Telegram Web Link
ጅማ ዩኒቨርስቲ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ተቋማት ጋር የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ፊርማ ተፈራረመ፡፡
*******************************************************************************************
(መስከረም 7/2014 ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ የምርምር ስትራቴጂ እና የትኩረት መስክ የረቂቅ ሰነድ ግምገማ ግብአት በመሰብሰብ፣ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የመግባቢያ ፊርማ ስነስርአት በመፈራረም ተጠናቋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እንደገለጹት የዚህ ስምምነት ዋና አላማ የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት፣ በላቀ ደረጃ አስተባብሮ ዉጤት ለመምጣት፣ ስትራቴጂዉን በትክክል ለመፈጸም እና የኢንደስትሪ ትስስር ለመፍጠር ነዉ፡፡
በተለይም ስምምነቱ የምርምር ወጪን ለመቀነስ፣ ሃብትን በጋራ ለመጠቀም፣ የምርምር ድግግሞሽ ለማስቀረት፣ችግር ፈቺ የሆኑ እና ለሃገር እድገት ጉልህ አስተዋጾ የሚያበረክት ምርምር ለመስራት ይጠቅማል ተብሏል፡፡
“የሶኮሩ ስምምነት” የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይህ ስምምነት ጅማ ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የምርምር ዩኒቨርስቲዎች፣ ከጅማ ክላስተርና ቅርበት ካላቸዉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምር ማእከሎችና ተቋማት ጋር የተፈራረመዉ እንደሆነ ተገልጸል፡፡
ፕሮግራሙ የችግኝ ተከላ እና ለምርምር እሮጣለሁ በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ ተጠናቋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከእስራኤል ፓርላማ አባላትና ከሻሎም ኮፕስ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

(መስከረም 12/2013 ዓም)የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከእስራኤል ፓርላማ አባላትና ከሻሎም ኮፕስ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው ሁለቱ አገራት በሳይንስና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን የቆየ ትብብር የበለጠ አጠናክረው በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

በአገራቱ መካከል የሚጠናከረው ትብብር በኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሻለ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የአለም አቀፍ ትብብር ትስስርና አጋርነት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ገልጸዋል።
2025/07/13 15:03:04
Back to Top
HTML Embed Code: