ኢትዮጵያ ኒዉክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋል ለምታደርገው ጥረት የአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ድጋፉን እንዲያጠናከር ጥሪ ቀረበ
==============
ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኦስትርያ ቬና እየተካሄደ በሚገኘዉ 69ኛው የIAEA ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በጉባኤው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ የኒዉክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አላማ ማለትም ለሀይል አቅርቦት፣ ለምርምር፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለአካባቢ ጥበቃ መጠቀም ያስችላት ዘንድ እ.አ.አ ከ1957 ጀምሮ የአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) አባል መሆኗ ይታወቃል።
ለዚሀ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አገናኝ ጽ/ቤት (Liasson Office) በመሆን የተለያዩ ብሄራዊ እና አህጉራዊ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የቴክኒክ ትብብር (Technical cooperation) በማድረግ በተለይም አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት በመስጠት ከኤጀንሲዉ ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።
ሀገራችን በዘርፉ በምታደርገው ጥረት IAEA ኒዉክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጁን በተመለከተ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና በሰዉ ሃብት ልማት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን ትብብሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
በጉባኤዉም ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኒኩለር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም የሚገልጽ ንግግር አድርገዋል።

❤1👍1
ክቡር ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ አገራዊ እድገት ያግዛት ዘንድ የኒዉክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አላማ ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህዳሴ ግድብን መርቀዉ በከፈቱበት ወቅት ይፋ ካደረጓቸዉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መካከል የኒዉክሌር ኃይል ልማትና ለሰላማዊ አላማ ማዋል መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም አስፈላጊ በሆነዉ መንገድ ሁሉ ኤጄንሲዉ እንዲያግዝ ሚኒስትሩ በንግግራችው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵየያ Rays of Hope የተሰኘዉን ፎረም ከጁን 30 እስከ ጁላይ 2/2025 በአዲስ አበባ በተሳካ ሁኔታ ባዘጋጅችበት ወቅት የIAEA ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ራፋይል ማርያኖ ግሮሲ (DG Rafael Mariano Grossi) ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በአካል ተገናኝተው መወያየታቸው እና በወቅቱም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን መጎብኘታቸው ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንስተዋል።
ይህንንም ተከትሎ በቅርቡ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በተደረገ ተጨማሪ የስልክ ልዉዉጥ ለሆስፒታሉ የካንሰር ህክምና የሚዉለዉን የLinear Accelerator (LINAC) ማሽን ለመለገስ ተቋማቸው ውሳኔ ላይ መድረሱን የገለጹ ሲሆን ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

❤2🔥2
ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
===============
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከመስከረም 15 እስከ 19 በቪየና ኦስትሪያ እየተካሄደ ካለው 69ኛው የ IAEA መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ራፋኤል ማርያኖ ግሮሲ ጋር በዛሬው እለት የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ ኢትዮጵያ በምታካሂደው የሰላማዊ ኒዉክሌር ሃይል ፕሮግራም፣ በሰው ሃይል አቅም ግንባታ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ በሚያደርጋቸው ድጋፎች ዙርያ ያተኮረ ነው።
በውይይቱ ወቅት ክቡር ሚኒስትሩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ለአገራችን የካንሰር ማከሚያ መሳሪያ (Linear Accelerator, LINAC) ድጋፍ ማድረጋቸውን አመስግነው፤ በቀጣይም በተለይ የሰው ሃይል አቅም ግንባታ ላይ ኤጀንሲው የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የሰላማዊ ኒዉክሌር ኢነርጂ ፕሮግራሞችን እውን ለማድረግ መሠረት በመጣል ላይ መሆኗን እና ወደትግበራ ለመግባትም ሰፊ ጥረት እያደረገች መሆኗን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ሀገራችን በምትጀምረው ብሄራዊ የኒውክለር ሃይል ግንባታ ላይ የቴክኒክ ድጋፍ እና የእውቀት ሽግግር ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ኤጀንስው በዚህ ረገድ ያላሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በዋና ዳይሬክተሩ የተጀመሩ ኢኒሼቲቮችን አድንቀው በተለይም በግብርናው እና በጤናው ሴክተር በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ ከኤጀንሲው ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚፈልጉም አያይዘው ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አላማ ለመጠቀም የጀመረችውን የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣች መሆኗንም የገለጹት ሚኒስትሩ ይህንንም በይበልጥ ለማጠናከር የኤጀንሲው ድጋፍ በዚህም ዙሪያ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ ዋና ዳይሬክተርም በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በቅርቡ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አንስተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም የጀመረችውን እንቅስቃሴ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንስ እንደሚደግፍም አረጋግጠዋል።

👍5❤2🔥1🐳1
ኢትዮጵያ በ36ኛዉ የAFRA የአባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ተሳተፈች።
*
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላማዊ ዓላማዎች የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ በ36ኛው የAFRA አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ በንቃት ተሳትፋለች።
የAFRA (African Regional Cooperative Agreement for Research, Development and Training Related to Nuclear Science and Technology) አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ከ69ኛዉ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ (IAEA) ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ጎን ለጎን ተካሄዷል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያን በመወከል ከሴፕቴምበር 2024 ጀምሮ ለአንድ አመት የAFRA ሰብሳቢ ሆነዉ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በትናንትናዉ እለትም ኢትዮጵያ የAFRA ሰብሳቢነቷን የ IAEA ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ራፋይል ማሪያኖ ግሮሲ በተገኙበት ለቦትስዋና በይፋ አስረክባለች፡፡
ኢትዮጵያ በዶ/ር በለጠ ሞላ የአንድ አመት አመራር በአፍሪካ የኒውክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም የአቅም ግንባታ፣ የምርምር ትብብር እና ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ማጠናከሯ በመድረኩ ተገልጿል።

❤1
ክቡር ሚኒስተሩ በተለይም የAFRA Steering Committee በማቋቋም የአቅም ግንባታ እና የሰው ሃይል ልማት ስራን ማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ በመስጠት መስራታቸው በአባል ሃገራቱ ያለን የሰው ሃይል አቅም መገንባት መቻሉንና በቀጣይም የሚጠናከርበት አሰራር እንዲቀጥል ማስቻሉ ተነስቷል።
በቪየና ላይ የተመሰረተ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን ((Vienna based African Ambassadors Group - VbAG) ጋር በቅርበት በመቀናጀት የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ አህጉር የሚያበረክቱትን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ለመጠቀም አባል ሀገራት በትብብር እና በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው፣ ህብረቱንም ይበልጥ ለማጠናከር አባል ሀገራቱ መዋጯቸውን በጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲፈጽሙ በማድረግ ረገድም ክቡር ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተው በመግልጽ ትብብሩ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም በአህጉሪቱ የሚገኙ ሪሰርች ሪያክተር ባለቤት አገራት በቴክኒክ ትብብር አብሮ መስራት የሚያስችል ቻርተር እንዲፈራረሙ በማድረግ በምርምር ዘርፍ አባል ሃገራቱ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የሚኖረውን ፋይዳ በመገንዘብ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት የሚያስችል ግንዛቤን ፈጥረዋል፡፡
ለAFRAን አባል ሃገራት የሚያስፈልግ የዲፕሎማሲ ስራን ከመተግበርና ከመፍጠር አንጻር ዶ/ር በለጠ ኢትዮጵያ AFRAን በሰብሳቢነት ስትመራ ቡድኑን በፋይናንስ እና በቴክኒክ ከሚደግፉ ሀገራት እና ተቋማቶች ጋር በመወያየት ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራን አከናዉነዋል፡፡
ከሴፕቴምበር 2024 ጀምሮ ኢትዮጵያን በመወከል ለአንድ አመት AFRAን በሰብሳቢነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር በለጠ ሀላፊነታቸዉን ለቀጣይዋ መሪ ሀገር ቦትስዋናዉ የኮሙኒኬሽን እና የኢኖቬሽን ሚኒስትር ክቡር ዴቪድ ሸሬ (Dr. David Tsere) በይፋ አስረክበዋል፡፡

❤4