Telegram Web Link
ከኢትዮጵያ ጀርባ ላይ ያልወረደው የሁለንተናዊ እድገት መሰናክልና እንቅፋት የሆነው የባዕድ ጣልቃ ገብነት አባዜን ለማስወገድ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የብሔራዊ ጥቅም ምንነት እና ጂኦስትራቴጂክ ቁመና፣ የኢኮኖሚ ብልፅግና፣ ፖለቲካዊ አቅምና ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን፣ የባህር በር ጉዳይ፣ ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ፣ ከፖለቲካ ሀይሎች ጋር ሰላማዊ አማራጭ መከተል፣ የባህል ነፃነት፣ የህዝቦች ማህበራዊ ልማትና ዋስትና የሚሉ ሀሳቦች ተዳሰዋል።
የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ግንዛቤ ለተቋም ዓላማ ስኬት መረጋገጥ ሚናው የላቀ እንደሆነ ተገለፀ።
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር ለመካከለኛ አመራሮች የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር የኦዲት ስራ አስፈፃሚ አቶ አሻግሬ አለሙ የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ላይ የጠራ ግንዛቤ መፍጠር ለተቋማዊ ውጤታማነት ያለውን ሚና አስረድተዋል።

ተቋማት ሳያውቁ ከሚሰሯቸው የኦዲት ግኝቶች ለመታደግ በዘርፉ ላይ ያሉ መመሪያና ደንቦች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ለሁለም የሚበጅ መሆኑን ገልፀዋል።

ኦዲት የሀገራዊ ኢኮኖሚ ውጤታማነትን የሚጨምር ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚው ተቋማት በዘርፉ ላይ የግንዛቤ አቅምን በመፍጠር የሀገራዊ ብሎም የተቋሙን የአሰራር ስርዓት በማሳለጥ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ምቹ ስነምህዳር ይፈጥራል ብለዋል።

የኦዲት ስራ ጫናን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለው የዲጂታል አገልግሎት ከሚያመጣው ታምራዊ ለውጥ ባሻገር የኦዲት ህግና ደንብ ዙሪያ የተቋም የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በቀጣይ የፋይናሻል ኦዲት የማይሸፍናቸውን ስራዎች በግብ ተኮር የሆነው የክዋኔ ኦዲትን ተግባራዊ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

በመድረኩ ሁሉም ሰራተኛ የመንግስትን ያሰራር ስርዓቶችን ጠንቅቆ በማወቅ የተመደበበትን ስራ በውጤታማነት ለማከናወን የሚያግዘውን የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ዕውቀት የሚያገኝበትን ዕድል በየጊዜው መፈጠር እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል።
👍52
የብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የፖሊሲ ግንዛቤ መፈጠር ለተግባራዊነቱ መረጋገጥ መሰረት መሆኑ ተገለፀ፡፡
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአሶሳ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ስራ አስፈፃሚዎች፣ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች የብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል፡፡

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሰን ሀሰን ተሻሽሎ የፀደቀውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች ግንዛቤ ማሳደግ እና ብቁ የሰው ሀይል መፍጠር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ምርምር እና ፈጠራ ስራዎችን ለማሳደግ፣ ከግል ዘርፉ ጋር በጋራ ለመስራት እና የሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለማልማት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ሀገራችን በቴክኖሎጂና ፈጠራ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ም/ፕሬዝዳንቱ የፖሊሲውን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ በዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሚሰሩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት የአካባቢውን ማህበረሰብ እና የሀገር ልማትን ማሳደግ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፓሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር በኩረፅዮን አለማየሁ በ2014 ዓ.ም የተከለሰውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ሀገራዊ ግንዛቤን ለማስፋትና አላማውን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፓሊሲና ስትራቴጂ፣ ጥናትና ምርምር አናሊስት ዶ/ር አበበ ሞላ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ተዋናይ የሆኑ ዩኒቨርስቲዎችና ሌሎች አካላት በፖሊሲው ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ ትግበራውን ማሳለጥ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

የብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ደንብና መመሪያዎችን ተገንዝቦ ወደ ውጤት ለመቀየርና የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የግንዛቤ ማስጨበጫው መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡
2025/10/27 14:16:22
Back to Top
HTML Embed Code: