Telegram Web Link
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Kesatebirhan)
Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
«ተዋሕድዋ» - ኦርቶዶክስ እና አድዋ
+++++++++++++++++++++++++++++++
ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው።
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

 ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤ 
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
ግጥም በእንተ #መጻጉዕ
@Mgetem

የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ
እኔ እኮ ብኩን ነኝ...
አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ
እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው

በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ
ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲ ነኝ መጻጉዕ ውለታ የምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ
ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም
ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ
አምንብህ ነበረ ስትፈውስ እያየሁ
አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መድኅኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም
አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም
እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ
አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ
የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር
መች እክድህ ነበር ልክ እንዲህ ከነበር ::

ዳዊት አየነው
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem
Forwarded from የዲ/ን ከሣቴብርሃን ስራዎች (ㅤㅤㅤㅤㅤ)
🟥 አዲስ ዘለሰኛ ዝማሬ
ዘማሪ ዲ/ን ብርሃኑ ዓለማየሁ
ምነው ሃገሬ ምነው
ግጥም: ዲ/ን ዶ/ር ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
https://youtu.be/WcLkSy_CqiA
https://youtu.be/WcLkSy_CqiA
አዲስ መንፈሳዊ መጽሐፍ

ርእስ፦ "መጽሐፈ መሠረት"
አዘጋጅ፦ ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ(ዶ/ር)
     

ቀድማችሁ ለማዘዝ
👇👇👇
@buchula36
አልያም 👉 @Kebras

ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም በ 0912239783 / 0936290305 ላይ በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኘት እና መጽሐፉን ማዘዝ ይችላሉ።
እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Kesatebirhan)
ተአምረ 27
፨፨፨፨፨

መውለድና መወለድ በአንድ ዕለት!

- እሳቸው 27 ዓመት ባገለገሉበት ቤት፣

-እኔም 27 ዓመቴን በሚይዝበት ዋዜማ ዕለት፣

- በመጋቢት 27 በዓለ ጥንተ ስቅለት፣

- "መጽሐፈ መሠረት" በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በይፋ ገበያ ላይ ይውላል። የቁጥሩ መገጣጠም ወይ ግሩም ያሰኛል። በአንድ ዕለት የበኩር ልጅን ልደትና የራስን ልደት ማክበር ያለውን ስሜት እንዴት ልንገራችሁ? ለማንኛውም በበዓለ ንግሡ ማንጊያው እስከ ማብቂያው ማታ በተሰናዱት የዳስ Stationoch "መጽሐፈ መሠረት"ን ታገኟታላችሁ። ዋጋዋ ሦስት መቶ ብር ነው። ሰማይ በደረሰ የወረቀት ዋጋ ፣ በሌለ ገንዘብ የታተመ ጥቂት ፍሬ ስለሆነ የማለቅ እድሉ ሰፊ ነው። ቶሎ ግዙና የአባታችሁን ዘለዓለማዊ ታሪክ አስቀሩ። የመጽሔቱ ዕጣ እንዳይደርሳችሁ!

በተረፈ መጽሐፉን የምትፈልጉ አዲስ አበቤዎች እኚህን ወዶ ገብ አከፋፋዮች ደውሉና መጽሐፉን አግኙ።

1.አስቻለው አሸናፊ
+251922705082

2.በረከት ጉዲሣ
+251913134524

3.ሳባ ሰሎሞን
+251931527516

4.ሜሮን ገነነ
+251936290305

መልካም ንባብ ለእናንተ! መልካም ልደት ለእኔ!
https://www.instagram.com/p/CqlPK1bI-X8/?igshid=MDJmNzVkMjY=
ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=
2025/07/05 12:45:26
Back to Top
HTML Embed Code: