Telegram Web Link
በሁሉም ሴክተሮች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የስነ ምግባር መርሆዎችን የተከተሉ መሆን አለባቸዉ ተባለ
=====================================
(ነሃሴ 28/2013) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከጅማ ዪኒቨርስቲና ከአውሮፓና ታዳጊ ሃገራት የክሊኒካል ሙከራዎች ትብብር (EDCTP) ጋር በመተባበር የምርምር ስነምግባር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናዉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ በሃገራችን በርካታ ጸጋዎች አሉ እነዚህም በጥናትና ምርምር ከታገዙ ከኢትዮጲያ አልፈዉ፣ አፍሪካን መቀየር የሚችሉ ናቸዉ ብለዋል፡፡ ስለዚህ በምናደርገዉ ማንኛዉም ጥናትና ምርምር የስነ ምግባር መርሆዎችን በመከተል የሃገራችን ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡
ወደ ማህበረሰባችን በመቅረብ የምርምር ስነ ምግባር በጠበቀ ሁኔታ በማጥናት ማሳወቅና ማሳተም ያስፈልጋል ያሉት ፕ/ር አፈወርቅ በመሆኑም የምርምር ተቋማት ጥናትና ምርምር ስንፈቅድ በምን መርህ ላይ ነዉ መሰረት አድርገን የምንሰራዉ የሚለዉን ትኩረት ማድረግና ለሃገር በቀል እዉቀት ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፕ/ር አፈወርቅ አክለዉም አሁን እየሰራን ያለነዉ 5ኛዉ እትም አገራዊ መመሪያ ሲሆን በአዲስ 6ኛዉ እትም እየተዘጋጀ ሲሆን በጥናትና ምርምር ሰራ ከግንዛቤ ዉስጥ የሚገቡትን የአካተተ ሆኖ እየተዘጋጀ ነዉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ሳይንስና ኢትዮጵያ አብረዉ የኖሩ ቢሆኑም በምርምርና ቴክኖሎጂ ደግፎ ከመጠቀም አንጻር ሰፊ ክፍተት አለ ስለዚህ ምሁራን በትኩረት ሊሰሩ ይገባል፡፡ ምርምር ለልማት፣ ለሃብት እና ለሃገር ግንባታ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ፕ/ር አፈወርቅ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸዉ የምንሰራቸዉ የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባርን መርህ ተከትሎ መስራት ወሳኝ ነዉ፡፡ የምርምሮች ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርህ ተከትለዉ በትክክለኛ መንገድ የማንሰራ ከሆነ ከግለሰብ ጀምሮ ሃገር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ይህንን ለመከላከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ህጎችና ሪፎርሞች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የጂማ ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ስልጠናዉ የሰልጣኞችን አቅም በመገንባት፣ በተለይም የምርምር ስነምግባር የተያያዙ ችግሮ ች አሉ በመፍታት በኩል በርካታ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ጅማ ፣ ቦንጋ ፣ ሚዛን ቲፒ ፣ ጋምቤላ ፣ አሶሳ ፣ ወልቂጤ ፣ ደንቢ ዶሎ ወለጋ እና መቱ ዩኒቨርስቲዎች፣ የጋምቤላ፣ የቤኔሻንጉል እና የኦሮሚያ የግብርናና ጤና ምርምር ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ ከየካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲውት(EPHI)፣ አርመን ወሃንሰን ምርምር ኢንስቲቲውት ፣(AHRI) እና ኢትዮጲያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን (EFDA )የምርምር አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
2025/07/14 21:55:47
Back to Top
HTML Embed Code: