Telegram Web Link
በራስ ቦታ ላልቆመ ሰው አንደዚህ ሆንኩ አያሉ አንደማብራራት አድካሚ ነገር የለም

ለጌታህስ ምን አንደሆንክ አያወቀ ለሱ መንገርህ ሰላምምም ነው ሃቂቃ
አትፍራ!

ሁሉም ነገር በአላህ እጅ እንጅ፥ በሰዉ እጅ አንደለም
ብዙ ልትናገሪ የምትችይው ነገር እያለ
ነገር ግን ፈገግታን መርጠሻል
ምክንያቱም ነገሮችን ማብራራት
እና ማስረዳት ስለሰለቸሽ!
ولو كانت الدنيا تدوم لأهلها ..... لكان رسول الله حيا وباقيا
ውሎህ ከማን ጋር ነው? ምን ይመስላል?
~
ሰው በአብዛኛው ውሎውን ይመስላል። ቁርኝቱ ከመጥፎ ሰዎች ጋር የሆነ ሰው ውስጡ ይደፈርሳል። ብዙ መጥፎ ልማዶችን ይወርሳል። በሱስ የተለከፉ ወገኖች በዚህ ወጥመድ ውስጥ የወደቁት በጓደኛ ነው።
- በጓደኛ ብልግና ውስጥ የተነከሩ አሉ።
- በጓደኛ ራሳቸውንም ሌሎችንም የሚጎዳ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ አሉ።
- በጓደኛ ቁማር ያናወዛቸው አሉ።
- በጓደኛ ከሶላት የራቁ አሉ።
- በጓደኛ በጠዋት በማታ በኳስ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ የተጠመዱ አሉ።
- በጓደኛ ሰንካላ ፍልስፍና ውስጥ ገብተው እምነታቸውን ያጡ ወይም አፋፍ ላይ ያሉ አሉ።
- በጓደኛ ስራቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ትዳራቸውን፣ ቤተሰባቸውን ያጡ አሉ።

በተቃራኒው ፡

- በጓደኛ ከሺርክ፣ ከቢድዐ፣ ከተለያዩ ወንጀሎች የወጡ፣ ወደ ዲን የመጡ አሉ።
- በጓደኛ ከወንጀል የራቁ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ትዳር የመሰረቱ አሉ።
- በጓደኛ ጥሩ ስራ ያገኙ፣ የተሻለ አቅም የገነቡ አሉ።
- በጓደኛ ዲንም ዱንያም የተማሩ፣ እውቀታቸውን ያሰፉ አሉ።
- በጓደኛ ከነበሩበት ፈተና ወጥተው ተስፋቸውን ያለመለሙ፣ ነፍሳቸውን ያረጋጉ አሉ።

ስለዚህ፡

ጓደኛችን ማነው? ዝንባሌውና ተፅእኖውስ ወዴት ነው? ወደ ኸይር? ወይስ ወደ ሸር? ጓደኝነታችን አትራፊ ነው ወይስ አክሳሪ? የቁም ነገር ነው? ወይስ እንዲሁ መደበሪያ? ሂሳብ መስራትና መወሰን ይገባል።
ከዚያ በፊት እኛ ለጓደኞቻችን ምን አይነት ሰዎች ነን? ሰዎችን ወደ ሱስ፣ ወደ ወንጀል፣ ወደ ክፋት የምንጎትት ከሆንን ወዮ ለኛ! በራሳችን ብቻ ሳይሆን ባጠፋናቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ነን። ጓደኝነታችን የኸይር ሰበብ ከሆነ ግን መታደል ነው።

ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ሰውበጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው" ይላሉ።
* አቡበክር ሲዲቅ ህይወታቸውን ሙሉ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ጓደኛ ነበሩ። እንደሳቸው ያተረፈ ማን አለ?
* አቡ ጧሊብ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አጎት ነው። ደጀናቸው፣ መከታቸው ነበር። የሳቸውን እውነተኝነት በሚገባ ያውቃል። መጥፎ ጓደኞቹ ግን ሐቅ እንደሆነ ለሚመሰክርበት ኢስላም እጅ እንዳይሰጥ ይልቁንም በሺርኩ ላይ እንዲሞት አድርገውታል። ከዚህ በላይ የመጥፎ ጓደኛን አደጋ የሚያሳይ ምን አለ?

ስለዚህ፡ ጓደኞችህ/ሽ እነማን ናቸው? ወዴት እየወሰዱህ/ሽ ነው? ወዴትስ እየወስድካቸው /ሻቸው ነው? ከልብ መገምገምና ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ይገባል።
=
IbnuMunewor
ደስ የሚል በቀል!

እልህ ይዞሽ ያውቃል? የሚንቁሽና የበታችነት እንዲሰማሽ የሚያደርጉሽ ሰዎች ህይወትሽን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልጊ ንብረት ለማውደም ትጠቀሚበታለሽ ስትፈልጊ ደግሞ ምግብ ታበስይበታለሽ፤ ታዳ ለናቁሽ ሰዎች ማንነትሽን ለማሳየት ጠንክረሽ ሰርተሽ ራስሽን ለውጠሽ በስኬትሽ የያዘሽን እልህ ለምን አትወጭውም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁሽ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው።

hiba_islamic_post
ሰዎችን ስትጠላቸው ብቻ ሳይሆን በጣምም ስትወዳቸውም ከነሱ መሸሽ መራቅ ትፈልጋለህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳንድ ላጤዎች አግቡ ሲባሉ......
ለድሀ ያልሠጠ
ለሐኪም መስጠቱ ግድ ነው ይላሉ ።

ምን ማለት ነው?
"ህመምተኞቻችሁን በሰደቃ አክሙ።" የሚል ሐዲሥ አለ።

ካልሆነ ለመታከሚያ ታወጣላችሁ።
ጥቆማ

🔻ኒቃብ አንድ ሸሪዓዊ ትዕዛዝ ነው።

🔻 ከዚህ በኋላ ነው ሚለበሰው ተብሎ ተርቲብ የለውም።

🔻ለሴት ልጅ ኒቃብ ለመልበስ ፆታዋ ሴት መሆኑ ብቻ በቂ ነው ።

🔻ኒቃብ ለመልበስ እውቀት ይቀደማል ለሚባለው
ሴት ልጅ መሰተር አለባት ሚለውን ማወቅ እውቀት መሆኑን አንዘንጋ?!

🔻ኒቃብ የለበሰችው የእውቀት ጫፍ ደርሳ ለማቆም ሳይሆን ባወቀችው ሰርታ ለመጨመር ነው።

🔻ኡምደቱል አሕካም ኪታብ ላይ በየእለቱ የሚማሩትን ነገሮች ለመተግበር እኮ ኪታቡን እስኪጨርሱ አይጠበቅም።

🔻ኒቃብ ለብሰው እስልምናን ያሰድባሉ ለሚባው  ሰዎች በእስላም ይለካሉ እንጂ እስልምና በሰዎች አይለካም።

🔻 ኒቃብ ለብሳም ተሳሳተች ሳትለብስም ተሳሳተች መሳሳቷ ምንም ከልብሷ ጋር ሊዛመድ አይገባም።

🔻ማህበረሰቡ ኒቃብ ያደረገችን ማትሳሳት እና ጥግ የደረሰች አድርጎ ስለሳላትና ስላሰባት ስህተቷ ይገናል እንጂ ያለበሱ ሴቶች ከሷ በላይ ቀይ መስመር እንደሚረግጡ አንዘንጋ?!

🔻ኒቃብን ለመልበስ እንሞክር ዱዓ እናድርግ እንጂ ኒቃብና ኒቃቢስቶችን ከመኮነን እንጠንቀቅ።

🤲አላህ ለእናንተ እህቶቻችን ሂጃብ የምትለብሱበትን ለኛ ለወንድሞቻቹ ደግሞ ዓይናችንን የምንሰብርበትን ኢማንን ይስጠን !!!
ሙስሊም ወንዶች ኒቃብ ለሚለብሱ ሴቶች ያለንን ክብርና ቦታ ብታውቁ ሁሉም ሴት ኒቃብ በለበሰ ነበር
እናንተ የምድር ላይ ኑርአልዓይኖች አላህ ከከፏ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ>>
ከወንዶች የተሰጠ ሃሳብ
ለምን እንደዚህ አደረግኩ ? ለምንስ እንደዚህ አላደረግኩም ? የምላቸው ብዙ ታሪኮች አሉኝ ። ለመሆን የምጣጣራቸው ብዙ ማንነቶችም ከፊቴ አሉ ። መሆን የምፈልገውንም በጊዜ ባለመሆኔም እራሴን የምወቅስበትና ተስፋዬን በማመናመን ስሜት የምተክዝበት ወቅትም ቀላል አይደለም ።

ነገር ግን ምን አልባት ይህ ሁሉ የሚሆነው ተሰርቼ ስላላለቅኩ ቢሆንስ ? የስኬቴ መንገድ በብዙ ውጣውረዶች የሚሸጋገርና አሁን ያለሁበት ተጨባጭም የዚያ መንገድ አንዱ አካል ቢሆንስ ?

እውነት ነው ዛሬ ከባድ ነው ። ቢሆንም ግን ታሪኬ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ፣ እኔም ተሰርቼ አላለቅምኩም ። ለጥፋቶቼ እና ስህተቶቼ እራሴን ይቅር ማለትና መማር ይኖርብኛል ። የምፈልገው ስኬት ላይ ለመድረስ ደግሞ ጊዜ መስጠት እና ጥረት ማድረግ ይኖርብኛል ። ታሪኬ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ፣ እኔም ተሰርቼ አላለቅኩም…

ኢን ሻ አላህ ነገ ቆንጆ ይሆናል ፣ . ወደፊት ኸይር አለ …..🌸

Inshallh
ሁሉም ነገር የሚሆነው
እኛ ስለፈለግነው ሳይሆን
አላህ ስላለው ብቻ ነው!!
...ሰው አይደለች ይደክማታል እኮ

ከዉጭም ከውስጥም ሰላሟን የሚነሳት ችግር ብዙ ነው...ሰዎች ችግሯን ሊረዷት ቀርቶ ሊሰሟትም ፍቃደኛ አይደሉም...ሁሉም የራሱን ፍላጎት እና ስሜት እየተከተለ የሷን ጭንቀትና ህመም ምንም አይመስለውም።ሰው አይደለችም እንዴ ይደክማታል እኮ!!

ህይወቷን በደስታና በተረጋጋ መንፈስ እንዳትመራ መኖር እንዳትመኝ ህልሟን ነጥቃችኋት   መልካምን ሳትሰንቅ ዱንያዋንም አኼራዋንም ብልሽትሽት አድርጋችሁ ውዷን ርካሽ ለማረግ አሰባችሁ
ግን
ግን
እሷ የኔ ሴት ተንኮታኩታ፣ፈርሳ፣ተሰብራ የምትቀር አይደለችም ይልቅ እምባዋን ጠርጋ ዳግም መንገድ የምትጀምር እንጂ...

hiba_islamic_post
«...ለሱሪ ለባሽ ጓደኛሽ ላኪላት...»

«.......አንቺ ማለት እኮ….…..»
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በጣት ጥፍሮችሽ ላይ ላስቲክ አስገጥመሽ፣
አርቲፊሻል የሆንሽ ዘመንሽን ቀድመሽ፡
በራስሽ ላይ ደግሞ የዊግ ቆብ አጥልቀሽ፡
ሰውነት የቸከሽ ሴት መሆንን ፍቀሽ፡
ከንፁህ እሳቤ በጣሙን እርቀሽ፡
ፆታሽን ቀይረሽ ወንድ መሆን ናፍቀሽ፡

በሰው ሰራሽ ነገር የምትመሰጪ፡
ለትዳር ለሀላል የማትቀመጪ፡
አሻንጉሊት የሆንሽ ከሰው ተራ ወጥተሽ፡
የተፈጥሮን ፀጋ አራክሰሽው ትተሽ፡
የሚገርመው ነገር እንደዚህ ነሽ አሉ፡
አብረውሽ ያደጉት ነገሩኝ በሙሉ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ዱርዬ ልበ-ቢስ ይሉሻል አንዳንዴ፡
ሴትነትን ጥለሽ የምትሆኝ ወንበዴ፡
ኸረ ብዙ ሰማሁ እውነት ይሆን እንዴ!!
የፈጣሪን ጥበብ አንች ቀይረሽው፡
የአለሙን ዳኛ አሏህን ደፍረሽው፡
ዛሬ ከእቃ በታች ረክሰሽ አረፍሽው⁉️
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ፋሽን ተከታይዋ ቆማ ተገትራ፡
ሙስሊሟ ቆንጆ ግን አምራ ተሰትራ፡
በኒቃብ አጊጣ ስራዋን ስትሰራ፡
ያች ሱሪ ለባሽ ገባች👉አሰንሰራ፡
ኒቃቢስት እህቴን ለማራከስ ደፈርሽ፡
ድንኳን ለባሽ ብለሽ ለመሳለቅ ሞከርሽ፡
በሸይጧን እሳቤሽ ቅናት ይዞሽ ሰከርሽ፡
ስሜቷን ትከተል በማለትም መከርሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▸ውድ ነሽ አይዞሽ...!!
ኒቃቢስቷ አንች ግን ቀጥ በይ በአቋምሽ፡
የማንም ዘለፋ ፈፅሞ እንዳያምሽ፡
ሁሌም ከአሏህ ዘንድ ከፍ ያለ ነው ስምሽ፡
አለልሽ ቃል ኪዳን ውብ ጀነት ነው ህልምሽ፡

እንደ ዘመኑ ሴት ቻፕስቲክ ያላየሽ፡
ከመጥፎ ጓደኛ ቀድመሽ የተለየሽ፡
ዘር ጎሳና ብሔር መልክ ሳትቆጥሪ፡
የሰጠሽ ተፈጥሮን ለማርከስ ሳ'ጥሪ፡
ዘመናይ ነኝ ምትል ኋላ ቀሯን ቀድመሽ፡
በኒቃብ ተውበሽ ሁሉን አስደምመሽ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

ከልብ የምትገቢ ነሽ የአይን አበባ፡
ወንድን የሚረብሽ የለሽም ወለባ፡
ምርት በአንች ታይቷል ሌላው ነው ገለባ፡
ከአሏህ ቃል ውጭ ያላቆመሽ ታኮ፡
ከነቢ ትዕዛዝ ውጭ ንግግርሽ ሾልኮ፡
ከውጭ ያልተሰማ ድምፅሽ አፈትልኮ፡
የሴቶች ልዩ ነሽ አንች ማለትኮ....!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በኑረዲን አል አረቢ➊❹❹❹
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አል-በይሀቂ አቡ በክር አል-አሽዕሪ እንዲህ ብለዋል፡-

**ኢማም ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል፡-

የሚከተለው የቁርኣን አንቀፅ
«{مَنْ فِي السَّمَاءِ}» («በሰማይ ያለው») የሚለውን ትርጉሙ፡- 
«ከሰማይ በላይ፣ ከዐርሽ ላይ ያለ ነው»
እሱም ፦ «{الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى}» («አል-ራህማን በዐርሽ ላይ ሆነ።») የሚለው አንቀፅ ያስረዳል። 

ማንኛውም ከፍ ያለ ነገር «ሰማይ» ይባላል። ዐርሸም ከሁሉም ሰማያት በላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ከዐርሽ ላይ ከፍ ያለ ሲሆኑ «እንዴት» ወይም «አኳሃኑ» ሳይጠየቅ (بلا كيف) እንደሆነ ተገልጿል። 

(መናቂብ አሽ–ሻፊዒ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 398)
ቀን አለ ......

ለልባችሁ ቀን እንዳለ ንገሩት። አዎ የሆነ ቀን አለ። ደስተኛ የምትሆኑበት። ስትመኙት የነበረውን ነገር የምታገኙበትና ከደስታችሁ የተነሳ «ጌታዬ ሆይ በከንቱ እንደማታስቀረኝ አውቅ ነበር» የምትሉበት ቀን አለ።

ትናንት ያልነበር ሊሆን ይችላል። ዛሬም ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አንድ ቀን አለ። ተስፋችሁን መቼም ቢሆን እንዳትጥሉት። አብሽሩልኝ። «ደስተኝነት ምንድነው?!» ስትባሉ «እኔ ያለሁበት ሁኔታ ነው» ብላችሁ የምትመልሱበትን ቀን አሏህ ቅርብ ያድርግላችሁ።
{وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ}
إنا لله وإنا إليه راجعون ......
"በወንዶች በሆነ ነገራቸዉ የምቀና ብሆን ኖሮ ወደ መስጅድ በሚያደርጉት ጉዞ እቀናባቸዉ ነበር።

=
2025/07/07 19:37:35
Back to Top
HTML Embed Code: