Telegram Web Link
፨እድሜ ለንስሃ፨
ያማረ ያጌጠ አዲስ ቤት ሰርቼ
እስክመለስ ድረስ አደራ ሰጥቼ
ሰፈሩን መንደሩን ቀየውንም ትቼ
ብዙ ዓመታትን ኖሬ ከዛ ሀገር ወጥቼ
አሁን ተመልሼ ስጎበኘው ቤቴን
አይኔን ማመን አቅቶኝ በእጄ ይዤ አፌን
እንዲጠብቅልኝ አደራ ይልኩት ሰው
እሳት ሲያነድበት ሲያጨስበት ኖሮ
ጣሪያውም ጠልሽቶ ግርግዳውም ጦቅሮ
ተረጋግጦ ሳየው ውስጡ ተሰባብሮ
እራሴን ታዘብኩት አዝኜ ከውስጤ
ድሮም!በሰው ተማምኜ ትቼው መቀመጤ
እንግዲ ፍረዱኝ!እስክመለስ ድረስ
ያደፈውን ዘመን በጊዜው እስካድስ
ጣርያ ግርግዳውን ወለሉን አፅደቶ
ያፈራርሰውን ካልጠበቀኝ ሰርቶ
እፋረደዋለው ህግ በፊት አቁሜ
ግን እስከዛው ድረስ
ሰጥቼዋለሁኝ ጥቂት ቀሪ እድሜ።
@Mgetem
#ማርያም
ማርያም ናት እናቴ
ብደክም ብርታቴ
ብረሳ አስታዋሼ
ብታረዝ አልባሼ
ቢርበኝ አጉራሼ
ብታመም ፈዋሼ
ወይኑን የሰጠችኝ
ስገፋ ያየችኝ
ቢከፋኝ መፅናኛ
ቀን ቢከዳ ዳኛ
ባጣ የሚገኝባት
ቢመሽ የማይባት
ልቤን ያሳረፈች
አምላኬን ያቀፈች
ማርያም ማርያም ስላት
መታለች የኔ እናት
እርፍ ብያለሁ
እመሰክራለሁ
እናንተም እንደኔ
ማርያም ማርያም በሉ
እርፍ በሉ።
@Mgetem
@Mgetem_bot
@Yohannes_mariyam
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
@Mgetem_bot
@Abawon
@Mgetem

በክርስቶስ ፍቅር በስመ ስላሴ፤
ከእግሬ በርከክ ብዬ ዝቅ ብዬ ከራሴ።c
በወልድ ሀብተ ወልድ በድንግል ተዋህዶ፤
በክርስቶስ ክርስትያን ያ’ረጋችሁ ፈቅዶ።
በሰማታት አማንያን የተሰኛችሁ፤
ወልደና ወለተ ይህ ድምፅ ሚሰማችሁ፤
እንደምን ከረማችሁ? እንደምን ሰነበታችሁ?
እንደምንስ እስከዚች ሰአት ደረሳችሁ?
አሜን አልፋና ኦሜጋ የሰራዊት ጌታ፣
ይመስገን በፍጥረት ከጥኋት እስከ ማታ።
አምላክ ሲመሰገን ሁሌም በባህሪ፣
ለአዳም ዘር በሙሉ የሆነች ተጠሪ፣
ሁል ጊዜም ከቀኙ አትለይም እና፣
ከፍጥረት ይድረሳት የፀጋ ምስጋና።
መላእክት ሰማታት ፃድቃናት በሙሉ፤
ስላዳም ዘር ድነት በመማፀን ያሉ፤
መርጦ ለኛ ድነት ፀጋ ያደላቸው፤
ሁሌም ይመስገኑ እንደዬ ክብራቸው።


#ቃል ነበረ

ጨረቃ ክዋክብት ፀሀይ እና ምድር፤
መላእክት ሰማእታት ስነ-ፍጥረት ሳይኖር፤
አልፋ እና ኦሜጋ የማይመረመር፤
የሁሉ መሰረት ያን ጊዜ ቃል ነበር።
ምድርና ሰማይን በአንድ ቀን ፈጠረ፤
ደግሞም ለአምስት ቀናት ሌሎችን ጨመረ፤
እንደየ አይነቱ ሁሉን አሳመረ፤

በሰባተኛው ቀን መፍጠር በጀመረ፣
እግዚአብሔር እንዲ አለ፦
“ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር፤
አዋፍትንም ይግዛ ይሰልጥን በምድር።”
ከሰባት ባህርያት በጆቹ አበጃጀው፤
የመጀመሪያም ሲል አዳም ብሎ ጠራው፤
ሁሉ ወደአለበት ገነትም ወወሰደው፤
የሞት ሞት እንዳይሞት አንዷን ከለከለው፤
አልፋ እና ኦሜጋ የማይመረመር፤
የሁሉ መሰረት ያን ጊዜም ቃል ነበር።
በሰባተኛው ቀን ከሰባት ባህርያት የተበጀው አዳም፤
የገነት ኑሮውን ከሰባት አመታት ማሳለፍ አልቻለም።
አምላኩን ሰረቀ፤
ሁሉንም አወቀ፤
አውቆም ተደበቀ፤
አልፋና ኦሜጋ ማይመረመረው፤
አዳምን እንዲ አለው፦
ወደምድር ሂድ ጥረህ ግረህ ብላ፤
እሷም ታብቅልብህ እሾህ አሜከላ።
ለአምስት ቀን ከግማሽ ይበዛል መከራህ፤
ስወለድ ነው ምትድን እኔ ከልጅ ልጅህ።
አዳም ተፀፅቶ እጅግ ብዙ ለፋ፤
ነገር ግን አልቻለም ሀፂያቱን ሊያጠፋ።
ከመጠበቅ በቀር ያንን ቃል በተስፋ።
ሁሉንም ከማድረግ አንዳች ማይሳነው፤
መፍረድ እና ማዳን ባህሪው የሆነው፤
የሚገለጥበት የው ደረሰ ጊዜው።
መኖር ሳይጀመር ይኖር የነበረ፤
አልፋና ኦሜጋ ጥንትም ቃል ነበረ።
በሰማይ በምድር ታላቅ ደስታ ሆነ፤
በከብቶቹ በረት ዛሬ ቃል ሰው ሆነ።
በኮከብ ተመርተው ሰባ ሰገል መጡ፤
ለንጉስነቱ ወርቁን አስቀመጡ ፤
ለሞቱ የሚሆን ከርቤውን አወጡ፤
ለአምላክነቱ እጣን ሰግደው ሰጡ።
በደስታ እልል እንበል ልዩ ቀን ነው ለኛ፤
ከድንግል ተወልዷል እውነተኛው ዳኛ፤
አዳምን ለማዳን ከሰይጣን ቁራኛ።
አሲናበል አሲና ገናዬ፤
ተወለደ ጌታችሁ ጌታዬ።
በነብያት የተነገረለት፤
አማኑኤል ነው የተኛው በበረት።
እመብርሃን አብሳሪተ ፀጋ፤
አትለየን ሁሌም ከልጇጋ።
ስናከብር በዐለ እልደቱን፤
ያስቀየምነ ይቅርታ ጠይቀን፤
የተቀየምን ከልብ ይቅር ብለን፤
እንዋደድ እርስበርስ ሁላችን።
እንዲህ ደምቀን እንደተሰባሰብን፤
የበዓሉ ባለቤት በረከት ያድለን።
በማልት በሰርክ ፀሎት ስታደርጉ፤
ለገብረ ሚካኤል ማለትን አዘንጉ።
ያስቀየምኋችሁ በምላስ ወለምታ፤
በእግዚያብሄር ስም ይቅርታ(3)።

ተፃፈ በመስፍን ምትኬ ፪፻፲፪/፬/፪፭ ዓ.ም
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
፨እልል የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል፨
በተባረከችው በዚያች በውብ ምሽት
እረኞችም ሁሉ እደጅ ባደሩበት
ህፃን ተወለደ በከብቶች ግርግም ውስጥ
ቤዛ ሊሆን ኋላ ለዓለም ነፍሱን ሊስጥ
ጌታ ተወለደ የእስራኤል ንጉስ
ከአለም እርኩሰት ትውልድን ሊመልስ
እልል..!የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
በዚያች ቅድስት ለሊት በከብቶች በረት ውስጥ በጨርቅ ተጠቅልሎ
በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ለሰው ልጅ አድሎ
ሊያኖረን ተወልዷል የሠራዊት አምላክ አልፋና ኦሜጋ
ከእናቱ ከማርያም ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ከስጋዋ ሥጋ
እልል... የምስራች ኢየሱስ ተወልዷል
አለምን ከጥፋት ሊያድን ምድር ወርዷል
ከእግዜር የተላኩት ቅዱሳን መላዕክት ብሥራት አብስረዋል
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሲሉም መዝሙር ዘምረዋል።
እኛም እስቲ እንዘምር እናሸብሽብላት በምሥጋና ዜማ
የጌታን መወለድ ያልሰማ እንዲሰማ የሰማ እንዲያሰማ።
እልል... የምስራች ክርስቶስ ተወለዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
፨ያኔ ጥንት ነበረ፨
በዱር በገደሉ በዓለም ዙርያ ሁሉ
አምላክ ይወለዳል ብለው ተናገሩ
የነቢያት ተስፋ የነበለአም
አምላክ ተወለደ መድሃኒዓለም
ያኔ ጥንት ነበር...
ይወለዳል ሲሉ በመንፈስ ሲመሩ
አምላክ አዶናይን ለማየት ሲጥሩ
እንደው ኩርምት ብለው በተስፋ ሲኖሩ
ድንግል ትፀንሳለች ብለው ሲናገሩ
ቀናትን ሲቆጥሩ ሳምንታት ሲሠምሩ
ሳምንታት በግንድ ላይ ወራትን ሲሠሩ
ወራት ተቀናጅተው ዓመትን ሲሰጡ
ዓመታት ተቆጥረው ዘመናት ሲመጡ
እናያለን ሲሉ ለማየት ሳይበቁ
በመንፈስ ሲሰክሩ እንዲውል ሲሳለቁ
ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር በመንፈስ መሰከሩ
አምላክ ይወለዳል ብሎ መዘከሩ
በርቀት ተሳልሞ ለዓለም ማብሰሩ
ያኔ ጥንት ነበር የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢአትን መፀነሱ የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢያትን መፀነሱ ሞትንም መውለዱ
ከገነት ተባሮ እንዲያው መዋረዱ
ፀጋውን ተገፎ በለስ ማገልደሙ
ያኔ ጥንት ነበር...
አዳምን ሊጎበኝ አምላክ መጣራቱ
አዳም አዳም አዳም ብሎ መፈለጉ
አትብሉ ያልኩህን በላህው ማለቱ
አዳምን በመፍጠር እንዲያው መፀፀቱ
አዳምም አዘነ በሔዋን ፈረደ
ሔዋንም አዘነች እባቡ ነው አለች
እባብ ተረገመች አፈራ ባይሆናት
አዳም ተባረረ ሄዋን አለቀሰች
ምድር ተረገመች እሾህ አበቀለች
አቤት ያኔ ነበር ያኔ ጥንት ነበረ
አዳም መበደሉ ሰዎችን ለውድቀት ለሞት መደረጉ
ያኔ ነበር ፅንሱ ሰዎችን ለሽንፈት ለሞት መፈለጉ
ዛሬ ግን ዛሬ ያ የጥንቱ ቀረና
እራሱን አዋርዶ አዳም ከበረና
ሲወለድ በቤተልሔም በነብዩ ተፅፎአልና
አምላክ ተወለደ በከብቶች መና
ታሪኩ ሲተርክ የሰማህ ወንድሜ
ራስክን መርምረው ና ይልሃል ዛሬ
አቤት ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር የአዳም ውድቀቱ
ዛሬ በክርስቶስ ሕይወትን ማግኘቱ
ዛሬስ እኛ ወገን
የያኔ የጥንቱ ትተን ለንስሐ ቀርበን
ስጋውንም በልተን ደሙንም ጠጥተን
በድያለሁ ብለን ከፊቱ ላይ ወድቀን
መመለስ ይሻላል ክርስቶስን ብለን
መመለስ ያሻል ኪዳነ ምህረትን ብለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
መልካም ጥምቅት
መልካም በዓል

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
           #አያምርበት


#ፍቅርህ_የቀመሰ ከማእድህ በልቶ
#ምህረት_የጠገበ ይቅርታን ጠጥቶ
#ምንስ ያምርበታል ደምህን ረግጦ ?
      በምክርህ ተቃኝቶ ተሰርቶ ያደገ
      በመንፈስህ ህይወትን ስቦ እየማገ
      መከራ ቢያይል ተስፋ አለው ለነገ
#በእጅህ_ተዳሶ በረከት ያገኘ
#በፍቅርህ_ጥልቅ ባህር በደስታ የዋኘ
#ምኑ_ማርኮት ይሆን ምድርን የተመኘ ?
      በትእግስትህ በር ወጥቶ እየገባ
     ዳዴን ከአንተ ተምሮ ከአንተው የጠባ
      ግና ዛሬ አድጎ ከወጥመድ ሊገባ
#በሰላምህ ምርኩዝ በደስታህ ዘይት
#ነፍሱ_የመገብሃት ቃልህ ያጠገብሀት
#ከአንተ_ሌላማ ጌጥም አያምርባት
      ድቅድቁን ጨለማ ረግጦ የመጣ
      ይቅርታን ተምሮ ለቂም ቦታ ያጣ
      እንዴት ያምርበታል ከቤትህ ቢወጣ ?
#ጠረንህን_ለምዶ ግሩሙን መዓዛ
#ምንጩ_ቀራኒዮ የህይወቱ ለዛ
#የነበረው_ፍሬ ስለምን ይጠንዛ ?
   መኖሪያ አጥሩ መሸሸግያ ቅጥሩ
   ለሆንህለት ጥላ እንዲፀና ስሩ
 #አያምርበት_ቢርቅ ቢስት ከመስመሩ 🙏
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
           #ወይ_ማወቅ_ደጉ !


#በባህር_በጥልቁ በሰማይ ተማክሮ
#ሊወጋው_ምስኪኑን ሃይል አስተባብሮ
#ሄደ ከምስኪኑ ሰፈር
ሊያጠፋው መታሰቢያው ሳይቀር
ዉጣ ይለይልህ ኪዳን አለኝ ማለት
ፀሎቱ መዝሙሩ አይደለም ከማጀት
ይህን ሁሉ ፉከራ የሰማው ምስኪን ሰው
ወዬው ጠፋሁ ብሎ ፍርሃት ብርክ ያዘው
የሞት ሞቱን ጨክኖ ብቅ ቢልባቸው
#የያዙት_መሳሪያ ወደቀ ከጃቸው
#እግሬ_አውጭኝ እግሬ አውጭኝ
እያሉ በሽቅድምድም
ሄዱ ከመጡበት አለም
#ይህ ሁሉ የሆነው..ምክንያቱ ምንድነው?
#ጋሻ ጦር አልያዝኩኝ....ይሄው ባዶየን ነኝ
#ምን አይተው ሮጡ......ሊገሉኝ የመጡ
እያለ ምስኪኑ ግራ እየተጋባ
ግድግዳው ላይ ካለው መስታወት ተጠጋ
ድንገት ቀና ብሎ ፊቱን ቢመለከት
#ለካስ_የኢየሱስ ደም በግንባሩ አለበት
#አሃ ! ደሙን አይተው ነው የተመለሱት
ወይ ማወቅ ደጉ!
#ለካስ_መፍትሄው ግንባርን ማሳየት
#ያኔ_ይመለሳል ሰይጣን ከመጣበት ። 🙏
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
፨እናምናለን በምስጢረ ጥምቀቱ፨
በመጋቤ ምስጢርነቱ
በመንግሥተ ሰማይ በርነቱ
ሰው ካልተወለደ ከውኃና ከመንፈስ
ሕይወት እንደሌለው ርስት እንደማይወርስ
ያመነ የተጠመቀ ይድናል
በጥምቀቱ ልጅነት ያገኛል
ባያምን ባይጠመቅ ከልጅነቱ ይወጣል
ኢጥዮጵያዊው ባኮስ በሐዋርያው በፊሊጶስ
ከነቤተሰቦቹ እስጢፋኖስ
ቅዱስ ጳውሎስ ከደማስቆ መልስ
በጥምቀት ተወልደዋል ከመንፈስ ቅዱስ
ሔዋን በሰማንያ አዳም በአርባ ቀኑ
ገነት እንደገቡ ልጅነት እንዳገኙ
ሴቶች በሰማንያ ወንዶች ደግሞ በአርባ
ልጅነት እንዲያገኝ ተጠምቆ እንዲገባ
እናምናለን በእውነት
ያለጥርጥር በእምነት፡፡

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ...!!!
በዓሉ የሰላም የጤና የንስሐ እንዲሆንላችሁ ምኞታችን ነው....!
*:ጊዜ ምን በደለ;*
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እውነትን ደብቀን ሀሰትን አንግሰን
አባቶች እያሉ ልጆች እያስተማርን
አርብ እሮቡን ሳናውቅ ሁልጊዜ አየበላን
ቤቱ መመላለስ ጭራሹን አቁመን
*
*
የእግዛብሔርን መቅደስ በሀጢያት ስንሞላ
እንደሰዶም ሆነን ህግን ስንጠላ
አህዛቦች ሲቀድሙን እኛ ቁመን ሇላ
ፀጋችን እያለ እሱን ሳናውቅበት ስንፈልግ ሌላ
*
*
የምንጓዝበት መንገዱ ረዝሞብን ቤቱ መሄድ ሲቀር
ሀይማኖት በገንዘብ እንደስም ሲቀየር
መፅሀፍትን ሳናነብ አባቶች እግር ስር ቁጭ ብለን ሳንማር
ቅዱስ ሁኑ ተብለን ምርጫችን ሲቀየር
*
*
ውበት ከአምላክ በላይ እኛ ስንሰራ
ቀለም እያማረጥን አለምን ስንመርጥ አምላክን ሳንፈራ
ማህሌት አዳር ትተን ስንመርጥ ጭፈራ
ሀብታችን ሀጢያት ገዝቶ ሲያስመስል ተራራ
*
*
ልብሳችንን ጥለን እርቃንን ስንመርጥ
በማናውቀው አለም ከላይ ሁነን ሳለ ወደ ታች ሰንዘቅጥ
አማርጠን ስንበላ ከደረቅ እስከ ቁርጥ
በደካማው ስጋ ለነፍሳችን ስንቅ ጭራሽ ሳናስቀምጥ
*
*
አወቀን ብለን ሳናውቅ በትቢት እየተጓዝን
ምርጫችን ከኛ በልጦ እኛኑ ሲመክረን
አልመለስ ስንል አምላክ እላይ ሁኖ በትዝብት ሲያዩን
ፍርጃ እላይ ቆመን ጌታ ሊመዝነን
እኛ ከሱ በልጠን ጭራሽ ፈራጅ ሁነን
*
*
ክፋትን አንግሰን ጠፋቶብን በጎነት
የውጩን አድንቀን ስንጓዝ በስህተት
ምርጫችን ተምታትቶ ስናማርጥ ውሸት
ሚስጥሩን ሳናውቀው ለመፋረድ ስንዋትት
*
*
በል በትርርህን አፅና የሚባል ሲጠፋ
መገንዘብ ሲያቅተን ምንድነን እንደሆነ የወደፊት ተስፋ
በማይጠቅም ህይወት ስንማስን ስንለፋ
ማወቁ ሲጠፋን ሁሉም ሟች መሆኑን ጠብቆ ወረፋ
*
መቶ ለማይሞላው ለዚህ አጭር እድሜችን
ምን ለማይጠቅመው እንጨነቃለን ለአፈሩ ስጋችን
አድሜአችን ሲቀንስ ከግባራችን ሲለቅ ፀጉራችን
መመለስ ሲያቅተን ዛሬ ነገ እያልን ሲመርሽ ቀናችን
*
አባቶችን ሰምተን ታሪክ ካልጠበቅን
ዘመናዊነት ሚስጥሩ ካልገባን
በአምና ተምረን ዘንድሮ ካልነቃን
ጊዜ ምን በደለ በሱ የፈረድን
*
ጊዜማ ሂደት ነው ድሮም የነበረ
እራሱን ሳይለውጥ ይሆን ሁሉ ዘመን በክብር የኖረ
ታዲያ ምን አጠፋ በሰው ተደፈረ
ንገረኝ ወንድሜ(ቴ) ጊዜ ምን በደለ":;"""''!?
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
የሚያጠፋት የለም።


ማዕበሉ ቢነሳ ቢነፍስ ነፋሱ
እሳት ቢንቀለቀል ቢጥጎለጎል ጢሱ
ሰይፎች ቢመዘዙ አበው ቢታረዱ
ወጣት አዛውንቱ እስር ቤት ቢወርዱ
ሰባኪው ዘማሪው ከመድረክ ቢባረር
መነኩሴው ካህኑ ወሕኒ ቢወረወር
ያንሰራራል እንጅ የስም አጠራሯ
ገኖ ያድራል እንጅ ተጽፎ ተአምሯ
የሴረኞች ሴራ እየተነገረ
መዝሙር በስማቼው እየተዘመረ
የሚያፈርሷት ፈርሰው
የሚያጠፏት ጠፈተው
የሚያነዷት ነደው
ጎስቁለው ተዋርደው
እናያለን እንጅ ኑራ ለዘለዓለም
ቤተክርስቲያንን የሚያጠፋት የለም።
አብ እሳት ወልድ እሳት ተብሎ ተቀድሶ
መንፈስ ቅዱስ እሳት ተብሎ ተወድሶ
ጠላት ቢያቃጥላት በእሳት ለኩሶ
እሳት ነው አምላኳ ያቃጥላል መልሶ
አወ እሳት ነው መንፈስ ቅዱስ
እሳት ነው ጰራቅሊጦስ
አሳት በላዒ ለአማፂያን
ወአቃጣይ ለከሀዲያን
ስሙን ለሚክዱ
መቅደሱን ለሚያዋርዱ
እንደቆሬ ካሕናት
የሚያቃጥል ሕያው እሳት
እንደ አዛርያስ ለቀነጣ
ግምባርን በለምጽ የሚቀጣ
በምድሩ እሳት በደካማው
ጥፋት ጥፋት በሚሰማው
የማይጠፋ እሳት ላያጠፉ
አሕዛብ በከንቱ ቢለፉ
ከንቱ ልፋት ከንቱ ድካም
ፍላጎትን አያሳካም
ዱለት ቢደወለት ቢፈጭ ቢቦካ
በግፈኞች ሚዛን ግፋችን ቢለካ
ጠላት ሰይፍ አንግቦ ቢሸልል ቢያሽካካ
ቤተክርስቲያን ክብሯ ሳይነካ
ትኖራለች እንጅ ጸንታ ለዘለዓለም
የክርስቶስን ቤት የሚያፈርሳት የለም።
አሕዛብ መናፍቃን በርሷ ላይ ቢነሱ
ሰይፍ ተሸክመው እሳት ቢለኩሱ
በሔሮድስ ቁጣ በክብሯ ቢዝቱ
አዋጅ አስነግረው በጋራ ቢዘምቱ
ከክርስቶስ ጋር ነው ፍልሚያው ጦርነቱ።
ያኔ ሰይፍ ያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ
ጉድጓድ የቆፈሩም በጉድጓድ ያልቃሉ
አሕዛብ መናፍቃን ይህነን አውቃችሁ
የሰይፍ የመሣሪያ ወጩን ቀንሳችሁ
ልብ እንድትገዙበት ልቦና ይስጣችሁ
ትኖራለች እንጅ ፀንታ ለዘለዓለም
ቤተክርስቲያን የሚያጠፋት የለም።
አንተ ግን አደራ
አንተ ግን አደራ በአፄ ካሌብ ገድል
በአብርሃና አጽብሃ በሰላማ መስቀል
በአቡነ አረጋዊ በክርስቶስ ሰምራ
በተክለሃይማኖት በነላሊበላ
በብርብር ማርያም በአክሱም በዝቋላ
በኤሊ ገብርኤል በደብረ ሊባኖስ
በደብር ማርያም በመስቀለ ኢየሱስ
በመስቀሉ ግማድ በግሸን ማርያም
በአቡነ ዐሮን በአሰቦት ገዳም
ምሥራቁ ምእራቡ ሰሜኑ ደቡቡ
ሁሉም በእምነቱ ሁሉም በማተቡ
ባንጃበበው ስቃይ መከራ ሰቁቃ
በቼልታ እንዳታልፍ ክርስቲያን ሲጠቃ
የተኛህ ተነሳ ያንቀላፋህ ንቃ
አንተ ለዘር ለጎጥ ስትገነጣጠል
ለወንዝ ለተራራ ልብህ ሲንጠለጠል
የወለጋን መቅደስ ለፓስተር እንትና
አርባምንጭ ጎፋን ለመንፈስ ትወና
የዝቋላን ገዳም ለኢሉማንቱ
ቅዱስ ላሊበላን ለ666ቱ
ጎንደርን ለጅዳ አክሱምን ለመካ
አማጭ እንደላኩ አልሰማህም ለካ
አንተ ግን አደራ ክርስቲያን ወገኔ
የደም እዳ አለብህ ከፈሰሰው ያኔ
በዮዲት ጭፍጨፋ በግራኝ ወረራ
ያጥንትና የደም አለብህ አደራ
ማነምን ሳታፍር ማነምን ሳትፈራ
መቅደስህን ጠብቅ ካባቶችህ ጋራ
አንተ ግን አደራ
አገልጋይ ካሕኑ
አማኙ ምእመኑ
የአቋቋም ምሁሩ
በላዜማ ባለመዝሙሩ
የቅኔው ዘራፊ
የድጓው ፀሐፊ
የዝማሬው የቅዳሴው
የትርጓሜው የውዳሴው
፬ ዓይናው ልበ ሰፊው
አስተዳደሩ ሀላፊው
መነኮሱ ቆሞሱ
ኤጲስ ቆጶሱ ጳጳሱ
የቴውሎጅው ተመራቂ
የምሥጢራቱ አርቃቂ
ሰንበት ተማሪው ማሕበራቱ
ማሕበረ ቅዱሳን ባለሕጉ
ደጆችሽ አይዘጉ
ኦረቶዶክሳዊ በሙሉ
ተማማለህ በመስቀሉ
ጠብቅ ያንተን አደራ
እንዳትሽሽ አንዳትፈራ
እንደበግ ጨው እያላሱ
እያሳሳቁ እያወደሱ
እያጠጋጉን ወደነሱ
ደሮን በጥሬ እንዲጥሉ
ሊበሉን እያታለሉ
ማዕዳቼውን ሊያቀርቡ
በደማችን ከታጠቡ
ይበቃል ከዚህ በላይ
ማን አታላይ ማን ተታላይ
ማንስ አግላይ ማን ተገላይ
ማን ሆነና ባለርስቱ
የሀገር መሠረቱ
የሀገር ፍቅርን እየመገብነ
እኛው አቅፈን ባሳደግነ
ከአውሮፖውያን ተልኮ
ከዓረብ ልጅ ልጁን ልኮ
እኛን እኛን ከገፋ
ድብቅ ሴራውን ካስፋፋ
አንተ ግን አደራ
እንዳትወሰልት እንዳትፈራ
ክርስቶስ የወለደህ
እስከሞት የወደደህ
በፍቅሩ ያሳደገህ
አንተንማ ምን አስፈራህ
ያምላክህ ስራ የተጻፈ
ሞትን በሞት ያሸነፈ
ሰይፍ አትሻ የገዘፈ
ሰይፍ አለህ የረቀቀ
ጎልያድን ያወደቀ
ሰይፍ አለን ባንገታችን
ማተባችን መስቀላችን
ሰይፍ አለን በእጃችን
ዳዊታችን ድርሳናችን
እንጠብቅ አደራችችን።
ጸልዩ በእንቲያነ ስለኛ ጸልዩ ።
አቡነ ናትናኤል አቡነ ፊሊጶስ
አቡነ አረጋዊ አባ መርሓ ክርስቶስ
አባ መልከ ጼዴቅ ወአባ ሰላማ
አቡነ አረጋዊ አቡነ ገሪማ
በአንድነት ሁናችሁ በገነት ከተማ
ስለኛ ጸልዩ ድምፃችሁ ይሰማ፡
ኦርቶዶክሳውያን እንደበግ ታርደዋል
አብያተ ክርስቲያን በእሳት ተቃጥለዋል
ቅዱሳት ንዋያት እንደጧፍ ነደዋል
ክርስቲያኖች ሁሉ ለመኖር ሰግተዋል
በግፈኞች ሰይፍ ተከበው ቁመዋል
ሱማሌ ጅግጅጋ ጅማና ሲዳማ
መለውና ጎፋ ያገሬ ከተማ
ኦርቶዶክሳውያን እየተሰደዱ
ካህናት ሊቃውንት እየተዋረዱ
ቅዱሳን ቦታዎች እየተነጠቁ
ምእመናን ካህናት እየተጨነቁ
እጅግ ስለበዛ ግፉና ስቃዩ
አሳስቡን ከጌታ ስለኛ ጸልዩ
➴ ከመምህር ኤፍሬም ተስፋ

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
፨ጊዜዬን ባርክልኝ፨
በዝናብ አብቅለህ በፀሐይ አብስለህ
የምትመግብ ጌታ ሁሉን አዘጋጅተህ
ነጻነቱን ሰጥተህ ጥበቡን አድለህ
እዚህ ላደረስከኝ ምስጋና ይድረስህ
ሁሌም ጠብቀኸኝ በምሕረት ጥላ
ጊዜን ባርክልኝ ሰርቼ እንድበላ
ከፍጥረታት ሁሉ አልቀህ ፈጥረኸኝ
የጸጋን ገዢነት በፍቅርህ አድለኸኝ
ከቤትህ እንድኖር ርስትአውረሰኸኝ
ለዚህ ያበቃህኝ ከቶ እኔ ማነኝ
ያለኝ ምስጋና ነው አምላክ ክበርልኝ
እኔ ስበድልህ አንተ ስትምረኝ
በምሕረት ታግለህ ፈጥነህ ሳታጠፋኝ
ንስሐ እንድገባ ጊዜን ባርክልኝ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
የፈጣሪ ችሎት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አባ ተቀምጠው ከሾላ
ለሊት አድርሰው ምህላ
ሲጠባበቁ ፅድቂቱን
ሲኖሩ ሲኖሩ አንድ ቀን
ያባን ዛፍ ላይ መኖር
ሽፍቶቹ ተረድተው
ጠጋ አሉ ከሥፍራቸው
አባም በጥርጥር
ዓይናቸው ሲማትር
አባ አባታችን
አንድ ገዜ ይስሙን
የቃየል መንፈስ እየተከተለን
አንዳች ሳንበደል
ብዙ ነፋስ አጠፋን
ግብራችንን ትተን
ንስሐ ሰጥተውን
ከራሶት እንድንሆን
ፍቃዶት ይሁነን!
አባም በተራቸው
የፈጣሪ ጥሪ እየገረማቸው
እንደዚህ አሏቸው
እኔ ካለሁበት
መራሩ ምግቤ ነው
የአራዊቱ ዜማ
ጣዕመ ዜማዬ ነው
እንደኔ ለመሆን
ፍፁም ከሻታችሁ
የጠራችሁ አምላክ
ፅናቱን ይስጣችሁ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
#ምንም_አይምሰልህ
የምትሰራው ሥራ ሰውን ካልበደለ፤
ክፋትና ተንኮል በልብህ ከሌለ፤
ጠንቅቀህ ከፈጸምክ ማድረግ ያለብህን፤
ለማንም ሳታድር ካመንክ አምላክህን፤
ላንተ ጥቅም ብለህ ካልጎዳህ ሌላውን ፤
ይቅርታ ከጠየቅህ አምነህ ጥፋትህን፤
የምታውቀው ታሪክ የምታውቀው ነገር፤
እንዳልሆነ ሁሉ ሲወራ ሲነገር ፤
የለብህም እና ዝም ብሎ መስማት፤
ቀስ ብለህ ብትሞክር እርማት ለመስጠት፤
ከኛ ሌላ አዋቂ ፍጹም የለም ባዮች፤
የወሬ አንበሳ የተግባር አንካሶች ፤
የነገር ሱሰኛ የወሬ ጥመኞች፤
ምንም እንደማታውቅ አድርገው ቢቆጥሩህ ፤
ዕውቀቱ ከአንተ ጋር እና ምን ቸገረህ፤
አምላክ ካንተ ጋር ነው ምንም አይምሰልህ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
#ነበርኩ_መች_ያድናል
@Mgetem

ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!

@Mgetem
@Mgrtem
@Mgetem_bot
የፈጣሪ ችሎት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አባ ተቀምጠው ከሾላ
ለሊት አድርሰው ምህላ
ሲጠባበቁ ፅድቂቱን
ሲኖሩ ሲኖሩ አንድ ቀን
ያባን ዛፍ ላይ መኖር
ሽፍቶቹ ተረድተው
ጠጋ አሉ ከሥፍራቸው
አባም በጥርጥር
ዓይናቸው ሲማትር
አባ አባታችን
አንድ ገዜ ይስሙን
የቃየል መንፈስ እየተከተለን
አንዳች ሳንበደል
ብዙ ነፋስ አጠፋን
ግብራችንን ትተን
ንስሐ ሰጥተውን
ከራሶት እንድንሆን
ፍቃዶት ይሁነን!
አባም በተራቸው
የፈጣሪ ጥሪ እየገረማቸው
እንደዚህ አሏቸው
እኔ ካለሁበት
መራሩ ምግቤ ነው
የአራዊቱ ዜማ
ጣዕመ ዜማዬ ነው
እንደኔ ለመሆን
ፍፁም ከሻታችሁ
የጠራችሁ አምላክ
ፅናቱን ይስጣችሁ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
በቃሉ ታክሜ
፨፨፨፨፨፨፨

ልጄ ሆይ ወዴትነሽ የት አለሽ እያለ
የወደቅኩበትን እየተከተለ
ሊያነሳኝ ሲመጣ ድምፁን ከፍ አድርጎ
ሀጢያቴን ረስቶ ከጥልቁ ሸሽጎ
ኮቴውን ሰማሁት ሲመጣ ወደኔ
ከእንግዲህ ሊበቃኝ የሐጥያት ኩነኔ
ጣቢታ በማለት ልጁን ይጠራኛል
ከያዘኝ የቁም ሞት ይቀሰቅሰኛል፡፡
ከዛም እነቃለሁ አልተኛም ደግሜ
ተነሽ ብሎ ሲለኝ በቃሉ ታክሜ።

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
https://youtu.be/WlfhrFA1K2w

እህታችን ስብስክራይብ ሼር እርጉላት በፍቅር ስም

ፍቅር ሁሉም አሽናፍ ነውና
2025/07/08 02:00:59
Back to Top
HTML Embed Code: