ጅማ ዩኒቨርስቲ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ተቋማት ጋር የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ፊርማ ተፈራረመ፡፡
*******************************************************************************************
(መስከረም 7/2014 ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ የምርምር ስትራቴጂ እና የትኩረት መስክ የረቂቅ ሰነድ ግምገማ ግብአት በመሰብሰብ፣ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የመግባቢያ ፊርማ ስነስርአት በመፈራረም ተጠናቋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እንደገለጹት የዚህ ስምምነት ዋና አላማ የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት፣ በላቀ ደረጃ አስተባብሮ ዉጤት ለመምጣት፣ ስትራቴጂዉን በትክክል ለመፈጸም እና የኢንደስትሪ ትስስር ለመፍጠር ነዉ፡፡
በተለይም ስምምነቱ የምርምር ወጪን ለመቀነስ፣ ሃብትን በጋራ ለመጠቀም፣ የምርምር ድግግሞሽ ለማስቀረት፣ችግር ፈቺ የሆኑ እና ለሃገር እድገት ጉልህ አስተዋጾ የሚያበረክት ምርምር ለመስራት ይጠቅማል ተብሏል፡፡
“የሶኮሩ ስምምነት” የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይህ ስምምነት ጅማ ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የምርምር ዩኒቨርስቲዎች፣ ከጅማ ክላስተርና ቅርበት ካላቸዉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምር ማእከሎችና ተቋማት ጋር የተፈራረመዉ እንደሆነ ተገልጸል፡፡
ፕሮግራሙ የችግኝ ተከላ እና ለምርምር እሮጣለሁ በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ ተጠናቋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከእስራኤል ፓርላማ አባላትና ከሻሎም ኮፕስ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ
(መስከረም 12/2013 ዓም)የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከእስራኤል ፓርላማ አባላትና ከሻሎም ኮፕስ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸው ሁለቱ አገራት በሳይንስና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን የቆየ ትብብር የበለጠ አጠናክረው በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
በአገራቱ መካከል የሚጠናከረው ትብብር በኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሻለ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የአለም አቀፍ ትብብር ትስስርና አጋርነት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍና የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕዉቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ግምገማ ተጀመረ
=================================
(መስከረም 13/2013) በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍ (Ethiopian Qualification Framework - ETQF) እና የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕዉቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ (Ethiopian Higher Education & Training Accreditation Strategy) ረቂቅ ሰነዶች ግምገማ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (ሱሉልታ) መካሄድ ጀምሯል።
መረሃ ግብሩ ከመስከረም 13-14 ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ ሲሆን በፕሮግራሙ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ሰነዶቹ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን በሚመለከት ከህዝቡ እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ይፈቱልናል ብለን እናምናለን ብለዋል።
ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ባለፉት አመታት በትምህርት ተደራሽነት እና ፍትሃዊነት ላይ የተሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው የጥራት እና አግባብነት ችግሮች ግን ያልተሻገርናቸው በመሆኑ እየተሰራባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዎች ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ እና ዶ/ር ሙሉ ነጋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ፣ የተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮች እና ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።