Telegram Web Link
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና በአርባንጭ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ይገኛል ፡፡

=====================================

(ጳጉሜ 2/2013 ዓም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀኔራሎች፣ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በአርባምንጭ እየሰጠ ይገኛል ፡፡
በስልጠናዉ መጀመሪያ ተሳታፊዎች በዛሬዉ ዕለት የተከበረዉን “የአገልጋይነት ክብር ቀን” ለማሰብ በጋራ ከመቀመጫቸዉ በመነሳት ለአገልጋይነት ያላቸዉን ክብር ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳምጠዉ ዳርዛ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ 19 ተፅዕኖ ጭምር ተቋቁሞ በመማር ማስተማር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ያሳካቸዉን ዋና ዋና ተግባራት የገለጹ ሲሆን የ2013 ዓም አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የማጠቃለያ ስነስርዓትም በነገዉ ዕለት እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመሰረተ-ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ስልጠናዉ በዋናነት ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመራ በመሆኑ የሰራ ሀላፊዎች በእቅድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ግዢ እና ፋይናንስ አንጻር የሚያጋጥሟቸዉን ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያግዝ ነዉ ብለዋል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ስልጠና የሰጡት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ “መሪ በየትኛዉም ደረጃ እና ወንበር ቢቀመጥ ግቡ አገልጋይነት በመሆኑ ለተገልጋያችን ተገቢዉን ክብር ልንሰጥ ይገባል፤በአገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አመት ዋዜማ ቀን ሰይሞ አገልጋይነትን ማሰብም ለበለጠ ስራ እና ሀላፊነት እንድንነሳሳ የሚያደርግ ነዉ” ብለዋል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ፣በእቅድ ክትትል፣ግብረመልስ እና ሪፖርት በከፍተኛ ትምህርት፤ የፋይናንስ፣ግዢ እና የሰዉ ሀብት አስተዳደር በከፍተኛ ትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ዉጤት አመላካቾች ስልጠና በዶ/ር ወርቁ ነጋሽ ፣በዶ/ር አባተ ጌታሁን እና አቶ ስንታዬሁ ደምሴ በተከታታይ ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆየዉ ስልጠና በነገዉ ዕለት በአርባምንጨር ዩኒቨርስቲ የአረንጓዴ አሻራ የማጠቃለያ ጭግኝ በመትከል እና ቀሪ ርዕሶችን በመዳሰስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
2025/07/14 09:11:29
Back to Top
HTML Embed Code: