የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትርና ተጠሪ ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ያሳደሷቸዉን አቅመ ደካማ ቤቶችን አስረከቡ
ግሜ 5/2014 ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካዛንቺስ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ያሳደሷቸዉን የሁለት አቅመ ደካማ ቤቶችን ግንባታዉን በማጠናቀቅና ቁሳቁስ በማሟላት ያስረከበ ሲሆን የበአል መዋያ በግ በስጠታ አበርክቷል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የክረምት በጎ ፈቃድ በጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ተጀምረዉ ወደ ስራ ከተቀየሩ ትልልቅ ሃሳቦችን አንዱ ነዉ፡፡ “ሀሳቡን ወደ መሬት አዉርደን በዚህ መንገድ ማገዛችን ከተባበርን ምን መስራት እንደምንችል ትምህርት ያገኘንበትና ሌሎች ትልልቅ ሃገራዊ የሆኑ ጉዳዮችን በትብብር መስራት እንደሚቻል ያሳየንበት ተግባር ነዉ” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ለሚኒስቴር መ/ቤቱ 45 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችም በተመሳሳይ መልኩ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ እያከናወኑ ነዉ ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይም ሌሎችን ተግባራትም አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ለሰሩ፣ ለመሩና ለተባበሩ ሰዎችም በተቋሙ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸዉ “ከተባባርንና ጥቂት ነገር ካዋጣን የተሻለ ሃገር መፍጠር እንደምንችል ማሳያ ነዉ፡፡ ካለን ትንሽ ነገር ላይ ቀንሰን ለተወሰኑት መድረስ እንችላለን፡፡ ይህንንም በየአመቱ እየሰራን ከሄድን ዜጎችን የተሻለ ኑሮ ደረጃ እንዲደርሱና የተሻለ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ማድረግ እንችላለን” ብለዋል፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር ከተጋገዝን አሁን ያለብንን ችግር አይደለም ሌሎችን መጋፈጥና መሻገር እንደምንችል ያሳየ ነዉ ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዉ፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል ረዲ በበኩላቸዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሰራዉ ስራ የአቅመ ደካሞችን ቤት አፍርሶ ከብርድና ዝናብ መከላከል ከእገዛዉ ሁሉ ትልቅ እገዛ ነዉ ፡፡ይህም በአዲስ አመት መልካምነትን ያሳየንበት በጋራ የተባበርንበት ነዉ ብለዋል፡፡
የቤት እድሳት የተደረገላቸዉ ወ/ሮ እየሩሳሌም ወንድሙና ወ/ሮ አባይነሽ አለሙ ከዛሬ ነገ ፈረሰብን እያልን እንፈራና እንጨነቅ ነበር ፡፡ ፈጣሪ ይመስገን ይህን የመሰለ ቤት ስለተሰራልንና ሙሉ የቤት ቁሳቁስና እንዲሁም የበአል መዋያ ስለተሰጠን ደስ ብሎናል እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሮች፣ የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማዉና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
ለከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሰራ አመራር ቦርድ፣ፕሬዚዳንቶች፣ መምህራን፣ተማሪዎች እና የትምህርቱ ማኅበረሰብ ፤ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዋና መ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች እንዲሁም ለመላ ኢትዮጵያዊያን መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን !
2014 ዓዲስ አመት የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የብልጽግና እና በሁሉም ዘርፍ የላቀ ዉጤት በማስመዝገብ ወደ እዉቀት - መር ኢኮኖሚ የምንሻገርበት እንዲሆን እንመኛለን!
በ2014 ዓዲስ ዓመት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ፣ የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስርን በማጠናከር በተግባር ጭምር የሰለጠነ እና በገበያም ተወዳዳሪ የሆነ ብቁና በቂ የሰው ሀብት ለማፍራት ፣በከፍተኛ ትምህርት የመምህራን ጥራት እና አቅርቦት ለማሳደግ የአገር በቀል የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመተግበር ፣ የት/ትና ስልጠና ጥራት ለማረጋገጥ ብሄራዊ የአክሬዲቴሽን ስትራቴጂና የብቃት ምዘና ተግባራዊ ለማድረግ በበለጠ ትከረት እና ሀላፊነት እንሰራለን!
ምርምሮችን በተገቢዉ ስነምግባር ለመምራትና አገር በቀል እዉቀቶችን በመጠቀም ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚያስችል ብሄራዊ የምርምር ስትራቴጂ ይተገበራል ፣ ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሻገር እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ እንዲሁም ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ኢትዮጰያን የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን በትጋት እንሰራለን!
በድጋሚ መልካም አዲስ አመት!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

በቤጂንግ 2021 የዓለም ዓቀፍ የሮቦት ውድድር (WRCC2021) ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን በተሳተፉበት ዘርፍ የወርቅ፣ብር እና ነሀስ አሸናፊ ሆኑ
=========================================
(መስከረም 06/2013 ዓም) እ.አ.አ ሴፕቴምበር 13 / 2021 በቤጂንግ የዓለም ዓቀፍ የሮቦት ውድድር ሻምፒዮና ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት፣ ኢንተርፕራይዞች እና 2,000 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በተሳተፉበት ዘርፍ የወርቅ፣ብር እና ነሀስ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ከውድድሩ በተጨማሪም Leading Brain Computer Interface (BCI) Devices መሣሪያዎችን ጨምሮ የዘመናዊ ሮቦቶች አውደ ሪዕይ ተካሂዷል፡፡ከምርምር ተቋማት እና ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ቡድኖችም በውድድሩ ላይ ዘመናዊ መሣሪያዎቻቸውን አሳይተዋል።
በውድድሩ ላይ የተገኙት የዓለም የሮቦት ውድድር ዝግጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ዣንግ ዩዌይ “የዓለም ዓቀፍ ሮቦት ውድድር እ.አ.አ በ2015 ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሰባተኛው ዙር እንደተካሄደ እና የውድድሩ አጠቃላይ ይዘት እና ስርዓት ቀስ በቀስ እየበለፀገ፣ የፈጠራ ማዕከል እየሆነና እና እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀዋል።
በውድድሩ 2,000 የሚጠጉ ትምህርታቸውን በቻይና ሀገር እየተከታተሉ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መካከል የTianjin University of Technology and Education (TUTE) እና WorldSkill Competition China Research Center Innovation Institute, LUBAN Workshop and EPIP ሰልጣኞች የሆኑት ተሳትፈውበታል።
ውድድሩ ለአራት ቀናት በአራት ምድቦች የተካሄደ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ከውድድሩ ጎን ለጎን የዓለም ዓቀፍ ሮቦት ኮንፈረንስም ተካሄዷል፡፡
በዘመናዊ ማምረቻ (Artificial Intelligent Manufacturing) እና በጤና እንክብካቤ (Healthcare) ሮቦቶች ትግበራ ላይ ያተኮረው የ“Tri-Co” Robots (Coexisting-Cooperative-Cognitive) ምድብ ሮቦቶች ከተለዋዋጭ አካባቢ ጋር መልመድ እና በስራ ሁኔታ ውስጥ ከሰዎች እና ከሌሎች ሮቦቶች ጋር መተባበር ይችሉ እንደሆነ ተፈትሿል።
ኢትዮጵያዊያን በተወዳደሩበት የውድድር መስክ በ“Tri-Co” Robots and Robot Application እጩ ዶ/ር ሰላሙ ይስሃቅ የወርቅ፤ አባኩማ ጌታቸው (የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ) እና ፀጋዬ አለሙ (የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ) የብር እና እጩ ዶ/ር ዮሐንስ ኃ/መስቀል እና ሄኖክ ሰይፉ (የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ) የነሀስ ሜዳሊያ እንዲሁም የዋንጫ ተሸላሚዎች በመሆን ውድድሩ ተጠናቋል።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ለአሸናፊዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡