Telegram Web Link
የመንፈሳዊ ግጥም ቻናል ቤተሰቦች
የመንፈሳዊ ግጥም ግሩፕ ስለከፈትን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀላሉ
👇

https://www.tg-me.com/joinchat-GvI-gxt-0dfDVv6kx2QYNg
✞የተባረከች.........✞


የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች
👁📖👁📖👁📖👁📖👁

የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች
🗣👂🗣👂🗣👂🗣👂

የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል
💧💧💧💧💧💧💧💧💧

የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች
👑👑👑👑👑👑👑👑👑

የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም
🗣🙏🗣🙏🗣🗣🙏🗣🙏

የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞

የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች
👐👐👐👐👐👐👐👐👐

የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች
🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶🚶

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

https://youtu.be/75GFp4SBUEg
የመንፈሳዊ ግጥም ቻናል ቤተሰቦች
የመንፈሳዊ ግጥም ግሩፕ ስለከፈትን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀላሉ
👇

https://www.tg-me.com/joinchat-GvI-gxt-0dfDVv6kx2QYNg
📌የመዝሙር ግብዣ
#በርባን_እኔ_ነኝ
ዘማሪት :- ትዕግሥት¶ ስለሺ

በርባን ይፈታ በርባን ይፈታ
ይሰቀል ክርስቶስ ይሰቀል ጌታ
የሚለው ጩኸት ሆነ መዳኛዬ
በርባን እኔ ነኝ ማረኝ ጌታዬ
በአንተ መታሰር እስሬ ተፈትቶ
በአንተ መጎተት ቀንበሬ ላልቶ
ነጻ የወጣሁ ኃጢአተኛ
እኔ ነኝ የዓለም ክፉ ወንጀለኛ
አንተ ተጠልተህ የተወደድሁት
አንተ ተዋርደህ የተከበርኩት
በርባን እኔ ነኝ ውለታ ቢስዋ
የዋልክልኝን ሁሌ የምረሳ
ዘውድ እንድቀዳጅ እሾኽ ደፍተሃል
ለነጻነቴ ተቸንክረሃል
እኔ ግን ተመለስኩ ወደ ኃጢአቴ
መች ተወኝና በርባንነቴ

ግጥም :- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ዜማ :- ዘውዱ ጌታቸው
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot

https://m.youtube.com/watch?reload=9&feature=youtu.be&v=mP5jWCOwyI8&fbclid=IwAR3m5ZQGcNfyAExazS23IVarEVBQ9eJfN2SbXMQLpB4gS4OarLtSDU2hLL8
Forwarded from Daregot Media
#ዜና_ህመሙ_የመድኃኔአለም
@Mgetem

አይሁድ አርብ ሌሊት ዘመድ መሰሉና
ወደ ጌታ መጡ እያበሩ ፋና
በመንፈቀ ሌሊት ልይዙት ሲመጡ
ግርማ መለኮቱን አይተው ደነገጡ
ማንን ትሻላችሁ ብሎ ጠየቃቸው
ኢየሱስ ናዝራዊ አሉት በቃላቸው
ኢየሱስ ናዝራዊ እኔ ነኝ ስላቸው
ኃይለ መለኮቱ የኋሎሽ ጣላቸው
ዳግመኛ አስነሳና አበረታታቸው
በሰውነቱም ላይ አሰለጠናቸው
ከእነርሱ ጋር ነበር ይሁዳ መሪያቸው
 ጫማውን ሳመና አመለከታቸው
ተረባረቡበት እንዳያመልጣቸው
የአምላክነት ስራው ትዝም አላላቸው
ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ሄደ ከላያቸው
ሴይጣን በጨለማ ስላሳወራቸው
የሃይማኖት ብርሃን ጠፋ ከልባቸው

ገመሱና ራሱን መቱት በብረት ዘንግ
ይጎትቱት ጀመር እንደ ሚታረድ በግ
የሚጎትቱበት ገመዱ ሁለት
አንደኛው ከአንገቱ ያጠለቁበት
አንደኛው የፈጥኝ የታሰረበት
አንዱ ወደ ኋላ አንዱ ወደፐፊት
አየተጓተቱ አመናተሉበት
ዓይኖቹን ሸፍነው እንደዚህ አሉት
#በጥፊ_ማን_መታህ
#በዱላ_ማን_ገጨህ
በል ተንቢይ ትንቢት
ኢየሱስ ናዝራዊን አሉት #በትእቢት
             

       የይህዳ ዘመዶች ምቀኞች አይሁድ
     አስረው አንገላቱት በቃጫ ገመድ
ከዮሃንስ በቀር የለውም ዘመድ
ከድንግል ማርያም ጋር እንባቸው ሲወርድ
ግሩማን መላእክት የሚሰግዱለት
እንስገድ እያሉ #አሽሟጠጡበት
ደረቱን በብረት ጦር አምጥተው #ወጉት
        በ አምስት እንጄራና በሁለት አሳ
       አጥግቦ ሲመግብ ለሐምሳ ሺ ጎሳ
መለኮቱን ቢገልጥ በደብረ ታቦር ላይ
ፊቱ ተለውጦ ባበራ እንደ ፀሃይ
    #ሸሽተው_ተደበቁ_እንዳያዩ_ስቃይ
ሙሴ በመቃብር ኤልያስ በሰማይ
ፊቱን በእጅ መታው የሐና አገልጋይ
መከራውን ሁሉ ችሎ በትእግስት
ሰሪ የሉም ብሎ ማለደ ስርየት
ሳያውቁ ነውና #የሚበድሉት
             

እሱም እንደ አንድ ሰው ስጋ ተዋሃደና
አስረው አስገረፉት ቀያፋና ሃና
         እንደ በደለኛ #ልብሱ_ተገፈፈ
        እንደ ወንጀለኛ #ጀርባው_ተገረፈ
     ደሙም እንደ ዝናብ #ከመሬት_ጎረፈ
የእናቱ ልቦና ምንም አላረፈ
የእርሱን ደም እያየ #እነበዋ_ረገፈ
የሚሰቅሉበትን መስቀል አሸክመው
እንደ ደካማ ሰው ጉልበቶቹ ደክመው
የግርፋት ቁስል ክንዱን ስለመታው
እጹን ተሸክሞ መራመድ አቃተው
በስጋው ስቀበል የአለምን መከራ
አምላክ #ተሰቀለ_ከወንበዴ_ጋራ
           

የግራውን ትቶ #የቀኙን_ወንበዴ
በቅፅበት መረጠው አምላክ
              #እንደ_ስንዴ
         ደመናን ለሰማይ ያለበሰ ጌታ
        አበባን ለመሬት የሸለመን ጌታ
በቀራንዮ ላይ እርቃኑን አይታ
ፀሐይ ጋረደችው ብርሃኗን አጥፍታ
ለታመመው አምላክ ለደረሰ ለሞት
ምነው ማጋታችው የመረረ ሐሞት
ከቅዱስ ስጋው ላይ ስለያት ነፍሱን
እየተገረሙ #ተነሱ_ሙታን

            
ከመስቀል አውርደው #ገነዙት_በልብስ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ እያሉ ቅዱስ
ወደ ሲዖል ወርዶ በአካለ ነፍስ
በሃይለ መስቀሉ መግቢያዋን ሲያፈርስ
ከነ ሰራዊቱ #ሸሸ_ዲያብሎስ
እስረኞችን ፈትቶ ይዞ ሲመለስ
ገነት አስገብቶ ክብሩን ለማውረስ
አለመለማቸው #በመንፈስ_ቅዱስ
የማትጨክነው ርሁሩህ አምላክ
ስለኛ ሃጢያት መስቀል ተሸከምክ
በዲያብሎስ ውጊያ እንዳንማረክ
#ስለ_እናትህ ብለህ ስራችንን ባርክ
አምላካችን ክርስቶስ ማነው ካንተ ሌላ
የምግባር መሶሶ #የሃይማኖት_ባላ

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
#የጅራፍ_ንቅሳት
(ኤፍሬምስዩም)
@Mgetem
=====//=====
ከጀርባህላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑትይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
#ያንተው_ነኝ_ምንጊዜም
@Mgetem

ያሰብህልኝ እና ያልኸው ስለማይቀር፤
ለኔ ምቾት ብለህ ብዙም አትቸገር፤
ለኔ ማይሆነውን ፈፅሞ አታሳዬኝ፤
በሚሆነው ብቻ አለምን ሙላልኝ፤
ያንተው ነኝ ምንጊዜም አትቸገርልኝ።
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_Group
@Mgetem_bot

@duksha 28/07/2012
#ማዕዶት
@Mgetem

በቀናቶች ትርጉም በሚስጥር የሞላ
ከጌታ መነሳት ከትንሳኤው ኋላ
ሳምንቱ ልዩ ነው ሚስጥር የተሞላ
በጌታ መነሳት አለም
ከበደሉ አረፍ ስላለ
ሰባቱን እለቶች በሰባት ሰንበቶች
መሰየም ተቻለ

ብላቴናው
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_Bot
#ወይ_ግሩም!!
@Mgetem

ዓለም ስትኖር ስትኖር ፈጣሪዋን ረስታ
ስትሄድ መጥፎ መንገድ ዓላማውን ሰታ
ቀና ሳይሆን በርኩስ መንገድ
የቆመች መስሏት ስትንገዳገድ
የፈጠራት አምላክ የዓለማት ንጉስ
አሳያት ርሱነቱን ከርሷም አልፎ ርሱን ስከስ


አንዴት ቢሉ
ወይ ግሩም ነው ነገሩ
🙊
ስሙ ሥስት ፊደል ሚጢጢ ትንሽ
ነገር ግን ነገሰ በነዛ በከሳሽ
ምደሩን ኹሉ ሰራለት ደና አርጎ
ሃብታም አይል ያደገ በማደጎ
ወይ ግሩም!!!!!
🙊
ይሄ ትንሽዬ ይሄ ሚጢጢዬ
ባለ ሥስት ፊደሉ ኮሮና ተብዬ
ሰውን አሳበደው ኃጢአት ስለ ሰራ
ይርቀን ነበረ ለሰዎች ብንራራ
ደምኮ ሚገርመው ይሄ ትንሽ ፍጡር
ሐኪም አባቶች ያሉትን ብናከብር
ይተወን ነበረ እየራቀን ሄዶ
አይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈለገው መሰለኝ "ና"አለው አስገድዶ
እኔ እንደሚመስለኝ ይሻላል መጠንቀቅ
እጅ ታጠብ ታጠብ እንቁም በተጠንቀቅ
ማሳል ማስነጠስ ካለብን ትኩሳት
8335 እንደውል በፍጥነት
😷
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
#ዮሐንስ
@Mgetem

ከሐዋርያቱ ብትሆንም ትንሹ፤
በስቅለቱ ነበርክ ሌሎቹ ሲሸሹ።
ብዙ ስምም ሰጡህ ባደረከው ነገር፤
ሁልጊዜም ለጌታ በነበረህ ፍቅር።
ታኦሎጎስ ብለው አንተን ሰይመዋል፤
ፍቁረ እግዚዕ ብለውም ፍቅርህን ገልፀዋል፤
ቁፅረ ገፅም ብለው በጌታ መሰቀል ምን ያህል እንዳዘንክ ተናግረውልሀል።
ለምን እንደሌሎች ዞሬ አላስተማርኩም ብለህ ስትከፋ፤
ክርስቶስ ግን ሰጠህ ከሁሉ የበለጠ የራዕዩንተስፋ።
የካህናት አለቆች መለየት ከብዷቸው፤
ይሁዳን ከፈሉት ጌታን እንዲስመው፤
ይህን ያደረጉት፥
ጌታህን በመልክም ስለምትመስለው ነው።
እስከ ቀራንዮ ሄደህ ተከትለህ፤
ለጢባርዮስም አስረክበኸዋል ስቅለቱንም ስለህ፤
የአምላክን ትምህርት አልቀበል ሲሉህ፤
ከወንድምህ ጋራ ቁጣውን ተናግረህ፤
ወልደ ነጎድጓድም ተብሎልሀል ስምህ።
ታዲያም፦
ጌታችን ፍቅርህን በግልፅ ተገንዝቧል፤
ድንግል ማርያምንም በአደራ ሰጥቶሀል፤
ሞትንም እንዳታይ ከአለም ሰውሮሀል።

ነብያት @TAOLOGOS4
@Mgetem
@Mgetem_group
ግጥም ለመላክ እና ለመፖሰት
@Mgetem_bot
#ወላዲተ_አምላክ
@Mgetem

በናዝሬት ገሊላ ብላቴና እያለች፣
ከቤቷ ተቀምጣ ጥጥ እየፈተለች፣
ሰላም ለኪ ድንግል የሚል ድምፅ ሰማች።
እሷም በመደንገጥ ወደ ኋላ ዞራ፣
ልታየው ብትሞክር እጅግ አተኩራ፣
መልአክ ነበረ ፊቱ የሚያበራ።
ይህ አይነት ሰላምታ ይደረግልኛል ፣
እንዴት ይሄ ክብር ለኔ ይገባኛል ?
ብላ ብትጠይቀው፦
የመንፈስ ቅዱስ ሐይል ይፀልልብሻል፣
እናቱ እንድትሆኚም እግዚአብሔር መርጦሻል፣
ስለዚህ ክርስቶስ በማህፀንሽ ያድራል፣
አላት በትህትና ወዳንቺ ይመጣል።
እሷም በመገረም ጥያቄ አቀረበች፣
እኔ እኮ ድንግል ነኝ ወንድ አላቅም አለች።
የእግዚአብሄር ስራ ነው የለም የሚሣነው፣
ለኤልሣቤጥ እንኳን በእርጅና ወራት ልጅን የሰጠ ነው።
ይህን ባላት ጊዜ ማርያምም መለሰች፣
እንደ እርሱ ፈቃድ ይሁንልኝ አለች፣
የሁሉን ፈጣሪ በሆዷ ተሸከመች፣
አለም ያልቻለውን በእጇ ታቀፈች፣
በፍጥረታት ሁሉ ብፅዕት ተባለች፣
ልጇንም ለማዳን ብዙ ተሰደደች፣
በመጨረሻም ግን በፈጠረው ፍጥረት ሲሰቃይ አየች።
ማቆም አልቻለችም የዛኔ እንባዋን፣
በመስቀል ላይ ስታይ ጌታ መድኃኒቷን።
እሱም ለሀዘኗ መፅናኛ እንዲሆናት፣
ልጅ ይሁንሽ ብሎ ዮሐንስን ሰጣት።
ካረገም በኋላ ቀራንዮ ሄዳ ልጇን ለመነችው፣
በዕልፍ አዕላፍ መላእክት ተከቦ አየችው፣
አምነው ሚጠሩኝን ማርልኝ አለችው።
ጌታም እንዳልሽ ይሁን እናቴ ሆይ አላት፣
ለጠየቀችውም ቃልኪዳኑን ሰጣት፣
እናም በኪዳኗ እንድታማልደን፣
ከልጅ ከወዳጇ እንድታስታርቀን፣
የተዋሕዶ ልጆች እንፀልይ በርትተን።

Nebiat&BK

@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
ገብርኤል
የኔስ መመኪያ ነው ገብርኤል አባቴ፣
ስሙን ስጠራ ነው የፀናው ጉልበቴ።
በችግር ውስጥ ስሆን ስሙን የማነሳው፣
ያሰብኩትን ነገር ዘወትር የማዋየው፣
ለየምክንያቱ ሁሌም መፍትሄ ነው።
በልቤ ዙፋን ላይ ነግሶ የሚኖረው፣
በሄድኩበት ሁሉ አብሮኝ የሚጓዘው፣
የኔ ልብ ገዢ ገብርኤል ብቻ ነው።
🖌Nebiat
@Mgetem
ራሷን #ንግስተ_ነገስት_ዘኢትዮጵያ በሚል የምትጠራው #እህተ_ማርያም በሚል ስም የምትታወቀው ግለሰብ ዛሬ ማምሻውን በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ግለስቧ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በሚፃረር መንገድ በእምነት ስም እስከ አንድ መቶ የሚደርሱ ተከታዮችን ሰብስባ በመገኘቷ ነው::የኮረና ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በወጣው አዋጅ ከአራት ሰው በላይ መሰብሰብ የተከለከለ ቢሆንም ግለሰቧ የዜጎችን ህይወት ለአደጋ በሚያጋልጥ መንገድ ሰብስባ መገኘቷ በቁጥጥር ስር እንድትውል ካደረጉ ወንጀሎች ቀዳሚ ነው ብሏል ፖሊስ::የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን በግለሰቧ ላይ በዚህና በሌሎች ወንጀሎች ሰፊ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል::

Via ETV

@Mgetem
@Mgetem_group
#ያለ_መታዘዝ_ፍሬ
@Mgetem

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሲፈጥር
ከኹሉ አልቆ አክብሮ ነበር
ኹሉን እንዲገዛ አሰናድቶ ሰጥቶ
በክብር በሞገስ አስውቦ አበርትቶ
በፍቅር እያኖረው ይህን አምላክ መሳይ
ንጉሥ አደረገው በዓለም በምድሩ ላይ
ታዲያ ይሄ ፍጡር ሲኖር ከአምላኩ ጋር
ኹሉ ተፈቅዶለት ነበር ከአንዲት ዕፅ በስተቀር
ታዲያ ይህን ሲመለከት ያ ክፉ ዲያቢሎስ
ተንኮሉን ጀመረ በማሴር ቀስበቀስ
ጀምሮም አልተወ ይልቅ ገፋበት
ከእሱ ይልቅ መክበሩ ቅናት ጫረበት
ያ ምስኪኑ ፍጡር አምሳለ እግዚአብሔር
እየኖረ ሳለ በፍቅር በክብር
በድንገት መጣበት ምንም ሳይታሰብ
ከዚያ ርጉም ከይሲ በጣም መጥፎ ሃሳብ
"አትብላ" የተባለውን እንዲበላ አምላክ ትሆናለህ አለው በሸንገላ
ርሱም ቀጥፎ በላ አምላክነት ሽቶ
ከዛ ግን ተቀጣ የሞት ሞትን ሞቶ
ሕዝቤ ሆይ ስማ ከዚህ ቃል
አለመታዘዝ ከአምላክ ያለያያል

ኤርምያስ ወልደ ሰለሞን (ኃይለሚካኤል )
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
#አባ_የትናንቱ
@Mgetem

ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?

አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ

በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው

የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ

የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ

በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ

ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ

የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ

በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
#አንተ_ግን_ደግ_ነህ
@Mgetem

በዝናብ አብቅለህ በፀሐይ አብስለህ
የምትመግብ ጌታ ፍፁም ደግ ቸር ነህ
የቸርነትህ ጥግ ቢነገር አያልቅም
የአንተ ምንጭ ውኃ ቢጠጣ ቢጠጣ በፍፁም አይደርቅም
አንተ ታላቅ አምላክ አንተ ታላቅ ጌታ
ሆነኸኛል መድኃኒቴ ፍፁም ባለውለታ
ለዚ ለውለታህ ባስብ ልከፍልህ
አንዳች አጣሁ ላንተ ሚሆን ቆሜ በፊትህ
እኔ ኃጢአተኛው ግን አሁንም በደልኩህ
እነዲያ እንዳላዳንከኝ አሁንም ከዳውህ
አታመንዝር ስትል ዝመትን ስሰራ
በሃብት በንብረቴ በከንቱ ስኩራራ
ስዘፍን ስሰክር ሰውን ሳላከብር
ስኖር ሳለ ሕጎችህን ስሽር
በኔ አዝነህ ሳለ በህይወቴ
ምድረበዳ ሆኖ ሳለ ማንነቴ
ምንም ባሳዝንህ እጅግ በጣም በጣም
አንተ ግን ደግ ነህ ፍፁም ሰው አረሳም

ዕለተ ዓርብ /ወርኀ ሚያዝያ/፳፫/፰/፳፻፩፪ዓ.ም
ኤርምያስ ወልዱ ለሰሎሞን

@Mgetem
ግሩፓችን👇
@Mgetem_group
ግጥም ለመላክ እና ለማስፖሰት 👇
@Mgetem_bot
መድሐኒያለም
እኔስ አባት አለኝ ሁሌ ሚያስብልኝ፣
በሀዘን በደስታ ካጠገቤ የሚገኝ።
ፈተና ላይ ስሆን ሁሌ ሚያበረታ፣
ፍጥረት የማይረሣ ያለም ሁሉ ጌታ።
የኔ መድሐኒያለም ስለው ደስ ይለኛል፣
እሱም ልጄ ብሎ ከአባት የበለጠ አባት ሆኖልኛል፣
የሚያስፈልግንም ያስፈለገኝንም ሁሉ አድርጎልኛል።
ጌታ ለኔ ስትል ቀራንዮ ወርደህ፣
በፈጠርከው ፍጥረት እጅግ ተሠቃይተህ፣
ፍቅርን አሳየኸኝ መስቀል ተሸክመህ።
ነገር ግን እኔ በሀጥያት የኖርኩኝ፣
የከፈልከው ዋጋ ሣይገባኝ እጅጉን በጠላት ሽንገላ እንዲሁ ተሸወድኩኝ።
ምን አለ ባረገኝ እንደ ሐዋርያት፣
ፊትህን እያየሁ ከስርህ ተምሬ ቢኖረኝ ፅናት።
እኔስ ደካማ ነኝ ይህንን አምናለው፣
የሚያበረታታ ሐይል እፈልጋለው።
የአንዲት ሀይማኖት የተዋህዶ ልጅ ነኝ፣
ለአምላኬ አገልጋይ መሆንን የሻትኩኝ፣
ጠላት ይህን ሰምቶ ከንቱ ሣያረገኝ፣
ጌታ ሆይ በሐይልህ በምህረት ጠብቀኝ።
Nebiat @TAOLOGOS4
@mgetem
@mgetem_group
@mgetem_bot
2025/07/06 11:44:12
Back to Top
HTML Embed Code: