የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን(HRART)አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ተላለፈ
*************************************************************
(ነሃሴ 27 /2013ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በየአመቱ እንዲያዘጋጅ የመግባቢያ ስምምነት ነሃሴ 26/2013 ዓም ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጽጌ ገ/ማሪያም ናቸው።
በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በቀጣይ 10 አመት በአግባቡ ለመምራትና ለመስራት ከታቀዱ ግቦች መካከል ትምህርትና ስልጠና እና ሳይንስ ይገኝበታል፡፡ ዘርፉንም ዉጤታማ ለማድረግ 2021 የተዘጋጀዉ የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽንና የሳይንስ ሽልማት አንዱ ነዉ ብለዋል፡፡
በመሆኑም ወደ “እዉቀት መር ኢኮኖሚ “ በሚል የተጀመረዉን ይህንን ትልቅ ስራ ለማስቀጠልና ለማሳካት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አብረዉ መስራት ስለሚገባ ይህ ስምምነት ተደርጓል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለሚቀጥሉት ተከታታይ አመታት የሳይንስ አካዳሚዉ በባለቤትነትና በነጻነት እንዲመራዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ደግሞ እንዲያስተባብር ስራዉ ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገ/ማርያም በበኩላቸው አካዳሚው እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአንድ አላማ ተቀራርበዉ መስራት አለባቸዉ ያሉ ሲሆን የተሰጠዉን ሃላፊነት ለማሳካት እንደሚሰሩ ገልጸዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን እድል ሰለፈጠረ አመስግነዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጽጌ ገ/ማርያም ምሁራንም መስፈርቱን የሚያሟሉ የአካዳሚዉ አባል በመሆን አብረዉን መስራት እንዲችሉ የማያሟሉም ለአባልነቱ የሚያበቁ አካዳሚያዊ ዉጤቶችን በማስመዝገብ እንዲሰሩ ጠይቀዋል ፡፡
የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን (HEART Convention 2021) “ወደ እውቀት-መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 5 እስከ 8 /2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነዉ፡፡

የፓርላማ የሰዉ ሃይል እና ቴክኖሎጂ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ሽኚት ተደረገላቸው
ለሁለት ቀናት ሲድካሄድ የነበረዉ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቃት ምዘና አክሪዲቴሽን ስትራቴጂ ዝግጅት ጉባኤም ተጓዳኝ መርሃግብሮችን አስተናግዶ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።
********************************************************
(ነሃሴ 26 /2013ዓ.ም) የፓርላማ የሰዉ ሃይል እና ቴክኖሎጂ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተመሰገኑ ላለፉት አመታት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍና ክትትል በማድረግ፣ የከፍተኛ ትምህርት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን ለማስወገድ፣ ፖሊሲና ስትራቴጅጂዎች በማጽደቅ፣ ስራ ላይ እንዲዉሉ በማገዝ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያትም ጭምር በመደገፍ ጠንካራ ተቋም እንዲገነባና የመማር ማስተማር ስራዉ በስኬት እንዲቀጥል ላደረጉት አስተዋጽኦ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ሚኒስቴር ዴኤታዎች ምስጋና እና እዉቅና ተሰጥቶቸዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረዉ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቃት ምዘና አክሪዲቴሽን ስትራቴጂ ዝግጅት ጉባኤ በተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ዉይይት በማድረግና ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ እንዲሁም የተለያ የጎንዮሽ መርሃግብሮችን በማስተናገድ ተጠናቋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ልማት ፎረም ጉባኤ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው
====================================
(ነሐሴ 27፣ 2013) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ልማት ፎረም ጉባኤ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በዩኒቨርሲቲዎች የሀብት ብክነትን ለማስቀረት የዲጂታል መሠረተ ልማቶች የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። በመሆኑም አመራሩን በዘርፉ ብቁ በማድረግ ወደ ዲጂታል ትራስፎርሜሽን ለመሸጋገር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸዉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአስተዳደር፤ በቢዝነስ ልማት የሚከናወኑ ተግባራት ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን በመጠቀም አሰራርን ለማዘመን፤የተቀላጠፈ እና ፈጣን አገልግሎትን ለመስጠት ቅንጅታዊ አሰራርን መተግበር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዉ አክለዉም መድረኩ በየተቋማቱ የአመራር፤ የአደረጃጀት እና የአሰራር ክፍተቶችን በመፈተሸ የአመራሩን አቅም መገንባት የሚቻልበት እና በተቋማት ሃብት ማመንጨት ብቻ ሳይሆን ያለውን ውስን የሃገር ሃብት እንዲሁም የሰው ሃይል በአግባቡ ወጭ ቆጣቢ በሆነ እና ጥራት ባለው መልኩ በውጤታማነት መጠቀም የምንችልበትን ግብዓት የምናገኝበት ነው ብለዋል፡፡
ተቋማት በተሰጣቸው የልየታ መስክ መሰረት ተልእኳቸውን በአግባቡ ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ፍላጎታቸውን፤ አሰራራቸውን እና የሰው ኃይል አደረጃጀታቸውን በውጤታማት መምራት የሚችሉበትን ምች ሁኔታ እንደሚፈጥርም አክለዋል፡፡
የተቋማትን ነፃነት ለማረጋገጥ የአሰራር ስርዓት የምንዘረጋበት ወቅት ላይ በመሆኑ መድረኩ በዝህ ረገድም ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡
መድረኩ የድሬዳዋን ዩኒቨርስቲ የስራ እንቅስቃሴ እና በሌሎች ተቋማት ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎች ለመቀመር እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግም ያለውን ፋይዳ አክለዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባ አደም ለተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሃገርን ለመበተን እና የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ በየአቅጣጫው የሚንቀሳቀሰውን አፍራሽ ኃይል መስዋእትነት እየከፈለ እና አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ላለው የመከላከያ ሰራዊታችን፤ የክልል ልዩ ኃይሎች እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ተሳታፊዎች ለ1 ደቂቃ ቁመው እንዲያጨበጭቡ በማድረግ የምስጋና፤ የሙገሳ እና የሞራል ድጋፍ እንዲሰጥ አድረገዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ መንግስት በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በነገዉ እለት በሚኖረዉ ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲው 195 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ በግቢው ያሰራቸዉ የኢንተርኔት ማስፋፊያና የዳታ ማዕከል ግንባታዎች እንደሚመረቁም ተናግረዋል፡፡
የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ዉሎ ፥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በመረጃ ደህንነትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ከመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ፣ከረዳት የላቦራቶሪ ቴክኒሺያኖች የስራ ልኬት እና ክፍያ፣ ከተማሪዎች ምገባ እና ሌሎች ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ማነቆዎች ዙሪያ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተጠቅሰዉ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ቀጣይ ስራ አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡
የዕለቱ ፕሮግራም በአንድነት ፓርክ የችግኝ ተከላ በማካሄድ የተጠናቀቀ ሲሆን ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምን ጭምሮ የመርሀግብሩ ታዳሚዎች ችግኝ በመትክል በከተማዋ አሻራቸዉን አኑረዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴር፤ የፌደራል ግዥ እና ንብረት አስተዳደር፤ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎችን ፣ ከ41 ዩኒቨርስቲዎች የአስተዳደር ፤ የቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዘዳንቶች፤ የ ICT ፤ የግዥ፤ የፋይናንስ፤ የሰው ሃብት አስተዳደር፤ የፕሮጀክት ግንባታ፤ የኦዲት ዳይሬክተሮችን እና ሌሎች ከ320 በላይ የስራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በነገዉ ዕለት ዉሎዉ በ2013 ዓም በዩኒቨርስቲዉ የተለያዩ ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች አዉደ ርእይን ጨምሮ ሌሎች የጎንዮሽ መርኃ ግብሮችም እንደሚከናወኑ ፕሮግራሙ ያመላክታል ።