Telegram Web Link
"የነገ ቀንን" ምክንያት በማድረግ የሀካቶን ውድድር እየተካሄደ ነው፡፡
===================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮቴሌኮም ጋር በመተባበር በአይሲቲ ፖርክ በሚገኘው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ኢኖቢዝ-ኪ ኢንኩቤሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በውድድሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የነገ ቀናችን ላይ ያደገችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት የሚያስችለን የሁሉም ኢትዮጵያ አሻራ የሆነው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ እንኳ ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት ግስጋሴ አጠናክራ ትቀጥላለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን ፅኑ መሰረት እንዲኖራት በሀገራዊ ስታርታፕ ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በማጎልበት አዳዲ ሀሳብና ፈጠራዎችን በማመንጨት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚ ስነምህዳር ማሳለጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ውድድሩ የሀገራችን የማህበረሰብ ችግር የሚፈቱ ትውልድን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና መጨውን የውድድር አለም ለመገዳደር የሚያስችል ስርዓት በመፍጠር የኢትዮጵያ ስኬት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለውድድሩ አሸናሪዎች ትልቅ አቅምና ማበረታቻ የሚሆን ሽልማት የተዘጋጀ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡
5👍1
የነገ ቀን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የምትዘምንበትን  መጪውን ጊዜ የምናሳይበት ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ
===================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በኢኖቬሽንና በዲጂታል ዘርፍ ያዘጋጁትን  ኤግዚብሽንና የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም እየተካሄደ ነው።

ኹነቱን የከፈቱት የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ የታላቁን የህዳሴ ግድብ ባስመረቀችበትና ድልን በተጎናፀፈችበት ማግስት ላይ ሆነን የነገን ቀን ስናከብር ታላቅ ኩራትና የወደፊት ጉዞ ስኬትን እንድናነግብ ያስችለናል ብለዋል።

የህዳሴ ግድባቸን ቤታችንን እና ኢንዱስትሪዎችቻችንን እንድሚያበራልን ሁሉ፤ ቴክኖሎጂም ፣ ኢኖቬሽንን የሚያለመልም፣ ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ሞተር የሚሆን እና ዜጎቻችንን  ከዚህ በፊት ሊታስቡ ከማይችሉ አዳዲስ  እድሎች ጋር የሚያስተሳስርልን እና የመጪ ግዜ መንገዳችንን ብሩህ የሚያደርግልን መሆኑን ተናግረዋል።

ነገዋን የምትጠብቅ ሳይሆን ነገዋን  በራሷ የምትፈጥር ኢትዮጵያን እንገንባ ያሉት ሚኒስትሩ የአዲስ አመት ዋዜማ ተስፋችንን የምናድስበት እና ለነገ  ብሩህ ተስፋችን ቃል የምንገባበት ቀን መሆኑን ገልፀዋል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አርትፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ኢኖቬሽን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ አይበገሬነትን ለማጽናት እና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እንዴት እንጠቀማቸው?የሚል ሀሳብ አንስተዋል።
1
ህዳሴ ኮንክሪት እና ተርባይን ብቻ አይደለም! ህዳሴ የአንድነታችን ምልክት፣ የአይበገሬነት ማረጋገጫ፣ እና የወደፊት እጣ ፈንታችንም በእራሳችን እንደምንወስን ማሳያችን ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ ከእንግዲህ ሲወራ የህልውናን የማረጋገጥ  ብቻ ሳይሆን የመቻል እና ለሌላውም  የመትረፍ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ እና ሌሎችንም ማሰገንዝብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
👍32💯1
2025/10/27 13:40:58
Back to Top
HTML Embed Code: