Telegram Web Link
በሁሉም ሴክተሮች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የስነ ምግባር መርሆዎችን የተከተሉ መሆን አለባቸዉ ተባለ
=====================================
(ነሃሴ 28/2013) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከጅማ ዪኒቨርስቲና ከአውሮፓና ታዳጊ ሃገራት የክሊኒካል ሙከራዎች ትብብር (EDCTP) ጋር በመተባበር የምርምር ስነምግባር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናዉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ በሃገራችን በርካታ ጸጋዎች አሉ እነዚህም በጥናትና ምርምር ከታገዙ ከኢትዮጲያ አልፈዉ፣ አፍሪካን መቀየር የሚችሉ ናቸዉ ብለዋል፡፡ ስለዚህ በምናደርገዉ ማንኛዉም ጥናትና ምርምር የስነ ምግባር መርሆዎችን በመከተል የሃገራችን ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡
ወደ ማህበረሰባችን በመቅረብ የምርምር ስነ ምግባር በጠበቀ ሁኔታ በማጥናት ማሳወቅና ማሳተም ያስፈልጋል ያሉት ፕ/ር አፈወርቅ በመሆኑም የምርምር ተቋማት ጥናትና ምርምር ስንፈቅድ በምን መርህ ላይ ነዉ መሰረት አድርገን የምንሰራዉ የሚለዉን ትኩረት ማድረግና ለሃገር በቀል እዉቀት ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፕ/ር አፈወርቅ አክለዉም አሁን እየሰራን ያለነዉ 5ኛዉ እትም አገራዊ መመሪያ ሲሆን በአዲስ 6ኛዉ እትም እየተዘጋጀ ሲሆን በጥናትና ምርምር ሰራ ከግንዛቤ ዉስጥ የሚገቡትን የአካተተ ሆኖ እየተዘጋጀ ነዉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ሳይንስና ኢትዮጵያ አብረዉ የኖሩ ቢሆኑም በምርምርና ቴክኖሎጂ ደግፎ ከመጠቀም አንጻር ሰፊ ክፍተት አለ ስለዚህ ምሁራን በትኩረት ሊሰሩ ይገባል፡፡ ምርምር ለልማት፣ ለሃብት እና ለሃገር ግንባታ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ፕ/ር አፈወርቅ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸዉ የምንሰራቸዉ የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባርን መርህ ተከትሎ መስራት ወሳኝ ነዉ፡፡ የምርምሮች ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርህ ተከትለዉ በትክክለኛ መንገድ የማንሰራ ከሆነ ከግለሰብ ጀምሮ ሃገር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ይህንን ለመከላከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ህጎችና ሪፎርሞች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የጂማ ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ስልጠናዉ የሰልጣኞችን አቅም በመገንባት፣ በተለይም የምርምር ስነምግባር የተያያዙ ችግሮ ች አሉ በመፍታት በኩል በርካታ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ጅማ ፣ ቦንጋ ፣ ሚዛን ቲፒ ፣ ጋምቤላ ፣ አሶሳ ፣ ወልቂጤ ፣ ደንቢ ዶሎ ወለጋ እና መቱ ዩኒቨርስቲዎች፣ የጋምቤላ፣ የቤኔሻንጉል እና የኦሮሚያ የግብርናና ጤና ምርምር ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ ከየካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲውት(EPHI)፣ አርመን ወሃንሰን ምርምር ኢንስቲቲውት ፣(AHRI) እና ኢትዮጲያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን (EFDA )የምርምር አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በ195 ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን የኢንተርኔት ማስፉፊያ ስራዎች አስመረቀ

"የላቀ የዩኒቨርሲቲዎች ትሰስር ለዘላቂ ልማት! " በሚል መሪ ቃል ትምህርታዊ ዓውደ ርዕይ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
================================ =====

(ነሃሴ 28/2013ዓም) “የላቀ የዩኒቨርሲቲዎች ትሰስር ለዘላቂ ልማት!” በሚል መሪ ቃል ትምህርታዊ ዓውደ ርዕይ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ሲሆን የሳይንስ ግኝቶችን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ክፍሎች የተሰሩ የቴክኖሎጂ እና ሌሎች ስራዎች ቀርበዋል፡፡

ከ28-30/2013 ለሶስት ቀናት በሚቆየዉ አዉደ-ርዕይ በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ አስራ ስምንት ባንኮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ፣ ቀይ መስቀል፣ የድረደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ኮካኮላ ለስላሳ መጠጦች ቦታ በመውሰድ ምርትና አገልግሎታቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች በትኩረት መስካቸው መለየታቸውን አስታውሰው አፕላይድ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሀገሪቱን ብልጽግና ለማሳካት ኢንዱስትሪውን በማገዝ ከፍተኛ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።

ዶ/ር ዑባህ አደም የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዓውደ ርዕዩ በአካባቢው የንግዱን ማህበረሰብ እና ኢንዱስትሪውን ለማስተሳሰር ያለመ መሆኑን እና ለዩኒቨርሲቲዎች የውስጥ ትስስርም ያለው ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር÷ ዩኒቨርስቲው ከተማዋን ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
ዓውደ ርዕዩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ፣ የፌደራል ተቋማት የተጋበዙ እና ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የአስተዳደርና ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራሎች እና ዳይሬክተሮች ፣ከ41 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የቢዝነስ ልማት ዳይሬክተሮች እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጎብኚተዋል።

ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ልማት ፎረም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ እና የትኩረት መስክ በማመላከት ተጠናቋል ።
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ ለ13ኛ ግዜ ያሰለጠናቸውን 969 ተማሪዎችን አስመረቀ
**********************************************************
ነሀሴ (29/2013ዓ.ም) ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ በመደበኛው የትምህርት ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 746 ወንድ እና 223 ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ 969 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ ትምህርት ፍትሃዊነት፣ ተደራሽነት አግባብትና ጥራት ላይ እየሰራ ሲሆን በተለይም የትምህርትን ጥራት ለማሳደግ ዩኒቨርስቲዎችን በትኩረትና በተልእኮ በመለየት ጥራታቸዉን የጠበቁ ምሁራንን እንዲያፈሩ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
በዚህ መሰረት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲና ሌሎችም የትኩረት መስካቸዉን ለይተዉ ወደ ስራ የገቡ የሃገራቸን ዩኒቨርስቲዎች ስራቸዉን አጠናክረዉ ከፍ ላለ ዉጤታማነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የዛሬ ተመራቂዎች በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቴፒ ካምፓስ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ በማጠናቀቃችሁ በቆይታችሁ ያካበታችሁትን እዉቀትና ክህሎት ከፍ ላለ ሃገራዊ ዉጤት ለማዋል መዘጋጀት ይጠበቅባችኋል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጦፋ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው በ1999 ዓ.ም በአንድ ኮሌጅ በሶስት ትምህርት ክፍሎች በ215 ተማሪዎች መጀመሩን ገልጸው በአሁኑ ስአትም በስድስት ኮሌጆች በሶስት ት/ቤቶችና በ45 ቅድመ-ምረቃ እና 25 ድህረ -ምረቃ ፕሮግራም በመደበኛ፣ በክረምትና ኤክስቴንሽን ከ20ሸህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለዉም ዩኒቨርስቲው በመንግሥት ለከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና የተሠጠውን ትኩረት በመጠቀም የ10አመት መሪ እቅድ በማዘጋጀት በሀገራችን ታዋቂ ከሆኑ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ ለመሆን የሰነቀውን ራእይ ለማሳካት እንዲሁም ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በተለይም በጥናትና ምርምር ዘርፍ የተጠናቀቁ የምርምር ፕሮጀክቶች በርካታ ቢሆኑም በተፈጥሮ ሃብት በበለፀገ አካባቢ የሚገኝ እንደመሆናችን በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን እምቅ እውቀት በሳይንሳዊ እውቀት ታግዞ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች ከምንም በላይ አሁን የደረሳችሁበት የትምህርት ደረጀ የህይወት ምእራፍ መጀመሪያ ላቅ ወዳለ የህይወት ምእራፍ መሽጋገሪያ ድልድይ መሆኑን በማወቅ በተሻለ እውቅናና ክብር ምን ግዜም ተግታችሁ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ ዩኒቨርስቲው በቴፒ ከተማ አንድነትና ህብረት ቀበሌዎች 200ሽህ ብር ድጋፍ ያስገነቡትን ከሁለት ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ያስረከቡ ሲሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና በክብር እንግዶች ተካሂዷል፡፡
2025/07/14 09:09:20
Back to Top
HTML Embed Code: