃጢአተኞች ወዳጅ መባል ያልጠላኸው
ጋኔን ይዞታልን የሰማህ በጸጋ
ለእኔም አስተምረኝ በቂም አልወጋ!
አልወጋ እባክህ በመራርነት ጦር
በቁጣ ጥላቻ ነፍሴ አትሰበር
እንዴት ነበር ያኔ የይሁዳን እግር

ዝቅ ብለህ ያጠብኸው ስታውቅ ሁሉን ነገር?
ለእኔም አስተምረኝ ብዙ ሳልናገር!
በችንካር ተጣብቀህ ከመስቀሉ ጋራ
የደምህ ነጠብጣብ ገና ሳያባራ
አያውቁትምና የሚያደርጉትን
ይቅርታን የለመንህ ላጠጡህ ሐሞትን
ምናል ብታስተምረኝ እንዲህ ዓይነት ሕይወትን?
አሁን ምን ቸገረህ ብትሰጠኝ ለአንድ አፍታ
የትሕትናን ቀሚስ የትዕግሥትን ኩታ
እያየህም አይደል ነፍሴ እንዲህ ተራቁታ?
የመሰደብን ዘውድ የመናቅን ካባ
ምናለ ብትኖር ይ’ች ልቤ ደርባ!?
ትዕቢት ለተሞላው ለአትንኩኝ ባይ ልቤ
ለክብሩ ለሚኖር ለኮርማው ሃሳቤ
ምናለ ብትቀባው የትሕትናን ሽቶ
እንደዚህ ከሚኖር ሸትቶ ተበላሽቶ!?
ኸረ እኔ አልቻልኩም አቅቶኛል በጣም
ስድብን መቀበል ሐሜትን ማጣጣም

ስተርከው እንጂ ስኖረው አቃተኝ
ይህን መራር ኑሮ አንተው ይዘህ ጋተኝ!
እንኳን እንደ አንተ ዝም ልል ሲረግጡኝ
ቁጣዬ ነደደ ስለገላመጡኝ
ያንን ሁሉ ታሪክ ያን ሁሉ ጥቅስ ረሳሁ
በቂምና በቀል በጥላቻ ከሳሁ
እንደ አራስ ነብር ለክብሬ ተነሣሁ!
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ /
ታላቁን ነጎድጓድ፥ ታላቁን ማእበል፤
እንዴት ያላንተ እኔ፥ ችዬ አለፍኩት ልበል።
የልቤን ስንፍና፥ ሀይማኖት ደግፎ፤
ዛሬ ማለት አልኩኝ፥ ትናንትና ታልፎ።

በርሀብ በጥጋብ፥ ሁሉን ለሚለኩ፤
በጽድቅህ ይሰፈር፥ የዘመኔ ልኩ።
የዛለው ጉልበቴን፥ አበርታልኝ አንተ፤
ገደል እንዳይጥለኝ፥ ሆዴ እየጎተተ።

ወንድምህ የት አለ፥ ወዴት ነው ለሚለኝ፤
ይቅርታ መጠየቅ ፥ሽንፈት ከመሰለኝ።
ልቤ ቂም አርግዞ፥ ሁሉንም ከጠላ፤
እፉኝት ሆኛለሁ፥ እናቱን የበላ።

ትዕቢት እንዳይሞላኝ፥ በራስ በመመካት፤
ለስጋዬ ተግሳጽ፥ ፈተናን አትንሳት።
ነፍሴ እንዳትደክም፥ ስጋ ተንተርሳ፤
በመንግስትህ ጊዜ፥ ልጅህን አትርሳ።
++++++
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
"ምን እላለሁ፤
ምን እናገራለሁ፤
የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው።
የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"*

አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥
ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ።
ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት፤
ምን አይነት ፍቅር ነው፥ ምን አይነት ደግነት።

በናቱ እቅፍ ሆኖ፥ በሰማያት አለ፤
በሰማያት ሆኖ፥ በናቱ እቅፍ አለ።
ከኪሩቤል ጀርባ፥ ሳይወርድ ከዙፋኑ፤
ይገርማል ይደንቃል፥ በኛ መመስገኑ።

ቅድመ አለም ያለ እናት ተወልዶ ከአባቱ
ድህረ አለም ያላአባት  ወለደች እናቱ
ይህን ድንቅ ጥበብ፥ ፍጥረቱ ተማክሮ፤
ድንቅ ይባላል እንጂ፥ ማን ያውቃል መርምሮ።

ነብያት የናፈቁት፥ ትንቢታቸው መጣ ፤
ከድንግል ማህፀን፥ ያለድካም ወጣ፤
መለኮት ሳይከፈል፥ ወደ አለም መጣ፤
የጽድቃችን ጸሀይ፥ ከሰማያት ወጣ።
++++++
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

*("ምን እላለሁ ምን እናገራለሁ..."
ሐይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ)
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ጌታ ሆይ..
የተዘጋው ልቤን ፥ክፈተው በመስቀል፤
የሚያስክደኝ ጠላት፥ ከስሩ እንዲቀል።
የጥርጥር ነገር፥ በኔ እንዳይበረታ፤
ከእውነት እንዳልሽሽ፥ ልቦናዬን ፍታ።
ካንተ ተልይቼ ፥መቼም አልሆን ደህና፤
እውነቴም ህይወቴም፥ መንገዴ ነህና።
++++++
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የክብርህ ቀዳሽ
የመንግስትህ ወራሽ
እንድሆን እርዳኝ
ወደእኔብረሪ
በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።
ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይ ሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርርበ ደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።
ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን ያኀያላንጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢችኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይንያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።
የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።
ነውር የሌለብሽ መልካም ጸጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።
++++
©መጋቤ ብሉይ ወ ሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
2025/06/29 16:30:48
Back to Top
HTML Embed Code: