🌹#በዓታ ለማርያም ማለት🌹
✞ 📌#እመቤታችን የብጸሐት ልጅ ናት ( የስለት ልጅ) 3 ዓመት ሲሆናት አፍዋ እህል ሳይለምድ ሆድዋ ስው ሳይውድ ብለው እናት አባትዋ ውስደው ለቤተ እግዚአብሔር ስጡዋት ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ይባላል ✞ የእመቤታችን መልኳ እንደ ፅሀይ ሲያበራ አይቶ ይእችን የመስለች ውብ ብላቴና ተረክቤ እንደምን አድርጌ አኖራታለው ብሉ ደውል አስምቶ ካህናትን ስብስቦ የምግቧን ነግር ሲማከሩ መልአኩ ቅዱስ ፋኖኤል ዕብስት ስማያዊ ጸዋ ስማያዊ ይዞ ከላይ እርቦ ታየ
ሊቀ ካህናቱ ዛሬ ሀብቴን ክብሬን በስው መካከል
ሊገልጥልኝ መስለኝ ብሎ ሊቀበል ቀርበ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀበት
+ ካህናቱም ሊቀበሉ ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
+ እህሩገ እስራኤልም ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
+ ሐና እያቄምም ሊቀበሉ ቀርቡመልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው
ሐና ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የውርደ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን አይቀርምና እስኪ ትተሻት ጥቂት እልፍ በይ አሏት ትታት ትንሽ እልፍ ብትል መልአኩ ውርዶ ግራክንፉን አንጥፋ ቀኝ ክንፈን አጉናጸፏ በቆመ ብዕሲ አድርጉ መግቧት አርጓል
"ምግቧ ሰማያዊ ነው ሲል ነው "
የምግቧ ነግር ከተያዘልን ይህችን ውብ ብላቴ ከስው ጋራ ምን ያጋፈታል ኖሮዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን ብለው ከቤተመቅደስ አግብተው አኖርዋት ሄደዋል
እመቤታችንም መላእክት ሊቃነ መላዕክት አያጫውትዋት እያርጋጓት 12ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀምጠች ከእናት አባትዋቤት 3ዓመት በአጠቃላይ 15ዓመት ሲሆናት
🌿💖 አይሁዶች መቼም ለምቀኝነት አያርፉምና ይእች ብላቴና ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች እሷን ያለ ጉልማሳ በቤተ መቅደሳችን አስገብተን ቤተ መቅደስሳችንን ታርክስብናለች እንዲያውም ጠረጠረናት ትውጣልን የጠየቀችሁን አድርግላት አሉት
🌿💖 ሊቀ ካህናቱም ዘካርያስ ከእመቤታችን ሄዶ ልጄ እንደምን ብለሽ መኖር ትውጃለሽ አላት
እመቤታችንም ፍፃምተ ፈቃድ ፤ ትሁት ናትና እንግዲህ ከእግዚአብሔር በታች ያለከኝ አባት አንተ ነህ ውደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ አለችሁ
🌿💖 ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ጌታ ስራውን ያለ ምክንያት አይስራውምና ከነገደ ይሁዳ ሚስቱ የሞተችበትን በትር ስብስበ በቀዳማይ ሰዓታት ሌሊት ይዘህ ገብተ ስትፀልይበት እደር ከዚያ ምልክት አሳይካለው ለዕዚያ ስው ስጣት አለው
🌿💖 ሊቀ ካህናቱም በትር ቢስበስብ 9መቶ 1985 በትር ሆነ ያንን በቀዳማይ ስዓት ሌሊት ይዙ ገብቶ ሲጸልይበት ቢያድር
+ በዮሴፍ በትር ላይ የሎሚ ቅጠል አብባ አፍርታ ታየች
+ እርግብም በዮሴፍ እራስ ላይ አርፈለች
+ እጣም ቢጥሉ ለዮሴፍ ደርስው በሦስት ምስክር ለዮሴፍ ደርስች
ሱባዬ ገብተን የስጠንክን ሱባዬ ገብተን እስክንቀበልክ ድርስ ጠብቃት ተንከባከባት አሉት የዮሴፍም ይዟት ውደ ቤቱ ሄደ።
ከቤቱ አኑሯት ዘመኑ የንግድ ውቅት ነበርና ወደ ንግድ ለመሄድ ዕለቱን ተሸኝቶ አድሯል ዮሴፍ ከ3ወር በሀላ ተመለስ ዮሐንስ የሚባል ፍላስፍ ወዳጅ ነበርው ሊጠይቀው መጣ ጥቂት ተጨዋወተው ሊሄድ ተነሳ ሊሽኘው ውጣ
ዮሴፍ ይህች ብላቴና ፀንሳለች ከአንተ ነው ወይስ ከሌላ አለው በምን አውቀው ቢሉ በፈልስፈና የጌታስ ፀንስ በፈልስፈና አይታውቅም ብሎ
ሴቶች ሲፀንሱ ከቀደመው ይልቅ መልካቸው ያምራል ጡታቸው ይጦቅራል ከንፈራቸው ይደርቃል በዚያ አውቆ።
🌿💖 ዮሴፍም አር እኔ እንኳን ግቢር ቀርቶ ሐልኦም አልውቅባትም አለው እንግዲያውስ ስስነች ተብላ እንዳትውገርብህ ገብተህ ጠይቀ ተረዳ አለው።
ዮሴፍም ውደ ቤት ተመልሶ ድንግል ማርያምን
የፀነሽው ከማን ነው ብሎ ጠየቃት
ድንግልም ከመንፈስ ቅዱስ ነው አለችሁ ከዚህ በፈት እንዲህ ተደርጉ አያውቅም እና ነገሩ እርቀቀበት ቢርቀው ከደጅ ወድቆ ይኖር የነበር ደርቅ ግንድ አለ ይሀንን አለምልማ አብባ አፈርታ አሳይታዋለች
🌿💖 በዚያውስ ላይ ዐፁቅ በባህሪያቸው እንዲያብቡ ንቦችን እንዲራቡ የሚያደርግ ጌታ እኔንስ በእቱም ድንግልና ፀንሼ በህቱም ድንግልና እንድውልድ ቢያደርገኝ ይሳነዋል ትላለክ???
ብላ ነገሩን እንደዚህ አስርድታዋለች
🌿💖 ይህም አልቀርም ውድያው ለባህል የሚውጡበት ጊዜ ደርስ የሴፍም ትቺያት ብሄድ ያደርገውን አውቆ ትቷት መጣ ይሎኛል
ይዥትም ብሄድ ሴስነች ብለው በድንጋይ ወግርወ በእሳት አቃጥለው ይገድሉብኛል ምን ይሻለኛል እያለ ይህን ሲያውጣ ሲያውርድ መላከ እግዚአብሔር በህልም ታየው ተነጋገርው
ዮሴፍ ከእርሷ የሚወለደው የአብ አካለዊ ቃል በግብር መንፈስ ቅዱስ ነውና አይዞህ አትፈሪ ይዘሀት ውጣ አለው ይዝዋት ውጥቷል ነገሩም አልቀርም
" 🌿💖 ማየ ዘለፈአጠጧት " ይህ በኦሪቱ ልማድ ነው ባልየው መንፍሳዊ ቅናት ተነሳስቶ ከሌላ ውንድ ደርሳለች ብሎ ሚስቱን የጠርጠራት እንደሆነ
" አሪፀ ስግምን ውሃ በገንቦ አሲዞ እራሷን አከናንቦ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟት ይሄዳል ሊቀ ካህናቱ ከምህዋሩ ለይ ሆኖ ክንብንብሽን ግለጭው ይላታ እንዲህ ይግለጥብኝ በይ ሲያስኛት ነው
🌿💖 ከኦሪቱ የሚደገም የሚነበብ የሚጸለይ አንዳንድ አለ
ሊቀ ካህናቱ ያንን ደግሞ ህራር እጣኑን አመደ ምስዋቶን በጥብጦ ባልሽ የጠርጠርሽን አድርገሽ ስውርሽ እንደሆነ
ስውነትሽ ይበጥ ፣ ጉንሽ ይላጥ ፣ አጥንትሽ ይርገፍ
አላደርግሽው እንደሆነ
በውንድ ልጅ ይታርቅሽ ብሎ ይስጣታል
እርሷም አሜን ውአሜን ብላ ተቀብላ ትጠጣዋለች ።
🌿💖 እርግማኑ ይደርግብኝ ምርቃኑ ይደርግልኝ ስትል ነው ባልዋ የጠርጠራትን አድርጋ ስውራ እንደሆነ ውድያው ስውነቷ ያብጣል ፣ጉንዋ ይላጣል ፣አጥንቷም ይርግፈል
ያላደርገችው እንደሆነ በውንድ ልጅ ይታርቃታል
በዚያ ልማድ ነው
🌿💖 ለእመቤታችንም ቢያጠጥዋት ፈትዋ ከፀሐይ ስባት እጅ አብርቶ ተገኘ ታየ ከዚያ የተስበስ ህዝቡ ይህችን ብላቴ ባላደርገችው ነገር በከንቱ አምተናታል ብለው
የተናገሩት ለእርሷ ስጥቶ ውይትፀርይ ብሉ ተናገር።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች እንዲህ ብላ ተናገርች መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ከነገርኝ ነገር ቃል በቀር ሌላ እንደማላውቅ እግዚአብሔር ያውቃል ብላ ተናገርች ።
✞ ንፅህት ድንግል ማርያም አምላክን ለመውለድ የታመነች ናት
✞ አምላክን ለመውለድ የታመነች ድንግል ማርያም ብቻ ናት
✞ የስውን ልጅ ለማማለድ ድንግል ማርያም የታመነች ናት
🌿💖 ድንግል ሆይ !!! የማይውስነውን ውስንሽ
የማይቻለውንን ቻልሽ ምንም ምንም ሊችለው የሌለውን ቻልሽ
ምልዕተ ፀጋ ምልዕተ ክብር እመቤታችን የአብ አካላዊ ቃል ማደሪያው ድንግል እመቤታችን
የማህፀኗ ፈሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ አዳነ
ከእኛ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አጠፈ
🌿💖 እመቤቴ ማርያም ሆይ
ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
🌿💖 ድንግል እመቤቴ ሆይ
ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡
🌿💖 እመቤታችን ድንግል ማርያም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
ድንግል ሆይ ከልጅሽ ከውዳጅሽ ከኢየሱስ ከክርስቶስ ለምኝልን ከሀጥያታችንን ያስተስርይልን ዘንድ አሜን!!!
✝ ወስብሓት ለእግዚአብሔርው ✝
✝ ወለወላዲቱ ድንግል ✝
✝ ወለመስቀሉ ክብር አሜን ✝

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ተሰሎንቄ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።
¹⁴ በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፥ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።
¹⁵ ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።
¹⁶ የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
¹⁷ በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።
¹⁸ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
¹² እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ.55(56)፥13
#ትርጉም፦ “ነፍሴን ከሞት፥ እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፥ በሕያዋን ብርሃን #እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።" መዝ.(56) 55፥13
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_3_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።
¹⁹ ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።
²⁰ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
²¹ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።
²² ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ አንበስ፣ የሊቀ ጳጳስ የአባ ዲዮናስዮስና የአባ ሙሴ ዘሲሐት የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

"#እንኳን_አደረሳችሁ_እመቤታችን_አምላክን ወለደች ሲባል ያልደነቃቸው ሰዎች በልጇ ኃይል ከሞት ተነሥታለች ዐርጋለች ሲባሉ በጣም ይከፋሉ። ለምን? ካልን ለእርሷ የኾነውን ኹሉ ሊኾኑት ስለማይችሉ በቅናት ነበልባል እስኪጨነቁ ድረስ እየተቃጠሉ።
ለእመቤታችን የተሰጣት ኹሉ የቱንም ያኽል ቢያስደንቅ የአምላክ እናት ከመኾኗ የሚደርስ የለም። ትንሣኤዋ እጅግ እጅግ በጣም ያስደንቀን እንጅ እመ አምላክነቷ ይበልጥ ያስደንቀናል።
🌹ድንግል_ሆይ ---የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው
❣️ንግስት_ሆይ --የሚያከብሩሽ የተከበሩ ናቸው🌹
🌹ንፅሕት_ሆይ ---የሚቀድሱሽ የተቀደሱ ናቸው❣️
❣️ፍስሕት_ሆይ ---የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው🌹
🌹ልዕልት_ሆይ ---የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው❣️
ውድስት_ሆይ ---ለንግሥትነትሽ የሚገዙ ሁሉ የተባረኩ ናቸው✝️❤️🤲
🌹✝️━━━━━━ ⊙ ━━━━━━✝️🌹
ድንግል_ሆይ ! ንፅህናን እንደ መላዕክት የለበሽ ፣ እንደ ነብያት መንፈስ ቅዱስን የተመላሽ ፣ ሁሉንም አሸናፊ በሚሆን በልዑል እግዚአብሔር እጅ የታነፅሽ የመለኮት ማደሪያ ነሽ ። ስለዚህ ክብርት ነሽ ።
ድንግል ሆይ _ባንቺ ያመን✝️❤️🙏
ወር በገባ በ3 ቅድስት እናታችን በዓታ ማርያም ናት።
ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን ።🙏❤
እናቴ ባዕታ ማርያም ጥላዬ ጥላዬ በሄድኩበት ሁሉ ሁኝ ከለላዬ። በጨነቃችሁ ጊዜ አለው ትበላችሁ
⛪ምልጃዋ ጥበቃዋ አይለየን!!🙏❤

❤2
††† 🌻✝️መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††🌻✝️
†††🌻✝️ እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††🌻✝️
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
†††🌻✝️ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን🌻✝️ †††
††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::
ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::
ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::
††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::
ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::
†††🌻✝️ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ🌻✝️ †††
††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::
ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::
ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::
ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::
ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::
††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት
††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::
†††🌻✝️ አባ ሙሴ ዻዻስ🌻✝️ †††
እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ #ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው::
ገዳማቸው #ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል::
††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን::
††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ (ነቢይና መስፍን)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ልደቱ)
3.ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ
4.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ሙሴ ዻዻስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::"(ኢያሱ 24:14)
✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝

✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ ✝✝✝
✝ መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" ቅድስት ሐጊያ ሶፍያ "+
✝ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::
+በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::
+በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ: እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔ ዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት::
+ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::
+የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::
+ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር::
+ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ::
+የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል:: ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው: የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር::
+በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው::
+" ቅዱስ ማማስ ሰማዕት "+
✝የሰማዕቱ ወላጆች ቴዎዶስዮስና ታውፍና ሲባሉ ማማስ የሚለው የስሙ ትርጉም 'ዕጉዋለ ማውታ - እናት አባቱ የሞቱበት' ማለት ነው:: ለምን እንደዚህ ተባለ ቢሉ:- በዘመነ ሰማዕታት ስደት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይዘውት ተሰደው ነበር:: ማምለጥ ባይችሉ ይዘው አሠሯቸው::
+በእሥር ቤትም ከስቃዩ ብዛት 2ቱም ልጃቸውን ማማስን እንዳቀፉት ሕይወታቸው አለፈች:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተች አንዲት ሴትም ራርታ እነርሱን አስቀብራ: እርሱን አሳድጋዋለች:: ስሙንም 'ማማስ' ብላዋለች::
+ቅዱሱ ባደገ ጊዜ የወላጆቹን ጐዳና በመከተሉ ተይዞ ለፍርድ ቀረበ:: ክርስቶስን አልክድም በማለቱም ብዙ ስቃይን አሳልፎ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱስ ማማስ ከዐበይት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በአንበሳ ጀርባ ላይም ይቀመጥ ነበር::
+" አቡነ አሮን መንክራዊ "+
✝ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ:: በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ::
+አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ:: የአቡነ አሮን ወላጆች ገብረ መስቀልና ዓመተ ማርያም የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ነበሩ:: ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::
+ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኳን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል::
+ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ወሎ መቄት ውስጥ በሚገኘው ገዳማቸው ዐርፈው ተቀብረዋል:: ገዳሙ እስካሁን ያለ ሲሆን ድንቅ ጥበበ እግዚአብሔር የሚታይበት ነው:: ጣራው ክፍት ሲሆን ዝናብ አያስገባም::
+" አፄ ልብነ ድንግል "+
✝እኒህ ንጉሥ ኢትዮዽያን ለዓመታት (ከ1500 እስከ 1532 ዓ/ም) ቢያስተዳድሩም 15ቱ ዓመት ያለቀው በስደት ነው:: ከደጋጉ አፄ ናዖድና ንግሥት ወለተ ማርያም ተወልደው: በሥርዓቱ አድገው ቢነግሡም: በክፉ መካሪዎች ጠንቅዋይ ወደ ቤታቸው ገብቶ ሃገሪቱን ለመከራ ዳርጉዋታል::
+ዛሬም ድረስ ጠባሳው ያለቀቀው የግራኝ ወረራ ለ15 ዓመታት ሃገሪቱን ያለ ካህንና ቤተ ክርስቲያን አስቀርቷት ነበር:: ብዙ ክርስቲያኖችም ሰልመው ቀርተዋል:: አፄ ልብነ ድንግል ግን ደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ገብተው ንስሃ ጀመሩ: አለቀሱ: ተማለሉ::
+እመቤታችን ተገልጣም "ይቅርታን በነፍስህ እንጂ በሥጋህ አታገኝም" አለቻቸው:: እርሳቸውም ሱባኤውን ቀጥለው: 'ስብሐተ ፍቁርን': 'መልክአ ኤዶምን' የመሰሉ መጻሕፍትን ደርሰው በዚህች ቀን በ ዓ/ም ዐርፈዋል:: እኛ ክርስቲያኖችም እናከብራቸዋለን::
+የቅዱሳኑ አምላክ የወዳጆቹን ፈተና አስቦ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቡንም ከስደት ይሰውርልን:: ከበረከታቸውም አይለየን::
+መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ
3.ቅዱስ ማማስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን ቴዎዶስዮስና ታውፍና
5.አቡነ አሮን መንክራዊ
6.አፄ ልብነ ድንግል
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን::(ሮሜ 6:5)