Telegram Web Link
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመታዊ የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡
====================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት በየዓመቱ የሚያካሂዱትን የደም ልገሳ መርሃ ግብር “ሕይወት የሆነውን ደም በመስጠት ሕይወት ያድኑ! ” በሚል መሪ ቃል አካሂደዋል፡፡

በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
5👍1😁1
የሀገር በቀል እውቀት፣ ቴክኖሎጂና ምርምር ፖርታል እየለማ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
====================
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እየለማ ባለው ፖርታል ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት የማሰባሰብ መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ በውስጥ አቅም የለማውን የሀገር በቀል እውቀት፣ ቴክኖሎጂና ምርምር ፖርታል ይበልጥ ለማጎልበት ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተክለማርያም ተሰማ ኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መረጃዎችን ለአለም አቀፍ ግብዓት በሚሆን መልኩ በማደራጀት ፖርታል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የአንድ ሀገር ዳታ ለሁለንተናዊ አለም አቀፍ ጠቀሜታ ፋይዳው የላቀ ነው ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው ሀገራችን በሁሉም ዘርፍ በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዳታ ቤዝ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ፖርታሉ ኢትዮጵያ ያላትን የሀገር በቀል እውቀት ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ ተጠሪ ተቋማትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ሲሆን በቀጣይ የሚጠናቀቅበትን እድል በመፍጠር ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
4😁1
መሶብ በመንግስት አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ሰው ተኮር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። አቶ ሙሉቀን ቀሬ
==========

የወላይታ ሶዶ  መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመሮቆ ስራ ጀምሯል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ  አቶ ሙሉቀን ቀሬ  መሶብ በመንግስት አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ሰው ተኮር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ኢንሼቲቭ መሆኑን ገልጸዋል።

የመሶብ ሀሳብ በመደመር እሳቤ የተመራ ነው ያሉት ሚኒስቴር ድኤታው የመንግስት አገልግሎቶችን ለተገልጋዮች በክብርና በቅልጥፍና የሚያቀርብ መሆኑን አመላክተዋል።

ከዚህ ቀደም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከመንግስት ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅ የገለጹት ሚኒስትር ድኤታው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለህዝቡ ቅሬታ ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ባሻገር በህዝብና መንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግልም ጠቅሰዋል።

በፌደራል ደረጃ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ወደ ክሎች የማስፋቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ሙሉቀን በማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ባለጉዳዮችን በኢትዮጵያዊነት ክብር ሊያገለግሉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የወላይታ ሶዶ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲጀምር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ላሳዩት ቆራጥ አመራር ሚኒስትር ድኤታው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
3
2025/10/25 01:37:31
Back to Top
HTML Embed Code: