Telegram Web Link
Forwarded from Tt
እኔ ጥቁር እለብሳለሁ እናተስ?
ማሳሰቢያ!!!!!!!!
የነነዌ ጾም 3ቱን ቀን ከጥር 29 - የካቲት 1 ቀን ጥቁር በመልበስ ጸሎተ ምህላ እና ጸሎተ ኪዳን እያደረስን ለቤተክርስታናችን እና ለአባቶቻችን ድጋፍ እናሳይ!
ለ10 ሰው እናጋራው ለራሳችን ለህሊናችን ስንል!
ዘር መሆኑን ሳያውቅ፥ የክርስቲያን ደም፣
አንዱ ወድቆ ሲሞት፥ እልፍ እንደሚቆም።
ዛሬም ይቸኩላል፥ ሄሮድስ ሊቀላ፣
አላወቀም መሰል ....
አንዱ ሞቶ ሲያድር፥ ሺህ እንደሚፈላ።
አትንኩን ብንልም፥ አንዴ ነካችሁን፣
ለሰማዓትነትን ፥ለድል ሾማችሁን።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
አትፍራ መሞት ነው ፥ከእግዜር የሚያደርሰው፣
የእስጢፋኖስ ዘመድ ፥ነውና ምንሆነው፣
የአርሴማ ዘመድ ነውና ምንሆነው፣
የቂርቆስ ዘመድ ነውና ምንሆነው፣
የሐዋርያት ዘመድ ነውና ምንሆነው።
ዋኖቻችን ሁሉ ፥እንዲህ ነው ያለፉት፣
የክብር አክሊልን፥ በሞት ነው ያገኙት።

እናት ተዋህዶ፣ ዛሬ ትጣራለች፣
እንደ አባቶቻችን ፥ጠብቁኝ ትላለች።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
ልባችሁ አይደንግጥ፥ አይሸበርባችሁ፣
የነገስታት ንጉስ፥ ጌታ እያለላችሁ።
ስጋን የሚገድልን፥ አትፍራ አትስጋ፣
ሰመዓትነት ነው፥ የነፍሳችን ዋጋ።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
ዖዝያን....
በክብር ቢቀባ ፥በአስራ ሶስት አመቱ፤
በዙፋን ቢቀመጥ፥ ፀንቶለት ሹመቱ።
እግዚአብሔር ነገሩን፥ እየከወነለት፣
እልፍ እየማረከ፥ እልፍ ቢያስገዛለት።

በበረታ ጊዜ፥ ለጥፋት ታበየ፤
በመቅደሱ ሊያጥን፥ ጽና ይዞ ታየ።
ካህኑ የአሮን ልጅ፥ ዓዛርያስ ሳለ፤
ንግስናውን ትቶ፥ ንጉስ ልጠን አለ።

የእግዚአብሄር ፍርድ፥አይለወጥምና ፤
ተመለስ ንጉስ ሆይ፥ በዙፋንህ ጽና፤
ጽና ይዞ ማጠን፥ ያንተ አይደለምና፤
ቢለው አልሰማ አለ፥ ካህኑን ናቀና።

የትዕቢቱ መጠን፥ ዙፋኑን ነቀነቆ፤
ለየው ከንግስና፥ ካባውን አውልቆ።
ያደረገለትን ሀይል፥ ክብሩን ዘንግቶ፤
ንጉስ ልጠን አለ፥ ቤተመቅደስ ገብቶ።

እግዚአብሄር ቀሰፈው፣ ለምጽን አተመበት፤
በቤተ መንግስቱ፥ ልጁ ነገሰበት።
የማይነካ ነክቶ፥ንግስናው ተሻረ፤
ከአባቶቹ ርቆ፥ በእርሻ ተቀበረ።

ዛሬም ዖዝያን ሆይ!
በበረታህ ጊዜ፥ ጌታህን አትርሳ፤
እርሱ ነው የሚሰጥ፥ እርሱ ነው ሚነሳ።
ካህኑን አትንካ፥ የጌታን አገልጋይ፤
ቁልፍ አለና በእጁ፥ የመንግስተ ሰማይ።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
+++++
ሰማይ ስማ፥ ምድር አድምጪ፤
ቀን ወጣልኝ ብለሽ፥ ከሕጉ እንዳትወጪ።
በበደል ላይ በደል፥ እየጨመራችሁ፤
ዖዝያኖች ዛሬም፥ ትቀሰፋላችሁ።
++++++
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
!
ጠብቅ...!
!
ተዋህዶ እምነትህን፣
ቤተክርስቲያንህን፣
የአርባ ቀን ቤትህን፣
አንዲት ስስትህን፣
የደም ስርህን፣
እናት አለምህን፣
ስም የሰጠችህን፣
ልጅ ያረገችህን።
!
ጠብቅ...!
!
አባት ካህንህን፣
የሚባርክህን፣
የሚናዝዝህን፣
ይፍታህ የሚልህን፣
ግርማ ሞገስህን፣
የሲኖዶስህን፣
የፓትሪያርክህን፣
ዶግማ ቀኖናህን፣
እምነት ማተብህን።
!
ጠብቅ...!
! አታስነጥቅ።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
++++++
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።

አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።

ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።

አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++
@Menfesawigetmoch
©ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)
አለምን የሰራ ሲሆን፥
ከእኛ እንዳንዱ ቢሆን።
እንደ በደለኛ ቆጥረነው፥
በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀልነው።
++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
Forwarded from Tazena /ታዜና/
"መንገዴ ነህ"
ተስፋዬ አደረኩህ፥ ሞተህ ስላኖርከኝ፤
በራሴ ላይ ሾምኩህ፥ አዳኝ ስለሆንከኝ።
መሄጃዬ አንተ፥ መደምደሚያ ሆንከኝ፤
ህይወትህን ሰተህ፥ ሞትን አሻገርከኝ።

በመንገዶች ላይ፥ እንቅፋት ኖሮበት፤
ወድቄ እንድቀር፥ጠጠር ዘርተውበት።
እንድመለስ ሽቶ፥ ሆኖ ሁሉ ከንቱ፤
እኔን መጣል ነበር፥ ጠላቴ ምኞቱ ።

በመንገዶችቼ ላይ ፥ አቋራጭ ቢኖርም፤
እኔ አንተን አለቅም፥ እኔ ያላንተ አልኖርም።
አውቀዋለሁ፥ ለኔ አይጠቅምም፤
ትግስቴ እስኪያልቅ፥ ብፈተንም።
አምናለው በእግዚአብሔር፥ አልፋለው ሁሉንም።

ተነሽ በርቺ ፥አይዞሽ ልጄ፤
እኔ ይዤሻለው፥ በበረከት እጄ።
ይለኛል ዘወትር፥ ጠላት እንዳልፈራ፤
አይበቅልም ከርሻዬ ፥እንክርዳድ ቢዘራ፤
እግዚአብሔር አለ፥ የሰማዩ ጌታ፤
ስወድቅ የሚያነሳ፥ ልቤን ያበረታ።
የረታኝን ጠላት፥ በመስቀል የረታ፤
ህይወቴን ፈጠረ፥ በትንፋሹ እፍታ

መንገዴን ጠራጊ፥ የአባቶቼ አምላክ፤
በፈተና እንዳልወድቅ፥ እኔን የጠበክ።
ለአንተ ለዘላለም፥ ይንበርከክ ጉልበቴ፤
አንተን ብቻ እናምልክ፥ እኔና ያ ቤቴ።

ሰቶኝ የማይቀማ፥ታማኝ አምላክ አለኝ፤
ጥሎኝ የማይተኛ፥ጠባቂ ጌታ አለኝ።
ታድያ በዚህ አለም፥ እኔ ምን ጎድሎኛል?
በእርሱ ህያው መንገድ፥ ሁሌም ያኖረኛል።

አሜን ክብር ይሁን፥ መንገዴን ላፀዳ፤
አሜን ምስጋና ይሁን፥ ልጁን ለሚረዳ።
አሜን አምልኮ ይሁን፥ ህይወቴን ለሰራ፤
በልቦናዬ እርሻ፥ የማያልቅ ፍቅሩን ሳይሰስት ለዘራ።
ምስጋና ይድረሰው፥ ክብር ይግባው ጌታዬ፤
መንገዴ ህይወቴ፥ ባለውለታዬ።
+++++++
©ምህረት/Mihert/
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
"ድህነት' ነሽ"
የለብን አበሳ፥ የለብን መርገም፤
ቀድሶናልና፥ የክርስቶስ ደም።
አንቺ የኖህ ርግብ፥ አማን በአማን፤
የጥፋቱ ውሀ፥ ጎደለ አሜን፤
አንቺ የዘርዓ ያዕቆብ፥ የዳዊት ሙሽራ፤
ከደረትሽ ያለው፥ መስቀልሽ አበራ።

ባንቺ በናታችን፥ በእመቤታችን፤
ህፃኑ ተሰጠን፥ ዳንን ሁላችን፤
አዳም የተከለው፥ የዘራው ጸደቀ፤
መሬትሽ ነውና፥ በጣም የታወቀ።

የድህነት' አዝመራ፥ ካንቺ እንለቅማለን፤
በመዳኛ ልጅሽ፥ በእርሱ እንድናለን፤
ከእንግዲህ ህመማችን፥ ጭንቃችን አይጥና፤
ክርስቶስ በደሙ፥ ቀድሶናልና።
ድልድዩ ይሰራ ጠማማውም ይቅና።

ተለያይቶ መኖር፥ አጉድሎናልና፥ በድሎናልና።
ጠማማውን መንገድ የቀና አድርገን፤
ጋራ ሸንተረሩን አስተካክለን ፥ሰርተን፤
ሀይማኖት ከምግባር፥ አስተባብረን ይዘን፤
ከድንግል ማርያም ጋር፥ አብረናት ተጉዘን፤
መላ አካላችንን፥ ከሐጥያት አንፅተን፤
የድህነት' ሰብል፥ እንሰብስብ በርትተን።
++++++
ድህነት' ላልቶ ይነበብ/መዳን፣መፈወስ/
©ምህረት/Mihert/
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
+ሰኔ ሚካኤል+
አምና የዛሬ አመት ፥ያልጠከረ ልጅ ፥ታቅፌ በእጆቼ፤
ከቤትህ ባቀና ፥አንተን ልሳለምህ ፥ከደጅህ መጥቼ።
እግሮቼ ሳያውቁ ቢሰነካከሉ ጉድጓድ ቢቀናቸው፤
እንዳይሰበሩ መራመጃ ምንጣፍ፥ ሚካኤል ሆንካቸው።
የተከፈተውን የገባሁበትን ጉድጓድ ዘጋህና፤
ከቤቴ መለስከኝ ንግስህን አንግሼ፥ ገባሁኝ በደህና፤
ባህራን አደገ፥ ዳግም ጠነከረ፤
ሚካኤል ከጉድጓድ፥ ጠብቆን ነበረ፤
ያንተ የኔ ጌታ ይጠብቅ ነበረ፥ ያፀድቅ ነበረ፤
ያንተ አምላክ፥ እግዚአብሄር ያሳድግ ነበረ።
በበጎ እንዳስብህ፥ ዛሬን በትዝታ፤
መላኩ ሚካኤል ፥አለብኝ ውለታ።
አንተ ዘጋህልኝ፥ ጫፌ ሳይነካ፤
ምስጋናዬን ውሰድ፥ መባዬንም እንካ።
የማትረሳ መላክ፥ ጠባቂ ነህና፤
አረሳህም እኔ፥ አልረሳህምና፤
የተከፈተውን፥ ጉድጓድ ዘጋህና፤
አመቱ ሲደርስ አሰብኩህ በደህና።
አልረሳም አንተን፥ በሰኔ በሰኔ፤
ሚካኤል ወዳጄ፥ ምርኩዜ ነህ ለኔ።
++++
"በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ"
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች:
+  በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +

ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ
መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!

ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል::

  "በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28

አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::
ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?

ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?

" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)

"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1ነገሥ. 19:4

ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ 4:3)

ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::

ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም::  "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: 1ኛ ቆሮ. 10:13

ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::

"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው::  የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::

ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው:: ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::

አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም::

ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል::

ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"

የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?

ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም::  "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል

ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው::  አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1ኛ ቆሮ. 3:17

ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?

"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም:: ፈጥነውም ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ቁጥር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም:: 

እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-

ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::

ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል:: እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::

"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም:: ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32

የይሁዳ ኃጢአቱ  ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::

ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም:: በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"

"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28

ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው::

ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ?  የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም?  ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::

ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::

ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::

ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-

"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
አለም ልቡ ታሞ …
አለም ልቡ ታሞ መድኒት ሲጠፋ
ጤነኛ ሊያደርገው ክርስቶስ ተገፋ
ይሄ ፍፃሜው የፍቅር ሁሉ ሚስጥር
ገነትን መክፈቱ ተግቶ መቃብር
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
-እንመለስ-
'
ወዴት ናችሁ ቢለን፥
ጌታ ቢጠይቀን?
መልሳችን ምንድንው፥
ወዴት ነው ምንለው፤
የጸጋ ልብሳችን፥ ከላያችን ወልቋል፤
እውነት፥ ህይወት፥ መንገድ፥ ዛሬ ከኛ ርቋል።

እንመለስ ወደ እውነት ፥ሀሰት ቅጥፈትን እናርቀው፤
እንመለስ ወደ ህይወት ፥የሞትን ሀይል እናድቅቀው፤
እንመለስ ወደ መንገድ፥ጎዳናውን እንልቀቀው፤ 
እንመለስ ወደ እግዚአብሄር፥ ይመጣል እንጠብቀው።
++++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
መርቆርዮስ/ፒሉፓዴር/

ፒሉፓዴር ና መርቆርዮስ፣
ከበሮ ስንመታ ድረስ በፈረስ 
መርቆርዮስ የአብ ወዳጅ ነህ
ሰማዕት ሆነሀል ጣዖትን ሰብረህ

በብረት አልጋ በቆዳ ጅራፍ፤
ደምህ ቢነጥብ ጀርባህ ሲገረፍ።
የነደደ እሳት አንተን ሊያጠፋ፤
የሚጠብሱበት በደምህ ጠፋ።

የአብ ወዳጁ ሙያህ ወታደር፤
ለአምላክህ ፍቅር የሌለህ ወደር።
ስልጣኑ ክብሩ ይቅርብኝ ብለህ፤
ተቀላህ በሰይፍ ትጥቅህን ፈተህ፥

የንጉስ ክብር ርስቱ ጉልቱ፤
ሳያታልልክ ክብር ሹመቱ።
አልሰግድም አልከው ዳኬዎስን፤
በደም ታመንከው አምላክህን።

ውጊያ ቢሰለፍ ጠላት ሰይፍ መዞ፤
ድል አደረገ አምላኩን ይዞ።
የተዋጋውን ድል አድርጎታል፤
ገጸ ከለባት ታዘውለታል።

ስዕልህ ይዝለል ከበሮ እንምታ፤
በፈተና አጽናው ወጣት ይበርታ።
መርቆርዮስ ሆይ በፈረስ ናና፤
ወጣቱን ጠብቅ ወጣት ነህና።
++++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
https://youtu.be/4s9LW4mhUqQ?si=RcFPwkJzBXfUPI1x
(መምህር ኢዮብ ይመኑ)
-እጠብቅሀለሁ-
እጠብቅሀለሁ በመጠቂያዬ፤
ትመጣለህና ሳትረሳ ጌታዬ።
ቀናት ቢያሰለቹ፥ ቢቆጠር ዘመናት፤
አምንሀለሁ ነፍሴን፥ እንደማትተዋት።
በምንም በየትም። በሁሉም ሁኔታ፤ 
እጠብቅሀለሁ፥ በእድሜ ጀምበር ማታ።

አማርሬህ፥ አኩርፌህም፥ አምቼህም፥ እኔ አውቃለሁ፤
ትግስትህን ሳልታገስ፥ ብዙ ነገር ብዬሀለሁ፤
ለዘመኔ እሾህ ሆኜ፥ ከቤትህም ጠፍቻለሁ፤
አትድረስብኝ አልደርስም፥ ብዬ በስምህ ምዬ አውቃለሁ።
ማታ እግሮቼን አጥበህ፥ በትህትና ለመከርከኝ፤
አላውቀውም፥ ማነው እሱ፥ ብዬ ባፌ መሰከርኩኝ።
ስታበራ ብቻ ሳይሆን፥ ጌቴሴማኒ ፀዳል ስትሆን፤
ቀያፋም ቤት መጥቻለሁ፥ ስትገረፍ ጅራፍ ልሆን።

ለካ እኔ ፈጠንኩ እንጂ፥ አንተ እኮ አልዘገየህም፤
በሰዓትህ ትመጣለህ፥ ቆየህ ምነው? አልልህም። 
እንደ ዕንባቆም እጮሀለሁ፥ አምላኬ ሆይ እልሀለሁ፤
ስትሰጠኝ ብቻ ሳይሆን፥ ብትከለክለኝም እጠብቅሀለሁ።
ፀጋህን ውሰድልኝ፥ እኔ አንተን ከማጣህ፤
እንደዘኪዎስ ዛፍ ላይ ልውጣ፥ ቤቴ ግባ አይቼህ።
በዝምታ ልቤን ክፈት፥ ግባ ማነው? ሳልልህ፤
አንተ ብቻ ናልኝ እንጂ፥ ከቤቴ ጋር ላምልክህ።


ደሞ እንዲህም ብዬሀለሁ፥ መቼ ጠይቄው መች መለሰ፤
ምነው ልቦናን ነሳኝ፥ እኔን ከሰው አሳነሰ።
ለምንድነው ያዋረደኝ፥ ዝም የሚለው እንዲህ ስሆን፤
ለካ አንተ የምትመጣው፥ እንደ አልዓዛር አፈር ስሆን፤
ለካ ህመም አይደለም፥ ሞትም አይደል የሚያቆምህ፤
በአራት ቀኔ ሳትፀየፍ፥ መቃብሬን ትከፍታለህ።
ለካ መሽቶም ትመጣለህ፥ እድሜ ዘመን አይገታህም፤
የጠበቀህ እርፍ ይላል፥ ላንተ ምንም አይሳንህም።
:
እንደ ዮሴፍ ብጠላ፥ በወንድሞቼ ብከዳ፤
በሰላሳ ዲናር ብሸጥ፥ ብንከራተት ምድረበዳ።
የአባቴ አይንም ቢፈስ፥ ቢናፍቀው የልጅ መልኬን፤ 
የሀሰት ፍርድ ቢፈርዱብኝ፥ ብወረወር እድሜ ልኬን።
ፍርድ አጣመው ቢያንገላቱ፥ ፍርዱም ቢሆን እድሜ ይፍታ፤
ማንም ዳግም አያስረኝም፥ አንተ መተህ ስትፈታ።
አንተ ምን ይሳንሀል፥ በወህኒው በኩል በር አለህ።
በጲጢፋራ መንበር፥ ልታነግሰኝ ትመጣለህ

ታማኝ ነህ  ለጠበቀህ፥ ማህጸንን ትፈታለህ፤
ሲስቁብኝ ልትባርከኝ፥ በመቅደስህ ትመጣለህ።
መካን ብባል የተጣለች፥ ስሜም እንኳ በቅሎ ቢሆን፤
መቶ ፍሬ ይገኝብኝ፥ አብዛኝና ለዘር ልሁን።
የሀናን ለቅሶ የሰማህ፥ የኤልሳቤትን እንባ ያበስክ፤
ልጅ የጠየቀችህን፥ በልጆች የምትባርክ፤
ዛሬ አለሁ ያንተ ሀና፥ ዛሬም አለሁ ያንተ ኤልሳቤት፤
እንደ ዮሀንስ ባርከህ ስጠኝ፥ ባንተ ጊዜ በለኝ አቤት።
:
መሮኛል ስልህ ወደላይ፥ የበታቼን ሳላየው፤ 
አንተ ባልቆረጥከው ቀን፥ የራሴን ሞት የተመኘው።
ምነው መታገስ ከበደኝ፥ ነገን ዛሬ ደመደምኩት፤
ምነው ተስፋ ቆረጥኩ፥ ዛሬን አሁን ቀበርኩት።
እንደ ሙሴ በእድሜ ማታ፥ ከከንዓን ሩቅ ብሆን፤
የልፋቴን ሳልቀበል፥ ዕጣ ፈንታ ሞትን ቢሆን፤
በታቦርም ትመጣለህ፥ ቃልኪዳንህ አይታጠፍም
ካንተ ይሰጠዋል እንጂ፥ ሰው በራሱ አያተርፍም
:
ከእሳት በፊት ትደርሳለህ፤
ወይስ ነዶ ትመጣለህ፤
ስወገር ትደርሳለህ፤
ወይስ ፍርዱን ትሽራለህ፤
ስትታመም ትመጣለህ፤
ወይስ ስሞት ታስነሳለህ።
መች ነው? አልልህም፥
አልነዘንዝህም።
አልወተውትህም እታገስሀለሁ፤
በሁሉም ሁኔታ እጠብቅሀለሁ።
++++
የተናቀን የተረሳን፥ አንተ ስታስታውሰው፤
የጠሉኝ ቢሰበሰቡ፥ ቢሉኝ እንዳንተ እናንግሰው።
ቋጠሮዬን ስትፈታ፥ ከቀበሮ ደስታ ጠብቀኝ፤
ጽድቅህን እኔ እሻለሁ፥ መንግስትን አትንፈገኝ።
+++
( መምህር ኢዮብ ይመኑ)
ግጥም ደራሲ©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ስጋዬንም ለእሳት፥ አሳልፌ ብሰጥ፤
ትራራን ለማፍለስ፥ ለብርታት ብመረጥ።
በሰው በመላእክት፥ ልሳን ብናገር፤
ትንቢትም ቢኖረኝ፥ ብፈታ ሚስጥር፤
ፍቅር ከሌለኝ ግን፥ ከንቱ ነኝ እላለሁ፤
እንደሚጮህ ነሀስ፥ ጽናጽል ሆኛለሁ።
'
ፍቅር ይታገሳል፥ በደልን አይቆጥርም፤
ፍቅር አይመካም፥ ፍቅር አይታበይም፤
ፍቅር አይቀናም፥  ፍቅር አይበሳጭም፤
ምላሽንም ሆነ፥ ምክንያት አይፈልግም።

እምነት!
ተስፋ!
ፍቅር!
ሶስቱ ይፀናሉ!
++++++
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ማእበል ማእበልን ጠራ፤
ዮርዳኖስ ለኤርትራ  ታምሩን አወራ።
በበትር ሲከፍል ዉሀ ሲደረደር፥
የሰራህ ሲጠመቅ ምን ይሰማህ ነበር።
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
2025/06/29 03:56:33
Back to Top
HTML Embed Code: