Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channel Manneger፹)
መስቀል እና ኢትዮጵያ
@boaneerges
መስቀል ማለት የተመሳቀለ ዕፅ/ እንጨት/ ማለት ነው፡፡ መስቀል በብሉይ ኪዳን ላይ/ በኦሪት ህግ/ የእርግማን ምልክት ነበረ፡፡ ‹‹በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚእሄር ዘንድ የተረገመ ነው፡፡›› (ዘዳ 21፣23) ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪሰቀልበት ድረስ የእርግማን ምልክት ተደርጎም ይወሰድ የነበረ ነው፡፡ ከክርስቶስ ስቅለት በኀላ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእንጨት/ዕፅ/ ምክንያት ከገባንበት እርግማን በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ከእርግማናችን ነፃ አውጥቶናል፡፡ስለዚህ ቅዱስ መስቀል የእርግማን ምልክት መሆኑ ቀርቶ የድኅነት ምልክት ፣የነፃነት አርማ፣ መመኪያችን፣ መዳኛችን፣ ትምክህታችን ሆኗል፡፡
ወደ ርዕሳችን መለስ እንበልና ስለ መስቀልና ኢትዮጵያውያን እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያውያን ስለ መስቀል መናገር ለቀባሪው ማርዳት ቢሆንብንም ባለን ውስን አቅም ግን አይንን ለመክፈት ልብን ለማንቃት የምትሆን ነገር ለመናገር እንሞክራለን፡፡
በአለም ላይ ለመስቀል ቅርብ ከሆኑት ሀገራት መካከል የግንባር ቀደሙን ቦታ የምትይዘው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ምንም እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በጊዜው ጠንካራ የአለም መንግስታት የነበሩት ሲከፋፈሉት ለኢትዮጵያውያን ባይደርስም በ15ኛው ክፍለ ዘመን በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ የንግስና ዘመን ላይ በግብፅ የነበረው የቀኙ ግማደ መስቀል ወደ ሀገራችን ገብቶ በግሽን አምባሰል ተራራ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡ለምን ወደ ሀገራችን ሊገባ ቻለ ለሚለው ሰፊ ማብራሪያ ቢኖረውም እኛ ግን አንድ ነገር ጠቅሰን እንለፍ፡፡ ስለ መስቀሉ ኢትዮጲያ መምጣት ባሰብን ጊዜ ወደ ልባችን ጊዜ አንድ ቃል ሁል ጊዜ ታቃጭላለች ‹‹ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ›› ለዚህች ቃል ብዙዎቻችን አዲስ አይደለንም፡፡ እስኪ አንድ ጊዜ የአዕምሮአችንን ባቡር እናስነሳና የኢትዮጲያን ትክክለኛ ካርታ አሰሳ እንውጣ ማለቴ ኤርትራ ያልተገነጠለችበትን መሬታችንም ለጂቡቲና ለሱዳንና ያልተሸጡባትን ካርታ ማለቴ ነው፡፡ አገኛቹት? አዎ ምልክቱ ምን ይመስላል? ብዙ አትጠራጠር የመስቀል ቅርፅ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ከላይ ባነበብነው ቃል መሰረት ለቅዱስ መስቀል ትክክለኛ ማረፊያ ማነች? ኢትዮጲያ!!! መስቀለኛው ተራራ ደግሞ ግሽን ላይ ነው፡፡
አሁን ደግሞ ኢትዮጲያ ለመስቀል ያላትን ክብርና ቦታ ለሁለት ከፍለን እንመልከት፡
ዕምነታዊ ክብርና ቦታ
ባህላዊ ክብርና ቦታ
❖ዕምነታዊ ክብርና ቦታ፡ ለስንዱዋ እመቤት ለኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መስቀል ማለት የክርስቶስ ምልክት፣ ከሲኦል መከራና ስቃይ የዳነችበት፣ የነፃነት አርማዋና መመኪያዋም ነው፡፡ ለዛም ነው በዕለት ተዕለት አገልግሎቶቿ ላይ መስቀልን በአፏ ትመሰክራለች፣ በወንጌልዋ ትሰብከዋለች፣ በአገልግሎቷ ትይዘዋለች፡፡ ይህም ማለት በመሰረታዊ የሃይማኖት ጸሎቶቿ ውስጥ ‹‹መስቀል ሃይላችን ነው ሃይላችን መስቀል ነው የሚያፀናን መስቀል ነው መስቀል ቤዛችን ነው መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም›› ብላ ዘወትር የምትጸልየውና የምትመሰክረው፡፡
ያዕቆብ ዘአልበረዲ ሰዎች ወደ ክርስትና ዕምነት አምጥቶ በሚያጠምቅበት ሰዓት ሁለቴ ጥምቀት ስለሌለ የተጠመቁትን ካልተጠመቁት ለመለየት በአንገታቸው ላይ ክር ያስር ነበር፡፡ የትውፊት ሁሉ መገኛ የሆነቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስቲያንም የያዕቆብ ዘአልበረዲን ፈለግ በመከተል ልጆቿን ከአሕዛብና ከመናፍቃን ለመለየት በአንገታቸው ላይ የክርስቶስን መስቀል እንዲያስሩ ታስተምራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ስታንፅ በጉልላቷ ላይ መስቀልን የምታደርግበትም ምክንያት መስቀል ለቤተክርስቲያኗ አርማና መለያ ስለሆነ ነው፡፡
በቅዳሴዋና በኪዳኗ ላይም መስቀልን ይዛ ስለ ነፃነታችን ትሰብካለች፡፡ ከመስቀሏ በረከትን እንድናገኝ በካህናቷ ታሳልማለች፣ ትባርካለችም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በአደባባይ ወታ ለመስቀሉ መገኘት ዋነኛ ምክንያት የሆነውን የደመራን በዓል በመስከረም 16 ላይ በድምቀት ታከብራለች፡፡ ከ18ቱ የጌታ በዓላትም አንዱ ነው ብላ ታስተምራለች፡፡
❖ባህላዊ ክብርና ቦታ፡ ኢትዮጵያውያንና ለመስቀል ያላቸው ቁርኝነት ጠበቅ ያለ ነው፡፡ ግንኙነታቸው የሚጀምረው ግማደ መስቀሉ ወደ ሀገራችን ከገባበት ዘመንም ይቀድማል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በስማቸው፣ በአለባበሳቸው፣ በመሀላቸው፣ በተለያዩ ኪነህንፃዎቻቸው ላይ መጠቀማቸው ነው፡፡
ለምሳሌ በ6ኛው ክፍለ ዘመን በሀገራችን ላይ የነገሰውን አፄ ገብረ መስቀልን ልብ ይሏል፡፡
በ12ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጲያ ኪነ ህንፃ ላይ ደማቅ አሻራውን ያኖረው ቅዱስ ላሊበላ የገነባቸው 11ዱ አብያተ ክርስቲያናት መመልከት በራሱ ኢትዮጵያና መስቀል ያላቸውን ግንኙነት በሰፊው ያሳያል፡፡ በተለይም የመስቀል ቅርፅ ያለውን ቤተ ጊዮርጊስን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡
የኢትዮጲያውያንን የባህል ልብስ ለተመለከተ ደግሞ ከላይ ከአንገታቸው አካባቢ በክብ ጥለት ይወርድና በእግራቸው ላይ ከፊት ለፊት በኩል መስቀል ከኃላ ደግሞ ጥለት ተደርጎ ይሰራል፡፡ጥለቱ የአለም ምሳሌ ሲሆን መስቀሉ ደግሞ የመንፈሳዊ ህይወት ምሳሌ ነው፡፡ ይህም ማለት ጥለት የሆነውን አለም ወደ ኃላ ትቼ መንፈሳዊነትን ከፊቴ አስቀድሜያለው ማለት ነው፡፡
አብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችም የዘመን መለወጫቸውን የመስቀል በዓል ላይ ተመርኩዘው ማክበራቸውም ለመስቀልና ኢትዮጵያውያን ግንኙነት እንደማሳያ ነው፡፡
በአጠቃላይ መስቀል በኢትዮጵያና በጵያውያን ላይ በእምነታቸው፣ በባህላቸውና በአመለካከታቸው ውስጥ ታላቅ ሚና ያለው ነው፡፡ ሁላችንም
ስንጀምር አብሮን የነበረ እስክንፈፅም የረዳን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ የመስቀሉ ፍቅርና በረከት በሁላችን ላይ ይደር፤ አሜን!!!
‹‹ወስበሀት ለእግዚአብሄር፣ ወለወላዲቱ ድንግል፣ ወለመስቀሉ ክቡር››
ተፃፈ በናሆም ግርማ
@Boaneerges
ለአስተያየት እና ጥያቄ
@AskBoaBot

#ተዋሕዶ
@Mgetem
በመንገድ ላይ ስብከት ያልተገኘች ነበጊታር ፒያኖ በጭፈራ ያልኖረች
ከመፅሀፍ ቅዱሱ አንዱን ያልዘዘለለች
አስቲ ለምሣሌ
የቅዱሣን ፃድቃን ምልጃቸውን ንቀው
ሰማዕታት የሞቱት ለይምሰል ነው ብለው
ዘመናዊ ሀይማኖት ይሻለናል ያሉ
በዘመን አመጣሽ ጌታን ተቀበሉ በአስመሳይ ትህትና ሰውን የሚያታሉ
በአለት ድንጋይ ላይ አሉ የበቀሉ
ሌላም አለ ደግሞ በጨረቃ ያመነ
በጨረቃ ስግደት ልቡ የደነደነ
በየዘመናቱ ሀይማኖት ተነስቶል
ለፅድቅ እና ለእዉነት ማን እንዳንቺ ሆኖል
በዘመን ቅብብል ምንሽ ተቀይሯል
እንደ ተዋህዶ በአምላክ የከበረ አረ የት ይገኛል
አቃጥልናት ያሉ የሉም በምድር ላይ
ተዋህዶ አዲስነሽ ሁል ጊዜ እንደ ሠማይ
ገና ትደምቃለሸ በዓለም አደባባይ
ክብርሽ ክርስቶስ ኤልሻዳይ አዶናይ
©ወልደ ሰንበት
@Mgetem
@Mgetem
@solasc

ውድ ቤተሰቦቻችን እባካችሁ ለሁሉም ይድረስ ይህ መልዕክት አሁን ምንኖርባት ጊዜ ፈተና መከራ ስርማህትነት የተመላች ናትና
ይድረስ ለሁሉም የተማማርናትን የእውነት ቃል እንተግብራት እባካችሁ እንጸልይ እናልቅስ እንመለስ
#እባካችሁ #እንጸልይ #እናልቅስ በእንባ ወደ እርሱ እንመለስ
#አምላክ ይታረቀን ዘንድ
#እንጸልይ
#እናልቅስ
ያወቅናትን ትንሽ እውነት እንኑር አምላክን እንማጸነው
#ስለ ሀገራችን ሰላም
#ስለ ካህናት አባቶቻችን
#ስለ ዲያቆናት ወንድሞቻችን
#ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን
#ስለ ህዝባችን
#ስለ በደላችን
#ስለ በዛው ኃጢአታችን
ስለ ሀገራችን ሰላም እናልቅስ እንጸልይ እንመለስ እባካችሁ አንድ እንሁን አምላክ ይታረቀን ከመሃቱ ይጠብቀን ዘንድ
#እንጸልይ #እናልቅስ
#ውድ ቤተሰቦቼ ስለ እውነት ንጽህት ስለ ሆነች ስለ እመ አምላክ እማጸናችኃለሁኝ
ከአሁኑዋ ሰዓት ጀምሮ እናልቅስ ስለ ሁላችንም ሰላም እባካችሁ እናልቅስ አምላክ ይታረቀን ዘንድ
የበረከት ሀገራችውን ቅዱሳን ያስምሩልን ዘንድ እባካችሁ እንጸልይ
#ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት
#ስለ አቡነ ሀብተ ማርያም
#ስለ አቡነ ዜና ማርቆስ
#ስለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
#ስለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#ስለ አቡነ ገብረ ክርስቶስ
#ስለ አቡነ አረጋዊ
#ስለ አቡነ ተክለ ሐዋርያት
#ስለ አቡነ ክርስቶስ ሞዓ
#ስለ አቡነ አባ ክርስቶስ ቤዛነ ስለ ቃልኪዳን ሀገራቸው ምህረትን ያሰጡን ዘንድ #እንጸልይ #እናልቅስ
#ሼር እናድርግ
ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በአንድነት የቤተክራቲያን ድምጽ እንስማ እንተግብር እንዳን የንስሃ እድሜ ይሰጠን ዘንድ ለማይረባ ከንቱ ሞት አሳልፎ እንዳይሰጠን እንጸልይ እናልቅስ እንመለስ
ሁላችንም በአንድነት በንቃት እንመላለስ እንጠንቀቅ
በእየ ቤተክርስቲያናችን ተሰባስበን ምዕላ እናድርስ ከአባቶቻችን ጋራ በእየ ቤታችን በለቅሶ እንጸልይ እንማጸን እንላለን።
አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅ
ይባርክ
ሁላችንንም ለተከበረ ሞት ያብቃን።
ሼር እናድርግ እባካችሁ ሁላችንም ቢያንስ 21 እህት ወንድሞቻችን ይደርሳቸው ዘንድ ሼር እናድርግ
Helansan
https://www.tg-me.com/joinchat-D81j2AzEDRapYwTb2nWMsQ

#እስከዛው_ተኝቼ_ልክረም
@Mgetem
ጌታ ሆይ!
በምድር በዚች ዓለም ላይ - ጥቂት ቀናትን መክረሜ፣
አሳዝኖህ አዝነህልኝ - ከጨመርክልኝ ዕድሜ፣
የአቤሜሌክን እንጂ - የማቱሳላን አልሻም፣
ከ60 ዓመታት እንቅልፍ የ9 ምዕት ኑሮ አልመርጥም፡፡
እንደማቱሳላ ኖሬ - ከድህነት ከምታገል - መከራ ችግርን ከማይ፣
በጎዶሎዋ ምድር - ሳይሞላልኝ ከምሰቃይ፣
60 ዓመት ላንቀላፋ - ዘመነ እንቅልፍ ስጠኝ ከላይ፡፡
ለተዳከመው ገላዬ - ኑሮ ላዛለው አካሌ፣
ልትጨምርልኝ ከዳዳህ - ለዕጣ ፈንታ ለዕድሌ፣
የእንቅልፍ ዕድሜን እንጂ - ቀን አልሻም የመከራ፣
መተኛት እንጂ መቅበዝበዝ -ይቅርብኝ ጌታ አደራ፡፡
እንደ ፃድቁ አቤሜሌክ - ኢትዮጵያዊ ነኝና፣
እንደው የዘር ሆኖብኝ - መተኛት ያምረኛልና፣
እንዳልሠራ እንድጋደም፣
ጥፋቷን መድማቷን ከማይ - የሀገሬን ርሃብ ጥም፣
ሲመቻት ብቻ ቀስቅሰኝ እስከዛው ተኝቼ ልክረም፣
እንዳንቀላፋ እንዳልደክም፣
ዘመነ እንቅልፍን ስጠኝ - ዕድሜ አድለኸኝ ልጋደም፣
መቼስ ስስት አያውቅህም፡፡
©ዘሕሊና
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨
(- አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ 66 ዓመት በተዐምር
እንዲተኛ የተደረገ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ /ትንቢተ ኤርሚያስ/
- ማቱሳላ 969 ዓመታትን የኖረ፣ በዕድሜ የሰውን ዘር ኹሉ የሚበልጥ
ነው፡፡ /ኦሪት ዘፍጥረት/
- የአቤሜሌክ 66 ዓመት መተኛት 60 መባሉ፣ የማቱሳላም 969 ዓመት
ዕድሜ 9 ምዕት/9 መቶ/ መባሉ አጠጋግቶ መቁጠር የአባቶች ልማድ
በመኾኑ ነው - 318ቱን ሊቃውንት ሠለስቱ ምዕት፣ 72ቱን ሊቃናትን
ሰባው ሊቃናት እንዲል፤)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

#ሰማያዊ_ፓርቲን_ይምረጡ
@Mgetem
ምርጫ ደርሷል። ማንን ለመምረጥ አስባችኋል? እኔ “ሰማያዊ ፓርቲ”ን ብያለሁ። ደሞ ሌላ እንዳታስቡ አደራ። “አባ ፣ አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ በጥምቀት የምታድለው ፤ “ሃገራችን በሰማይ ነው” ብለን ምንመካበትን ሰማያዊ ዜግነት ምታጎናጽፈው ፤ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም መንግሥተ ሰማያት ምታወርሰውን ሰማያዊ ተቋም “ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን” ማለቴ ነው።
የምርጫ ምልክቷ - መስቀል
ማኒፌስቶ - ወንጌል
ጽ/ቤት ቅርንጫፍ - አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በራፍ
የፓርቲው መሥራችና ሊቀመንበር - መድኃኔዓለም (ስሙ ይክበር)
ምክትል - ድንግል
የቦርድ አባላት - ቅዱሳንና ቅዱሳት
፨ ሰማያዊ ፓርቲ ተዋሕዶን ይምረጡ ፤ ጽፈው አጥፈው በልቡና ኮሮጆ ያስቀምጡ!! ፨
___________
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc

ለካስ ዛሬም አለ
(የኃዘን እንጉርጉሮ)
በዲ/ን ሕሊና በለጠ
@Mgetem
ትዕቢት ያጀገነው
ራሱን መውደዱ ልቡን ያሳበጠው
አምላኩን ለመግደል ሰይፍ የመዠረጠው
እንደ ነዳጅ ረግጦ ሰይጣን 'ሚሾፍረው
የጋኔን መኪና ሄሮድስ የተባለ
144 ሺህ ጠርቶ የገደለ
ለካስ ዛሬም አለ።
ጳውሎስ ቃል ሲያወጣ ጴጥሮስም ሲፈውስ
'ግደል' የሚል ጋኔን ከአንጀቱ ተጣብቆ ክፋቱ 'ሚላወስ
ከነገሥታት መኻል ኔሮን የተባለ ነበረ አንድ ቀውስ።
የስንቱን ከተማ መኖሪያ አቃጠለ
አንዱን በሰይፍ ጣለ
በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ አንዱንም ሰቀለ።
ለካስ ንጉሥ ኔሮን ዛሬም ሰይፉን ስሏል
ዘቅዝቆ የመስቀሉ ሥራውም ቀጥሏል
መቅደሱን አቃጥሎ እሳቱንም ሞቋል
እንደ በቆሎ እሸት የሰው አካል ጠብሷል
ለካስ ዛሬም ኖሯል!
በቅድስቲቱ አገር ባገሬ በ'ማማ
ከጥንት ግፍ መኻል ምን አለ ያልተሰማ?
መንኮራኩር ሠርቶ አካል የሚፈጨው
የሰው አካል ገፎ የሚነሰንስ ጨው
ከአንበሳ 'ሚያታግል
በዕብን ወግሮ 'ሚገ'ል
በቁም አሥሮ 'ሚያነድድ
ቆዳ 'ሚቀረድድ
እንደ ጥንቱ ኔሮ
እልፍ ነው ዘንድሮ።
ግራኝ ግብሩ አልሞተም ሕያው ነች ዮዲትም
መቅደስ ሚያነድና ካህንን የሚሰድ አይታጣም የትም።
የነ ሜንዴዝ እሾኽ መቼ ተነቀለ?
ይኸው አመርቅዞ ስንት አማኝ ገደለ።
በአየር ላይ በሮ መርዙን የረጨብን ጥልያን መች ጠፋ
መርዝ የሚያዘንብ ኪይ ቦርድ በዘመኑ አየር ቀጥሏል ቀጠፋ።
እነ ሄሮድስ አሉ
እነ ኔሮን አሉ
እነ ግራኝ አሉ
እነ ዮዲት አሉ
ድምጥያኖስ አለ ዲዮቅልጥያኖስ
የጋኔን ቀኝ እጅ የዲያቢሎስ በርኖስ::
መክስምያኖስ አለ አማኝ እየቀጣ
ቆስጠንጢኖስ 'ሚባል ንጉሥ እስኪመጣ
______
@Mgetem
@Mgetem
(የኃዘን እንጉርጉሮ)
በዲ/ን ሕሊና በለጠ
@Mgetem
ትዕቢት ያጀገነው
ራሱን መውደዱ ልቡን ያሳበጠው
አምላኩን ለመግደል ሰይፍ የመዠረጠው
እንደ ነዳጅ ረግጦ ሰይጣን 'ሚሾፍረው
የጋኔን መኪና ሄሮድስ የተባለ
144 ሺህ ጠርቶ የገደለ
ለካስ ዛሬም አለ።
ጳውሎስ ቃል ሲያወጣ ጴጥሮስም ሲፈውስ
'ግደል' የሚል ጋኔን ከአንጀቱ ተጣብቆ ክፋቱ 'ሚላወስ
ከነገሥታት መኻል ኔሮን የተባለ ነበረ አንድ ቀውስ።
የስንቱን ከተማ መኖሪያ አቃጠለ
አንዱን በሰይፍ ጣለ
በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ አንዱንም ሰቀለ።
ለካስ ንጉሥ ኔሮን ዛሬም ሰይፉን ስሏል
ዘቅዝቆ የመስቀሉ ሥራውም ቀጥሏል
መቅደሱን አቃጥሎ እሳቱንም ሞቋል
እንደ በቆሎ እሸት የሰው አካል ጠብሷል
ለካስ ዛሬም ኖሯል!
በቅድስቲቱ አገር ባገሬ በ'ማማ
ከጥንት ግፍ መኻል ምን አለ ያልተሰማ?
መንኮራኩር ሠርቶ አካል የሚፈጨው
የሰው አካል ገፎ የሚነሰንስ ጨው
ከአንበሳ 'ሚያታግል
በዕብን ወግሮ 'ሚገ'ል
በቁም አሥሮ 'ሚያነድድ
ቆዳ 'ሚቀረድድ
እንደ ጥንቱ ኔሮ
እልፍ ነው ዘንድሮ።
ግራኝ ግብሩ አልሞተም ሕያው ነች ዮዲትም
መቅደስ ሚያነድና ካህንን የሚሰድ አይታጣም የትም።
የነ ሜንዴዝ እሾኽ መቼ ተነቀለ?
ይኸው አመርቅዞ ስንት አማኝ ገደለ።
በአየር ላይ በሮ መርዙን የረጨብን ጥልያን መች ጠፋ
መርዝ የሚያዘንብ ኪይ ቦርድ በዘመኑ አየር ቀጥሏል ቀጠፋ።
እነ ሄሮድስ አሉ
እነ ኔሮን አሉ
እነ ግራኝ አሉ
እነ ዮዲት አሉ
ድምጥያኖስ አለ ዲዮቅልጥያኖስ
የጋኔን ቀኝ እጅ የዲያቢሎስ በርኖስ::
መክስምያኖስ አለ አማኝ እየቀጣ
ቆስጠንጢኖስ 'ሚባል ንጉሥ እስኪመጣ
______
@Mgetem
@Mgetem
#ማስታወቂያ
#አድሚን_ስለሚፈለግ
ውድ የመንፈሳዊ ግጥም ብቻ ቻናላችን ተከታዮች እንደሚታወቀው መንፈሳዊ ግጥም ቻናላችን እስከዛሬ ድረስ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ሲያቀርብላችሁ የነበረ ቻናል ነው።
ነገር ግን በአድሚኖች እጥረት እና ሥራ መደራረብ ምክንያት ባለፉት 2 ወራት ተቀዛቅዞ የቆየ መሆኑን ከእናንተ በሚመጡ አስተያየቶች ለማወቅ ችለናል። ስለሆነም የቻናላችን አድሚን በመሆን ግጥሞችን ማዘጋጀት እና መልቀቅ የምትፈልጉ 2 አድሚኖች(1 ወንድ እና 1 ሴት) ስለምንፈልግ ፍላጎቱ ያላቹ እና ከታች ያሉትን መስርት የምታሟሉ
@Solasc ላይ አናግሩን።
#መስፈርት
1, ኦርቶዶክስ መሆን
2, በሳምንት 2 ግጥም መልቀቅ የሚችል

#ማን_እንዳቺ
@Mgetem
#ማን_እንደ_አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
#ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
#የአምላክ_እናት ድንግሊቱ
#አማላጅ_ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
#ማን_እንዳቺ አስታራቂ
#ሀጢአተኛን የማትንቂ
#ጆሮ_ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ ተቆርቋሪ
#የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
#አዛኝ_አፅናኝ ንፁህ እንቁ
#ሰው_ረስቶአቸው ለተናቁት
#በሀዘን_መከራ ለወደቁት፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
#ስምሽ_ግሩም_ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
#ዛሬም_እባክሽ_ነይ_ወደኛ ! 🙏
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
@Mgetem
#ማን_እንደ_አንቺ ፈጥኖ ደራሽ
#ሰላማዊት ልብን አዳሽ
አረጋጊ እንባን አባሽ፡፡
ማን እንዳቺ አዛኝቱ
#የአምላክ_እናት ድንግሊቱ
#አማላጅ_ነሽ የፍጥረቱ
ሰውን መላሽ ከስህተቱ፡፡
ማን እንዳቺ የሚየፅናና
የሚያወጣ ከፈተና
ደግፎ ከቅፎ የሚያቀና
#ማን_እንዳቺ አስታራቂ
#ሀጢአተኛን የማትንቂ
#ጆሮ_ዳባን የማታወቂ
መልካም ስራሽ አስደናቂ፡፡
ማን እንደ አንቺ መከለያ
ታማኝ እናት መጠለያ
ቀና መንገድ መታመኛ
የንስሀ በር መግቢያ፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ ተቆርቋሪ
#የማታልፊ የሰው ጥሪ
አቤት ብለሽ አናጋሪ
ሰማያዊት ንግሰት የኛ አብሳሪ፡፡
ማን እንዳቺ ለወደቁት
#አዛኝ_አፅናኝ ንፁህ እንቁ
#ሰው_ረስቶአቸው ለተናቁት
#በሀዘን_መከራ ለወደቁት፡፡
#ማን_እንደ_አንቺ የሚረዳ
የመትሞይ የሁሉን ጓዳ
እባክሽ አውጪን ከዓለም ፍዳ
ሁዋላ ጠፍተን እንዳንጎዳ፡፡
ፀበልሽ ፈዋሽ ያለዋጋ
ለእኛ እኮነሽ ባለ አደራ
እባክሽ አውጪን ከሐጢአት ተራ
እንድንኖር ከአንቺ ጋራ፡፡
መን እንደ አንቺ ያለው ለዛ
ንግግር የሚያዋዛ
በረከትን የሚያበዛ፡፡
ማን እንደ አንቺ ልዩ ስጦታ
አምላክ ያደለን የነፍስ እርካታ
ደስ አለን ዛሬ ዲያብሎስ ሲመታ
መግቢያ መውጪያ አጥቶ ሲሄድ በአንድ አፍታ
#ስምሽ_ግሩም_ነው የህይወት ገበታ፡፡
ማን እንደ አንቺ ታምረኛ
የኔ ላሉሽ ምስጢረኛ
አማላጅ ነሽ እውነተኛ
#ዛሬም_እባክሽ_ነይ_ወደኛ ! 🙏
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
#ታሪክህን_እወቅ
@Mgetem
ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፈቅ
ትውልዱ ተጠንቀቅ ፈጥነህ እንዳትወድቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ መቅሰፍት
መለየት ያቃተው እሬት ከፍትፍት
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ተልካሻ
መለየት ያቃተው በጎችን ከውሻ
ምን ያለ ዘመን ነው ያረጀ ያፈጀ
ወንድም ከወንድሙ እርስበርስ ያፋጀ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ውጥንቅጥ
የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጥያት የሚያጠልቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ዘለፋ
ወንድም ለወንድሙ የማይሆነው ተስፋ
ምን አይነት ዘመን ነው ክህደት የበዛበት
የዲያቢሎስ ሥርዓት የተንሰራፋበት
ወገኔ ተው ዕወቅ ተው ዕወቅ
እባክህ ተጠንቀቅ ለራስህም ዕወቅ
ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
@Mgetem
ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፈቅ
ትውልዱ ተጠንቀቅ ፈጥነህ እንዳትወድቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ መቅሰፍት
መለየት ያቃተው እሬት ከፍትፍት
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ተልካሻ
መለየት ያቃተው በጎችን ከውሻ
ምን ያለ ዘመን ነው ያረጀ ያፈጀ
ወንድም ከወንድሙ እርስበርስ ያፋጀ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ውጥንቅጥ
የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጥያት የሚያጠልቅ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ዘለፋ
ወንድም ለወንድሙ የማይሆነው ተስፋ
ምን አይነት ዘመን ነው ክህደት የበዛበት
የዲያቢሎስ ሥርዓት የተንሰራፋበት
ወገኔ ተው ዕወቅ ተው ዕወቅ
እባክህ ተጠንቀቅ ለራስህም ዕወቅ
ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
#የተማሪ ወዳጅ
@Megtem
የተማሪ ወዳጅ ቢቀር ምን አባቱ
ዱላ ሲያነሱበት ይላል ባዛኝቱ
እንኳን ባዛኝቱ ይበል በሥላሴ
እኔ እወደዋለሁ እስኪ ወጣ ነፍሴ
አንቺ ባለ ጠላ ሁልጊዜ ቅራሪ
እኔስ እሞታለሁ ለዛ ለተማሪ
ገበሬ ቢያገቡት አፈር አፈር ይላል
ነጋዴ ቢያገቡት ቅመም ቅመም ይላል
ወታደር ቢያገቡት ባሩድ ባሩድ ይላል
ከሁሉም ከሁሉም ተማሪ ይሻላል
ቀድሶ ሲወጣ እጣን እጣን ይላል
@Mgetem
@Mgetem
@Yohnnes_mariyam
@Megtem
የተማሪ ወዳጅ ቢቀር ምን አባቱ
ዱላ ሲያነሱበት ይላል ባዛኝቱ
እንኳን ባዛኝቱ ይበል በሥላሴ
እኔ እወደዋለሁ እስኪ ወጣ ነፍሴ
አንቺ ባለ ጠላ ሁልጊዜ ቅራሪ
እኔስ እሞታለሁ ለዛ ለተማሪ
ገበሬ ቢያገቡት አፈር አፈር ይላል
ነጋዴ ቢያገቡት ቅመም ቅመም ይላል
ወታደር ቢያገቡት ባሩድ ባሩድ ይላል
ከሁሉም ከሁሉም ተማሪ ይሻላል
ቀድሶ ሲወጣ እጣን እጣን ይላል
@Mgetem
@Mgetem
@Yohnnes_mariyam
#አትደንግጡ
@Mgetem
ማዕበል ባነሣ
ወጀብ ቢበረታ
ሁከትና ዋይታ
ቢሆን እንኳን ላፍታ
መታወክ መረበሽ
ከቶ አያስፈልም
ከእርሷ ጋር እያላችሁ
አትደንግጡ አይዟችሁ
መርከቧ ጽኑ ናት
አትሰምጥም አጠፋም
ጌታዋ ትጉህ ነው
ከቶ አያንቀላፋም
ይህች መርከብ ድንቅ ናት
እስኪ እንቀኝላት
አማናዊት መርከብ
#ቤተ-ክርስትያን ናት።
የእምነታችሁን ጽናት
ትዕግሥታችሁን ሊያይ
ተኣምራቱን ሊገልጥ
ማዳኑንም ሊያሳይ
ያንቀላፋ መስሎ
ጸጥ ቢል ባርምሞ
ተስፋችሁ አይጨልም
ዝም አይልም ፈጽሞ።
ምክንያት ሳታበዙ
ሁሌ ብትጸልዩ
አድነን ብላችሁ
በእምነት ብትዘምቱ
ያኔ ይገሠጻል
ማዕበል ነፋሱ
ኑፋቄ ክህደቱ።
መ/ር ኃይለሚካኤል ብርሃኑ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
@Mgetem
ማዕበል ባነሣ
ወጀብ ቢበረታ
ሁከትና ዋይታ
ቢሆን እንኳን ላፍታ
መታወክ መረበሽ
ከቶ አያስፈልም
ከእርሷ ጋር እያላችሁ
አትደንግጡ አይዟችሁ
መርከቧ ጽኑ ናት
አትሰምጥም አጠፋም
ጌታዋ ትጉህ ነው
ከቶ አያንቀላፋም
ይህች መርከብ ድንቅ ናት
እስኪ እንቀኝላት
አማናዊት መርከብ
#ቤተ-ክርስትያን ናት።
የእምነታችሁን ጽናት
ትዕግሥታችሁን ሊያይ
ተኣምራቱን ሊገልጥ
ማዳኑንም ሊያሳይ
ያንቀላፋ መስሎ
ጸጥ ቢል ባርምሞ
ተስፋችሁ አይጨልም
ዝም አይልም ፈጽሞ።
ምክንያት ሳታበዙ
ሁሌ ብትጸልዩ
አድነን ብላችሁ
በእምነት ብትዘምቱ
ያኔ ይገሠጻል
ማዕበል ነፋሱ
ኑፋቄ ክህደቱ።
መ/ር ኃይለሚካኤል ብርሃኑ
@Mgetem
@Mgetem
@Yohannes_mariyam
"መሳል መልካም ነው ብረትን ያሰላዋልና፤ መጽሐፍም መልካም ነው ልብን ያበራዋልና፡፡ መጽሐፍ መነጽር ነው፣ ለሚመለከተው ሰው ከሩቅ ያሳያልና"
መጽሐፈ ጨዋታ መንፈሳዊ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
መጽሐፈ ጨዋታ መንፈሳዊ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
#ወንድምህን_አትናቀው
@Mgetem
ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን?እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደ ኾነ አስተውል።"እንዴት?" ያልከኝ እንደ ኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቀከው ማለት ክርስቶስን ናከው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከኾነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት ዕራቆቱን ከሰቀሉት ሐሞትና ከርቤን ቀላቅለው ካጠጡት በፊቱ ላይም ከተፉት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዚህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

#እሳት_ውሀ_ሲሆን
እሳት ቢንቀለቀል ነበልባል ቢያበራ
ዲኑ ውሀ ሆኖል በመላኩ ስራ
ብንገባ ከሳቱ ወጥተናል በግርማ
የሚያድነን መላክ መጥቶልን ከራማ
ዛሬም እሳት ቢነድ ገብርኤል ብለናል
እሳት ውሀ ሲሆን ዱራ ሜዳ አይተናል
@Mgetem
@Mgetem_bot
@Yohannes_mariyam
እሳት ቢንቀለቀል ነበልባል ቢያበራ
ዲኑ ውሀ ሆኖል በመላኩ ስራ
ብንገባ ከሳቱ ወጥተናል በግርማ
የሚያድነን መላክ መጥቶልን ከራማ
ዛሬም እሳት ቢነድ ገብርኤል ብለናል
እሳት ውሀ ሲሆን ዱራ ሜዳ አይተናል
@Mgetem
@Mgetem_bot
@Yohannes_mariyam
✝✝እንጠይቅ ታምሯን✝✝
🔖🔖🔖🔖🔖🔖🔖
፦ዮሐ ፦2 ፥1-11
፦ሉቃ ፦1 ፥ --
እንጠይቅ ስለሷ እውነታው ያልገባችሁ
ከምትናገሩ እንደመጣላችሁ
አበዉን እንጠይቅ ይንገሩን ባካችሁ ።
ብዙ አባቶች አሉ የለበሱ ፍቅሯን እነሱን እንጠይቅ የንገሩን ታምሯን ።
ታምራቱዋን ያየው የተደረገለት
ዶኪማስ ይመስክር ይናገር ስለ እውነት ፦
በዛ በሰረጉ ቤት ቃና ዘገሊላ
ሰርገኛዉ ታድሞ ሲጠጣ ሲበላ ፦
ድንገት በመሀከል ወይኑ በመጥፋቱ
ዶኪማስ ተጨንቆ ሲርድ ሰዉነቱ
የነበረው ደስታ ሁሉም ሲሆን ከንቱ
መቋቋም አቅቶት ሲዝል ጉልበቱ
ተዋረድኩኝ ብሎ ሲታየዉ ሽንፈቱ
እማምላክ አንብባ ጭንቀቱን ከፊቱ ።
እሩህሩህ ናትና እናቴ አዛኚቱ
የዶኪማስ ጭንቀት ሀዘኑ እንዲፈታ
ድንግል ልታማልድ ሄደች ወደ ጌታ
ተዓምር የሚያደርግ ስላላት ቃልኪዳን
"ወይንኪ ዓልቦሙ "አለችው ልጇን ።
ልጇም ሰማና የናቱን ልመና
ውሃውን ቀየረዉ ወደ ወይን ቃና ።
ትናገር ኤልሳቤጥ ትመስክር ታምሯን
የሰላምታዋን ቃል ስትሰማዉ ድምጿን
በምንፈስ ተሞልታ ለክብሯ መስገዷን
በማሕፀኗ ያለዉን ፅንስ ማዘለሏን ።
ልቧ ሀሴት አርጎ መጮኋን በደስታ
ፅንሱም እደዘለለ በድንግል ሰላምታ ።
ምድራዉያንን እኛን ወክላ
ለክብሯ ሰገደች "ሰላም ለኪ "ብላ
ሰማያዉያንን ሁሉ ወክሎ
ገብረኤል አበሰራት" ሰላም ለኪ "ብሎ
ታደያ በኛም ዘመን አሁን ባለንበት
የድንግል ተዓምር በሚገለጥበት
ዓለም በምልጃዋ ድህነት ባገኝበት
ታድያ ለምን ካዱ ጠፋባቸው እውነት ።
አይናቸው እያየ ገድል ታምራቷን
ጆሮአቸውም ሰምቶ ሙታን ማስነሳቱዋን
ታድያ ለምን ይሆን ሰው ናት ማልታቸዉ
ስላልተፃፈ እንጂ ፍቅሯ በልባቸው ።
ከዚህ ሓጥያት ለመዉጣት ለመቅመስ ፍቅሯን
እንጠይቅ ስለሷ ይንገሩን ታምሯን ።
እውነትን ተማሩ ግቡ ወደ በረቱ
የእውነት አማላጅ ናት ድንግል አዛኚቱ ።

ሀ ብሎ ጀምሮ የፊደል ገበታ
ለመማር አስቦ ከጥዋት እስከማታ
የሰው ሀገር ሂዶ ተጠርቶ ከጌታ
ያለ ምግብ ዋለ የትንሳኤ ለታ
የናቱን ቤት ትቶ
በልጅነት ወጥቶ
ልመና ሲለምን የሚዘከር አጥቶ
በረሃብ ይሰቃያል ውሻውን ፈርቶ
ቢለምንም እንኳን በርትቶ ተፅናንቶ
ትንሽ ነው የሚያገኝ ብዙ ሰአት ለፍቶ
ውሻውን ራቡን ሁለቱን ታግሶ
ይማራል ትምህርቱን ድሪቶውን ለብሶ
የውሻውን ነገር
እረ እንዴት ልናገር
ይመስክረው እንጂ የተማሪው እግር
በውሻ እግሮቹን ተነግሶ ተነግሶ
ለምጡ ምስክር ነው ተጠብሶ ተጠብሶ
ከውሻ ጋር ታግሎ
የሚበለው ቆሎ
ሰውነቱ ከስቶ በውሻ ቆሳስሎ
ሌት ተቀን ቀፅሎ
ተምሬ መምህር እሆናው ብሎ
ከናት ካባቱ ቤት
የላመ የጣመ ሁሉ እያለለት
ይሄን ሁሉ ትቶ ወጣ ትምህርት ቤት
እራቡ ጥማቱ
እንቅልፍ ማጣቱ
የዘመድ ናፍቆቱ
ትምህርቱ ብዛቱ
ብርዱ መሰልቸቱ
ተሎ አይመሽ መአልቱ
አይነጋ ሌሊቱ
የቆሎ ተማሪ ስቃዩ መብዛቱ
ይህን ሁሉ ችሎ
ዳዊቱን ተምሮ ዜማውን ቀፅሎ
ቅኔ ቤት አመራ ጓዙን ጠቀላሎ
ቅኔውን ለመማር ከቅኔ ቤት ገብቶ
ቅፀላ ጀመረ ከሁሉ ተስማምቶ
የሚያውቀው ሰው የለም
አይተዋወቅም
ከዛ ያለው ሁሉም
ሀገር ወዴት ነው ተብሎ አይጠየቅም
መቀፀል ብቻ ነው የቅኔውን ቀለም
የሚለምንበት መንደር ተደልድሎ
መንደሩ እንዲደርስ በቁጥር ተከፍሎ
ለእንግደው ተማሪ መንደሩ ተሰጠው
ለምኖ እንዲማር ትምርት እንዲገባው
ልመና ሲለምን ትንሹ ተማሪ
ውሻው ቢመጣበት እረዳው ፈጣሪ
አኩፋዳ ሞልቶ የያዘው ኮቸሮ
ሲታገል ተደፋ ነጋ ጦሙን አድሮ
ግሱን እያጠና ቅኔውንም ቆጥሮ
ቅኔ እንደተቀኘ አቋቋም ለመማር
አቋቋም ቤት ሄደ ወጣ ሌላ ሀገር
እንዲህ ሁኖ ሳለ ትምህርት የሚማረው
አንዳንዱ ይቀራል ሞት እየነጠቀው
ተረቱም ይባላል
በተለያየ ቃል
ተማሪ በሞተ በሰባት ዓመቱ
ተምሮ ይመጣል ትላለች እናቱ
የተማሪ ነገር ይሄ ነው እውነቱ
አንዱ ውሃ ወስዶት
አንዱ ውሻ በልቶት
አንዱ ወባ ገድሎት
አንዱ ትምህርት ከብዶት
ሀገሩ ሳይመለስ እንደወጣ ቀረ
በትምህርት እንዳለ ስንቱ ተቀበረ
መከራውን አልፎ የሚቀረው ከሞት
እከኩ እርሃቡ መልኩን ቀይሮት
እናቱ ስታየው ሌላ ሰው መሰላት
ሙሉ ሰውነቱን እከኩ አቁስሎት
ይህን ሁሉ ስቃይ የተቀበለው
የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር ነው
ልምና የወጣ ስላጣ አይደለም
በስሟ ሲለምን ብሎ በእንተ ማርያም
ቃል ኪዳኗን ይዞ ሊማር ነው ዘላለም
በግብፅ በረሃ ድንግል ስትለምን
ያነን በማሰብ ነው ተማሪ የሚለምን
የማርያም ወዳጂ የቆሎ ተማሪ
ምግቡ ማርያም ናት ሁሌም ስሟን ጠሪ
ሲጠራት ውሎ ሲጠራት አዳሪ
~የተማሪ ስንቁ ድንግል ማርያም ናት
ትምህርት ቤት ሲሄድ የተጓዘ ይዟት
አንድ አኮፈዳ ቁራሽ መለመኚያ
አንድ ዳዊት ጸሎት መፀለያ
ሁለት ዘንጎች ውሻ መከልከያ
አንዲት ቅምጫና የውሃ መቅጂያ
አንድ ደበሎ ብርድ መከልከያ
የተማሪ ሀብቱ እነዚህ ናቸው
ከናት ካባቱ ቤት ይዞ የወጣቸው
የቆሎ ተማሪው እንደዚህ ተምሮ
ቅኔውን ድጓውን መጻፉን ተምሮ
አቋቋም ቅዳሴ ዝማሬን ጨምሮ
አቡሻህር ሳይቀር አራቆ አስመስክሮ
የቤተ ክርስቲያን የሀገር አለኚታ
ተብሎ እየተጠራ የኔታ የኔታ
መምህር መርጌታ ቀኝ ጌታ ግራጌታ
መከራውን አይቶ ተምሮ ሲመጣ
ስራ አላገኘም የሚበላው አጣ
ያልተማረው በዘር ከላይ ተቀምጦ
በጉቦ በጎሳ ስልጣን ተቆናጦ
የተማረው ቀረ ዘበኛ ተቀጥሮ
ይግባኝ ለፈጣሪ እንዲህ ነው ዘንድሮ
የተማረው ከላይ ሲሰቃይ እያየ
ከስር ከስር ያለው ለመማር ዘገየ
የኔታ ተምረው ከወዴት ደረሱ
እያለ ያወራል ትንሹ እርስ በርሱ
አልማርም እኔ ለመሆን እንደሱ
ጉባኤ ቤት ገብቶ የሚማር ሳይጠፋ
ቤተ ክርስቲያን እንድትኖር በተስፋ
የአብነት ትምህርቱ በሁሉ እንዲስፋፋ
ቅድሚያ ለተማረው
ቦታ እንዲኖረው
የተዋህዶ ልጆች ድምፃችን ይሰማ
የጉባኤ ቤቶች ሳይሆኑ ባድማ
የተማረው ታዛዥ
ያልተማረው አዛዥ
ያልተማረው ከላይ
ባማረ ወንበር ላይ
ባበባ ምንጣፍ ላይ
የተማረው ከታች ከሚዳው አፈር ላይ
አይምሮ ይነሳል ይሄ ሁሉ ሲታይ
ወይ ስቃይ ወይ ስቃይ
እረ እሰከመቸ ነው
እንዲህ የሚኖረው
የተማረው ላልተማረው ጉቦ እየከፈለ
ካልከፈለ ጉቦ ስራ እየተከለከለ
እረ መቸ ይሆን ?
የሚያልፍ ይህ ዘመን
በአፈ ቀላጤ ቦታው ሁሉ ሞልቶ
ያልተማረ መምር ዳር እስከዳር በዝቶ
የተማረው ምሁር መድረሻ ቦታ አጥቶ
የምሁራኑ ግፍ
በድርሳናት ቢፃፍ
ወረቀት አይበቃም
ብእርም የለም
ምድርም አይችለውም
@ይግባኝ ለእልመክኑ
ስለ ምሁራኑ
እባክህ አምላኬ አንድ ነገር ስማኝ
የተማረው ከላይ ሁኖ እንድታሳየኝ
የዚህ ፅሁፍ መታሰቢያነቱ
ይሁንልኝ ለሊቃውንቱ
ለደቀ መዛሙርቱ
በረሃብ በግፍ ለሚንገላቱ
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ነሐሴ 15/2009 (ሸር)
መካነ ጉባኤ ዘቅኔ ተጻፈ
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
ለመማር አስቦ ከጥዋት እስከማታ
የሰው ሀገር ሂዶ ተጠርቶ ከጌታ
ያለ ምግብ ዋለ የትንሳኤ ለታ
የናቱን ቤት ትቶ
በልጅነት ወጥቶ
ልመና ሲለምን የሚዘከር አጥቶ
በረሃብ ይሰቃያል ውሻውን ፈርቶ
ቢለምንም እንኳን በርትቶ ተፅናንቶ
ትንሽ ነው የሚያገኝ ብዙ ሰአት ለፍቶ
ውሻውን ራቡን ሁለቱን ታግሶ
ይማራል ትምህርቱን ድሪቶውን ለብሶ
የውሻውን ነገር
እረ እንዴት ልናገር
ይመስክረው እንጂ የተማሪው እግር
በውሻ እግሮቹን ተነግሶ ተነግሶ
ለምጡ ምስክር ነው ተጠብሶ ተጠብሶ
ከውሻ ጋር ታግሎ
የሚበለው ቆሎ
ሰውነቱ ከስቶ በውሻ ቆሳስሎ
ሌት ተቀን ቀፅሎ
ተምሬ መምህር እሆናው ብሎ
ከናት ካባቱ ቤት
የላመ የጣመ ሁሉ እያለለት
ይሄን ሁሉ ትቶ ወጣ ትምህርት ቤት
እራቡ ጥማቱ
እንቅልፍ ማጣቱ
የዘመድ ናፍቆቱ
ትምህርቱ ብዛቱ
ብርዱ መሰልቸቱ
ተሎ አይመሽ መአልቱ
አይነጋ ሌሊቱ
የቆሎ ተማሪ ስቃዩ መብዛቱ
ይህን ሁሉ ችሎ
ዳዊቱን ተምሮ ዜማውን ቀፅሎ
ቅኔ ቤት አመራ ጓዙን ጠቀላሎ
ቅኔውን ለመማር ከቅኔ ቤት ገብቶ
ቅፀላ ጀመረ ከሁሉ ተስማምቶ
የሚያውቀው ሰው የለም
አይተዋወቅም
ከዛ ያለው ሁሉም
ሀገር ወዴት ነው ተብሎ አይጠየቅም
መቀፀል ብቻ ነው የቅኔውን ቀለም
የሚለምንበት መንደር ተደልድሎ
መንደሩ እንዲደርስ በቁጥር ተከፍሎ
ለእንግደው ተማሪ መንደሩ ተሰጠው
ለምኖ እንዲማር ትምርት እንዲገባው
ልመና ሲለምን ትንሹ ተማሪ
ውሻው ቢመጣበት እረዳው ፈጣሪ
አኩፋዳ ሞልቶ የያዘው ኮቸሮ
ሲታገል ተደፋ ነጋ ጦሙን አድሮ
ግሱን እያጠና ቅኔውንም ቆጥሮ
ቅኔ እንደተቀኘ አቋቋም ለመማር
አቋቋም ቤት ሄደ ወጣ ሌላ ሀገር
እንዲህ ሁኖ ሳለ ትምህርት የሚማረው
አንዳንዱ ይቀራል ሞት እየነጠቀው
ተረቱም ይባላል
በተለያየ ቃል
ተማሪ በሞተ በሰባት ዓመቱ
ተምሮ ይመጣል ትላለች እናቱ
የተማሪ ነገር ይሄ ነው እውነቱ
አንዱ ውሃ ወስዶት
አንዱ ውሻ በልቶት
አንዱ ወባ ገድሎት
አንዱ ትምህርት ከብዶት
ሀገሩ ሳይመለስ እንደወጣ ቀረ
በትምህርት እንዳለ ስንቱ ተቀበረ
መከራውን አልፎ የሚቀረው ከሞት
እከኩ እርሃቡ መልኩን ቀይሮት
እናቱ ስታየው ሌላ ሰው መሰላት
ሙሉ ሰውነቱን እከኩ አቁስሎት
ይህን ሁሉ ስቃይ የተቀበለው
የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር ነው
ልምና የወጣ ስላጣ አይደለም
በስሟ ሲለምን ብሎ በእንተ ማርያም
ቃል ኪዳኗን ይዞ ሊማር ነው ዘላለም
በግብፅ በረሃ ድንግል ስትለምን
ያነን በማሰብ ነው ተማሪ የሚለምን
የማርያም ወዳጂ የቆሎ ተማሪ
ምግቡ ማርያም ናት ሁሌም ስሟን ጠሪ
ሲጠራት ውሎ ሲጠራት አዳሪ
~የተማሪ ስንቁ ድንግል ማርያም ናት
ትምህርት ቤት ሲሄድ የተጓዘ ይዟት
አንድ አኮፈዳ ቁራሽ መለመኚያ
አንድ ዳዊት ጸሎት መፀለያ
ሁለት ዘንጎች ውሻ መከልከያ
አንዲት ቅምጫና የውሃ መቅጂያ
አንድ ደበሎ ብርድ መከልከያ
የተማሪ ሀብቱ እነዚህ ናቸው
ከናት ካባቱ ቤት ይዞ የወጣቸው
የቆሎ ተማሪው እንደዚህ ተምሮ
ቅኔውን ድጓውን መጻፉን ተምሮ
አቋቋም ቅዳሴ ዝማሬን ጨምሮ
አቡሻህር ሳይቀር አራቆ አስመስክሮ
የቤተ ክርስቲያን የሀገር አለኚታ
ተብሎ እየተጠራ የኔታ የኔታ
መምህር መርጌታ ቀኝ ጌታ ግራጌታ
መከራውን አይቶ ተምሮ ሲመጣ
ስራ አላገኘም የሚበላው አጣ
ያልተማረው በዘር ከላይ ተቀምጦ
በጉቦ በጎሳ ስልጣን ተቆናጦ
የተማረው ቀረ ዘበኛ ተቀጥሮ
ይግባኝ ለፈጣሪ እንዲህ ነው ዘንድሮ
የተማረው ከላይ ሲሰቃይ እያየ
ከስር ከስር ያለው ለመማር ዘገየ
የኔታ ተምረው ከወዴት ደረሱ
እያለ ያወራል ትንሹ እርስ በርሱ
አልማርም እኔ ለመሆን እንደሱ
ጉባኤ ቤት ገብቶ የሚማር ሳይጠፋ
ቤተ ክርስቲያን እንድትኖር በተስፋ
የአብነት ትምህርቱ በሁሉ እንዲስፋፋ
ቅድሚያ ለተማረው
ቦታ እንዲኖረው
የተዋህዶ ልጆች ድምፃችን ይሰማ
የጉባኤ ቤቶች ሳይሆኑ ባድማ
የተማረው ታዛዥ
ያልተማረው አዛዥ
ያልተማረው ከላይ
ባማረ ወንበር ላይ
ባበባ ምንጣፍ ላይ
የተማረው ከታች ከሚዳው አፈር ላይ
አይምሮ ይነሳል ይሄ ሁሉ ሲታይ
ወይ ስቃይ ወይ ስቃይ
እረ እሰከመቸ ነው
እንዲህ የሚኖረው
የተማረው ላልተማረው ጉቦ እየከፈለ
ካልከፈለ ጉቦ ስራ እየተከለከለ
እረ መቸ ይሆን ?
የሚያልፍ ይህ ዘመን
በአፈ ቀላጤ ቦታው ሁሉ ሞልቶ
ያልተማረ መምር ዳር እስከዳር በዝቶ
የተማረው ምሁር መድረሻ ቦታ አጥቶ
የምሁራኑ ግፍ
በድርሳናት ቢፃፍ
ወረቀት አይበቃም
ብእርም የለም
ምድርም አይችለውም
@ይግባኝ ለእልመክኑ
ስለ ምሁራኑ
እባክህ አምላኬ አንድ ነገር ስማኝ
የተማረው ከላይ ሁኖ እንድታሳየኝ
የዚህ ፅሁፍ መታሰቢያነቱ
ይሁንልኝ ለሊቃውንቱ
ለደቀ መዛሙርቱ
በረሃብ በግፍ ለሚንገላቱ
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ነሐሴ 15/2009 (ሸር)
መካነ ጉባኤ ዘቅኔ ተጻፈ
📌ሼር
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc
🌺---------------------------------- 🌺
#አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
----------------------------------
📌 ታህሳስ 24 በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው ፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር ፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ ፤ ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች ፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብ...ዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ ፤ ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክልዬ ተጸነሱ በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Bot