Telegram Web Link
ዱአ አድርጉልኝ ማለት ከባድ አማና መጣል ነው
🔖ሴቶች ለመጽናናት እና ከፈተና ለመዉጣት ማድረግ ያለባቸዉ ሶስት ቁልፍ ነገሮች..!

የሚያስጨንቃችሁን ነገር መቀነስ
ጤናን መጠበቅ
⓷አንች ከሌለሸ ሁሉ ነገርእንደሚቆም (እንደሚቀጥል)መረዳት
🖋ወንድ ሆይ!!!
ሴት ልጅ የማይቻለውን ነገር አድርግልኝ ብላ አትጠይቅህም ነገር ግን አንተ ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ወንድ ሁንላት!
ሴቶች የሌሉበት ቤት ከእስር ቤት የተለየ መሆኑን እጠራጠራለሁ….🌸
🎁 10ሩ የዙል ሂጃ ቀናቶች❗️

ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ የተባሉ የ ዙል-ሂጃ አስርቱ ቀናቶች ሊገቡ ትንሽ ቀናት ብቻ ይቀሩናል።

የአላህ መልዕክተኛ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ

أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّة

ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስርቱ የዙል ሂጃ ቀናቶች ናቸው።

በሌላም ሀዲስ እንዲህ በማለት በነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለው ደረጃ ያስቀምጣሉ

ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،*
  قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟
     قال ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء

ከነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላህ ሚወደድበት ቀን የለም አሉ

ሶሀቦችም በአላህ መንገድ ላይ መታገል{መጋደል}ቢሆንም? ብለው ሲጠይቋቸው
"አዎ በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም ግን አንድ ሰው ሲቀር'' አሉ
እሱም "በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረው" አሉ

አላሁ አክበር! በመሆኑም እነዚህን አስርት ውድ ቀናቶች ተጠባብቀን በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል። አላህ በሰላም አድርሶን ተጠቅመንባቸው የምናልፍ ያርገን

የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)“ወደ መልካም ያመላከተ እራሱ እንደሰራው ነው” ብለዋል፡፡ ስለዚህ ሼር በማድረግ ላልሰሙ ሙስሊሞች እናሰማ።
:
ከ አሏህ ፊት እንዳትቀርብ ለ አሏህ ከመስገድ የያዘክ ምንድን ነው?
የረሂሙ እገዛ ለዚያች ነፍስ የጌታዋን መንገድ ላለመሳት እየተወላገደች ላለች
.
.
.
አላህ ምን አንደፃፈልህ ብታቀዉ ኖሮ መጠበቅ አይከብድም ነበር
Audio
የዙልሒጃ አስር ቀናቶች


📝በነዚህ ውድ ቀናቶች፦

⭞ የሰዎች መዘናጋት !
⭞ ግንዛቤን ማስፋት !
⭞ ከረመዷን ይበልጣሉን?

ክፍል፦ ①】በድጋሜ የተለጠፈ!

🏷 ኢንሻአላህ ይቀጥላል……

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
📋 በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ቁርኣንን ለማኽተም የሚረዳ ፕሮግራም👇

📆 ዙልሒጃ 01 : ከፋቲህ - አል ዒምራን
📆 ዙልሒጃ 02 : ከኒሳእ - ማኢዳህ
📆 ዙልሒጃ 03 : ከአንዓም - ተውባህ
📆 ዙልሒጃ 04 : ከዩኑስ - ኢስራእ
📆 ዙልሒጃ 05 : ከከህፍ - ኑር
📆 ዙልሒጃ 06 : ከፉርቃን - ፋጢር
📆 ዙልሒጃ 07 : ከያሲን - ሐዲድ
📆 ዙልሒጃ 08 : ከሙጃደላህ - ናስ

📆 ዙልሒጃ 09 : ፆም፣ተክቢራ ...
📆 ዙልሒጃ 10 : የዒድ ቀን

✔️ እንጠቀምባቸው
AbuSufiyan_Albenan
አስቸኳይ ማሳሰቢ


ማክሰኞ  የወሩ የመጨረሻው ቀን ሊሆን ይችላል።

የወሩ መጨረሻ ከሆነ ደግሞ ከነገ በኋላ «ኡዱሒያ» ማድረግ የፈለገ ሰው ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ምንም ነገር መንካት አይፈቀድለትም።

ስለዚህ ወዳጆች ፦

ፀጉሩን መቁረጥ፣
ቀድሞ ቀመሱን ማሳጠር፣
ጥፍሩን መቁረጥ፣
የብብትና የብልት ፀጉሩን ማስወገድ የፈለገ ሰው ማክሰኞ ማሳለፍ የለበትም።

ነብያችን ﷺ እንዲህ ይሉናል፦
«إذا دخلت العشر، وأراد أحدكم أن يُضحي فلا يمس من شعره وبشره شيئًا»

«አስሩ ቀናቶች ሲገቡ ከእናንተ አንደኛችሁ ኡዱሒያ ማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከሰውነቱ ምንም ነገር እንዳይነካ»

ይህንን አሳሳቢና አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም ሙስሊም ሼር በማድረግ ሙስሊሞችን ከስህተት እንታደጋቸው።
       
    Darutewhide
2025/07/07 08:20:58
Back to Top
HTML Embed Code: