አሁን....
ሀጢያት እና ነውሬን፥ በበደል ከብቤው፤
ይህ ቀን እስከሚደርስ፥ አላውቅም አስቤው።
ዘመኔ ተሰፍሮ፥ ጊዜ እየቀነሰ፤
የሀጢያቴ ደሞዝ ፥ሞት ደጄ ደረሰ።
++++++
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
ሀጢያት እና ነውሬን፥ በበደል ከብቤው፤
ይህ ቀን እስከሚደርስ፥ አላውቅም አስቤው።
ዘመኔ ተሰፍሮ፥ ጊዜ እየቀነሰ፤
የሀጢያቴ ደሞዝ ፥ሞት ደጄ ደረሰ።
++++++
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
እንኳን አደረሳችሁ
——ተነስቷል——
መቅደላዊት ማርያም፥ ለምን ታለቅሻለሽ፤
ህያውን ከሙታን፥ ስለምን ትሻለሽ፤
ጌታ አልተወሰደም፥ ቆሟል ከጀርባሽ፤
ረቡኒ በይው፥ ማርያም አታልቅሽ።
መግነዙ ተፈቷል ፥የተልባ እግር ልብሱ፤
እንደተናገረ፥ ተነስቷል ንጉሱ።
፡
መስቀል ላይ ውለሀል፥ ልትሆነን ቤዛ፤
በስጋ በደምህ፥ አለምን ልትገዛ፤
በኤፍራታ ሰምተን፥ በዱር አገኘንህ፤
ፍቅርህን ጠገብን፥ በላንህ ጠጣንህ።
ከነፍስና ስጋው፥ ህዝቡን ያስበለጠ፤
የትኛው ንጉስ ነው፤ ስጋ ደም የሰጠ።
አንተ ትለያለህ፥ አለብን ውለታ፤
ትንሳኤው ንጉስ፥ የትንሳኤው ጌታ።
፡
ድንጋይ ተንከባሎ፥ መቃብር ተከፍቷል፤
ሲዖል ተበርብሮ ፥ሞት በሞት ተረቷል።
መቅደሱን በሶስት ቀን፥ አፍርሶ ሰርቶታል፤
ከሙታን መካከል ፥አልቀረም ተነስቷል።
++++++++++++++++++++++++
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን
ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።”
— ሉቃስ 24፥5
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
——ተነስቷል——
መቅደላዊት ማርያም፥ ለምን ታለቅሻለሽ፤
ህያውን ከሙታን፥ ስለምን ትሻለሽ፤
ጌታ አልተወሰደም፥ ቆሟል ከጀርባሽ፤
ረቡኒ በይው፥ ማርያም አታልቅሽ።
መግነዙ ተፈቷል ፥የተልባ እግር ልብሱ፤
እንደተናገረ፥ ተነስቷል ንጉሱ።
፡
መስቀል ላይ ውለሀል፥ ልትሆነን ቤዛ፤
በስጋ በደምህ፥ አለምን ልትገዛ፤
በኤፍራታ ሰምተን፥ በዱር አገኘንህ፤
ፍቅርህን ጠገብን፥ በላንህ ጠጣንህ።
ከነፍስና ስጋው፥ ህዝቡን ያስበለጠ፤
የትኛው ንጉስ ነው፤ ስጋ ደም የሰጠ።
አንተ ትለያለህ፥ አለብን ውለታ፤
ትንሳኤው ንጉስ፥ የትንሳኤው ጌታ።
፡
ድንጋይ ተንከባሎ፥ መቃብር ተከፍቷል፤
ሲዖል ተበርብሮ ፥ሞት በሞት ተረቷል።
መቅደሱን በሶስት ቀን፥ አፍርሶ ሰርቶታል፤
ከሙታን መካከል ፥አልቀረም ተነስቷል።
++++++++++++++++++++++++
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን
ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።”
— ሉቃስ 24፥5
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
--አቤቱ--
------------
ደግ ሰው አለቀ፤
ሁሉ ክንድህ ስር ወደቀ።
ልጆችህ ተጨንቀናል፤
ከእግርህ በታች ወድቀናል።
እምነታችን አልፀና፤
ማእበል በረታና።
አለም መአት ወረደባት፤
መርከባችንን ምጥ ያዛት።
አቤቱ....
በደቃቃ ደዌ፥ ትውልድ ረገፈ፤
አንም አልተገኘ ፥መከራን ያለፈ።
ጌታ ካላቆምከው፥ በቃችሁ ካላልከን፤
በሰማይ በምድር፥ ረዳት ማን አለን።
የቤትህ ግርግዳ፥ በሳት የተሰራ፤
ይበቃሻል በላት፥ ያለምን መከራ።
መፍረስ የሌለብህ፥ የመድሀኒት ደጃፍ።
አንተ ትችላለህ፥ መከራን ማሳለፍ፤
እማማ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ቅድስት ሀገር፤
እናቴ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ታላቅ ሀገር።
በዘመናት ችግር፥ ትከሻዋ ጎብጧል፤
በሸክሟ ጽናት፥ ጀርባዋ ተልጧል፤
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች።
ቀና ካላረካት፥ ጎብጣ ትቀራለች፤
አትችልም ሀገሬ፥ መከራ በቅቷታል።
ችግር በየአይነቱ፥
ጦርነት ባይነቱ፥ ተፈራርቆባታል።
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች፤
ይበቃል ካላልካት፥ ጎብጣ ትቀራለች።
አንድ ጻድቅ ጠፍቶ፥ ከቶም በምድሪቱ፤
ከፈርኦን መከራ፥ ጨከነ መአቱ።
ቸነፈር ፀናብን፥ ቀባሪ እስኪጠፋ፤
ዋኔ ዋኔ ሆኗል፥ የእንባችን ተስፋ።
ክንድህን የቻለ፥ የምድር ሀይል የለም፤
ሀያል ነህ ዘላለም ጌታ መድሀኔአለም።
አንድም ሶስትም ፥ሆነህ አለምን የገዛህ፤
ዛሬም ለዘላለም፥ የምትኖር አንተ ነህ።
የመጻጉን አልጋ፥ በራሱ ያሸከምክ፤
የጣቢታን ትንፋሽ፥ በቃልህ የመለስክ።
በልብሶችህ ቁጨት፥ የደም ምንጭ ያደረክ፤
በምራቅህ ስለህ አይን፥ የፈጠርክ አምላክ።
ታምራትህ ብዙ፥ ፍቅርህ ለዘላለም፤
ምረትህን ስጠን፥ ጌታ መድሀኔ አለም።
++++++++++++++++++++
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
------------
ደግ ሰው አለቀ፤
ሁሉ ክንድህ ስር ወደቀ።
ልጆችህ ተጨንቀናል፤
ከእግርህ በታች ወድቀናል።
እምነታችን አልፀና፤
ማእበል በረታና።
አለም መአት ወረደባት፤
መርከባችንን ምጥ ያዛት።
አቤቱ....
በደቃቃ ደዌ፥ ትውልድ ረገፈ፤
አንም አልተገኘ ፥መከራን ያለፈ።
ጌታ ካላቆምከው፥ በቃችሁ ካላልከን፤
በሰማይ በምድር፥ ረዳት ማን አለን።
የቤትህ ግርግዳ፥ በሳት የተሰራ፤
ይበቃሻል በላት፥ ያለምን መከራ።
መፍረስ የሌለብህ፥ የመድሀኒት ደጃፍ።
አንተ ትችላለህ፥ መከራን ማሳለፍ፤
እማማ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ቅድስት ሀገር፤
እናቴ ኢትዮጵያ፥ ይቺ ታላቅ ሀገር።
በዘመናት ችግር፥ ትከሻዋ ጎብጧል፤
በሸክሟ ጽናት፥ ጀርባዋ ተልጧል፤
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች።
ቀና ካላረካት፥ ጎብጣ ትቀራለች፤
አትችልም ሀገሬ፥ መከራ በቅቷታል።
ችግር በየአይነቱ፥
ጦርነት ባይነቱ፥ ተፈራርቆባታል።
አትችልም ጌታዬ፥ እናቴ ደክማለች፤
ይበቃል ካላልካት፥ ጎብጣ ትቀራለች።
አንድ ጻድቅ ጠፍቶ፥ ከቶም በምድሪቱ፤
ከፈርኦን መከራ፥ ጨከነ መአቱ።
ቸነፈር ፀናብን፥ ቀባሪ እስኪጠፋ፤
ዋኔ ዋኔ ሆኗል፥ የእንባችን ተስፋ።
ክንድህን የቻለ፥ የምድር ሀይል የለም፤
ሀያል ነህ ዘላለም ጌታ መድሀኔአለም።
አንድም ሶስትም ፥ሆነህ አለምን የገዛህ፤
ዛሬም ለዘላለም፥ የምትኖር አንተ ነህ።
የመጻጉን አልጋ፥ በራሱ ያሸከምክ፤
የጣቢታን ትንፋሽ፥ በቃልህ የመለስክ።
በልብሶችህ ቁጨት፥ የደም ምንጭ ያደረክ፤
በምራቅህ ስለህ አይን፥ የፈጠርክ አምላክ።
ታምራትህ ብዙ፥ ፍቅርህ ለዘላለም፤
ምረትህን ስጠን፥ ጌታ መድሀኔ አለም።
++++++++++++++++++++
©ታዜና
@Menfesawigetmoch
ማህተቤ….
ማን ይበጥሳታል፣ ማህተቤ ክሬን፤
ማን ወንድ ይቀማኛል፣ ማርያም መዝሙሬን፡፡
ከመስቀሉ ማዶ ይታየኛል ፅድቅ፤
ጠላቴ በልጇ፣ ተመቶ ሲወድቅ::
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
ማን ይበጥሳታል፣ ማህተቤ ክሬን፤
ማን ወንድ ይቀማኛል፣ ማርያም መዝሙሬን፡፡
ከመስቀሉ ማዶ ይታየኛል ፅድቅ፤
ጠላቴ በልጇ፣ ተመቶ ሲወድቅ::
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
ኪዳነምህረት እናቴ
ስምሽ ይጣፍጣል፣ ማር ነው ለአንደበቴ፤
ትውልድ የሚወድሽ፣ ብፅይት እመቤቴ፡፡
በእጆችሽ የታቀፍሽ፣ የአለምን ዳኛ፤
ኪዳነ ምህረት፣ የልቤ መፅናኛ፡፡
++++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@MenfesawiGetmoch
ስምሽ ይጣፍጣል፣ ማር ነው ለአንደበቴ፤
ትውልድ የሚወድሽ፣ ብፅይት እመቤቴ፡፡
በእጆችሽ የታቀፍሽ፣ የአለምን ዳኛ፤
ኪዳነ ምህረት፣ የልቤ መፅናኛ፡፡
++++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@MenfesawiGetmoch
#መንፈሳዊ_ግጥሞች #MenfesawiGetmoch
——ቅዱስ እስጢፋኖስ ——
ድንጋይ እንደ ዝናብ፣ ሲወርድ የታገሰ፤
ሲወግሩት ይቅር፣ በል እያለ መለሰ፡፡
ስጋውን ለመግደል፣ እጅጉን ቢለፉ፤
ቀዳሜ ሰማዕት፣ አርገውት አረፉ፡፡
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
——ቅዱስ እስጢፋኖስ ——
ድንጋይ እንደ ዝናብ፣ ሲወርድ የታገሰ፤
ሲወግሩት ይቅር፣ በል እያለ መለሰ፡፡
ስጋውን ለመግደል፣ እጅጉን ቢለፉ፤
ቀዳሜ ሰማዕት፣ አርገውት አረፉ፡፡
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
@Menfesawigetmoch
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ #Share
——ዳግም ትንሳኤ——
በተዘጉ ደጆች፣ ገባ አምላካችን፤
ሰላም ለናንተ ይሁን፣ አለን ሰላማችን፡፡
ቶማስ ሆይ አስገባ፣ ጣትህን በጎኑ፤
እጅግ ብፁዓን ናቸው፣ ሳያዩ የሚያምኑ።
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
——ዳግም ትንሳኤ——
በተዘጉ ደጆች፣ ገባ አምላካችን፤
ሰላም ለናንተ ይሁን፣ አለን ሰላማችን፡፡
ቶማስ ሆይ አስገባ፣ ጣትህን በጎኑ፤
እጅግ ብፁዓን ናቸው፣ ሳያዩ የሚያምኑ።
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
++ገብርኤል ወዳጄ+++
በአማላጅነትህ ይፈር፣ ዱራ ሜዳ፡፡
አብርድልን አንተ፣ የእሳቱን ግድግዳ፤
የራማው ልኡል፣ ሊቀ መላእክት፤
ገብርኤል ወዳጄ፣ አድነን ከእሳት፡፡
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች Follow Us
©ታዜና
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
በአማላጅነትህ ይፈር፣ ዱራ ሜዳ፡፡
አብርድልን አንተ፣ የእሳቱን ግድግዳ፤
የራማው ልኡል፣ ሊቀ መላእክት፤
ገብርኤል ወዳጄ፣ አድነን ከእሳት፡፡
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች Follow Us
©ታዜና
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ #Share
——እናቴ ነሽ——
ርቆ ያለውን፣ ያገኘ በቅርቡ፤
ያረፈ ያውቅሻል፣ እፎይ ያለ ልቡ፡፡
ካረፉት መካከል፣ አንዱ ነኝና እኔ፤
እናቴ ነሽ ማርያም ፤ ልጅሽ በመሆኔ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
——እናቴ ነሽ——
ርቆ ያለውን፣ ያገኘ በቅርቡ፤
ያረፈ ያውቅሻል፣ እፎይ ያለ ልቡ፡፡
ካረፉት መካከል፣ አንዱ ነኝና እኔ፤
እናቴ ነሽ ማርያም ፤ ልጅሽ በመሆኔ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
——እዘምራለሁ——
የተቆለፈ፣ ልቤን ከፍቶታል፤
የሚኮላተፍ፣ አፌን ፈቶታል፡፡
ጥቂት መተናል፣ ብዙ ቢጠሩ፤
እዘምራለሁ፤ እኔም ለክብሩ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
——እዘምራለሁ——
የተቆለፈ፣ ልቤን ከፍቶታል፤
የሚኮላተፍ፣ አፌን ፈቶታል፡፡
ጥቂት መተናል፣ ብዙ ቢጠሩ፤
እዘምራለሁ፤ እኔም ለክብሩ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
—— ልደታ ——
ኢያቄም ሀና፣ አባት እናትሽ፤
አንቺን ወለዱ፣ እንድንድንብሽ፡፡
ልጅሽ ወዳጅሽ፣ ሰላማችን ነው፤
የልደትሽ ቀን፣ ልደታችን ነው፡፡
++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
©ታዜና
—— ልደታ ——
ኢያቄም ሀና፣ አባት እናትሽ፤
አንቺን ወለዱ፣ እንድንድንብሽ፡፡
ልጅሽ ወዳጅሽ፣ ሰላማችን ነው፤
የልደትሽ ቀን፣ ልደታችን ነው፡፡
++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
©ታዜና
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ #Share
+++እንኳን ለጌታችን የዕርገት አደረሳችሁ+++
——ዐረገ በክብር ——
ዐረገ በክብር፣ ዘምሩ በእልልታ፤
የነገስታት ንጉስ፣ የሠራዊት ጌታ፡፡
ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ምድር መጣ፤
ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
፤
እስከ ቢታንያ፣ ወደ ውጭ አውጥቶ፣
ጌታችን ባረከን፣ እጆቹን አንስቶ፡፡
አይናችንን ተክለን፣ ሰማይን አየነው፣
ከፍ ከፍ እያለ፣ ደመና ሸፈነው፡፡
፤
ወላጅ እንደሌለው፣ አይተወንም እርሱ፤
ከሠማይ የላከው፣ አፅናኝ ነው መንፈሱ፡፡
እንዲሁ ይመጣል፣ ሲያርግ እንዳያችሁ፤
በአስራ ሁለቱ ዙፋን፣ ትቀመጣላችሁ፡፡
፤
ዘስልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ፤
እጹብ ድንቅ ነው የጌታ ዕርገቱ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
+++እንኳን ለጌታችን የዕርገት አደረሳችሁ+++
——ዐረገ በክብር ——
ዐረገ በክብር፣ ዘምሩ በእልልታ፤
የነገስታት ንጉስ፣ የሠራዊት ጌታ፡፡
ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ምድር መጣ፤
ፀሀዩ በምስራቅ፣ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
፤
እስከ ቢታንያ፣ ወደ ውጭ አውጥቶ፣
ጌታችን ባረከን፣ እጆቹን አንስቶ፡፡
አይናችንን ተክለን፣ ሰማይን አየነው፣
ከፍ ከፍ እያለ፣ ደመና ሸፈነው፡፡
፤
ወላጅ እንደሌለው፣ አይተወንም እርሱ፤
ከሠማይ የላከው፣ አፅናኝ ነው መንፈሱ፡፡
እንዲሁ ይመጣል፣ ሲያርግ እንዳያችሁ፤
በአስራ ሁለቱ ዙፋን፣ ትቀመጣላችሁ፡፡
፤
ዘስልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ፤
እጹብ ድንቅ ነው የጌታ ዕርገቱ፡፡
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
@Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
ለጨረቃ በርቶ፥ለፀሀይ ጨለመ፤
አለምን ስትጋርድ፥ ፍጥረት ተገረመ።
ፀሀይ ስትከለል፥ቀለበት ስትሰራ፤
ግሩም ነው ጥበብህ፥ እጹብ ያንተ ስራ።
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
Follow Us
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
©ታዜና
ለጨረቃ በርቶ፥ለፀሀይ ጨለመ፤
አለምን ስትጋርድ፥ ፍጥረት ተገረመ።
ፀሀይ ስትከለል፥ቀለበት ስትሰራ፤
ግሩም ነው ጥበብህ፥ እጹብ ያንተ ስራ።
+++++++++++++++++++++++
™ #መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
Follow Us
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
©ታዜና