Telegram Web Link
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ pinned «​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ (ውርስ ትርጉም) ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ @Mgetem “ብላቴና” የሚል፤ ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤ በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤ መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤ ጨቅላ ነው ፤ ትክክል! ምንም ነፍስ የማያውቅ፤ እሳትና ውሃን መለየት የማይችል። ቢለይማ ኖሮ፤ ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ? …»
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ

አዝ________________

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም

አዝ________________

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ

አዝ________________

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ

አዝ________________

እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4

"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"

💚 @yeorthodoxmezmur 💚
💛 @yeorthodoxmezmur 💛
❤️ @yeorthodoxmezmur ❤️
#አልችልም_አስችለኝ
እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ልብስ
አስጨንቀዋለሁ እራሴን በእርስ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኖአቸው
እግሮች ጉዞዬን መጓዝ አቅቶአቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባል ለሊት
ጩኽት ይስማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቀቴን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ
https://youtu.be/LrUMwlzym5I
ዝማሬ መልክት ያስማልን
​​#የአምላክ_እንባ
(በላይ በቀለ ወያ)
@Mgetem
.
.
ከላይ ከሰማያት...
በሰው ተበድሎ ፤ ፈጣሪ ያለቅሳል
ከታች ያለ ፍጥረት...
"ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል።
ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ
የሀገሬ ገበሬ...
በፈጣሪ እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ።
እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው
ትእግስት አጠራቅሞት...
ለወራት የቆየ ፤ የአምላክ እንባ ነው።
።።።

ከማንባቱ በፊት...
ማዘኑን ሊያረዳ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ፤
ፈጣሪ ሲቆጣ...
ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ።
የሀገሬ ገበሬ.....
ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል
የገበሬው በሬ...
ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል
በፈጣሪ እንባ
በሰው ልጆች ደባ
የታረሰ መሬት...
ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል
ከላይ ከሰማያት...
ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል
ከታች ያለ ፍጥረት
ርሀቡን ሊያስታግስ
ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል።
።።።

ለእንደገና ክረምት
ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ
የሀገሬ ገበሬ……
ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ።
።፣
ከላይ ከሰማያት.
የፈጣሪ እናት
ልጇን ለማባበል ፤ ፈገግ ትላለች
ከታች ያለች እናት...
"ፀሐይ ወጣ"ብላ ፤ ብቅል ታሰጣለች።
እንዲያው በተለምዶ፤ ፀሀይ የምንላት
ልጇን ለማባበል….
ብርሀን የሰጠች፤ የአምላክ እናት ናት።

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Bot
#አዳም_ሆይ_የት_አለህ?
(ዲ/ን ዐብይ ሙሉቀን)
@Mgetem
@Mgetem
አትብላ ስትባል በለሲቱን በላህ
አምላክ መሆን ስትሻ ከክብርህ ተዋርደህ
ከገነት ኮብልለህ ወዴት ነው የገባህ?
አዳም ሆይ የት አለህ?
ዛሬም እንደ ጥንቱ መብላትን ትሻለህ?
አንተን የፈለገህ ላንተ የሞተልህ
በለሲቱን ሳይሆን ዕፅ ህይወት ሰጠህ
አዳም ሆይ የት አለህ?
ብላ ይኸውልህ።
@Yohannes_mariyam
አምስተኛ ሰንበት(ሳምንት)
፨፨፨፨፨፨፨፨✞፨፨፨፨፨፨፨
ደብረ ዘይት ተብሎ ይታወቃል።
በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም
ምፅአቱ) ይሰበካል። ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ
መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል ደ/ሰ/መ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤ/ት/ክ
የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ
የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸው ክፉም ላደረጉ
የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል። ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን
የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
ምስባኩም፦ መዝ.፵፱፡፫ ነው።
እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
ወአምላክነሂ ኢያረምም አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ እሳት በፊቱ ይቃጠላል
ወንጌሉም ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ነው።
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት ጥቅሶችም፦
፩ተሰ.፬፡-፲፫-እስከ ፍጻሜ፤
፪ጴጥ.፫፡፯-፲፭፤
የሐዋ.ሥራ ፳፬፡፩-፳፪ ።

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
🔔ቅዱስ ፓትርያርኩ ኮሮናን በተመለከተ ሃይማኖታዊ መመሪያ ሰጡ
--------------
ፓትርያርኩ በዓለም ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመቋቋም እንዲያስችል ምእመናንም ሆኑ ካህናት ማድረግ ያለባቸውን እና ማድረግ የሌለባቸውን ተግባራት የለየ ዝርዝር መመሪያ ሰጡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት ዛሬ ባስተላለፉት አባታዊ መመሪያ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ያስተላለፈው ነው ያሏቸውን 13 ነጥቦች በጽሑፍ አቅርበዋል።

የትኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ጉዞዎች፣ የትምህርት እና የስብከት ጉባኤዎች የተከለከሉ ሲሆን በቅዳሴ እና በሌሎች የቤተ መቅደስ አገልግሎቶች ሊኖር ስለሚገባው የሰዎች መቀራረብም መመሪያ ሰጥቷል።
(የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን
+++++++++++++++++
በመላው ዓለም የተስፋፋውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ፤

በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር፣ በከተማና በመላው ዓለም ለምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ!

ወቅታዊ የሰው ልጅ ሥጋት በመሆን በመላው ዓለም በፍጥነት በተስፋፋው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ሥጋት ስለተከሰተ መንግሥታት ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከሞት ለመጠበቅ አዋጆችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ እምነትና ቀኖናን ጠብቆ ሃይማኖታዊ መመሪያ የመስጠት ሐዋርያዊ ኃላፊነት አለባት፡፡

ስለዚህ ቋሚ ሲኖዶስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መሠረተ እምነትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ለሁሉም ካህናትና ለሕዝበ እግዚአብሔር ደኅንነት ሲባል የሚከተሉትን መመሪያዎች አስተላልፏል፡-

1. በሰሙነ ሕማማት እንደምናደርገው የእርስ በርስ መሳሳም ቀርቶ ራስን ዝቅ በማድረግ፣ እጅ በመንሳት ወይም በእማሄ ሰላምታ በማቅረብ እንዲፈጸም፣

2. ወረርሽኙ በሰዎች መሰባሰብ የሚስፋፋ ስለሆነ ማናቸውም መንፈሳዊ ጉባኤያት፣ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት፣ ወደ ገዳማትና አድባራት የሚደረጉ ጉዞዎች እና ምዕመናን የሚሳተፉባቸው ታላላቅ መርሐ ግብሮች ለጊዜው እንዲቋረጡ፣

3. ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባም ሆነ አሰፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ እጆቻንን በመታጠብና ዘርዘር ብሎ በመቆም ሥርዓተ አምልኮ እንዲፈጸም፣

4. ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓላት በቅዳሴና በማኅሌት ታስበው ክብረ በዓላቱ በሌላ ጊዜ እንዲከበሩ፣

5. የጉንፋን ምልክት ያለባቸው ለሌሎች እንዳያስተላልፉ በቤታቸው በጥንቃቄ ተለይተው በጸሎትና በሕክምና እንዲቆዩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋቸውን መንፈሳዊ አገልግሎትም በልዩ ሁኔታ እንዲያገኙ፣

6. በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የተስፋ ልዑክ በመሆን እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ተደራጅቶ ተልዕኮውን በአስቸኳይ እንዲጀምር

7. ሥርዓተ ቅዳሴን በተመለከተ፡-

• በቤተ መቅደስ ቀዳስያን በሆኑት ልዑካን ብቻ ሥርዓተ ቅዳሴው እንዲፈጸምና ሌሎች አገልጋዮች በቅድስቱ ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያገለግሉ፣

• በዕለቱ ለሚቆርቡ ምዕመናን ለአረጋውያን፣ ለወጣቶችና ለሕፃናት የፈረቃ ተራ በማዘጋጀት ቆራቢዎች ብቻ ወደ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያስቀድሱ፣

• ሌሎች ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ቢያንስ ሁለት የትልቅ ሰው እርምጃ ያህል በመራራቅ ቆመው እንዲያስቀድሱ፣

• የቅዳሴ ጠበል በየግል መጠቀሚያ ምእመናን በየቆሙበት ቦታ በጥንቃቄ እንዲሰጥ፣

• ሌሎች ከቅዳሴ ጋር የተያያዙ ዝርዝር የአፈፃፀም ጉዳዮችን ግብረ ኃይሉ አዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ በማጸደቅ ለአህጉረ ስብከት በሚልከው መመሪያ መሠረት ተግባራዊ እንዲደረግ፤

8. ከሥርዓተ ቅዳሴ በተጨማሪ እንደ ስብሐተ ነግሕ፣ ሰዓታት፣ ቁመተ ማኅሌት፣ ጥምቀተ ክርስትና፣ ጸሎተ ፍትሐት፣ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለሥርዓቱ በሚያስፈልገው ቁጥር ብቻ እና በውሱን ሊቃውንት በተራ እንዲፈፀም፣

9. ወረርሽኙ ከዓለም እንዲጠፋ ካህናት ብቻ በቤተ መቅደስ፣ በዐውደ ምኅረትና በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ጸሎተ እጣን በማድረስ ማዕጠንት እንዲፈጽሙ፣

10. በማኅበራዊ ግንኙነት በደስታ፣ በሐዘን፣ በእድር፣ በሥርዓተ ቀብር አፈፃፀምና በመሳሰሉት መሰባሰቦች በሽታው እንዳይሠራጭ አገልግሎቱ በውስን የሰው ቁጥር በጥንቃቄ እንዲፈፀም፤

11. ምዕመናን ራሳቸውን እየጠበቁ በቫይረሱ የተጠቁና አገግመው የወጡ ወገኖችን፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ከሃይማኖትና ከምግባር የወጣ መገለልና ጥቃት እንዳይደርስባቸው በክርስቲያናዊ ፍቅርና በኢትጵያዊ ጨዋነት እንክብካቤ እንዲደረግላቸው፣

12. ለነዳያን እና ለተቸገሩ ወገኖች አስፈላጊው ማኅበራዊ እና ቁሳዊ እገዛ በሁሉም አጥቢያዎች እንዲደረግ፣

13. ቤተ ክርስቲያንን ከማይወክሉና ቀኖናዊ ካልሆኑ አሳሳች መረጃዎች በመቆጠብ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጡ መመሪያዎችን በየአጥቢያችሁና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንድትፈጽሙ እና እንድታስፈጽሙ ተወስኗል፡፡

በአጠቃላይ በበሽታው እስካሁን ለተያዙት፣ በጊዜያዊ ማቆያ ለሚገኙት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን ምህረቱን እንዲሰጥልን እንጸልያለን፤

በመላው ዓለም ዜጎቻቸውን በበሽታው ለተነጠቁ ሁሉ መጽናናቱን እንዲሰጥልን ያረፉትንም እንዲምርልን እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቃለን፤

በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን የራሳችሁና የሌሎች ሕይወት ከወረርሽኙ እንዲጠበቅ እንዲሁም የበሽታው ሥርጭት እንዲቆም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን የተሰጡት መመሪያዎች ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ የጸኑ እንዲሆኑ በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ዓለማችንን ከጥፋት የሰውን ልጅ ሁሉ ከመከራ ሞት ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ/ም
አዲስ አበባ

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
ለሙሴ የተጻፈ ደብዳቤ

አንተ የእግዚአብሔር ወዳጅ ነቢዩ ሙሴ ሆይ ለጤናህ እንዴት ነህ?
ለነገሩ አንተ ጤነኛ ነህ በሰማይ ቤት ሁነህ ደግሞ ምን ያገኝህ።እኔ ምልህ ሙሴ ባለቤትህ ሲጳራ ደህናናት አማትህስ ዮቶር እንዴት ናቸው?ሰሞኑን በሀገራቸው ኢትዮጵያ በተሰማው ወሬ ምን ተሰምቷቸው ይሆን?መቼም ሲያስነጥሱ ይበክሉናል ብለው ፊታቸውን አላዞሩብንም አይደል?ስማኝማ ሙሴ ቆይ ያኔ እስራኤልን ከፈርኦን መንጋጋ በ10 መቅሰፍት በ 11ኛ ስምጠተ ባህር ስትታደግ በበኩር ልጅ ሞት ግብጻውያን ሲያልቁ እስራኤላውያን ግን በፍሲካ በግ ደም መቃንና ጉበኑን ረጭተው ከሞት እንደተረፋችሁ፤ፍርኦን ሊገድላችሁ ኪትላዎቹን አስከትሎ ሲመጣ በብትርህ ባህር ከፍለህ እንደተሻገራችሁ፤በዛ በበረሀ እባብ ተነስቶ ህዝቡን ሲጨርሰው የእባብ ምስል ሰርተህ እንደታደግሀቸው እናውቃለን።እግዚአብሔርም እንዴት እንዳከበረህ እንደወደደህ በፈርኦን ላይ አምላክ ዘበጸጋ አድርጎ ሲያሰለጥንህ ተርድተናል።ሙሴ ሆይ ከእህትህ ከማርያም ጋር በተቀያየምህባት በሚስትህ በሲጳራ ሀገር የመጣውን ውርጅብኝ እንደሰማህ እንዳየህ ተስፍ አደርጋለሁ።ስማኝማ ሙሴ እስራኤል ዘነፍስ የተባሉ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ተሸብሯል።እንደዚህም ሁኗል፦
1 ሰላም በጠፍባት ሀገር ሰላምታተከልክሏል።ይሄ መከልከልስ በሰሙነ ህማማት በሆነ ጥሩ ነበር
2 ህዝቡ እንዳይቀራረብ በ 2 ሜትር እርቀት እንዲጓዝ ተወስኗል
3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከግቢ መውጣት ተከልክለው ቤተ እግዚአብሔር ናፍቋቸዋል።
4 ህዝቡ በወሬ ብቻ ሳይታመም ታሟል።
ሙሴ ሆይ መቸም በነፍስም በስጋም ተዛምደናል እና ታዲያ ዝምድናችን በችግር ጊዜ መረዳጃ ካልሆነ ምኑን ዝምድና ሆነ።እባክህ መፍትሄ ንገረን ያደረግንልህን እንክብካቤ መቼም አትረሳም።ምን እናድርግ ንገረን መቼም በግ አርዳችሁ ደም እርጩ በትሬንም እንኩ የኮሮና ምልክት ስቀሉ አትለንም።ምክንያቱም እንኳን በምሳሌው እውነተኛ የክስቶስን ደም የአፍችንን እና የልባችንን መቃንና ጉበን ቀብተን እምነት ጎድሎን ውሃ ላይ እንዳለች ኩበት ሁነናል፤በትርህንም አንፈልግም ምክንያቱም እውነተኛው የክርስቶስ መስቀል በእጃችን ነው።ለነገሩ ትንሽ ከሰነበትን ሥጋ እና ደሙን የምንቀበልበት ከቤታችን እናምጣ የሚያቀብሉን መስቀል የሚያሳልሙን ካህናትና ዲያቆናት አፍቸውንና እጃቸውን ይሸፍኑ ማለታችን አይቀርም።አሜሪካ እና ቻይና የሆኑትን ነበር መሆን ምንፈልግ ይሄው እዛ ሳንሄድ እዚሁ መሰልናቸው።በብልጽግናቸው ባንመስላቸው እግዚአብሄር ይመስገን ኮሮና አመሳስሎናል።እባክህ እነሱን አንምሰል ጤነኛ እንድንሆን ምን እናድርግ ንገረን።ወይ ከእግዚአብሔር ተማክረህ ሀኪም ሉቃስን ላክልን አልያም እኔን ከህይወት መጽሐፍ ሰርዘኝ እንጅ ህዝቡን አትንካ የሚል እረኛ ይነሳልን።ምንደኛው እኮ በዛብን።በዛውም አማትህ ዮቶርን ላክልን ህዝብ እንዴት እንደሚመራ መሪያችንን ያስተምርልንን።
@Mgetem_bot
"የቤተ ክርስትያን መመሪያ ከእምነት መጉደል ቆጥሮ የሚተች ሰው ካለ በጠንካራ እምነቱ ኮሮናን በማስወገድ እንዲገላግለን በትሕትና እንማፀናለን"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#stayathome
#በቤትመሆንመልካምነው
#Manaturuungaaridha

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Bot
Forwarded from Daregot Media
ውድ የዳረጎት መጽሔት አንባቢዎች

እነሆ ዳረጎታችን በቁጥር 6 ዕትሟ ወደ እናንተ ልትደርስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቷታል፡፡ ዳረጎትን ለመቋደስና ከማዕዷ ለመካፈል የምትሹ ሁሉ እጃችሁን ታጥባችሁ፣ ማህበራዊ ርቀታችሁን ጠብቃችሁና እንደው ግድ ካላለ በቀር ከቤት ሳይወጡ በጸሎት ተግተው እንዲጠብቁን እያልን ከቀናት በኀላ ዳረጎታችንን ይዘን እንቀርባለን፡፡

ከጥንቱም ተካፍሎ መብላት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነውና በዚህ ሰዓት ሥጋዊ መብል ላጡት ካለን እያካፈልን ለመንፈሳዊው መብል ደግሞ ዳረጎት ይዛ የቀረበችውን መጽሔታችንን ለሚወዱት እንዲያጋሩና ከገበታችን እንዲሰየሙ ( ገጻችንን እንዲቀላቀሉ ) ከወዲሁ በክርስቶስ ፍቅር እንለምናችኀለን፡፡

Join Us @daregot
#ሚካኤል
@Mgetem

ከአለቆች መካከል አንዱ እና ነው ዋና፤
መሰረት የሆነ ለኔ ህልውና፤
አይርቅም ፈፅሞ ላፍታ ከአጠገቤ፤
የህይወቴ ዋልታ አዋቂ የልቤ።
ሚቀድም ሚከተለኝ በሄድሁበት ሁሉ፤
የሚንከባከበኝ ዘመኔን በሙሉ፤
ጠባቂዬ ለኔ እሱ ነው ሀያሉ።
አልጠራጠርም አልፈራም ፈተና፤
ለጥማቴ እርካታ ለእራቤ መና፤
አዳኝ ጠባቂዬ አለኝታዬ አለና።
...... ምንም ባስቸግረው በሃጢአት ስራዬ፤
ነፍሴን እረስቼ ብኖር ለስጋዬ፤
አሁንም አራቀኝ ሁኗል ጠበቃዬ።
በተሰበረ ልብ ስሙን ለሚጠራ፤
በፈጠነ እርዳታው ልቦናን ሚያበራ፤
በትህትና ግርማ በፍቅር የሚመራ፤
ለፍጥረት በሙሉ የሚያዝን የሚራራ፤
የእርህራሄ አባት የማይዘገይ መልሱ፤
ለድህነት ተልኮ ሚፈጥን ከንፋሱ፤
ዋሴ ጠበቃዬ ሚካኤል ነው እሱ።
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@duksha
ቦሌ መድሐኔዓለም የሆሳሕና በዓል ተከብሯል ህዝብ ክርስቲያኑ ርቀቱን መጠበቁን የተላከልን ፎቶ ያመለክታል።

Via~Yenetube
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Bot
2025/07/07 02:50:04
Back to Top
HTML Embed Code: