Telegram Web Link
ምርምሮች የምርምር የስነ ምግባር የተከተሉ እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሰራ ነው
========================
(መስከረም 13/2014ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሐሮማያ ዪኒቨርስቲና ከአውሮፓና ታዳጊ ሃገራት የክሊኒካል ሙከራዎች ትብብር (EDCTP) ጋር በመተባበር የምርምር ስነምግባር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በሐረማያ ዩኒቨርስቲ እየሰጠ ይገኛል፡፡

ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ በበየነመረብ ባደረጉት መክፈቻ እንደተናገሩት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለምርምር ልዩ ትኩረት በመስጠት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አዘጋጅቶ እየሰራ ሲሆን እነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ተጠቅመው የሃገራችንን የትምህርትና ስልጠና ምርምር ተቋማት ምርምሮች እያካሄዱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ይህ በምርምር ስነምግባር ዙሪያ የሚሰጠዉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዋና አላማ በሃገራችን ያሉንን የምርምር ስራዎች ያሉ እድሎችን ለማጠናከር እንዲሁም ተግዳሮቶች ተብለዉ የተለዩትን የተመራማሪ እጥረት ለማሳደግ፣ ወጣት ተመራመሪዎችን ለማበረታታት፣ የምርምር አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፣ ትብብርና ትስስርን በተቋማትና ምርምር ማእከላት ለመፍጠር፣ ዘላቂነት፣ ጥራትና አግባብነት፣ የመሰረተ ልማትና በጀት ችግር ለመሻገር እንዲሁም የተሰሩ ምርምሮችን በአግብቡ እንዲሰራጩ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸዉ የምንሰራቸዉ ምርምሮች ስራዎች የምርምር ስነምግባርን መርህ የተከተሉ እና የምናሳትማቸው ጆርናሎች በትክክለኛ ዌብ ሳይት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን በርካታ የምርምር ስነ ምግባር ችግሮች መኖራቸውን ገልጸው ይህም ከግለሰብ ጀምሮ ዩኒቨርስቲውን ፣ ፈንድ አድራጊውን ፣ ሃብትን፣ ጊዜና ገንዘብ በማባከን ሃገር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡
ይህንን ለመከላከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥራቱን የጠበቀ የምርምር ስራዎችና ጆርናሎች እንዲሰሩ የተለያዩ ህጎችና ሪፎርሞች አውጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናዉ በሃገር ደረጃ ለ5ኛ ግዜ በሓሮማያ ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ግዜ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የምርምር ስነምግባር ዳይሬክተር ዶ/ር ዳኒኤል ታደሰ ናቸው።

በስልጠናው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጀኔራል ዳይሬክተሮች፣ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች፣ የሃሮማያ ክላስተር የሚገኙ የመንግስት ዪኒቨርስቲዎች (ድሬዳዋ ፣ ሐሮማያ ፣ ቀ/ዳሃር ሰመራ ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሰቲዎች)፣ ከግል ዩኒቨርስቲዎች ዩኒቲ፣ አድማስ፣ ሃራምቤና ሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲዎች፣ የሃረሪ፣የድሬዳዋ ፣ የአፋር እና የሶማሊ የግብርና፣ አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የምርምር ማእከሎች፣ ጤና ቢሮ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ‹‹የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት›› ህዝባዊ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ
ከመስከረም 13-14/2014 ሲካሄድ የነበረዉ የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍና የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕዉቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ግምገማ ተጠናቋል
======================================================
(መስከረም 15/2014) ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
"የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ዘመቻ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ላይ ተመስርተው በኢትዮጵያ ላይ ኢ-ፍትሃዊ አመለካከት ለያዙ አሜሪካን ጨምሮ ላሉ ለሌሎች አገራት ምላሽ የሚሰጥ እና በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለዉን ተገቢ ያልሆነ ጫና ለማስቀረት እውነታውን ለማስረዳት ዕድል የሚፈጥር ነዉ ብለዋል።
ዘመቻው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች፣ በሁሉም ተጠሪ ተቋማት እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚካሄድና ከ7 መቶ ሺ በላይ ዜጎች እንደሚሳተፉበት ገልጸዋል ሚኒስትሩ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊቱ በተግባር እያሳዩት ያለውን ድጋፍና አጋርነት በ"የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ላይም በመሳተፍ ታሪክ እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮች፣የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሮች፣የአገር አቀፍ ተማሪዎች ህብረት እና የየዩኒቨርስቲዎች ተማሪ ፕሬዝዳንቶች፣እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች‹‹የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት›› ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተሳትፈዋል፡፡
ጎን ለጎን ከመስከረም 13-14/2014 ሲካሄድ የነበረዉ የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍና የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕዉቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ግምገማ ተጠናቋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና የአክሬዲተሸን ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደዉ የአገርዓቀፍ ምክክር ጉባዔ ፣ ሰነዶቹ በቂ የዝግጅት ሂደት ያለፉና በጥራት መዘጋጀታቸውን ማመላከቱን ገልጸዋል።
በቀጣይም፣ በተለያዩ እርከን ላሉ የተቋማት አመራሮች በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመሥጠት፣ ወደትግበራ እንደሚገባ እና ሁሉም የግልና የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ ፕሮግራሞቻቸው በአገር ዓቀፍ ብቃት ማዕቀፍ መሠረት፣ ዝቅተኛውን መስፈርት ሊያሟሉ እንደሚገባ እና ለዚህም በቀጣይ ዝቅተኛውን የጥራት ደረጃ ስለማሟላት፣ በገለልተኛ አካል ተመዝኖ/ተጣርቶ ዕውቅና እንደሚሰጥ አክለዋል ሚኒስትሩ፡፡
በአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ከመስከረም 13-14/2014 ሲካሄድ የነበረዉ ፕሮግራምም በትናንትናዉ ዕለት ማምሻዉን ተጠናቋል፡፡
2025/07/09 15:54:17
Back to Top
HTML Embed Code: