ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን 3237 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
===================================
(ነሃሴ 29/2013ዓም)ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን 3237 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው በስምንት ኮሌጆች ስር በሚገኙ 45 ትምህርት ክፎሎቸ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆኑ ከተመራቂዎቹ መካከል 2,098 ወንድ እና 991 ሴት በድምሩ 3,089 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም የቀሩት 122 ወንድ እና 26 ሴት በድምሩ 148ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ የወራቤ፣ የመቱ እና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝደንቶች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ከምረቃ ፕሮግራሙ በኋላም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት ከተመራቂ ተማሪዎች ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ ማከናወናቸውን ከዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት አድርሶናል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዓመት እስከ 150 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ እየሰራ መሆኑን ገለጸ
=====================================
(ነሀሴ 30/2013ዓም) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ በሆኑ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በዓመት እስከ 150 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በአራዳ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ያረጁ እና ያዘመሙ የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤቶችን የማደስ ስራ ነሃሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከመማር-ማስተማር እና የምርምር ስራዎች በተጨማሪ በሚያከናውነው የማህበረሰብ አገልግሎት ስራው አማካይነት ያረጁ የአቅመ ደካማ ቤቶችን አድሶ ዜጎችን ለመደገፍ ባቀደው መሰረት
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ቀበሌ 24 አማኑኤል አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ተማሪዎች በተገኙበት የእድሳት መርሀግብሩ ተጀምሯል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና መርሀግብሩን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ በሆኑ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በዓመት እስከ 150 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ በማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ከምርምር በተገኘ ውጤት የምንሰራው ስራ የህብረተሰቡን ህይወት ለመቀየር ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ በከተማ የእለት ጉርስና የጎናቸው ማረፊያ ቤት የሌላቸውን ወገኖች በርካታ በመሆናቸው ዩኒቨርሲቲው ይህንን ታሳቢ አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በአራዳ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ለማሳያ ያክል የሚሆኑ እያንዳንዳቸው 6 ቤተሰብ ያላቸው ሁለት ቤቶችን የማደስ ስራ ቢጀመርም በሌሎች ክፍለ ከተሞች እንደነ ቂርቆስ፣ ልደታ፣ የካ፣ ጉለሌ እና በመሳሰሉት ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት ለሌሎች አርአያ ለመሆን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል ፕ/ር ጣሰው፡፡
እድሳቱ ለአንድ ቤት እስከ 200 ሽህ ብር ዋጋ ሊጠይቅ እንደሚችል የጠቆሙት ፕሮፌሰር ጣሰው ዋናው አላማ አቅሙ ላላቸው ሁሉ አርአያ ለመሆን እና ህብረተሰቡ የተቸገረውን ወገን እየደገፈ ችግሮችን በጋራ የማቃለል ነባር ባህሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማሳሰብ ያክል ነው ማለታቸውን የዩኒቨርስቲው ህዝብ ግንኙነት መረጃ ያላክታል።

2ኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በቦንጋ ዩኒቨረሲቲ ተቋቋመ
=====================================
(ነሃሴ 30/2013 ዓም) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ይፋ ያደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተቋቁማል።
በዩኒቨርስቲው ለሚገኙ መምህራን ተማሪዎችና የሴኔት አባላትም የማዕከሉን አስፈላጊነት አደረጃጀት በተመለከተ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ሁሉንም ዩኒቨርሲቲ እርስ በእርስ የሚያገናኘው የአባይ ልጆች የተሰኘ ሶፍትዌር ላይም ምሁራንና ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያደርጉ ተደርጓል ።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ስልት በመከተል ምሁራንና ተማሪዎች ለሀገራቸው የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያግዝ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል።ምሁራንና ተማሪዎች ይህን የቴክኖሎጂ መዋቅር በመጠቀም በዲጂታል ዲፕሎማሲ ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀገራዊ ትግል እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ማዕከሉ የያዘዉን አገራዊ ተልዕኮ እንዲያሳካ የዩኒቨርሲቲው አመራር ; ምሁራንና ተማሪዎች ብርቱ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለማዕከሉ መቋቋም የሚያስፈልግ ጽ/ቤትም ያዘጋጀ ሲሆን ተማሪዎች የሚሰባሰቡበት "የአባይ ልጆች" የተሰኘ ፓርክም ለማዕከሉ አባላት ክፍት አድርጓል።በእለቱም በፓርኩ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።
"የተግባቦት እጥረት የውድቀት መሰረት ነው፤ እኛ በማኅበረሰብ ውስጥ ነን" በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተወያይተዋል።