Telegram Web Link
🌺❖በልዑል እግዚአብሔር ስም ይቅርታ❖🌺

ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላች የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦ በክርቶስ ክርስትያ በወልድ ውሉድ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የሆናችው የድግል ማርያም ለጆች እንኳን ለታላቁ የአብይ ፆም በሰላም ቤጤና አደረጋች ፆሙ የበረከት የረድኤት የነብሳችን ድህነት የዳቢሎስ ድል መንሻ የአጥያት መደምሰሻ ይሁንልን ❖🌺ዘወረደ🌺

ሳላውቅ በስህተት አውቄም ሆነ በድፍረት በንፈሳዊ ማህበሮቼም ሆነ በጉደኝነት በኮሜን በማህበራዊ ሚድያም ብሆን ብበድል ባስከፋ ያስቀየምኳች ካላች በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ አድርጉልኝ እወዳችዋለው 😰
ይቅርታ ውዴ ሆይ
ይቅርታ እህቴ ሆይ
ይቅርታ ወንድሜ ሆይ
ይቅርታ ወዳጄ ሆይ
ይቅርታ 🌺🌺
ይቅርታ 🌺🌺
https://youtu.be/dMoqfYGoPE8
የንስሀ መዝሙርነው

@Mgetem

@Mgetem

@Mgetem
👍2👏1
    🍟🎂ተጠቃሚ ያጡ መድኃኒቶች🍛🍧🍟

🍡🍢1/ ቃለ እግዚአብሔር
               🌕🌒ጠዋት አንድ
               🌒🌙ማታ አንድ

🍢🍡2/ ንስሐ
           🌺በየሳምንቱ አንድ አንድ

🍢🍡3/ ስጋወ ደሙ
        🌹🌺🌼 ቢያንስ በ40 ቀን አንዴ

🍢🍡4/ ጸበል
      ከምግብ በፊት በየቀኑ አንዴ

🍢🍡5/ እምነት
         ❤️ዘወትር በየሰከንዱ ያለማቋረጥ

🍢🍡6/ ፍቅር
         💔ዘወትር ያለማቋረጥ ለሁሉም

🍢🍡7/ ሰላም
      🍁ለተከታታይ ሰዓታት እስከ ዘላለም

🍢🍡8/ጸሎት
 📕📗🙏 በቀን ሰባት ግዜ ያለማቋረጥ

🍢🍡9/ ፆም
   😒☺️ ከምግብ በፊት

🍬🍢10/ ምፅዋት
💰💷 በየቀኑ ከምታገኘው ጥቂቱን

🍢🍡11/ ስግደት
🙇🙇‍♀ ጠዋት 21
🙇‍♀🙇 ማታ 20

☞☞ማሳሰቢያ፡- ሁሉም መድኃኒቶች ተስፋ በተባለ ውሃ ማወራረጃነት መዋጥ ይኖርባቸዋል።
https://youtu.be/dMoqfYGoPE8
@Mgetem
👍52🥰2
Forwarded from Daregot Media
ተዋሕድዋ
የዓድዋ ድልና ተዋሕዷዊ ገድል

በዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

፩.የእግዚአብሔርና የምኒልክ ሰይፍ

፪.ጣይቱ ምዕመኒቱ

፫. ካህናት፣ ታቦታት ፣መነኮሳት ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር

፬. የኢትዮጵያ ገበዝ በዓድዋ ጦሩን ሲመዝ

፭.የወታደሩ ሃይማኖት ይባስ!

፮. ቤተ ክርስቲያን ግን ለምን በጦርነቱ ተሳተፈች?

እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓልና ለ124ኛው የአደዋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ተከታዩን ጹሑፍ ታነቡት ዘንድ ዳረጎት ማዕዷን አቅርባለች፡፡

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/ተዋሕድዋ-03-01

©ዳረጎት ዘተዋሕዶ

Join us @daregot
👍1
፨የልቤ ማድጋ፨

ዘወትር ጠዋት ማታ
ስለፋ ስተጋ
እሞላለሁ ብዬ
የልቤን ማድጋ
ዛሬ በንስሐ
ሞላችልኝ ብዬ
በሐሰት ስቦርቅ
አይሎ ደስታዬ
ነገ ደግም ባዶ
ወና ሆና ሳያት
ኀዘኔ በርትቶ
ስሞክር ልሞላት
ጠብም ላይልላት
ደግም እየሞላች
ዳግም ስትጎድል
ምሬቴ አይሎ
ደክሜ እንዳልዝል
ከዚያ ከምንጩ ዳር
አግኝቼ አምላኬን
ዳግም ላይጎድልብኝ
ሞልተህ ማድጋዬን
ለስምህ ልዘምር
ላብዛ ምስጋናዬን።
@Mgetem
👍83
ይህቺ ጥፊ የኔ ናት"
መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ፣ እግዚአብሔርን
እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር
ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ
ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ
አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን
ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ
እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡"
እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ
አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ጊዜ ነገሩን የተከታተለዉ
አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር እኛን ባጠፋነዉ ቅጣት የግድ እስከሚቀጣን ቁጭ
ብለን መጠበቅ የለብንም ፣ከሌላዉ ጥፋት፣ ከሌላዉ ቅጣት መማር
አለብን፡፡ ከሌላዉ ጥፋት መማር ትልቅ ዕዉቀት፣ ታላቅ ማስተዋል
ነዉ፡፡ አርሳንዮስ ጓደኛዉ በጥፊ ሲመታ፣ ይች ጥፊ የኔ ናት አለ እንጂ
ባጠፋዉ ጥፋት ነዉ የተቀጣዉ ብሎ አልፈረደበትም፡፡ እኛም ቁጣ፣
መቅሰፍት፣ እኛ ጋር እስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ከጓደኞቻችን
ከጎረቤቶቻችን በሌላም ሀገር ከምናየዉ ከምንሰማዉ ተምረን ንስሓ
መግባት አለብን ጾም ማለትም ይህ ነዉ፡፡ ንስሐ የምንገባዉም
ኃጢአታችንን ስናስተዉል ነዉ፡፡ ማስተዋል ከሌለን ኃጢአቱን እንደ
ጽድቅ ቆጥረን ለንስሐ አንበቃም፡፡
ማስተዋልን ገንዘብ ያደረገ ምዕመን በሌላ ላይ የተደረገ ቅጣት
በርሱ ላይ እንደመጣ ይጠነቀቃል፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ
ብልህ በመሆን የነገሮችን ሁኔታ በማስተዋል ይከታተላል፡፡ ከሰብአ
ትካት ከሰዶም ይማራል ሎጥ የዳነበትን መንገድ ይከተላል ቃሉን
በመስማት በኖህ መርከብ በተመሰለች ቅድስት ቤተክርስቲያን
ይገኛል እራሱን በንስሐ በሥጋ ወደሙ በጸሎት በእግዚአብሔር
ቸርነት ከሚመጣዉ መቅሰፍት ያድናል፡፡
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡
https://youtu.be/dMoqfYGoPE8
@Mgetem
👍63
የአብይ ፆም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሦስተኛ ሰንበት(ሳምንት)

ምኩራብ ተብሎ ይታወቃል።
በዚህ ቀን ቤተ መቅደስን አስመልክቶ ትምህርት ይሰጣል። ጌታችንም በምኩራብ ገብቶ
ስለማስተማሩ በሰፊው ይነገራል።
ምስባኩም፦ መዝ.፷፰፡፱ ነው።
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ የቤትህ ቅናት በልቶኛል
ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ የሚሰድቡህምስድብ በላዬ ወድቆብኛልና
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ ነፍሴን በጾም አስመረርኩአት
ወንጌሉም ዮሐ.፪፡፲፪-እስከ ፍጻሜ ነው።
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት ጥቅሶችም፦
ቆላ.፪፡፲፮-እስከ ፍጻሜ፤
ያዕ.፪፡፲፬-እስከ ፍጻሜ፤
የሐዋ.ሥራ ፲፡፩-፱ ።
@Mgetem
Forwarded from Daregot Media
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
👍2
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
👍2
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ pinned «​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ (ውርስ ትርጉም) ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ @Mgetem “ብላቴና” የሚል፤ ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤ በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤ መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤ ጨቅላ ነው ፤ ትክክል! ምንም ነፍስ የማያውቅ፤ እሳትና ውሃን መለየት የማይችል። ቢለይማ ኖሮ፤ ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ? …»
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ

አዝ________________

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም

አዝ________________

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ

አዝ________________

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ

አዝ________________

እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4

"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"

💚 @yeorthodoxmezmur 💚
💛 @yeorthodoxmezmur 💛
❤️ @yeorthodoxmezmur ❤️
👍74🥰1
#አልችልም_አስችለኝ
እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ልብስ
አስጨንቀዋለሁ እራሴን በእርስ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኖአቸው
እግሮች ጉዞዬን መጓዝ አቅቶአቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባል ለሊት
ጩኽት ይስማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቀቴን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ
https://youtu.be/LrUMwlzym5I
ዝማሬ መልክት ያስማልን
👍83🤬1
​​#የአምላክ_እንባ
(በላይ በቀለ ወያ)
@Mgetem
.
.
ከላይ ከሰማያት...
በሰው ተበድሎ ፤ ፈጣሪ ያለቅሳል
ከታች ያለ ፍጥረት...
"ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል።
ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ
የሀገሬ ገበሬ...
በፈጣሪ እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ።
እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው
ትእግስት አጠራቅሞት...
ለወራት የቆየ ፤ የአምላክ እንባ ነው።
።።።

ከማንባቱ በፊት...
ማዘኑን ሊያረዳ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ፤
ፈጣሪ ሲቆጣ...
ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ።
የሀገሬ ገበሬ.....
ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል
የገበሬው በሬ...
ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል
በፈጣሪ እንባ
በሰው ልጆች ደባ
የታረሰ መሬት...
ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል
ከላይ ከሰማያት...
ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል
ከታች ያለ ፍጥረት
ርሀቡን ሊያስታግስ
ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል።
።።።

ለእንደገና ክረምት
ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ
የሀገሬ ገበሬ……
ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ።
።፣
ከላይ ከሰማያት.
የፈጣሪ እናት
ልጇን ለማባበል ፤ ፈገግ ትላለች
ከታች ያለች እናት...
"ፀሐይ ወጣ"ብላ ፤ ብቅል ታሰጣለች።
እንዲያው በተለምዶ፤ ፀሀይ የምንላት
ልጇን ለማባበል….
ብርሀን የሰጠች፤ የአምላክ እናት ናት።

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Bot
👍95
2025/07/13 18:38:46
Back to Top
HTML Embed Code: