Telegram Web Link
የቻይና ህዝብ ሪፐብሊክ የኢንዱስትሪ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሚስተር ሊ ሌቼንግ (Mr. Li Lecheng) ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን አጋርነት ይበልጥ በማጠናከር ለሁለትዮሽ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያላትን ቁርጠኝነት ትልቅ አላማ ያለው አጀንዳ አድርጋ እንደ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የኢ-መንግስት አገልግሎቶች፣ የዲጂታል ክህሎት ግንባታ እና የኢኖቬሽን ማዕከላት ምስረታ እና ሌሎችን የመሳሰሉ አስደናቂ ጉዞዎችን አድርጋለች።

በዝግጅቱ ላይ ኢትዮጵያና ቻይና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የቻይና ህዝብ ሪፐብሊክ የኢንዱስትሪ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሚስተር ሊ ሌቼንግ ፈርመውታል።
👍32
የቻይና አፍሪካ ኢኖቬሽን ትብብር እና ልማት ጉባኤ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት ተካሄደ።
====================
“የቻይና አፍሪካ ኢኖቬሽን ትብብር ቀንን” አስመልክቶ የቻይና መንግስት የቻይና አፍሪካ ኢኖቬሽን ትብብር እና ልማት ጉባኤ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በአንድነትና በጋራ ዓላማ የአፍሪካ መግቢያ እንደሆነች እና ለቀሪው አፍሪካ አብነት ከሚሆነው ከቻይና ጋር ያለው የትብብር አሪያነት አጠናክራ ታስቀጥላለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላት አጋርነት ለደቡብ-ደቡብ ትብብር ፅናት ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጄክቶች እስከ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ እድገቶች ድረስ በትብብራችን ሰፋ ያሉ ስኬቶችን መመዝገባቸውን አንስተዋል።

በአገራችን ውስጥ ዛፎችን በመትከል ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ርምጃ ትልቅ አስተዋጽኦ ላለው ታላቁ ፕሮጄክታችን ለአረንጓዴው ሌጋሲ ኢኒሼቲቭ ቻይና የምታደርገውን የማያቋርጥ ድጋፍ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ እንደምታደንቅም ገልፀዋል።

የቻይና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚስተር ዪን ሄጁን (Mr. Yin Hejun) ቻይና ከአፍሪካ ጋር የምታደርገውን ትብብር በማጠናከር የቻይናንና የአፍሪካን የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደምትሰራ አስገንዝበዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት ጋር ባደረገቻቸው ዘርፈ ብዙ ትብብሮች የተመዘገቡ ውጤቶች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት መሰረት የጣሉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ባለችበት ወቅት የቻይናን አጋርነት አብዝታ እንደምትሻም ገልፀዋል፡፡

በጉባዬው ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፈዎች የተገኙ ሲሆን ከጉባዬው ባሻገር የቻይና መንግስት በአፍሪካ ሀገራት የሰሯቸውን ፕሮጀክቶች ዓውደ ርዕይ ለተሳታፊዎች አስጎብኝተዋል፡፡
3
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ።
====================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ የሁለትዮሽን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ  ለመስራት መክረዋል።

ምክሩን ያካሂዱት የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያና ቻይና የጋራ ስትራቴጂካዊ አላማዎቻችንን ከግብ ለማድረስ እና የኢትዮጵያና የቻይና ቤተሰብ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን ከፈለግን እንዲህ ያለው ከፍተኛ ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራትም የሚጠቅሙ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማበረታታት ከቻይና ጋር ተቀራርበን ለመሥራት ቁርጠኞች ነን ብለዋል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ እና ፈጠራ የFOCAC አጀንዳ አፈፃፀም ውስጥ ዋና ምሳሌ መሆን እንፈልጋለን ያሉት ሚኒስትሩ የበለፀገ እና በዲጂታል የነቃ ማህበረሰብን ለማራመድ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ላይ  መሆኑን ጠቅሰዋል።
2
2025/10/22 11:34:21
Back to Top
HTML Embed Code: