ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን 3237 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
===================================
(ነሃሴ 29/2013ዓም)ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን 3237 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው በስምንት ኮሌጆች ስር በሚገኙ 45 ትምህርት ክፎሎቸ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆኑ ከተመራቂዎቹ መካከል 2,098 ወንድ እና 991 ሴት በድምሩ 3,089 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም የቀሩት 122 ወንድ እና 26 ሴት በድምሩ 148ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ የወራቤ፣ የመቱ እና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝደንቶች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ከምረቃ ፕሮግራሙ በኋላም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት ከተመራቂ ተማሪዎች ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ ማከናወናቸውን ከዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት አድርሶናል።