Telegram Web Link
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ

አዝ________________

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም

አዝ________________

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ

አዝ________________

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ

አዝ________________

እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4

"ክርስቲያን ወገኖቼ እኛን የሚጠብቅ
አይተኛም እና አትፍሩ"

💚 @yeorthodoxmezmur 💚
💛 @yeorthodoxmezmur 💛
❤️ @yeorthodoxmezmur ❤️
#ዛፏ_አስተማረችን
@Mgetem

አለም ለስጋው ያንተን ፍቅር ትቶ
ለክብሩ ቢጨነቅ ዋጋውን እረስቶ
ለስጋው ሲያደላ ነብሱን እየረሳ
ከትቢያ ከደይኑ ያወጣውን ከአበሳ
ለዲያቢሎስ ተገዝቶ
ፀጋውን ተቀምቶ
ተስፋው ጨላልሞ
በጨለማ ቆሞ
የከፈለውን ዋጋ ለአፍታ እንኳን ቢረሳ
ጠላት እያደባ ሲያጓራ እንደ አንበሳ
ምንም እንኳን ቢረሳ የአምላክ ቸርነቱ
ፈጥሮ አሳልፎ ማይሰጥ ለጠላቱ
እየበደልነው የሚያነሳ
ሚያስታውስ ብንረሳ
ብንወድቅ የሚያነሳን
ተርበን ያጠጣ ያበላንን
እንደ ወዳጅህ ይሁዳ ስንበድል አንተን
ንስሃ እንድንገባ ዛፏ አስተማረችን
ለብዙ ምክንያትም ወንጌል እያወጀች
መዳን አሁን ነው ብላ እየሰበከች
አንታዘዝ ብለን አድልተን ለስጋ
የሞታችን ጦማር ከፊት ቢዘረጋ
በሃጥያት ተጨማልቀን ቢገፈፍ ፀጋችን
በባርነት ግዞት ዲያቢሎስ ሲገዛን
በእጃችን ላይ ያለው አርነት ባርነት
ነብሳችን ከወዴት ከሲኦል ወይስ ገነት
ንስሃ ገብተን እንዲምረን በእውነት
አምላክ ይጠብቀን በፍፁም ቸርነት

ምንጭ በኀይሉ ተፈሪ
ግንቦት 3/9/2012ዓ.ም
ወቅታዊ ግጥም
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
ቅዱስ ሲኖዶስ: የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎቱ በፀረ ኮቪድ-19 የጥንቃቄ ተግባራት እየተመራ እንዲፈጸም አዘዘ

• ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከመንግሥት ጋራ በመነጋገር ትእዛዙን እንዲያስፈጽም መመሪያ ሰጠ፤
• አገልግሎቱን በጥንቃቄ ተግባራቱ መሠረት ለማስፈጸም አጥቢያዎች ሓላፊነቱን ይወስዳሉ፤
• የሰንበት ት/ቤቶችን በማስተባበር፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በአግባቡ እንዲከናወን ያደርጋሉ፤
• ጥምቀቱ፣ ቊርባኑ፣ ተክሊሉ፣ ፍትሐቱ፥ርቀትን ጠብቆ በተገቢ የልኡካን ቁጥር ይፈጸማል፤
***
• ቅዱስ ሲኖዶሱ፥ የቤተ ክርስቲያን በር በግድ እየተዘጋ በፖሊስ የሚደረገውን ጥበቃ ተችቷል፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፥ “በስሜ የተደረገ እንጂ የእኔ ውሳኔ አይደለም፤” ሲል አስተባብሏል፤
• የጠቅላይ ቤተ ክህነት ፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልኡክ ዐቢይ ግብረ ኀይል፣ ሪፖርቱን ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቧል፤
• አስቸኳይ ዐዋጁን በማስፈጸም ሰበብ፣ ፖሊስ፣ በአገልጋይ ልኡካንና ምእመናን ላይ ጥቃቶችንና ማጥላላቶችን መፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶሱን አሳዝኗል፤
• ማንም እገዛ ሳይጠይቃቸው በበሯ ቆመው እየተሳደቡ እና እየደበደቡ ከፍተኛ የኀይል ርምጃ መውሰዳቸው ሳያንስ፣ ሥርዐተ አምልኮዋን የሚያጥላሉ የሌላ እምነት ተከታይ ፖሊሶችም እንዳሉበት በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
ከግንቦት 4- ግንቦት 6 ድረስ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶሱ የተሰጠ መግለጫ

@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_bot
#ዝ ጎራ....
@Mgetem

ተርቦ ያጠገበ
ተጠምቶ ያረካ
.
.
ደም ግባት አጥቶ ያስዋበ
ጥላቻን ደምስሶ ትሕትና የከተበ
.
.
በእስሩ ያስፈታ
ተሰቅሎ ያወረደ
ነብሱን አሳልፎ
ማኖር የወደደ
አምላክን ከመንበር
ከላይ ያወረደ

የክፋትን ክንድ የሰበረ
ቅንነትን ያበሰረ
እየተበደለ ሥርየት
የማለደ ከላይ ምሕረት

በእውነት ቅባት የወዛ
በሞት ሕይወት የሚገዛ
ለረገሙት የመረቀ
ጸላኢን ግንብ ያደቀቀ
የማይታይ የረቀቀ
ጀርባን ከሆድ ያስታረቀ

የጸለየ ላሳደደው
የማይቀየም ልቦናው
ፍርድ ወንበሩን ያላዛባ
ለወንድሙ የሚያነባ

ርኩሳንን የሚቀድስ
ርጉማንን የሚባርክ
ድውያንን የሚፈውስ

የማይደምን የሚፈካ
ማየ ሕይወት የሚያዘንም
ፍሬ 'ሚሰጥ የሚያረካ

ተንበርካኪ ለወገሩት
ወደ ሰማይ እያቀና
"ሥረይሎሙ ዘንተ ኀጢአት"

በጋ ያጣ ቸርነቱ
ሁሌ ክረምት
እልፍ የሆነ ትዕግስቱ
የማይደኸይ ብልፅግናው
የማይደርቅ ምንጭ የይቅርታው

ለዚህ ግሩም ፍቅር ማኅደር የሆነ
ፀሐይ የተመላ ፍጹም ያልደመነ
ደሀ አደጉን ያነገሠ መውደድ ያለው
.
.
ዝ ጎራ
.
.
ይህ ስፍራ
.
.
❤️ይህ ልብ ታላቅ ነው❤️



ረድኤት~፯/፱/፳፻፲፪~በዕለተ ዓርብ ተጻፈ::
___________________
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
📢📣
የተለያየ አይነት ዲዛይን (መንፈሳዊ ወይም ዓለማዊ) ማሠራት የምትፈልጉ በቅናሽ እንሠራለን

#አገልግሎቶች
Pro logos, Banner and Covers
◆ Telegram Stickers
◆ Cartoon effect
◆ Wallpapers & Icons
◆ Business card

#ዋጋ

Telegram sticker___ 1ዱን በ5 ብር (minimum order 15)
Channel profile pic ____ #50 Birr
birthday card____ #70 Birr
Thanks Card_____ #65 Birr
normal design for ur name &pic #50birr

For order ለማዘዝ
@solasc12
@Solasc12
@Mgetem_bot
[የፀሐይ የእሳት ቀለበት ሥነ ሥርዓት]
(በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ለፀሐይ የተጻፈ ግጥም)
@Mgetem

በሠኔ ተቃጥረው ኢትዮጵያና ፀሐይ፤
ቀለበት ለማሰር ደስ በሚል ሰማይ።
በፍቅር ሊጓዙ ደግሞም ላይከዳዱ፤
በላሊበላ ላይ ተተከለ ዐምዱ።
ምስክር ለመሆን ሠርጉን ለመታደም፤
ጋበዘችን ፀሐይ የብርሃን ዓለም።
ውለታ ሳትረሣ የካሲዮፕያን፤
ደግሞም የሴፌውስ የነአንድሮሜዳን።
ልታሣየን ክስተት ባለንበት ዘመን፤
ከዓመታት በፊት ተመካክረን ነበር።
በጠፈር የሚሆን ውበቷን ለማየት፤
ወደ ላሊበላ ተጓዝን በአንድነት።
በዚያም እንደደረስን ያየነውን ምስጢር፤
መዝግበን አኖርነው በተገቢው ክብር።
የላሊበላ ጥበብ የሥነ ፈለክም ቁልፎቹ ያሉበት፤
ደሞም ያ ሰሌዳ የሰማይ ሥርዓት የተቀረጸበት፤
በክብር ተቀምጧል ትውልዱ በምስጢር እንዲራቀቅበት።
ደግሞም እስከ ጣሊያን በሚወስደው መንገድ ተገኝቼ በአካል፤
ትክክል መሆኑን በማረጋገጤ የሳይንቲስቶችን ቃል፤
ቤተ ጊዮርጊስ ለካ ምስጢራዊ ነበር የማይገለጽ በቃል።
ሠኔ 12 በቅዱስ ላሊበላ በዕረፍቱ በዓል፤
ገድሉን በመተርጎም ደግሞም በማገልገል፤
ተሳትፌ ዋልኩኝ በረከትን በአካል።
ሠኔ 14ት መጣ የቀጠሮ ዕለት፤
ሊደገስ ድግሱ በሰማይ ሰገነት።
የአጥቢያ ኮከብ ቬኑስ የጠፈር እንክብል፤
ፀሐይን በመቅደም የጠፈሯን አክሊል፤
ደምቃ ትታይ ነበር በምሥራቁ በኩል።
ቀዝቀዝ ባለው ሌሊት ነፋስ በበዛበት፤
የሰማይ ከዋክብት በዝተው በታዩበት፤
ተራራ ላይ ወጣን ውበትን ለማየት፤
ፀሐይ ቀለበቷን በውል ልታስርበት።
12:10 ላይ ኦርያሬስ ወጣች ደግሞም ቶማስስ፤
ፀሐይ ጀምበራችን ልትኩነሰነስ።
ውበቷ ፈንጥቆ እንዲያ ስትታይ፤
መመሰጥ ጀመርኩኝ በደማቁ ሰማይ።
ለግርዶሽ ለጥሎሽ 12:45 ላይ ጨረቃ ብቅ አለች፤
ብናሴና ኤራዕ ተብላ የተሠየመች።
ሙሽራን መጋረድ ደግሞም መሸፋፈን፤
ወግ ነውና ይኼ ለባህል መታመን።
ጨረቃ ናትና የደማቋ ፀሐይ ዋና ፕሮቶኮል፤
መጋረድ ጀመረች የፀሐይን ክፍል።
የፀሐይን ውበት ደግሞም ዘውድ አክሊሏን፤
ሰንፔር የመሰለ ደማቅ ቀለበቷን።
የሙሽራ ልብሷን ንጹሕ ብርሃኗን፤
ለማየትም ጓጓሁ ያንን ውብ አካሏን።
ሚዜዎቿ መጡ ሁለቱ ፕላኔት፤
ከግራና ከቀኝ አጅበዋት ድንገት።
ተገለጡ ዛሬ በውበት በድምቀት፤
ሜርኩሪና ቬኑስ ለሠርጓ ሥርዐት።
ለሙሽሪት ፀሐይ ለሠርጓ ድግስ፤
ሳተርን፣ ጁፒተርም ደግሞም ቀይዋ ማርስ፤
በክብር እንግድነት ሰመር ሶልስቲስ፤
ጋላክቲክ አላይመንት ሠራ ስካይ ክሮስ።
ትንፋሼ ጨመረ የልቤም ትርታ፤
ተሠርቶም አያቅም እንዲህ ያለ ምስጢር በሰማይ ላይ ካርታ።
በስቶንሄንጅ፣ በጊዛ፣ በማያ ቀመር ላይ፤
የሠኔ 14ቱ የ2012ትም መሠራቱንም ሳይ፤
በአድናቆት በፍርሃት ተዋጥኩኝ በሰማይ።
2 ሰዓት ሆነ ጊዜውም ደረሰ፤
ሰማይ በሮዝ ቀለም ውበት አፈሰሰ።
ለአቀባበሏ አምላክ ለፈጠራት ለዚች ውብ ፍጥረት፤
ለሙሽሪት ፀሐይ ለሠርጓ ዕለት፤
ሁሉም ሰልፉን ሠራ ደምቆ በማብራት።
ብቅ አለች ቶማስስ ዘውዷን ተቀዳጅታ፤
እሳት ቀለበቷን በሰማይ አብርታ።
እልልታው ጩኸቱ ከምድር አስተጋባ፤
ኃይሎጋው ከጠፈር ደምቆ እየገባ።
ድግሱ ቀጠለ ጫጫታው በረታ፤
የአድናቆትን ጮቤ በእግሩ እየመታ።
በሰማይ ላይ ድግስ በዚች ውብ ዕለት፤
የወደፊት ምስጢር ተቀመረባት፤
ያስተዋለ ብቻ ያውቀዋል ድንገት።
3:15 ላይ የሠርጓን ሥርዓት በማጠናቀቅ፤
ለጫጉላ ሽርሽር ጉዞ አደረገች ወደ ሩቅ ምሥራቅ።
እንደዚህ የደመቀ የሠርጓን ሥርዓት አይቼ በዐይኔ፤
ኬክሮሷን ለማወቅ አደረብኝ ወኔ።
ቀጠሮ ያከበረች ሙሽሪት ፀሐይ፤
ንፍገት የለምና በፈለክ ሰማይ።
ኬክሮስ ኬንትሮሷን ጥንተ ኦንን ብመኝ የፀሐይን ሥርዓት፤
ውበቷ ታይቶኝ በሠኔ 14 በሙሽሪት ቀኗ ሰንፔር ቀለበት።
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
#ይኸው_ዛሬም_አለ!
@Mgetem

*
*
አምላኬ አምላኬ!
ተመስገን ጌታዬ ለዚ ላደረስከኝ
በህይወት አኑረህ ዛሬን ላሳየኸኝ
ላልተውከኝ እንዲሁ ምግባሬን አስበህ
ከ ሀፅያቴ ብዛት በኔ ተስፍ ቆርጠህ!።

እኔማ እኔማ!
ምግባረ ከንቱ ነኝ ስሜም አመንዝራ
በሞት አደባባይ ለሞት የምሰራ
ባዶ ነው ኑሮዬ ታሪክ ነው ህይወቴ
ሳልቀበር የሞትኩ ሳልሞት አስቀድሜ
ሻማ የሚበራልኝ በመቃብሬ ላይ ሊከበር ልደቴ!
ኖሬ ማላውቅ አኔ ልታሰብ በሞቴ!!።

ግን ግን አምላኬ ግን!
ይኸው ዛሬም አለ....ልጄ ሆይ እያለ!
ለሀጥአን ነዉ እንጂ ለፃድቃን ያይደለ
ያ የደም መስዋት ላንቺ የተከፈለ
ህይወት አለሽ ልጄ በቃል የታተመ
ነይ ተመለሽ ልጄ...ነይ ወደኔ እያለ!......ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ....ልጄ ሆይ አያለ!
ተስፋ ላይቆርጥብኝ በራሱ እየማለ
ነይ ወደ አባትሽ ቤት ተመለሸ ወደኔ
ላንቺ ከሰጠሁሽ ከስጋ እና ደሜ
ያዘጋጀሁልሽ የዘላለም ህይወት በዚያ አለ እያለ
..................ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ!...አሳዝኜው ሳለ!
ይሰማኛል ድምፁ ከበስተሇላዬ ልጄ ሆይ እያለ!
መልካሙ እረኛ የጠፋሁት እኔን እየተከተለ
ፈፅሞ ላይተወኝ በራሱ እየማለ
እጆቹን ዘርግቶ በፍቅር አንደበት ነይ ወደኔ እያለ!
...................ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ!.....ልጄ ሆይ እያለ!
በሀፅያት ወድቄ በሀጥያት ስዳክር
ህይወት ጨልማብኝ መሄጃ ሲጠፍኝ አዝኖ እያስተዋለ
እኔነቴ ጠፍቶኝ ማንነት አጥቼ እንዲሁ ስባዝን
ውስጤ ተስፋ አቶ የኑሮዬ ክብደት አስጨንቆኝ ሳለ
የካድኩት አባቴ! ዛሬም ከኔ ጋር ነው...ልጄ ሆይ እያለ!

ይኸው ዛሬም አለ!...
በድዬው እያለ ስለኔ ተጨንቆ ልቡ እየቆሰለ
ይሰማኛል ድምፁ ከበስተሇላዬ እየተከተለ
ሸክሜን አውርዶ በፍቅር ሊሸከም ነይ ወደኔ እያለ!
ልጄ ሆይ!...ልጄ ሆይ!...ልጄ ሆይ! ይለኛል በራሱ እየማለ
ይኸው ዛሬም አለ!...ይኸው ዛሬም አለ!...ልጄ ሆይ እያለ!!!
ይመስገን አምላኬ!..ሩህሩሁ አባቴ ከኔጋ ስላለ!!!

ፌቨን ሰለሞን
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
ውድ የመንፈሳዊ ግጥም ብቻ ቤተሰቦች በሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት ግጥሞችን ሳንለቅ በመቆየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ከዛሬ ጀምሮ እንደ በፊቱ አዳዲስ ግጥሞችን ይዘን እንቀርባለን፡፡ @Mgetem
ኢየሱስ ሲመጣ በግርማ መንግሥት
@Mgetem

በመላእክት ጭፍራ በእልፍ አእላፋት
እምቢልታ ሲነፋ ደግሞም መለከት
እየተለጎ ታላቅ ነጋሪት
ምድር ስትናወጥ ሲጨነቅ ፍጥረት
ዓመፀኛ ሁሉ ይላበሳል ሐፍረት
በሠራው ኃጢኣት
አልቅሶ ተጨንቆ ያበዛል ጩኸት
ከሚያስፈራው አምላክ ከግሩሙ ፊት
ተራሮች ክደኑኝ ትዋጠኝ መሬት
ብሎ ይማጸናል በዚያች ሰዓት
ሕጉን የጠበቁ ያልሠሩ ኃጢኣት
በአምላክ ያመኑ በጸጋ ጥምቀት
በርሱ ደስ ይላቸዋል ተነሥተው ከሞት
በቀኝ ይቆማሉ ለመውረስ ሕይወት
ኢየሱስ ንጉሡ የዓለም መድኃኒት
በቃሉ አመስግኖ ይሰጣል ርስት
በዚያ ያኖረዋል በተዋበ ቤት
ለሰማዩ ጌታ ለዓለሙ ንጉሥ ለአምላክ ጸባኦት
በዚያ ይዘመራል እንደ መላእክት
ሁሉን ይነግረናል ድርሳነ ሰንበት
መመልከት ይገባል ዕለት በዕለት
ሁልጊዜ መጸለይ ያለመታከት
አስፈሪዋ ሰዓት ከመድረሷ በፊት

@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
Daregot 7th Magazine.pdf
2.9 MB
ዳረጎት ዘተዋሕዶ 3ኛ ዓመት ቁጥር 7
አውርደው ያንብቡ

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @daregotmedia

ለአስተያየት @DaregotMediaComment_bot
ስንቄን ይዣለሁኝ
@Mgetem

በእንተ ስለማርያም ኮሮጆዬን ይዤ
ልለምን አይደለም ልማር ልወቅ ብዬ
ጌታዬን ማመስገን ሰዓታት ዜማውን
ውዳሴ ቅዳሴ ቅኔ ማኅሌቱን
ምን እበላ ብዬ መች አስባለሁኝ
በእንተ ማርያም ስንቄን ይዣለሁኝ
ለአባ ሕርያቆስ ጸጋው ቅዳሴሽ
የአባ ጊዮርጊስ ሰዓታት ዜማሽ
ደግሞ ለአባ ኤፍሬም ምግቡ ውዳሴሽ
ይህንን ስሰማ መሰጠኝ ፍቅርሽ
ከመምር መምር ለመማር ምስጢር
በቅሎ ፈረስ አልል አልመኝ ባቡር
ለምለም ሣር ፍራሼ ድንጋይ ነው ትራሴ
አንቺን ሳመሰግን ትረካለች ነፍሴ
ከአንዱ ሀገር ሌላ ሀገር መምር ፍለጋ
ልማር ልመራመር ድጓ ጾመ ድጓ
#ሐመር

@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
በደብረ ታቦር
@Mgetem

መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ
በተቀደሰው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት
ዮሐንስ ጴጥሮስን ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አንሥቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮቱ በብርሃን ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ሰሙት እስከ ዘለዓለም
ሕይወት በእርሱ ነው ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።

ከሀብታሙ ገበያው
@Mgetem
@Mgetem_bot
@MENFESAWItsufoche
የደብረ ታቦር ግጥሞች ላኩልን ብላችሁ ለጠየቃችሁን 👇
አስተያየታችሁን እዚህች ቦት ላይ ላኩልን
@Mgetem_bot
#የቆሎ_ተማሪ
@Mgetem
........................
ግዕዙን ለማወቅ ቅኔ ማህሌቱን
ታሪክ ወግ ባህሉን ሊያስቀጥል ያባቱን
ቁምጣውን አጥልቆ ኩታውን ደርቦ
ደግሞም ይለምናል እንዲሠጠው ዳቦ
.....................
ስለ እመብርሃን ስለ አዛኝቷ
ይኅው መጥቻለሁ አለው ከዛች ቦታ
እማዬ እናቴ እንዳስለመድሽኝ
ቁራሺቷን ዳቦ በጠላ ስጪኝ
............................
እያለ ቢለምን ከበራፍ ላይ ሁኖ
አያፍርም ነበረ በእርሷ ተማፅኖ
ጠላውን በጣሳ ቂጣውን በሰፌድ
ተብሎ ይሠጣል ቢሆንህ ለመንገድ
...................................
ሲሄድ ሲገሰግስ ሲሄድ በየዋርካው
ደግሞም ይለምናል ቢሆን ለማደሪያው
.............
የቆሎ ተማሪው ተርቦ ቢጠይቅ
የቆሎ ተማሪው ተጠምቶ ሲጠይቅ
ተስፋው ቅኔ ሁኖ አያቅም ዘር ብሔር
ይጣደፋል እንጂ ሠጪውን ለማክበር።
@MsganaAk

@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem_bot
የጠዋቱ ጮራ
@Mgetem

ዘመነ ሐዋርያት የጥንቱ
የክርስትና ጎህ የጠዋቱ
ተመልሰህ ና! እንደገና
የጽዋዕው ማኅበር ....
በአንድ ልብ መምከሩ በአንድ ቃል መናገሩ
ከቶ ጠፍቷልና ጨርሶ ከምድሩ
እባክህ ተመለስ ዛሬም እንደገና
መሠረተ እምነት መቅድመ ክርስትና
የሐዋርያት ዘመን የዘለዓለም ፋና
በአንድ መሶብ ዙሪያ ተቋርሶ መብላቱ
በአንድ ጽዋዕ ዋንጫ ቀርቶ መጠጣቱ
የያኔው አሻራ የጠዋቷ
ኧረ ለምን ይሆን ደብዝዞ; ደብዝዞ መቅረቱ
የነደደው እሳት ፍቅር ፍም መጥፋቱ
እንዳይተርፍ ተብሎ ስስት ተጀመረ
በረከት መባሉ ያኔ ድሮ ቀረ
መሶቡ ተነሥቶ በእጅ ሆነ ገበታው
ተድበለበለች ቁርጥ ሆነ እንጀራው
ጸጋው መቆረጡን ማንም አላሰበው
ያኔ! ለጴጥሮስ ሲያስረክብ ርስቱን እየሸጠ
የያኔው ክርስቲያን መች በረኀብ ተዋጠ
መቼ ጎደለበት መቼ ተንገላታ
በፍቅር ኖረ እንጂ አንዴም ሳይፈታ
በረከት በዝቶበት በብዙ ገበታ
እንያ ሐናንያ ሲጳራ ልባቸው የዋለለ
ወደ ገንዘብ ፍቅር ወዲያው ያጋደለ
በሊቀ ሐዋርያት በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል
በመንፈስቅዱስ ጅራፍ ተቀጥቅጠዋል
ባለሙት ሁሉም ላይ ሄዶ ቀርቷል
ቀዳሚት ተዋሕዶ የሐዋርያት
የፍቅር ጸጋ በረከት
አትራቂ አትሽሺ አትለይን በእውነት
ከፊት ምሪን እንጂ በመሆን አብነት
ሁሉም እንደወጣ በአንቺ አርነት
ጽዋዕና መሶቡን ዓለም ሲጥለው
በእኛ ዘንድ ተገኘ የጥንት አሻራው
ሸክላ ነህ ስላለህ እንዳይቀር አደራ
እንደ ገዳማቱ እንኑር በጋራ
ብርሀን ነውና የጠዋቱ ጮራ

@Mgetem
@Mgetem
@Solasc12
2025/07/05 19:52:13
Back to Top
HTML Embed Code: