Telegram Web Link
ምስለ ፍቁር ወልዳ pinned «https://youtu.be/FCSe5xn3rnw?si=maFYirfiF22uhsE0»
🌹🌹🌹🌹🌹

እንኳን ለፆመ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ

ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡

በግዕዝ ጸገየ ማለት  አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡  

በማኀሌቱም እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር  በግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

🌹
''እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት›› 
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) ደሙ አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

🌹
በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡-
‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡
ትርጉሙም፡-
‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና››

🌹
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡ 

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

ምንጭ: የማኅሌተ ጽጌ ምንጭና ትርጉም: መዝገበ ታሪክ:የቤተክርስቲያን ታሪክ መረጃወች

🌹🌹🌹🌹🌹
መድኃኔዓለም

💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።ምን ዓይነት ፍቅር ነው????? ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

✝️ነገ❷❼ የቀራንዮ ንጉስ የድንግል ማርያም ልጅ  ቸሩ  መድኃኔዓለም ነው እንኳን በሰላም በጤና አደረሳችሁ።🙏❣️
1🔥1
2025/10/19 22:41:49
Back to Top
HTML Embed Code: