Telegram Web Link
#የመስከረም_5_ግጻዌ

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጢሞቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።
³ በእውነት ባልቴቶች የሆኑትን ባልቴቶች አክብር።
⁴ ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።
⁵ ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፥ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤
⁶ ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
⁶ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።
⁷ እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።
⁸ በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፥ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፥ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፥ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤
⁹ ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
⁹ ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።
¹⁰ ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።
¹¹ ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤
¹² ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርስዋም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።
¹³ በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።
¹⁴ ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
¹⁵ እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት"። መዝ.44(45)÷9

#ትርጉም፦ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” መዝ.44(45)÷9
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_5_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
³² እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
³³ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
³⁴-³⁵ ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
³⁶ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
³⁷ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
³⁸ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
³⁹ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
⁴⁰ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
⁴¹ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
⁴² ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
⁴³ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት ወይም የ #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ መስከረም ፮ (6) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይና
ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳይያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

"+ ቅዱስ_ኢሳይያስ_ነቢይ +"

=> በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የኢሳይያስን ያህል ትንቢት የተናገረ ነቢይ አይገኝም:: ከትንቢቱ ብዛትና ከምስጢሩ ጉልህነት የተነሳ አንድም ደፋር ስለ ነበር 'ልዑለ ቃል'ተብሎ  ተጠርቷል:: ቅዱስ ኢሳይያስ የተወለደው
ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት ሲሆን ለነቢይነት የተመረጠው ገና በወጣትነቱ ነበር::

+ ወላጆቹ 'ኢሳይያስ' (መድኃኒት) ያሉት በትምሕርቱ፣በትንቢቱ የጸጋ መድኃኒትነት ስላለው ነው:: እርሱ በነቢይነት በተሾመበት ወራት ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ንጉሡ ደግሞ ዖዝያን ይባሉ ነበር:: በሊቀ ካህናቱና በንጉሡ መካከል በተነሳ ጠብ ንጉሡ የበላይነቱን ለማሳየት ሃብተ ክህነት ሳይኖረው ሊያጥን ወደ ቤተ መቅደስ ገባ::

+ ይህንን የተመለከተው ኢሳይያስ ሊገስጸው ሲገባ'ወዳጄ ነው' በሚል ዝም አለው:: ፈታሒ እግዚአብሔር ግን ዖዝያንን በለምጽ መታው:: የግንባሩን ለምጽ በሻሽ ቢሸፍነው ከሻሹ ላይ ወጣበት:: በእሥራኤል ለምጽ ያለበት እንኩዋን በዙፋን ከተማ ውስጥም መቀመጥ አይችልምና አስወጡት:: በእርሱ ፈንታም ኢዮአታም ነግሷል::

+ ኢሳይያስ ደግሞ እግዚአብሔር በሰጠው አንደበት ሙያ አልሠራበትምና ከንፈሩ ላይ ለምጽ ወጣበት:: እርሱንም ወስደው ጨለማ ቤት ዘጉበት:: ሃብተ ትንቢቱንምተቀማ:: ቅዱሳን ትልቁ ሃብታቸው ንስሃቸው ነውና በዚያው ሆኖ ንስሃ ገባ:: ተማለለ፣ ጾመ፣ ጸለየ::

+ እግዚአብሔርም ንስሃውን ተመለከተለት:: ከዚያም ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት ኢሳይያስ እግዚአብሔርን በረዥም (ልዑል) ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ኪሩቤል ተሸክመውት ሱራፌል (24ቱ ካህናተ ሰማይ)"ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ" እያሉ ሲያመሰግኑት ተመለከተ::(ኢሳ 6:1)

+ አበው ሲተረጉሙ "አንተ ያፈርከው ዖዝያን እነሆ ሞተ::እኔ ግን መንግስቴ የዘለዓለም ነው" ሲለው ነው ይላሉ::ያን ጊዜ እግዚአብሔር "ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ?"አለ:: ኢሳይያስም "ጌታየ! እኔ ከንፈሮቼ የረከሱ አለሁ"አለው:: እግዚአብሔርም ሱራፊን ላከለት:: መልአኩም ፍሕም (እሳት) በጉጠት አምጥቶ ከንፈሩን ቢዳስሰው ነጻ:: ሃብተ ትንቢቱም ተመለሰለት:: ይኸውም የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው::

+ ከዚህች ቀን በሁዋላ ግን ኢሳይያስ የተለየ ሰው ሆነ::ማንንም የማይፈራ እውነተኛ የልዑል ወታደር ሆነ::ከኦዝያን በሁዋላ በየዘመናቸው 4ቱንም ነገሥታት ገሰጸ::እነዚህም ኢዮአታም፣ አካዝ፣ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው::

+ ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::

+ ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጎን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::

+ መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::"

+ በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ::(1ነገ 18:13, 19:1)

+ ታላቁ ነቢይ ልዑለ ቃል ኢሳይያስ ሐረገ ትንቢትን ያፈስ ነበርና ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር::(ኢሳ 7:14)

+ በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ መካሪዎች ቀርበው ንጉሡን በውዳሴ ከንቱ ጠለፉት:: "ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ:: እንዳንተ ያለ ማንም የለም:: ነቢዩ የተናገረው ትንቢትም እኮ ላንተ ነው:: 'ድንግል' የተባለች ኢየሩሳሌም ስትሆን 'ወልድ ወንድ ልጅ'የተባልክ ደግሞ አንተ ነህ" አሉት::

+ ይሕንን ጠማማ ትርጉም እህ ብሎ የሰማቸው ቅዱስ ሕዝቅያስ አልወቀሳቸውም:: በዚህ ምክንያት
እግዚአብሔር ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው:: ነቢዩም መጥቶ ንጉሡን አለው:- "ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ::"

+ ወዲያውኑ ሕዝቅያስ ታመመ ደከመ:: ንጉሡ ወደ ፈጣሪ:- "ጌታ ሆይ! እንደ ቸርነትሕ በፊትህ በቅን መንገድ መሔዴን አስብና ይቅር በለኝ" ሲል ተማጸነ::ይህ ሲሆን ቅዱስ ኢሳይያስ ገና ከንጉሡ አካባቢ አልራቀም ነበርና የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ::

+ ሕዝቅያስን በለው:- "ጸሎትህን ሰምቼ ስለ ባለሟሌ ስለ ዳዊት ብየ ምሬሐለሁ:: በዘመንህም ላይ 15 ዓመታትን ጨምሬልሃለሁ በለው" አለው:: ነቢዩም ወደ ንጉሡ ተመልሶ ይሕንኑ ነግሮ "እስከ 3 ቀን ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ ድነህ ትመለሳለህ" አለው::

+ ቅዱስ ሕዝቅያስ "ይሕ እንደሚደረግ በምን
አውቃለሁ?" አለው:: ኢሳይያስም ፀሐይን ዓለም እያየ 10 መዓርጋትን ወደ ሁዋላ መለሳት::

+ ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳይያስ ለ70 ዘመናት ሕዝቡን አስተምሮ ነገሥታቱን ገስጾ 68 ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ጽፎ አረጀ:: በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ምናሴ ግን ይባስ ብሎ ጣዖትን አቆመ ለጣዖትም ሰገደ:: ቅዱሱ ይህንን ሲያደርግ ዝም አላለውም:: በአደባባይ ገሰጸው እንጂ::

+ በዚህ የተበሳጨ ምናሴም ሽማግሌውን ነቢይ በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው:: ቅዱስ ኢሳይያስ በዚህ ዓይነት ሞት በጎ ሕይወቱንና ሩጫውን ፈጸመ::የተናገራቸው ትንቢቶች ግልጽ ስለ ሆኑ 'ደረቅ ሐዲስ'በመባል ይታወቃሉ::

=> ቸሩ አምላክ 'ደሃ ተበደለ ፍርድ ተጉዋደለ' የሚሉ መምሕራን አባቶችን አይንሳን:: ከነቢዩም በረከቱን ይክፈለን::

=> መስከረም 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ (ልዑለ ቃል)
2.ቅድስት ሰብልትንያ ሰማዕት
3.አባ ያዕቆብ ገዳማዊ
4.ቅዱስ አናቲሞስ ኤዺስ ቆዾስ
5.አባ ሳሙኤል ዘዋሊ (ፍልሠቱ)

=> ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=> + ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር:: ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች:: እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች:: እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ:: እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላቹሃል::የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና::(ኢሳ 1:18)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🌹☞ወር በገባ በ6 የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች፡ኢየሱስ ስንል አምላከ አማልእክት፡  የአማልክት አምላክ ኢየሱስ ስንል እግዚእ ወአጋእዝት፡ - የጌቶች ጌታ

☞ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ነገሥት፡ - የነገሥታት ንጉሥ
☞ኢየሱስ ስንል አልፋ ወ ኦሜጋ፡ - መጀመሪያው እና መጨረሻው፣ ፊተኛው
ኋለኛው
☞ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ሰማይ ወምድር፡ - የሰማይና የምድር ንጉሥ
☞ኢየሱስ ስንል ኤልሻዳይ፡- ኹሉን ቻይ
ኢየሱስ ስንል አዶናይ፡ - መድኃኔዓለም
☞ኢየሱስ ስንል ወልደ አብ ወልደ ማርያም፡ - የአብ ልጅ የማርያም ልጅ
በተዋሕዶ
ልደት የከበረ
☞ኢየሱስ ስንል ፈጣሬ ኩሉ፡ - ኹሉን የፈጠረ
☞ኢየሱስ ስንል እግዚአብሔር ማለታችን ነው፡፡
ስሙን ስንጠራ ይኽ ሁሉ በልባችን ሰሌዳ ታስቦ ነው፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ አበቃቀሉ ለሚያምር ክቡር ለሆነው የራስ ፀጉር ሰላምታ
ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፀሐይ ብርሃን ይልቅ እጅግ ለሚያበራው ፊትህ
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የፍጥረትን ጥሪ ከመስማት ቸል ለማይሉ
ጆሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ እጅግ ያማረ የከርቤ መፍሰሻ ለሆኑ ከንፈሮችህ ሰላምታ
ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ በታቦር ተራራ ምሥጢረ መለኮትህን ለመግለጽ
ተለንቀሳቀሰው አንደበትህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ቸር ማኅያዊ ለሚሆን ቃልህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ለሰው ፍቅር ሲል ለተጠማ ጉሮሮህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኅብረታቸው ነጭ ለሆነ የእጅ ጥፍሮችህ ሰላምታ
ይገባል፡፡
☞ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ምጥቀቱ ለማይ መረመር ዕርገትህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞(መልክአ ኢየሱስ)
🛐#ማርያም መግደላዊት 🌹

📍☞ወር በገባ በ6 ቀን የምትታሰው የመድኃኔዓለምን ትንሳኤ ቀድማ ያየች የተመረጠች የቅድስ ማርያም መግደላዊት ወርሐዊ መታሰቢያዋ ነው☞ማርያም መግደላዊት አስቀድሞ ጌታ 7 አጋንንትን ያወጣለት ደግ እናት ናት፡፡
ከዚያ ጀምራ ጌታን ተከተለች፡፡
☞እነዚህም ክፍ አጋንንት መንፈሰ ትዕቢት፤ መንፈሰ ጽርፈት(ስድብ)፤መንፈሰ
ቅንዓት፤ መንፈሰ ትውዝፍት(ምንዝር ጌጥ የማድረግ) መንፈሰ ዝሙት፤ መንፈሰ
ሐሜትና መንፈሰ ሐሰት ነበሩባት፡፡
☞ከሁሉ ሐዋርያቶችም እንኳን በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ትንሳኤውን የገለጠላት
እጅግ ዕድለኛ ሴት ነች፡፡
☞---ከሣምንቱ በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማልዳ
ወደ መቃብሩ መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች -- ማርያም ግን
እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተውጭ ቆማ ነበር ስታላቅስም ወደ መቃብሩ ዝቅ
ብላ ተመለከተች ሁለት መላእክት ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት
በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች -- ኢየሱስም ቆሞ
አየች እነሱም አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ?አሉት፡፡ አርሷም ጌታዬን
ወስደውታል ወዴት እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው፡፡ ይህን ብላ ወደ ኃላ ዘወር
ስትል ኢየሱስ ቆሞ አየችው ኢየሱስም እንደሆነ አላወቀችም አንቺ ሴት ሰለምን
ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ አላት፡፡
☞እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎት ጌታ ሆይ አንተ ወስደኽው እንደ ሆነህ
ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም ወስጄ ሽቱ እቀባው ዘንድ አለቸው፡፡
☞ኢየሱስም ማርያም አላት፡፡ እርሷም ዘወር ብላ በዕብራይስጥ ረቢኑ አለቸው
ትርጓሜውም መምህር ሆይ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስም ገና ወደ አባቴ አላረግሀምና
አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ
አምላኬ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሏል ብለሽ ንገሪያቸው አላት፡፡
☞መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታ እንዳየች ይህን እንዳላት ለደቀ መዛምርቱ
ነገረቻቸው፡፡(ዮሐ 20 1-8)
☞ከጌታ ዕርገት በኃላ በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላ
ወንጌልን ሰብካለች፡፡
]ብዙ ሴቶችም ወደ ሃይማኖት መልሳለች፡፡
☞ማርያም መግደላዊት ቁጥሯ ከ36 ቅዱሳን እንስት ወገን ነው፡፡
☞ይቺ ሴት ስለ ክርስቶስ እየመሰከረች ስታስተምር ስድብና ግርፋት ደርሶባት
ከዚያም ከብዙ ተጋድሎ በኃላ በዚህ በነሐሴ 6ቀን ተጋድሎዋን ፈጽማ
በሰማዕትነት አርፋለች፡፡
☞(መድብለ ታሪክ)
☞የቅድስት መግደላዊት ማርያም የጸሎቷ በረከቷ አይለየን፡፡
🌹#እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ  ወር በገባ በ6 እናታችን  ቅድስት አርሴማ ናት🌹

👰"ውበት ሐሰት ነው፤ ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች" ምሳሌ 30፥31። "ቅድስት አርሴማ"እግዚአብሔርን የምትፈራ በቅዱሳን ሰማዕታት ማህበርና በገነት በሮች የሕይወት ፍሬ ያፈራች ሰማዕት ናት።

የምድር ሀብት ጌጥ ብሎም #የንጉሥ ሚስት #ንግሥት መባልን ሁሉ እንቢ ብላ ለምድርም ለሰማይም ንጉሡ ለሆነው ለ #ክርስቶስ የተሞሸረች ስለእርሱም #በነፍሷ መከራን የተቀበለች ብፅዕት ሰማዕት ናት "በብዙ መከራና ስቃይ የእግዚአብሔርን #መንግሥት ልንገባ ይገባናል" እንዳለ መጽሐፍ.ቅዱስ #የሐ.ሥራ. 14፥22) ቅድስት #አርሴማም የመከራውን ሸክም የእሳቱን ዋዕይ #ታገሠች። ስለዚህም መንግሥተ ሰማያትን #ወረሰች። እርሷ ከ #ድንግል ማርያም #በታች ከሴቶች ልጆች #ትበልጣለችና በዚህች ቅድስት ሰማዕት #አርሴማ ጸሎት የሚታመን ብፁዕ ነው። #መታሰቢያዋንም በዕጣንና በመሥዋዕት #የሚያደርግ ብፁዕ ነው። ስለ ቅድስት #አርሴማ እንጀራንና ጽዋ ውኅ #ለድሃ የሚሰጥ ብፁዕ ነው። በዚህ ዓለም በሥጋው መዳንን ዕጥፍ ድርብ ያገኛል። በሚመጣው ዓለም መልካም ዋጋንና #የማያልፍ ሕይወትን ፈጽሞ ያገኛል። #ጌታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ በወንጌል ቃል=> "በነቢይ ስም ነቢይን የሚቀበል የነቢይን #ዋጋ ያገኛል በጻድቅ ስም ጻድቅን የሚቀበል የጻዲቁን #ዋጋ ያገኛል፤ በስሜና በደቀመዝሙሬ ስም ከታናናሾች ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኅ ያጠጣ እውነት እላችኃለሁ #በሰማያት ዋጋውን አያጣም" ብሏልና። (ማቴ 10፥40-42)። የእናታችን ቅድስት አርሴማ ባረከቷ ይዳርብን አሜን።
አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት
ዳግመኛም ወር በገባ በ6 በደመና ሲያርግ የታየ ብፁዕ ቅዱስ  ኤልያስ ነው።

ቸሩ መድኃኔዓለም ከዚህ ክፉ ዘመን እኛንም በኪነጥበቡ ይሰውረን።🙏
#የመስከረም_6_ግጻዌ

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።
³⁰ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤
³¹ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም።
³²-³³ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።
²⁰ ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
²¹ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦
²⁶ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤
²⁷ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው ሲል መልካም ተናገረ።
²⁸ እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ድኅነት ለአሕዛብ እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ ደግሞ ይሰሙታል።
²⁹ ይህንም በተናገረ ጊዜ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።
³⁰ ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፥ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
  "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ104(105)፥14-15።

#ትርጉም፦ “የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።”— መዝሙር 104(105)፥14-15
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበውን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው።
³⁷-³⁸ ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ በእርሱ አላመኑም።
³⁹-⁴⁰ ኢሳይያስ ደግሞ፦ በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው።
⁴¹ ክብሩን ስለ አየ ኢሳይያስ ይህን አለ፥ ስለ እርሱም ተናገረ።
⁴² ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤
⁴³ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።
⁴⁴ ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤
⁴⁵ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።
⁴⁶ በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
⁴⁷ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም።
⁴⁸ የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
⁴⁹ እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
⁵⁰ ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ፍልሰተ አጽም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
እንኩዋን ለቅድስት ኤልሳቤጥ: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ እና አባ ሳዊርያኖስ ክቡር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅድስት ኤልሳቤጥ

=>በወንጌላዊው አንደበት የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም ከቅዱስ አሮን ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና በጥሪቃ ወርዶ ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::

+ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3 ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም' አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን 'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች::

+ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት:: እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም: ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች ልጆች ናቸው::

+ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት:: እርሷ የሊቀ ካህናቱ ሚስት ናትና ክብሯ ከፍ ያለ ነበር:: ምንም ልጅ ባይኖራትም ዘወትር በጸሎትና በጾም: ምጽዋትንም በማዘውተር: ነዳያንንም በማሰብ የምትኖር እናትም ነበረች::

+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

+ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅድስቲቷ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::

+ድንግል እመቤታችን ወደ እርሷ መጥታ 'ሰላም' ባለቻት ጊዜ ምንም ያሳደገቻት ልጇ ማለት ብትሆን: መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን አመስግናታለች:: ቡርክት: ብጽእት: ከፍጥረተ ዓለሙ የከበረች መሆኗንም መስክራለች::

+በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ አቅርቧል:: ቅድስት ኤልሳቤጥ አክላም "ወምንትኑ አነ ከመ ትምጽኢ ኀቤየ እሙ ለእግዚእየ-የጌታየ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይገባኛል?" ስትል በትኅትና ተናግራለች:: ከጌታ እናት ጋር ለ3 ወራት በአንድ ቤት ቆይታለች::

+ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

+እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ኤልሳቤጥ ማለት 'እግዚአብሔር መሐላየ ነው': አንድም 'የጌታ አገልጋይ' ማለት ነው::

+" ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ "+

=>ይህ አባት የተዋሕዶ ሃይማኖታችን ምሰሶ ነው:: በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ተወልዶ አድጐ: በልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ: የምናኔ ሕይወትን መርጧል:: ቆይቶም የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ ረድእ ሆኖ ተምሯል: አገልግሎታል::

+በጉባኤ ኤፌሶን ጊዜም ቅዱስ ቄርሎስን ተከትሎ ሒዶ ተሳትፏል:: በ444 ዓ/ም ታላቁን ሊቅ ተክቶ የእስክንድርያ 25ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሹሟል:: ለ7 ዓመታትም መጽሐፈ ቅዳሴውን (እምቅድመ ዓለምን) ጨምሮ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመልካም እረኝነትም ሕዝቡን ጠብቇል::

+ዘመነ ሰማዕታትን ተከትሎ የመጣው የመናፍቃን ዘመን ሲሆን ለ150 ዓመታት ያህል መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተዋል:: በዚያው ልክ ከዋክብት ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና በየጊዜው ጉባኤያትን እየሠሩ: መናፍቃንን አሳፍረዋል:: ምዕመናንንም አጽንተዋል::

+በ451 ዓ/ም የተፈጸመው ድርጊት ግን ዛሬም ድረስ ጠባሳው የሚለቅ አልሃነም:: ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የንስጥሮስን ትምሕርት አለባብሰው ሊያስተምሩ ሲሞክሩ ግጭት በመፈጠሩ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 2 ተከፈለች::

+በጉባኤው የነበሩ 636 ዻዻሳት ስቃይና ሞትን ፈርተው በኑፋቄ መጽሐፍ ላይ በመፈረማቸው "መለካውያን" (ከእግዚአብሔር ይልቅ ለንጉሥ የሚታዘዙ) ተባሉ:: ጉባኤውም "ጉባኤ ከለባት" (የውሾች ስብሰባ): "ጉባኤ አብዳን" (የሰነፎች ጉባኤ) ተብሏል::

+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ግን "በኑፋቄው ላይ አልፈርምም" ከማለቱ አልፎ መናፍቃኑን አወገዛቸው:: በዚህ ምክንያት ወደ ጋግራ ደሴት ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር አሳደዱት:: በዚያም ለ3 ዓመታት ቆይቶ በ454 ዓ/ም ዐረፈ::

+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከማረፉ በፊት በተሰደደባት ደሴተ ጋግራ ለ3 ዓመታት ብዙ መከራ ከመናፍቃን ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱና በትምሕርቱ ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሷል::

+ቤተ ክርስቲያን እርሱን 'አበ ተዋሕዶ' (የተዋሕዶ እምነት አባትና አርበኛ) ትለዋለች:: የተነጨ ጺሙ: የረገፉ ጥርሶቹና የፈሰሰ ደሙ ዛሬም ድረስ ትልቅ ምስክርና የሃይማኖት ፍሬ ነውና::
"ያስተጻንዕ ህየ እለ ኀለዉ ደቂቀ:
ዘተነጽየ እምነ ጽሕሙ ወእም አስናኒሁ ዘወድቀ:
ፍሬ ሃይማኖቱ ፈነወ ብሔረ ርሑቀ" እንዲል::

+" ታላቁ አባ ሳዊርያኖስ "+

=>የዚህን ቅዱስ ሰው ስም የሚጠራ አፍ ክቡር ነው:: ጣዕመ ሕይወቱ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም:: እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የበቀለ: 30: 60: 100 ፍሬዎችን ያፈራ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ነው:: በትውልድ ሮማዊ ሲሆን የተወለደው በ309 ዓ/ም ነው::

+ወላጆቹ በዚህ የንጉሥ ዘመዶች: በዚያ ደግሞ ባለጠጐች ነበሩ:: እነርሱ ለልጃቸው ጥበብን መርጠዋልና የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ:: ከዚያ በአንድ ልቡ ብሉይን: ሐዲስን ተምሮ ሲጠነቅቅ ወላጆቹ ዐረፉ::

+ቅዱሱ ሳዊርያኖስም "የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት አለብኝ" ብሎ ቀን ቀን ያለፈውን: ያገደመውን ሁሉ ሲያበላ: ሲያጠጣ: ነዳያንን ሲጐበኝ ይውላል:: ምሽት ሲል ደግሞ ወደ ቅዱሱ ንጉሥ (አኖሬዎስ) ቤተ መንግስት ገብቶ: ወገቡን ታጥቆ ከንጉሡ ጋር ሲጸልይና ሲሰግድ ያድራል::

+ውዳሴ ከንቱ ሲበዛበት ንብረቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ገብላ ወደምትባል ሃገር ሒዶ መነኮሰ:: ባጭር ጊዜም የብዙ ነፍሳት አባት ሆነ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የገብላ (ኤላ) ጳጳስ ሆኖ ተሾመ:: በዘመነ ሲመቱም እንቅልፍን አልተመለከተም:: ባጭር ታጥቆ ያላመኑትን ለማሳመን ደከመ እንጂ::
2025/10/21 11:42:30
Back to Top
HTML Embed Code: