Telegram Web Link
የቻይና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዪን ሄጁን (Mr. Yin Hejun) ቻይና በሁለቱ ሀገራት ያለውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በጋራ የምርምር ውጥኖች እና አካዳሚክ ትብብር፣ እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የጤና ቀውሶች እና ዘላቂ ልማት ያሉ አሳሳቢ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የጋራ እውቀታችንን ማሰባሰብ እንደመገባ  በምክክሩ ላይ ተነስቷል።

በFOCAC 2024 የመሪዎች ጉባኤ ላይ የታቀዱትን አስር የአጋርነት የድርጊት መርሃ ግብሮችን በተግባር ላይ በማዋል እንደ ንግድ፣ የኢንዱስትሪ ሰንሰለት ትብብር፣ አረንጓዴ ልማት እና የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ፣ ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ከሳይበር ደህንነት እና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተያያዙ ጥረቶችን ለማራመድ በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
👍1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!
#መልካም-በዓል!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
5👍1
የዓለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች ጥምረት (Alliance of International Science Organization ) እና የአፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል  በትብብር ለመስራት የሚያስችለው ጉባኤ አካሄዱ።
=====================
የዓለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች ጥምረት (Alliance of International Science Organization ) እና አፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ጉባዬ በአዲስ አበባ አካሂደዋል፡፡

ጉባኤው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉር ያለውን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ለማጉላት እና ሃብ በአለም አቀፍ ትብብር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የሀብት ልውውጥና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አቅሞችን በህብረቱ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ነው።

የጉባኤውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፈሰር ካሳሁን ተስፋዬ ትብብሩ በኢትዮጵያና ብሎም በአፍሪካ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽንን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
በተለያዩ ሀገራት የሳይንስ ማህበረሰቦች መካከል ውህደትንና ትብብርን ለመፍጠር መድረኮች ወሳኝ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የዓለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች ጥምረት(ANSO) እና የአፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በሚያደርጋቸው ትብብር በዓለም አቀፍ  ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻልበትን እድል መፈጠር እንዳለበት ገልፀዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ አፍሪካን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ለማጎልበት የአፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል ትብብር  ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በአፍሪካ እና በቻይና ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት አፍሪካ ለዘላቂ ልማት እና ለአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የምታደርገውን አስተዋፅኦ ያፋጥናል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው ኢትዮጵያ ሀገራዊ የምርምር እና የፈጠራ ስርአቶችን ከአለም አቀፍ እና ክልላዊ የልማት ማዕቀፎች ጋር ለማጣጣም ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የዚምባቡዌ የኢንጂነሪኒግ ድርጅት፣ የኬንያ አፍሪካ አካዳሚ፣  የናይጄሪያ የምርምር ተቋም፣ የአለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች አሊያንስ (ANSO)፣ የቻይና ሳይንስ አካዳሚ፣ እና ሌሎች ከአጋር ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮችን ተሳትፈውበታል።
5
2025/10/25 18:24:36
Back to Top
HTML Embed Code: