Telegram Web Link
ለእቅድ ዝግጅት እና ክትትል ተገቢዉን ትኩረት በመስጠት ዉጤታማ መሆን ይገባል ተባለ
=============================================================
(ጳጉሜ 3/2013 ዓም) ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዳይሬክተር ጀኔራሎች፣ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ሲሰጥ የነበረዉ የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና በበየነ መረብ ባደረጉት ማጠቃለያ የህዝብ አመኔታን ለማግኘት ለእቅድ ዝግጅት እና ክትትል ተገቢዉን ትኩረት በመስጠት እና የተገልጋይ እርካታን በየጊዜዉ መለካት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ፣በእቅድ፣ግዢ እና ፋይናንስ እና አስተዳደር ነክ ጉዳዮች ላይ ያተኮረዉ ስልጠና በ2013 ዓም የተሰሩ ስራዎችን መነሻ ያደረገ በመሆኑ አመራሩ ለ2014 ዓ.ም ምን ላይ መድረስ አለብን፣ግባችንን ለማሳካት ምን ምን ተግባራት እንፈጽማለን የሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎችን በመረጃ ላይ ተመስርቶ እንዲመልስ የሚያግዙ ናቸዉ ብለዋል፡፡
ስልጠናዉ ከበጀት እና ፋይናንስ አመራራችን ጋር በተገናኘ የሚገጥሙንን መነቆዎች ለመፍታት የሚያግዝ በመሆኑ በጀትን በዉጤታማት መምራት እንዲሁም በሀብት እና ቴክኒክ የሚደግፉንን የልማት አጋሮች መረዳትና በተገቢዉ ለማሰማራት በአዲሱ ዓመት በትኩረት መስራት እንደሚገባም አክለዋል፡፡

ስልጠናዉ በዛሬ ዉሎ የሳይንስ ፣ አስተዳደርና መሰረተ ልማት፣ቴክኒክና ሙያ፣አለምአቀፍ ትብብር እና ትስስር እና ስትራቴጂክ እቅድ ዘርፎች ዉጤት አመላካቾች በየዳይሬክተር ጀነራሎች በዶ/ር ሰለሞን ቢኖር፣ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ፣አቶ መለሰ…፣አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል እና አቶ ከበደ ግዘዉ ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀኔራሎች፣ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ሲሰጥ የነበረዉ የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የ2013 ዓም አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማጠቃለያ ችግኝ በመትከል ተጠናቋል፡
2025/07/12 16:07:39
Back to Top
HTML Embed Code: