Telegram Web Link
ውበት ነው ዘመን ውበት እርጅና፤
ታኖረኛለህ በፀጋህ ገና።
የፊቴ መስመር የእድሜዬ ልኩ፤
የአይኔ ውሀዎች  አንተን ይስበኩ።
አንተን የያዙ ባንተ ይመኩ፥
ቆቤ ሽበቴ አንተን ይስበኩ።
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
‹‹በዓታ ለማርያም››
በተወለደች፣ በሶስት አመቷ፤
መቅደስ አመጧት፣ እናት አባቷ፡
ለዘካርያስ፣ ቀን አሳይቶ፤
በሰላም ሄደ፥ማዳኑን አይቶ፡፡

ማን ይመግባት፣  ብሎ ሲጨነቅ፤
ወላዲተ አምላክ፣ መሆኗን ሳያውቅ፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል፣ ክንፉ ዘርግቶ፤
ይመግባታል ፣ ከሰማይ መቶ፡፡

ሙሽራዬ ሆይ፤
ከሊባኖስ ነይ፡፡
ልጄ ስሚኝ ይላል፣ አባትሽ ዳዊት፤
የልዑል ማደርያው፣ ስትሆኚ ታይቶት፡፡

በዓታ ለማርያም፤
ስጪን ፍቅር ሰላም፤
<<ኢያቄም ወሀና፥ ወለዱ ሰማይ፤
ሰማያቸው ደግሞ፥ አወጣች ፀሀይ።>>


+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በተራራ ላይ ነው፥ የተሰራው ቤቱ፤
ክብራቸው ያበራል፥ ፃድቃን ሰማእታቱ።
በመጋዝ በድንጋይ፥ በሰይፍ ቢቀሏቸው
በብዙ መከራ፥ ያበራል ፅድቃቸው
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የጻድቃንን ነገር፥ ፈጽሞ አታቃሉ፤
የእግዚአብሄር አይኖች፥ እነርሱን ያያሉ፤
ጆሮዎቹ ዘወትር፥ ጩኸት ይሰማሉ፤
አማልዱኝ ላላቸው፥ ማራቸው ይላሉ።
++++
የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን፣ ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው።
መዝ33÷15
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
አለን ብዙ ቅኔ አለን ብዙ ዜማ
ለጅሩ ለይርጋለም ለስሪንቃ አርሴማ
ደጇን የረገጠ ረድታው  ሰማዕቷ
ተፈውሶ ሄደ በፀበል በእምነቷ
+++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በቅዱስ ስጋው በክቡር ደሙ
በመስቀሉ ሞት ድኗል አለሙ
ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ርስታችንን ሰጠን መልሶ
+++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ይሁዳ ቢፀፀት፥ ምንም አላመጣ፤
በዛፍ ላይ መንጠልጠል ሆነ እንጂ የሱ እጣ
መንግስቱን ለመውረስ የማይፈልግ የለም
መቁረጥ ነው ንስሀ መጸጸት አይደለም:: +++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ምርጫ እየጠፋበት፥ ልብሽ ያመነታል፤
ምን እንደሚፈልግ፥ አይምሮሽ ጨንቆታል።
የልብሽን ስሚ፥ አትሂጅ በሰው ግፊት፤
ምረጥልኝ በይው፥ ከመምረጥሽ በፊት። +++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ልጄ ሆይ
ፀሀይን በእንቅብ አሙቀኝ
ውሀ በወንፊት አምጣልኝ
ቢል ቢጠይቅ አባትህ
እሺ በለው ከልብህ
++++
ልጄ በርጅናው ጊዜ አባትህን እርዳው በጉልበትም ሳለ አታሳዝነው።
ሲራክ ፫፥፲፪
+++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
+++በበረዶ ሌሊት+++
ካንተ በፊት ያሉት፥ የኖርኳቸው ቀናት፤
ያለፉት ለሊቶች፥ ወራትና አመታት።   
መለሼ ካንተ ጋር፥ ዛሬ ብኖራቸው፤
ያለፉትን ሁሉ፥ አብሬህ ባልፋቸው።   
መልሰው ቢመጡ፥ ቢያሳዝኑኝ እንኳን፥
ምንም አያስፈሩኝ፥ ዛሬ ባንተ ድንኳን።

ከፍቶኝ ባለቅስ፥ እንኳን ታባለኛለህ፤
ብቻዬን ስተክዝ፥ አለሁ ትለኛለህ።      
በበረዶ ሌሊት፥ ብቻዬን ስሰበር፤              
ክረምትን በበጋ ፥ትለውጠው ነበር።

ያለፈውን ሁሉ፥ ያላንተ ሳስበው፤
ይታየኛል ልቤን፥ ሰው ብቻ ሲርበው።
ተመስገን የተስፋዬ፥ ጽልመት ነጋ፤
ማያልፍ ሚመስለው፥ አለፈ ካንተጋ።
አንተ ማለት ለኔ...፤
ብርሀኔ ነህ ለዘመኔ...።
+++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
+++እንኳን አደረሰን+++
ዱራ ሜዳ አድምጭ፥ ንጉስ ሆይ ስማ፤
መለከት ቢጮህ፥ አዋጅ ቢሰማ።
እንኳን አድኖን፥ ባያድንንም፣
አንተ ላቆምከው፥ ምስል አንሰግድም።

ፍሙ እየጋለ ፥እጥፍ ቢነድ፤
ገብርኤል መጣ፥ እሳት ሊያበርድ።
እንደ ንጉስ፥ ልጅ ተመላለሱ፤
እሳቱን ውሀ፥ አርጎት ቅዱሱ።

ሰልስቱ ደቂቅ፥ ሞትን ሳፈሩ፤
ነበልባል መሀል፥ በእምነት ዘመሩ።
ለአምላካቸው እጅ እየነሱ፤
በእሳት መካከል ተመላለሱ።

አንዷን ቤታችንን፥ ሊያቃጥል ሊያነዳት፤
ሀገር እንዳልሰራች፥ ጠላት ተነሳባት።
የእሳቱን ነበልባል፥ አብርደው መላኩ፤
በቁጣህ ተመለስ፥ ተዋህዶን ለነኩ።

አመቱን በሰላም፥ እንዳስጀመርከን፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ ሰላም አድርሰን፤
+++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ቸርነቱን ደጅ እንጥና፤
እግዚአብሄር መሀሪ ነውና።
በመከራ እንዳትወድቁ፤
ፍጹም ከርሱ አትራቁ።
+++
©ታዜና @Tazena291
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
"ምን እላለሁ፤
ምን እናገራለሁ፤
የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው።
የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"*

አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥
ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ።
ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት፤
ምን አይነት ፍቅር ነው፥ ምን አይነት ደግነት።

በናቱ እቅፍ ሆኖ፥ በሰማያት አለ፤
በሰማያት ሆኖ፥ በናቱ እቅፍ አለ።
ከኪሩቤል ጀርባ፥ ሳይወርድ ከዙፋኑ፤
ይገርማል ይደንቃል፥ በኛ መመስገኑ።

ቅድመ አለም ያለ እናት ተወልዶ ከአባቱ
ድህረ አለም ያላአባት  ወለደች እናቱ
ይህን ድንቅ ጥበብ፥ ፍጥረቱ ተማክሮ፤
ድንቅ ይባላል እንጂ፥ ማን ያውቃል መርምሮ።

ነብያት የናፈቁት፥ ትንቢታቸው መጣ ፤
ከድንግል ማህፀን፥ ያለድካም ወጣ፤
መለኮት ሳይከፈል፥ ወደ አለም መጣ፤
የጽድቃችን ጸሀይ፥ ከሰማያት ወጣ።
++++++
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

*("ምን እላለሁ ምን እናገራለሁ..."
ሐይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ)
©ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
+++ሄኖክ መምህሬ+++
በል እስኪ ንገረኝ፥ እንዴት ነው ነገሩ፤
አእላፋት ጠርተህ፥ መዝሙር የዘመሩ።
ምን አይነት ፀጋ ነው፥ ምን አይነት መጠራት፤
ይህንን ሁሉ ህዝብ፥ ለዝማሬ መጥራት።
:
 ጃንደረባ ትውልድ፥ ምን ስትል አሰብከው፤
የባለ ልደቱን፥ ልደት አስከበርከው።
ደግሞ ሌላ አዘጋጅ፥ ገስግሼ እመጣለሁ።
ደግሰህ ስትጠራኝ፥ እንዴት እቀራለሁ።
:
ለትውልድ ትረፍ፥ ፀጋህን ያብዛልህ፤
የአባቶችህ አምላክ፥በሞገስ ያኑርህ።
ያከበርከው ልጇ፥ አንተንም ያክብርህ፤
ሄኖክ መምህሬ፥ ላንተስ እድሜ ይስጥህ።
+++
©ታዜና 
       #መንፈሳዊ_ግጥሞች 
      www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
#መንፈሳዊ_ግጥሞች #MenfesawiGetmoch

——ቅዱስ እስጢፋኖስ ——
ድንጋይ እንደ ዝናብ፣ ሲወርድ የታገሰ፤
ሲወግሩት ይቅር፣ በል እያለ መለሰ፡፡
ስጋውን ለመግደል፣ እጅጉን ቢለፉ፤
ቀዳሜ ሰማዕት፣ አርገውት አረፉ፡፡
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
ክብር ነው አንተን መፍራት፤
ስምህ የደስታ ዘውድ ናት።
አንተን ትቶህ ያላለፈ፥
ብዙ ዘመን አተረፈ።
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
2025/06/28 20:43:34
Back to Top
HTML Embed Code: