++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።
አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።
ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።
አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++
©ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።
አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።
ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።
አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++
©ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)
+++++++++++++++++++
ነፍሱን ሰጠ…
የአለምን ንጉስ ፣የፍጥረትን ጌታ፤
የኋሊት አሰሩት፣ ፊቱ እየተመታ፡፡
ህጋቸው ጨክኖ፣ አይሁድ በምክራቸው፤
የሚሰቀል መግረፍ፣ ባይፈቅድም ህጋቸው፡፡
አምላካችንን ግን፣ ፍርድ እያጓደሉ፤
በጅራፍ ገረፉት፣ ለአርባ እያጎደሉ፡፡
በዙ እንደበደለ፣ እንደ ጢያተኛ ሰው፤
ተቆጠረ አጥንቱ፣ ስጋውን ጨርሰው ፡፡
የአዳምን ሞት ሊወስድ፣ መከራን ታገሰ፤
ለሚጠይቁትም፣ አንዳች አልመለሰ፤
ወድቆ እየተነሳ፣ አይኑ እያለቀሰ፤
ደም ግባት አሳጡት፣ ደሙ እየፈሰሰ፡፡
አይን የሚፈጥረውን፣ በምራቁ አቡክቶ፤
ጉንጮቹ ተፀፉ፣ በፊቱ ተተፍቶ፡፡
የዘመንን ደዌ፣ በቃል የሚፈታ፤
በመጻጉዕ እጆች፣ በጥፊ ተመታ፡፡
አንዳች በደል እንኳ፣ የሌለውን ንጉስ፤
በፍርድ አደባባይ፣ አቆሙት በመክሰስ፡፡
ጲላጦስ ሆይ ፍረድ፣ በርባንን ፍታልን፤
ወንበዴውን ለቀህ፣ ጌታን ሰቀልልን፡፡
በሚፈርደው አምላክ፣ ፍርድ እያሰፈረዱ፤
መስቀል አሸክመው፣ ሊሰቅሉት ወሰዱ፡፡
የራስ ቀል በሚባል፣ ጎልጎታ ሰቀሉት፤
በሰፍነጉ ሞልተው፣ ሀሞትን አጠጡት፡፡
ከመስቀሉ በታች፣ ሲብቱ አይቷቸው፤
የሚያደርጉትንም፣ አያውቁም አላቸው፤
አባት ሆይ ስለዚህ፣ ይቅርም በላቸው፡፡
የአዳምን የሞት ሞት፣ በህይወት ለወጠ፤
በገዛ ስለጣኑ ጌታ፣ ነፍሱን ሰጠ፡፡
+++++++++++++++++++
" ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ።
ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
ነፍሱን ሰጠ…
የአለምን ንጉስ ፣የፍጥረትን ጌታ፤
የኋሊት አሰሩት፣ ፊቱ እየተመታ፡፡
ህጋቸው ጨክኖ፣ አይሁድ በምክራቸው፤
የሚሰቀል መግረፍ፣ ባይፈቅድም ህጋቸው፡፡
አምላካችንን ግን፣ ፍርድ እያጓደሉ፤
በጅራፍ ገረፉት፣ ለአርባ እያጎደሉ፡፡
በዙ እንደበደለ፣ እንደ ጢያተኛ ሰው፤
ተቆጠረ አጥንቱ፣ ስጋውን ጨርሰው ፡፡
የአዳምን ሞት ሊወስድ፣ መከራን ታገሰ፤
ለሚጠይቁትም፣ አንዳች አልመለሰ፤
ወድቆ እየተነሳ፣ አይኑ እያለቀሰ፤
ደም ግባት አሳጡት፣ ደሙ እየፈሰሰ፡፡
አይን የሚፈጥረውን፣ በምራቁ አቡክቶ፤
ጉንጮቹ ተፀፉ፣ በፊቱ ተተፍቶ፡፡
የዘመንን ደዌ፣ በቃል የሚፈታ፤
በመጻጉዕ እጆች፣ በጥፊ ተመታ፡፡
አንዳች በደል እንኳ፣ የሌለውን ንጉስ፤
በፍርድ አደባባይ፣ አቆሙት በመክሰስ፡፡
ጲላጦስ ሆይ ፍረድ፣ በርባንን ፍታልን፤
ወንበዴውን ለቀህ፣ ጌታን ሰቀልልን፡፡
በሚፈርደው አምላክ፣ ፍርድ እያሰፈረዱ፤
መስቀል አሸክመው፣ ሊሰቅሉት ወሰዱ፡፡
የራስ ቀል በሚባል፣ ጎልጎታ ሰቀሉት፤
በሰፍነጉ ሞልተው፣ ሀሞትን አጠጡት፡፡
ከመስቀሉ በታች፣ ሲብቱ አይቷቸው፤
የሚያደርጉትንም፣ አያውቁም አላቸው፤
አባት ሆይ ስለዚህ፣ ይቅርም በላቸው፡፡
የአዳምን የሞት ሞት፣ በህይወት ለወጠ፤
በገዛ ስለጣኑ ጌታ፣ ነፍሱን ሰጠ፡፡
+++++++++++++++++++
" ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ።
ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
ፋሲካችን ክርቶስ ታርዷልና
በትንሳኤው ከሙታን ተነስተናልና
እልል በሉ ተነስቷል ብላችሁ
እልል በሉ ሞት ሞተ ብላችሁ
፡
የመቃብር ደጃፍ ድንጋይ ተንከባሎ
በስልጣን ተነስቷል ሞትን ገድሎ ጥሎ
አጥጠራጠሪ አትክልተኛ አይደለም
የቆመው ጌታሽ ነው ደስ ይበልሽ ማርያም
፡
በመንገድ እያለፍን መንገድ ጠፍቶብን
መንገደኛ ነህ ወይ ብለን ጠየቅን
አሁን ግን አወቅን አሁን አየንህ
ለካስ መንገዳችን አምላካችን ነህ
፡
ሞትን ድል እንዳረክ በሀይል በስልጣንህ
ዳግም ስትመጣ አቁመን በቀኝህ
+++++++++++++
እንኳን አደረሳችሁ
+++++++++++++
አይናችሁ ይገለጥ እጆቹን እዩና
ደሞ ለዛሬ አመት ያድርሰን በደህና
++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በትንሳኤው ከሙታን ተነስተናልና
እልል በሉ ተነስቷል ብላችሁ
እልል በሉ ሞት ሞተ ብላችሁ
፡
የመቃብር ደጃፍ ድንጋይ ተንከባሎ
በስልጣን ተነስቷል ሞትን ገድሎ ጥሎ
አጥጠራጠሪ አትክልተኛ አይደለም
የቆመው ጌታሽ ነው ደስ ይበልሽ ማርያም
፡
በመንገድ እያለፍን መንገድ ጠፍቶብን
መንገደኛ ነህ ወይ ብለን ጠየቅን
አሁን ግን አወቅን አሁን አየንህ
ለካስ መንገዳችን አምላካችን ነህ
፡
ሞትን ድል እንዳረክ በሀይል በስልጣንህ
ዳግም ስትመጣ አቁመን በቀኝህ
+++++++++++++
እንኳን አደረሳችሁ
+++++++++++++
አይናችሁ ይገለጥ እጆቹን እዩና
ደሞ ለዛሬ አመት ያድርሰን በደህና
++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በባህር በጠፈር ይሄዳል እንዳሻው
መብራት አይፈልግም ለመመላለሻው
ብርሀን ነው ና ግርማ መለኮቱ
የጨለመን ህይወት ያበራል በሞቱ
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
መብራት አይፈልግም ለመመላለሻው
ብርሀን ነው ና ግርማ መለኮቱ
የጨለመን ህይወት ያበራል በሞቱ
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
አንቺ ስትወለጅ ፥እኛም ተወለድን፣
ገና በልጅነት፥ ቤተ መቅደስ ሄድን።
ማርያም ስትወለጅ፥ ልደታችን ሆነ፣
እንኳንስ ያመነሽ፥ ያላመነሽ ዳነ።
፣
የአምላክ እናቱ፥ ልደታ ማርያም፣
በግንቦት ተወልደሽ፥ ተምሯል አለም።
ልጅሽ ወዳጅሽ፥ ሰላማችን ነው።
የልደትሽ ቀን፥ ልደታችን ነው፣
፥
በሄዋን ቢዘጋ፥ የገነት ድንበሩ፤
ባንቺ ተከፈተ፥ የሰማያት በሩ።
ባንቺ ልደት፥ ቀን ሆነ ልደት፣
አዳምም ገባ፥ ወደ ገነት።
፡
የእናት ክብር ታየ፥ ከፍ ብሎ፣
በድንግል ጀርባ ላይ፥ ፋሲካችን ታዝሎ።
ከሴቶቹ መካከል፥ አንቺን ለይቶሽ፣
አምላክ አንቺን ሰጠን፥ እንድንድንብሽ።
+++++++
ከሴቶች መካከል ብፅይት ነሽና
ደግሞ ለዛሬ አመት አድርሺን በደህና
ግንቦት ልደታ 2013
+++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ገና በልጅነት፥ ቤተ መቅደስ ሄድን።
ማርያም ስትወለጅ፥ ልደታችን ሆነ፣
እንኳንስ ያመነሽ፥ ያላመነሽ ዳነ።
፣
የአምላክ እናቱ፥ ልደታ ማርያም፣
በግንቦት ተወልደሽ፥ ተምሯል አለም።
ልጅሽ ወዳጅሽ፥ ሰላማችን ነው።
የልደትሽ ቀን፥ ልደታችን ነው፣
፥
በሄዋን ቢዘጋ፥ የገነት ድንበሩ፤
ባንቺ ተከፈተ፥ የሰማያት በሩ።
ባንቺ ልደት፥ ቀን ሆነ ልደት፣
አዳምም ገባ፥ ወደ ገነት።
፡
የእናት ክብር ታየ፥ ከፍ ብሎ፣
በድንግል ጀርባ ላይ፥ ፋሲካችን ታዝሎ።
ከሴቶቹ መካከል፥ አንቺን ለይቶሽ፣
አምላክ አንቺን ሰጠን፥ እንድንድንብሽ።
+++++++
ከሴቶች መካከል ብፅይት ነሽና
ደግሞ ለዛሬ አመት አድርሺን በደህና
ግንቦት ልደታ 2013
+++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ዛሬ....
የፀሀይ መውጫ፥ ሰማይ ተዘረጋ፣
ማርያም ስትወለድ፥ ጨለማችን ነጋ።
፣
የህይወት ውሀ፥ ምንጩ ፈለቀች፣
የመድሀኒታችን፥ ሙዳዩ ተገኘች።
፣
የሊባኖስ ህልም፥ ሶልያና፤
ዛሬ ተወለደች፥ ከኢያቄም ከሀና።
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
የፀሀይ መውጫ፥ ሰማይ ተዘረጋ፣
ማርያም ስትወለድ፥ ጨለማችን ነጋ።
፣
የህይወት ውሀ፥ ምንጩ ፈለቀች፣
የመድሀኒታችን፥ ሙዳዩ ተገኘች።
፣
የሊባኖስ ህልም፥ ሶልያና፤
ዛሬ ተወለደች፥ ከኢያቄም ከሀና።
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
እኔ ቶማስ...
ዛሬም ባለማመን፥ እጆቼን አንስቼ፣
ለኔ በቆሰልከው ፥ጣቶቼን ከትቼ።
፡
የፍቅርህን ዋጋ፥ እሳቱን ላልችለው፤
በቆሰልክልኝ ላይ፥ ጣት መክተት ምንድነው።
፡
በደሌን ይቅር በል፥ አለማመኔን፤
ሳይከፈት ግባና፥ ክፈተው ልቤን።
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
ዛሬም ባለማመን፥ እጆቼን አንስቼ፣
ለኔ በቆሰልከው ፥ጣቶቼን ከትቼ።
፡
የፍቅርህን ዋጋ፥ እሳቱን ላልችለው፤
በቆሰልክልኝ ላይ፥ ጣት መክተት ምንድነው።
፡
በደሌን ይቅር በል፥ አለማመኔን፤
ሳይከፈት ግባና፥ ክፈተው ልቤን።
++++++++++++++++++++
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
Forwarded from እልመስጦአግያ+++ (አሜን)
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች በሙሉ ይህንን ፕሮፋይል በማድረግ ከቅዱስ አባታችን ጎን መሆናችንን እናሳይ ጥላቶቻቸውን እናሳፍር።
ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር
ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ሼር
ሐማ ሆይ...
ባቆምከው እንጨት፥ ላይ አንተ ትቆማለክ፤
በቆፈርከው ጉድጓድ፥ ዘለህ ትገባለህ።
ይመስልሀል እንጂ፥ እስከጊዜው ድረስ፣
ፍርድ ቀን አያጣም፥ በራስ እስኪመለስ።
፡
ዛሬ ለመቆምህ፥ አትፎክር አትደንፋ፤
ቅቤ ነው 'ሚሆነው፥ ወተትም ሲገፋ።
የመከራህ ዝናብ፥ አንተ ላይ ይጎርፋል፤
የራስህ ደመና፥ አበስብሶህ ያልፋል።
ቢመስልህም ላንተ፥ ዘመን የማይለወጥ፤
መድረሻ ታጣለህ፥ ነገር ሲገለበጥ።
++++
ኢዮብ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ባቆምከው እንጨት፥ ላይ አንተ ትቆማለክ፤
በቆፈርከው ጉድጓድ፥ ዘለህ ትገባለህ።
ይመስልሀል እንጂ፥ እስከጊዜው ድረስ፣
ፍርድ ቀን አያጣም፥ በራስ እስኪመለስ።
፡
ዛሬ ለመቆምህ፥ አትፎክር አትደንፋ፤
ቅቤ ነው 'ሚሆነው፥ ወተትም ሲገፋ።
የመከራህ ዝናብ፥ አንተ ላይ ይጎርፋል፤
የራስህ ደመና፥ አበስብሶህ ያልፋል።
ቢመስልህም ላንተ፥ ዘመን የማይለወጥ፤
መድረሻ ታጣለህ፥ ነገር ሲገለበጥ።
++++
ኢዮብ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
©ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
"የትዕግስት ጽዋ"
የጦሩን አንደበት፥ የእሳቱን ወላፈን፤
የመጋዙን ስለት፥ የመንኮራኩሩን፤
እንዲያ ፋት እንዳልከው፥ ፍጹም በመታመን፤
እኛም እንድንወደው፥ አንተን ተከትለን፤
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።
፥
ባለቤቱ እንዳለ፥ ይች ጽዋ ትለፍ፤
ብርሐኑን ገልጦ፥ ጨለማን ለመግፈፍ፤
የተጋድሎን ማዕድ፥ ከእርሱ ለመሳተፍ፤
ፍጹም ደስ እንዳለህ፥ ብዙ ስትገረፍ፤
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ፥ አብሬህ ልሰለፍ።
፥
በብረት ሊፈጩሕ፥ ሊወጉህ በካራ፤
ወደ እሳት ሲወስዱሕ፥ ደግሰው መከራ፤
እንደ ሸለሙት ሰው፥ ሠርግ እንደተጠራ፤
ለምን ነው ደስ ያለህ፥ እንኳን ልትፈራ፤
ስለምታይ ነዋ፥ የሰማዩን ጌራ!።
፥
በጦር አልተወጋሁ፥ ስለት አላገኘኝ፤
እሳት አልነደደ፥ ሾተል አልጎሰመኝ፤
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት፥ ትርጉሙ እንዲገባኝ፤
የሰማዩን ምስጢር፥ ለእኔ ሹክ በለኝ።
፥
የመበለቷን አምድ፥ አንተ ስትጠጋው፤
ሥር እንደሰደደ፥ እንዳለመለምከው፤
መሶቡን በኅብስት፥ ቶሎ እንደ መላኸው፤
ደረቁን ሕይወቴን፥ ለፍሬ ክብር አብቃው፤
ቀዝቃዛውን ልቤን፥ ምውቅ ጽዋ ምላው።
+++++
©አባ ገብረኪዳን ግርማ
ምንጭ:- መሠረተ አሚን
ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የጦሩን አንደበት፥ የእሳቱን ወላፈን፤
የመጋዙን ስለት፥ የመንኮራኩሩን፤
እንዲያ ፋት እንዳልከው፥ ፍጹም በመታመን፤
እኛም እንድንወደው፥ አንተን ተከትለን፤
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።
፥
ባለቤቱ እንዳለ፥ ይች ጽዋ ትለፍ፤
ብርሐኑን ገልጦ፥ ጨለማን ለመግፈፍ፤
የተጋድሎን ማዕድ፥ ከእርሱ ለመሳተፍ፤
ፍጹም ደስ እንዳለህ፥ ብዙ ስትገረፍ፤
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ፥ አብሬህ ልሰለፍ።
፥
በብረት ሊፈጩሕ፥ ሊወጉህ በካራ፤
ወደ እሳት ሲወስዱሕ፥ ደግሰው መከራ፤
እንደ ሸለሙት ሰው፥ ሠርግ እንደተጠራ፤
ለምን ነው ደስ ያለህ፥ እንኳን ልትፈራ፤
ስለምታይ ነዋ፥ የሰማዩን ጌራ!።
፥
በጦር አልተወጋሁ፥ ስለት አላገኘኝ፤
እሳት አልነደደ፥ ሾተል አልጎሰመኝ፤
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት፥ ትርጉሙ እንዲገባኝ፤
የሰማዩን ምስጢር፥ ለእኔ ሹክ በለኝ።
፥
የመበለቷን አምድ፥ አንተ ስትጠጋው፤
ሥር እንደሰደደ፥ እንዳለመለምከው፤
መሶቡን በኅብስት፥ ቶሎ እንደ መላኸው፤
ደረቁን ሕይወቴን፥ ለፍሬ ክብር አብቃው፤
ቀዝቃዛውን ልቤን፥ ምውቅ ጽዋ ምላው።
+++++
©አባ ገብረኪዳን ግርማ
ምንጭ:- መሠረተ አሚን
ታዜና ™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
፲፮ ኪዳነ ምህረት ፲፮
ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለአለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምህረት።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ከአምላክ መታረቂያ፥ የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ ለጠላሽ እናት ነሽ።
"ኪዳነምህረት፥ ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ ፍጥረት ሁሉ ዳነ።"
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለአለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምህረት።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ከአምላክ መታረቂያ፥ የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ ለጠላሽ እናት ነሽ።
"ኪዳነምህረት፥ ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ ፍጥረት ሁሉ ዳነ።"
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
፲፮ ኪዳነ ምህረት ፲፮
ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለአለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምህረት።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ከአምላክ መታረቂያ፥ የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ ለጠላሽ እናት ነሽ።
"ኪዳነምህረት፥ ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ ፍጥረት ሁሉ ዳነ።"
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለአለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምህረት።
፲፮ ፲፮ ፲፮
ከአምላክ መታረቂያ፥ የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ ለጠላሽ እናት ነሽ።
"ኪዳነምህረት፥ ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ ፍጥረት ሁሉ ዳነ።"
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
እግዚአብሄር ሆይ...
አንተ ሰላሜ ነህ፥ እርፍ የምልብህ፤
ከዘላለም ጭንቀት፥ የምረጋጋብህ።
አንተ መንገዴ ነህ፥ የጽድቄ መድረሻ፤
የእረፍት ውሀዬ፥ እስከመጨረሻ።
፥
አንተ ህይወቴ ነህ፥ ነፍሴን የፈጠርካት፤
ስጋና ደም ከፍለህ፥ ከሲኦል ያዳንካት።
አንተ እረኛዬ ነህ፥ ጠፍቼ ማተወኝ፤
በለመለመ መስክ፥ የምታሰማራኝ።
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
አንተ ሰላሜ ነህ፥ እርፍ የምልብህ፤
ከዘላለም ጭንቀት፥ የምረጋጋብህ።
አንተ መንገዴ ነህ፥ የጽድቄ መድረሻ፤
የእረፍት ውሀዬ፥ እስከመጨረሻ።
፥
አንተ ህይወቴ ነህ፥ ነፍሴን የፈጠርካት፤
ስጋና ደም ከፍለህ፥ ከሲኦል ያዳንካት።
አንተ እረኛዬ ነህ፥ ጠፍቼ ማተወኝ፤
በለመለመ መስክ፥ የምታሰማራኝ።
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ከብዙ መከራው፥ትንሽ ተስፋው በልጦ፤
የረገመውን ቀን፥አሳየው ለውጦ።
በአምላክ ተመክቶ፥ በፀሎት ቢፀና፤
ህይወትን ሀ ብሎ፥ጀመረ እንደገና።
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የረገመውን ቀን፥አሳየው ለውጦ።
በአምላክ ተመክቶ፥ በፀሎት ቢፀና፤
ህይወትን ሀ ብሎ፥ጀመረ እንደገና።
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ማርያምን ምረጡ
ሚስጥረኛ እናቴ
ብርታት የጉልበቴ
ሳለቅስ አባብላ
የጣለኝን ጥላ
ሳያት ቢገርመኝ
እሷን ወደድኩኝ
ከሁሉ አስበልጬ
ማርያምን መርጬ
ተሳካ ምኞቴ
ረድታኝ እናቴ
በድል እንድትወጡ
ማርያምን ምረጡ+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ሚስጥረኛ እናቴ
ብርታት የጉልበቴ
ሳለቅስ አባብላ
የጣለኝን ጥላ
ሳያት ቢገርመኝ
እሷን ወደድኩኝ
ከሁሉ አስበልጬ
ማርያምን መርጬ
ተሳካ ምኞቴ
ረድታኝ እናቴ
በድል እንድትወጡ
ማርያምን ምረጡ+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch