Telegram Web Link
ያው እንደተጠበቀው ነው። የማድሊን መልካም ኒያ መንገድ ላይ ቀርቷል። የጀልባዋ ጉዞ ተገቷል። ምሽቱን ከገዛ የባህር ዳርቻ ሳትደርስ በኃይል ተቆጣጥረው ወስደዋታል። ማድሊን ካሰበችው የመድረስ ዓላማዋ ባይሳካም በአቅሟ ለተራቡትና ለተቸገሩት ገዛውያን ድምፅ ሆናለች። ብዙ የነፃነት ወዳጆች ፈለጓን ይከተላሉ ተብሎ ይታሰባል ።


https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ከላይ ባያችሁት ቪዲዮ የቀድሞው የሶሪያ አማጽያን መሪ የአሁኑ ፕሬዚዳንቷ አሕመድ አሽ-ሸርዕ ስለባለቤቱ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

“ በ 2012 ባልተለመደ ሁኔታ ነበር የተጋባነው፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታ ነበር፡፡ ከተጋባን በኋላ ስለሥራዬ ብዙ መረጃ አልሠጣትም ነበር፡፡ በሂደት ግን እጅግ አስቸጋሪ ራሷ ደረሰችበት፡፡ ግና ሁሉንም ሁኔታ ትቋቋም ነበር፡፡ የአየር እና የከባድ መሣርያ ድብደባውን፣ ስደትና መፈናቀሉን ሁሉ ችላ ነው አብራኝ የዘለቀችው፡፡ በዚህ ሂደት ወደ 49 ቤቶችን ቀይረናል፡፡ በየሦስት ወሩ አንድ ቤት እንደማለት ነው፡፡ ለሴት ልጅ ይህ ከባድ ነው፡፡ ኑሯችን እንደ ዘላን ነበር፡፡ በርግጥ እነርሱ ለሕይወት አስፈላጊያቸው የሆነን ነገር ይዘው ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡ እኛ ግን ሁኔታው ያን ሁሉ ስለማይፈቅድልን እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ውስጥ ኖረናል፡፡ በዋሻዎች፣ በምሽጎችና በሌሎችም፡፡ በርግጥ አልፎአልፎ እንደሥራው ሁኔታ ጥሩ ቦታዎች ላይም ኖረናል፡፡ ብዙ ጊዜ ለሷም ለልጆቻችንም ደኅንነት ስል ወደተሻለ ቦታ እንድትሄድ እመክራት ነበር፡፡ እሷ ግን ፈጽሞ አትቀበልም፡፡ በዓላማዋ ፀንታ ቆየች፡፡ ከጎንህ ሆኜ ፈገግታህን ማየት ነው የምፈልገው ትለኝ ነበር፡፡ በርግጥ ባለፉት 14 ዓመታት ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ አልፈናል እውነት ነው፡፡ ውጤቱ ግን ይኸው እንደምታዩት ነው፡፡ ዛሬ እዚህ ተቀምጠናል፡፡ እዚህ ከመድረሳችን በፊት ግን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አሳልፈናል፡፡ በያንዳንዱ ሁኔታና ቅጽበት ጽኑ ሆና ከጎኔ ቆማ ዘልቃለች፡፡ አላህ በመልካም ሁሉ ይመንዳት፡፡ አሁንም ያጽናት፡፡ በቀጣይም አገራችንን በመገንባቱና በማሳደጉ ረገድ በሚኖረው ሁለተኛው የሕይወታችን ክፍል የሴት ልጅ ሚና ወሳኝ ነውና አብረን እንዘልቃለን፡፡”

ትዕግሥት መራራ ብትሆንም ፍሬዋ ጣፋጭ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
የመሠናበቻ ጦዋፍ
*
ትናንት ዙል-ሒጃ 13 የአያመ ተሽሪቅ የመጨረሻ ቀን ነበር። አያመ ተሽሪቅ ከዒድ ቀን በኋላ የሚገኙ እንደ ዒድ ቀን የሚቆጠሩ 3 ደማቅ ቀናት ናቸው። በነኚህ ቀናት ውስጥ ሑጃጆች በሚና የጠጠር ውርወራ ሥርዓት ሲያከናውኑ ይቆያሉ ። ውርወራውን ካጠናቀቁ በኋላ ከዚያም ወደ መካ በመመለስ የመሠናበቻ ጦዋፍ (ጦዋፈል ወዳዕ) ይፈጽማሉ ።

ጦዋፈል ወዳዕ ከሐጅ ሥራዎች ውስጥ የመጨረሻው ሥርዓት ነው። ሥርዓቱ ከዕባን በመዞር የሚፈፀም ሲሆን ዙሩም ሰባት ጊዜ ነው። ጦዋፍ አድራጊ የግራ ትከሻውን በገለጠበት ሁኔታ ከዕባን በግራ እጁ በኩል በማድረግ ይዞረዋል። መነሻና መድረሻው ሐጀር አል-አስወድ ነው። ጦዋፉን ከጨረሰ በኋላ ከመቃም ኢብራሂም ኋላ፤ ካልተመቸው ደግሞ ከመስጂዱ የትኛውም ክፍል ሁለት ረከዐህ ይሰግዳል።

ጦዋፈል ወዳዕ ከሐጅ ግዴታዎች መካከል አንዱ ሲሆን የተወው ሰው ለማካካሻው እንሰሳ አርዶ ለመካ ድሆች ማከፋፈል ይኖርበታል ። ይህን ያልቻለ ደግሞ የ10ቀን ፆም ይጠበቅበታል ።

ከሐጅ ሥራዎች መጠናቀቅን ተከትሎ ቅድስት መካን መሠናበት ከባድ ነው። ለዚህም ነው ብዙዎች ይህን የተቀደሰ ምድር በከፍተኛ ናፍቆት፣ በዱዓና በእንባ ይሠናበታሉ።
አላህ አድሎት አንድ ጊዜ ሐጅ ያደረገ ለመመላለሱ ይገጥመው ዘንድ አላህን አብዝቶ መማፀን ይኖርበታል። ሐጅ ማለት እንደገና መወለድ ነውና። ምክንያቱም የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ "ሐጅን በትክክል የፈፀመ ሰው ልክ እናቱ የመጀመሪያ ቀን እንደወለደችው ሆኖ ይመለሳል ።" ብለዋልና።

ሐጁን በተሳካ ሁኔታ የፈፀመ ሰው አላህ ለዚህ ዕድል ስለመረጠው አብዝቶ ያመስግን ።

https://www.tg-me.com/NejashiPP
እዚህ ቦታ ላይ መልካም ነገር ብቻ ነው የምናስተላልፈው።
ቁምነገር ብቻ ነው የምንማማረው።
የመልካም መልዕክት ወዳጆች ተከተሉኝ ።
መልዕክቶችን አጋሩ።


https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
አንበሶቹ
ከላይ ☝️እንደምታዩት እንዲህ ከጉድጓድ ይወጡና አንዳች የሚፈነዳ ነገር እጅግ ዘመናዊ በሚባለው አይደፈሬ ሜርካፋ ታንክ ሥር አስቀምጠው ይሮጣሉ ። እንደቀልድ። ተመልሰው ወደ ምሽጋቸው ይገባሉ። ከዚያ ታንኩ እንደባሉን ይፈነዳል ። ተዓምረኛ ትውልድ!!። የጀግንነት ጥግ።


ሰዎቹ ሕይወትን ጠልተው አይደለም እንዲህ አንዲት ነፍሳቸውን አስይዘው የሚታገሉት። ነፃነትን ናፍቀው እንጂ።
ስለናፈቁም ነው ለነፍሳቸው ቅንጣት ታክል የማይሳሱት።
ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት ይባል የለ። ከነፃነት በላይ ምን አለ!!።


ይህን ጀግና ሕዝብ ነው እንግዲህ ያች ተንከሲስ ካልገዛኋችሁ ብላ በጅምላ የምትፈጀው። ተንቀሳቃሽ ነገር ሁሉ አጥቂዋ ስለሚመስላት በደመነፍስ ትተኩሳለች። ሰላማዊውን ሁሉ ትጨርሳለች።
ወዲህ ባዶ እጅ ሆነው እልም ያሉ ጀግኖች ፣ ወዲያ እስከ አፍንጫ ታጥቀው እልም ያሉ ፈሪዎችን ታገኛለህ። ወላሂ እንድ የሁድ ፈሪ የለም።


እነኚህ ገዛውያን እኮ በጣም ይገርሙኛል። ዙርያ መለስ እንደ እሥር ቤት ተከበው ስለሚኖሩ አይደለም ብረትና ጥይት ዱቄትና ውሃ የማይገባላቸው የዛለ የደከመ ሰውነት ባለቤት ናቸው።
እንዲህም ሆነው ግን በእጃቸው ባገኘት ነገር አምርረው ይታገላሉ ።
ከበባው ቢነሳላቸው ደግሞ እንዴት ሊታገሉ እንደሚችሉ አስቡት።


በርግጥም ይቆይ ይሆናል እንጂ በፈለስጢን ምድር የነፃነት ጮራ መፈንጠቁ አይቀርም።

ኢንሻአላህ ።


https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
☝️
ለዐረቡና ለሙስሊሙ ዓለም
በአጠቃላይ ለሰው ልጆች በሙሉ
ከዚህ በላይ ምን ውርደት
ምን አሳፋሪ ነገር አለ።

ዛሬ
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ፈራርሳ ወደሜዳማነት በተለወጠችው ረፈሕ በአንድ የእርዳታ ጣቢያ ለርሃብ ማስታገሻ ለሚላስ ለሚቀመስ ነገር ሲጯጫሁ።

https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ነቢዮ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ።
ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ።
ሲወጡ የሱን ነገር ለአለቃቸው እንዲነግሩለት አደራ አላቸው።
እነርሱ ግን ረሱት።
ሓጃዉን ከነርሱ ይልቅ ለአምላካቸው መናገር የነበረባቸው ዩሱፍም ለዓመታት በእስር ቤት ቆዩ።
ቀድመዋቸው ከወጡት አንደኛው አገልጋይ ሆነ።
ሁለተኛው በስቅላት ተገደለ።
ዘግይተው የወጡት ዩሱፍ ግን ከግብጽ ሚኒስቴሮች አንዱ ሆኑ።
እናሳ
እናማ
ያንተ/ያንች ፋይል አልተረሳም።
ጌታህም ረሺ አይደለም።
ጉዳይህ የዘገየው ለምክንያት ሊሆን ይችላል።
በደንብ አብስሎ ሊሰጥህ ይሆናል።
እስቲ አትቸኩል ንጉሥ ትሆን ይሆናል።
ሚኒስቴር ትሆን ይሆናል።
ይቅናህ አቦ ..

ሰባሐል ኸይር !


https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
2025/07/02 05:27:28
Back to Top
HTML Embed Code: