Telegram Web Link
ስለ ተክልዬ ሳስብ

1. ወደ 200 ከሚጠጉ የዝማሬ ሥራዎቼ አንድ የፃድቁ ሥራ አለመገኘቱ

2. ደብረ ሊባኖስን ከረገጥኩ ድፍን 8 ዓመት መሙላቱ እንደ እግር እሳት ያንገበግቡኝ ነበር። አንደኛውን ይኸው ፈጽሚያለሁ። ሁለተኛውን ደግሞ እግዜር ያውቃል።
ስለ ተክልዬ ሳስብ

1. ወደ 200 ከሚጠጉ የዝማሬ ሥራዎቼ አንድ የፃድቁ ሥራ አለመገኘቱ

2. ደብረ ሊባኖስን ከረገጥኩ ድፍን 8 ዓመት መሙላቱ እንደ እግር እሳት ያንገበግቡኝ ነበር። አንደኛውን ይኸው ፈጽሚያለሁ። ሁለተኛውን ደግሞ እግዜር ያውቃል።
https://youtu.be/qQ0VXrDcz-U
ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
#ስለምንታገልለት_ዕውቀት_ይኑረን


ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በKesatebirhan Ze Tewahdo Telegram Channel በLive stream በሰሞናዊ የቤተ ክርስቲያን ትኩሳት መነሻነት መታወቅ ያለባቸውን መሠረታዊ ነጥቦች እንማማራለን።

#የሚነሡ_ጉዳዮች

1. ዶግማ ፣ ቀኖና ፣ ትውፊት ምንድናቸው? ዶግማ ፈረሰ ፣ ቀኖና ተጣሰ ፣ ትውፊት ተፋለሰ ሲባል ምን ማለት ነው። ቅጣቱስ ምንድን ነው?

2. ምሥጢር ክህነት ፣ ምን? ለምን? እንዴት? ፣ ክብረ ክህነት።

3. መፈንቅለ ክህነት በዘመነ ሙሴ ፣ የደብተራ ኦሪት ግርግርና መዘዙ

4. አቤሴሎማዊነትና ዖዝያናዊነት በቤተ ክህነት

5. የጵጵስና ታሪክ በኢትዮጵያ

5. የጳጳሳት ስም ፣ ብፁዕ አቡነ እገሌ መባልና የስም ለውጥ የአስኬማ ፣ የጽሕምና የልብሳቸው ፣ የበትራቸውም ምሥጢርና ውክልና

5. ኦርቶዶክስ በኦሮሞ ታሪክና ፖለቲካ መነጽር

6. የአሁኑን ፈተና እንዴት እንመልከተው? እንዴትስ እንመክተው?


#ሰዓት_ከምሽቱ_3_ሰዓት

#ዕለታት_ቅዳሜና_እሑድ

የስሜት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትም ጦር ዕቃ ለውጊያው ያስፈልገናል።

#ሊንኩን ተጭነው የChannelu Member በመሆን ይጠብቁ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/KesatebirhanZeTewahdo
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Kesatebirhan)
Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
«ተዋሕድዋ» - ኦርቶዶክስ እና አድዋ
+++++++++++++++++++++++++++++++
ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው።
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
ግጥም በእንተ #መጻጉዕ
@Mgetem

የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ
እኔ እኮ ብኩን ነኝ...
አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ
እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው

በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ
ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲ ነኝ መጻጉዕ ውለታ የምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ
ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም
ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ
አምንብህ ነበረ ስትፈውስ እያየሁ
አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መድኅኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም
አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም
እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ
አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ
የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር
መች እክድህ ነበር ልክ እንዲህ ከነበር ::

ዳዊት አየነው
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem
Forwarded from የዲ/ን ከሣቴብርሃን ስራዎች (ㅤㅤㅤㅤㅤ)
🟥 አዲስ ዘለሰኛ ዝማሬ
ዘማሪ ዲ/ን ብርሃኑ ዓለማየሁ
ምነው ሃገሬ ምነው
ግጥም: ዲ/ን ዶ/ር ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
https://youtu.be/WcLkSy_CqiA
https://youtu.be/WcLkSy_CqiA
አዲስ መንፈሳዊ መጽሐፍ

ርእስ፦ "መጽሐፈ መሠረት"
አዘጋጅ፦ ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ(ዶ/ር)
     

ቀድማችሁ ለማዘዝ
👇👇👇
@buchula36
አልያም 👉 @Kebras

ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም በ 0912239783 / 0936290305 ላይ በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኘት እና መጽሐፉን ማዘዝ ይችላሉ።
እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=
2025/06/30 15:56:22
Back to Top
HTML Embed Code: