Telegram Web Link
#እንኳን_አደረሳችሁ

#የኢትዮጵያን_ነገር…..
@mgetem

አባ አባ ብዬ - በለመንኩህ ለቅሶ - ተሰምቷል ጩሀቴ
በውን ያስጨነቀኝ - ተራራው ፈተና - ተነስቷል ከፊቴ
የተማመንኩበት - የሥምህ ስንቅነት - አንዳች አልጎደለ
ተስፋ ያደረግሁት - የጸሎትህ ሥምረት - በሕይወቴ አለ
የተደገፍኩበት - የደጅህ ዋስ’ነት - ሜዳ አልጣለኝም
እንባ የረጨሁበት - የ’ስማኝ!’ ዋይታዬ - አልወደቀብኝም
ከህጻንነቴ - አንተን ተማምኜ - የሄድኩበት መንገድ
በጥቅጥቁ ጫካ - አንበሳው አልነካኝ - አልሆንኩ አልቦ ዘመድ
ልጅነቴ ሁሌ - ገብረ ሕይወት እያለች -በምልጃህ ተማምና
ትናንት እንዳልተውካት - ዛሬም ስትጣራህ -ለነፍሴ ጭንቅ ና፡፡
Abboo! - Aabboo! ብዬ - ሀገር አሻግሬ - ስምህን እጠራለሁ
ከግብጽ በረሃ - ለምትሻህ ኢትዮጵያ - ቶሎ ና እላለሁ
ታስፈልጋታለህ - እንኳንና ለሰው - ለአናብስት ሁሉ
የጽድቅህን ፍሬ - የቀመሱ ነፍሳት - አባ አባ ይላሉ
የንጽኅናህ ግርማ - ከግብጽ እስከ ኢትዮጵያ - ሀገር እያወደ
አንበሳውም ነብሩም - እያገለገለህ፣- አንተን እያጀበ- ካንተ ጋራ ሄደ፡፡
አቡዬ ና ድረስ- ና ገስግስ ዘንድሮም - ቶሎ ና ለሀገሬ
እረፉ በላቸው - እንዳይናከሱ - ሰውንና ሰውን - ሰውንና አውሬ፡፡
ዛሬም ቁም ዝቋላ - ግባ ከባህሩ - እጆችህን ዘርጋ
ፈልግ ልጆችህን - የጸሎት ፍሬህን - የጠበቅኸውን መንጋ
ከሰሜን ከደቡብ - ከምስራቅ ከምዕራብ - የተጋደልህለት
“ኢትዮጵያን ማርልኝ !” - ብለህ ከአምላክህ ፊት - ብዙ የጸለይክለት
የረገጥከው መሬት - ያረፍክበት ደብር - የነካህ አፈሩ
ዳግም በዛሬው ቀን - ጸሎትህን ይሻል - መላው ሀገሩ
ምድረ ከብድ ድረስ - ተገኝ በዝቋላ - አንሳ እጆችህን
እስከምንጠገን - ተሰብረናልና - እየን ልጆችህን
አታሳፍረንም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ - ብለን ስንጠራህ
እንግዲህ አቡዬ - የኢትዮጵያን ነገር - አሁንም አደራህ!!

(አክሊሉ ደበላ ጥቅምት 5.2009ዓ.ም)
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc12
Watch "መቅድመ ነገር - Kesatebirhan Intro" on YouTube
https://youtu.be/MS4oIQ4qcUA
እንኳን አደረሳችሁ
ይህ መንፈሳዊ ግጥም የክርስቶስን የዓለም መድኃኒትነት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በማስረገጥ "የግል አዳኝ" ባዮችን ይሞግታል።
እኛም ይኼን ድንቅ የሥንኝ ቋጠሮ በዕለተ ንግሡ ጥቅምት 27 ቀንን በማስታከክ ጀባ ብለናችኋል።
👇👇 ዩቱብ ላይ
https://youtu.be/2T9kWYsC7w0
#​መድኃኔዓለም_ወይስ_የግል አዳኝ
ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

መዳን እንደ ቀለብ ፤ መዋጀት እንደ እህል፤
በቁና ተሰፍሮ የተሰጠ ይመስል፤
መሲሑን ለብቻ ፤ ኢየሱስን የግል፤
አ’ርገህ ምትቀበል፤
አድራሻህ ከየት ነው ስምህን ማን ልበል?

በእንተዝ ነገር ስምዐ ኮነ መልአክ፤
በጊዜ ልደቱ ወደ እረኞች ሲላክ።
መድኃኒት ክርስቶስ ግርግም መወለዱ ፤ በጨርቅ መጠቅለሉ፤
ለእረኞች በግል የተሰጠ ሳይሆን ለዓለሙ ሁሉ፤
እነሆ ሲታወቅ በምሥራች ቃሉ፤
አልሰማህም አሉ።

ራሱ ባለቤቱ፤
በወንጌል ትምህርቱ፤
“ለድኅነተ ዓለም በመልዕልተ መስቀል
ከምድር ከፍ ብዬ ዕርቃኔን ስሰቀል”
አንድ ሁለት ሰው ሳይሆን “ሁሉን እስባለሁ”
ሲል እየሰማነው፤
ጆሮ ነሳህ ምነው?
.
.
.
ሙሉ ግጥሙን #በድምጽ ቅንብር ከታች ያገኙታል

👇👇 ይሄን ይጫኑ


https://youtu.be/2T9kWYsC7w0
እስከ ኅዳር ዐሥራ ሁለት ባሉት 12 ተከታታይ ቀናት ከሚለቀቁ በአራት ክፍል ከተከፈሉ ወረቦች #እግዚኡ_ረሰዮ" የመጀመርያው ሆኖ ተለቋል።

በዚህ አቅርቦት የወረቡ ጥሬ ዘር(ቀለም)፣የአማርኛ ትርጉም ፣ የዋናው ወረብና የቸብቸቦውን ዜማ ከነምልክቱ ታገኙበታላችሁ።

please like share and subscribe
👇👇👇👇
https://youtu.be/YExQSQykdwc
ይህ የሥንኝ ቋጠሮ ከየትኛው ብሔር ነህ ለሚል የቸከ ዘመነኛ ጥያቄ የማያዳግም ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ይሰጣል። የአቋም መግለጫው የተወረሰው ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ጥያቄ ከመለሰለት መልስ ነው። ተጋበዙልን።

👇👇👇
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
ይህ የሥንኝ ቋጠሮ ከየትኛው ብሔር ነህ ለሚል የቸከ ዘመነኛ ጥያቄ የማያዳግም ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ይሰጣል። የአቋም መግለጫው የተወረሰው ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ጥያቄ ከመለሰለት መልስ ነው። ተጋበዙልን።

👇👇👇
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
"አንተኑ ሚካኤል መና ዘ አውረድከ" የሚለውን ወረብ በሦስተኛት እነሆ ጀባ ብለናችኋል።

በዚህ አቅርቦት የወረቡ ጥሬ ዘር(ቀለም)፣የአማርኛ ትርጉም ፣ የዋናው ወረብና የቸብቸቦውን ዜማ ከነምልክቱ ታገኙበታላችሁ።

https://youtu.be/M5BW2jiam8Q
"አንተኑ ሚካኤል መና ዘ አውረድከ" የሚለውን ወረብ በሦስተኛት እነሆ ጀባ ብለናችኋል።

በዚህ አቅርቦት የወረቡ ጥሬ ዘር(ቀለም)፣የአማርኛ ትርጉም ፣ የዋናው ወረብና የቸብቸቦውን ዜማ ከነምልክቱ ታገኙበታላችሁ።

https://youtu.be/M5BW2jiam8Q
Forwarded from Deleted Account
እንኳን_ለታላቁ_መልአክ_ቅዱስ_ሚካኤል_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ

የኅዳር ሚካኤል ወረቦችን,
የወረቡን ጥሬ ዘር(ቀለም)፣የአማርኛ ትርጉም ፣ የዋናው ወረብና የቸብቸቦውን ዜማ ከነምልክቱ ተካተው ከታች ባሉት ሊንኮች ታገኛላችሁ።

የኅዳር ሚካኤል ወረብ 1 ''እግዚኡ ረሰዮ"👇👇
https://youtu.be/YExQSQykdwc

የኅዳር ሚካኤል ወረብ 2 "ውእቱ ሚካኤል"👇👇
https://youtu.be/YeAdlJa8r3Y

የኅዳር ሚካኤል ወረብ 3 "አንተኑ ሚካኤል" 👇👇
https://youtu.be/M5BW2jiam8Q

ሰብስክራይብ ያድርጉ👇👇
Kesatebirhan Ze Tewahdo

https://www.youtube.com/channel/UCH5c3LZnu5c-cVbPT0ZI-rg
#አሻግረን_ባህሩን
@Mgetem

ለነፃነት ያልነዉ፣ የግብፅ ህልም እንጀራ ፣ ባርነት ሆኖብን፤
የሸጥነዉም ዮሴፍ፣ በሕሊና ወንበር ፣ እየፈረደብን፤
በባዕድ ሀገር በዝተን ፣ የበረከት ፈንታዉ ፣ ጥሎን ከሥጋቱ፥
የወለድነዉን ልጅ ፣ መልሰን ከጭቃዉ ፣ ረግጦ መጫወቱ፥
ያኘክነዉም ጮማ ፣ ከጥርሳችን ሳይወርድ ፣ የመርገም ሞት ጠርቶ፥
የመኖር ህግ ሲጎድል፣ በሞት ተጠግቶ…ሞትን ተመክቶ፤
ከአስሩ መቅሰፍት፣ ቸነፈር ረሃቡ ፣ ተዓምር ድንቃ ድንቁ፤
አንድ አማኝን አጥተዉ ፣ በኩረ ሞት እስኪደርስ፣ ድንጋን ላይ ሲወድቁ፤
የምፅዓት ምልክት፣ በበሮቹ መቃን፣ ቢቀባ በበግ ደም፤
የግብፃዉያን ዓይን- የጡቡን ግንብ እንጂ ፣ ይህን ማየት አይወድም።
የተፈራዉ ደርሷል፣ ሞት ገብቷል በየቤት ፣ ሀገር ተሸብራል፤
የመቅሰፍት ወላፈን ፣ መጥቶ ሲጥል እንጂ፣ ሲሄድ ተሰዉሯል፤
ለእምነት የሚሆን ፣ የበግ ደም ያለበት ፣ የእምነት ፍሪዳ፥
አንሶ ዋይታ ሆኗል፣ በፈረኦን ቤትም ፣ በእስራኤልም ጓዳ፤
ለነፃነት ብለን ፣ ሌሊት የተጓዝነዉ፣ ሌሊቱ ረዝሞብን፥
ከቀመስነዉ መና ፣ የለመድነዉ ሽንኩርት ፣ ያምናዉ አይሎብን፥
የጨረቃዉ ድምቀት፣ የኮከቡ ምሪት ፣ የሌሊቱ መንገድ፥
አንተ ካላበራህ ፣ ለመቆም አይሆንም፣ እንኳንስ ለመሄድ፤
የጪንጫ ላይ ወሃ፣ አይፈልቅም ያለ አንተ ፣ ለጥማችን አይሆን፤
የበረሃ ልብሳችን ፣ ለቀን አይበረክት፣ አያረካ ለዓይን፤
የገመጥነዉ ሥጋ ፣ ከጉሮሮ ሳይወርድ ፣ ሆኖብን ሞት ጠሪ፤
በሄድንበት ጉዞ፣ ያለ ሩኅሩኅ መልአክ ፣ ያለ መንገድ መሪ።
ከፊታችን ቆሟል ፣ የኤርትራ ባህር ፣ ግንብ ሆኖ በመፍሰስ፤
ከኋላችን መጥቷል ፣ የፈረኦን ሠራዊት ፣ ጦር ሰብቆ በፈረስ፤
ከሁለቱም በፊት ፣ ከሙሴ በትር ጋር ፣ ሚካኤል ሆይ ድረስ።
በጦርም በባህርም ፣ የኢትዮጵያ ድንኳን፣ አይተህ መሸበሩን፤
ልንሰጥም ነዉና፣ መልአከ ምህረት ሆይ ፣ አሻግረን ባህሩን።

(አክሊሉ ደበላ 2013ዓ.ም)

@Mgetem
@Mgetem
@Solasc12
#ጾመ_ነቢያት_ክፍል_1_ብፁዓት_ዓይኖች

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

በዚህ በመጀመርያው ክፍል ትምህርት ስለ ብፅዕና ምንነትና ስለ ብፁዓን እንዲሁም ብፅዓን ስለተነገረላቸው የሐዋርያት ዓይንና ጆሮዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ተዳሷል።
👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI

ቀጣዩ ክፍል እንዲደርስዎት ሰብስክራይብ በማድረግ የደውል ምልክቱን ይጫኑ
👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI
#ጾመ_ነቢያት_ክፍል_1_ብፁዓት_ዓይኖች

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

በዚህ በመጀመርያው ክፍል ትምህርት ስለ ብፅዕና ምንነትና ስለ ብፁዓን እንዲሁም ብፅዓን ስለተነገረላቸው የሐዋርያት ዓይንና ጆሮዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ተዳሷል።
👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI

ቀጣዩ ክፍል እንዲደርስዎት ሰብስክራይብ በማድረግ የደውል ምልክቱን ይጫኑ
👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
#የማንነት_ጥያቄ - ግጥም

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

ይህ የሥንኝ ቋጠሮ ከየትኛው ብሔር ነህ ለሚል የቸከ ዘመነኛ ጥያቄ የማያዳግም ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ይሰጣል። የአቋም መግለጫው የተወረሰው ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ጥያቄ ከመለሰለት መልስ ነው። ተጋበዙልን።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
___________
ሰብስክራይብ | Subscribe 👇 Kesatebirhan Ze Tewahdo

🔔
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
#የላሜሕ_ጥያቄ

ከመጻሕፍት ገጾች በሚለው አምዳችን ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ እና ትዕግስት ታፈረ ሞላ በጋራ ጽፈውት ማኅበረ ቅዱሳን በ2010 ዓ.ም ካሳተመው ደንገጡሯ እመቤት እና ሌሎች ልብ ወለዶች እና ግጥሞች ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ #የላሜህ_ጥያቄ የሚለውን ነው።

ንባብ ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
👇👇👇

https://youtu.be/GSU0V__L6vI
https://youtu.be/GSU0V__L6vI

Subscribe
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
🎬 "መድኃኔዓለም ወይስ የግል አዳኝ" ግጥም
👤 ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
🕥 02:41 💾 - 2.5 MB

ለተጨማሪ መንፈሳዊ ግጥሞች
ሰብስክራይብ ያድርጉ
👇👇👇
http://www.youtube.com/watch?v=2T9kWYsC7w0
2025/07/05 06:40:05
Back to Top
HTML Embed Code: